የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ BG.Bureau of Women and Social Affairs

  • Home
  • Ethiopia
  • Asosa
  • የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ BG.Bureau of Women and Social Affairs

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሴቶችና  ማህበራዊ  ጉዳይ ቢሮ  BG.Bureau of Women and Social Affairs TO CONVEY MESSAGE ABOUT WOMEN ,CHILDREN,YOUTH ,ELDERS and Disable .

ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻደሊ ሀሰን በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ  የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል ተወካይ ሚስተር አርጃን ደ ዋግት ጋር ተወያዩ *************(አሶሳ፣ ነሃሴ 25/2018 ዓ/ም) የቤ...
31/08/2026

ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻደሊ ሀሰን በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል ተወካይ ሚስተር አርጃን ደ ዋግት ጋር ተወያዩ
*************

(አሶሳ፣ ነሃሴ 25/2018 ዓ/ም) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻደሊ ሀሰን በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል ተወካይ ሚስተር አርጃን ደ ዋግት የተመራ ልዑክ ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ተወያዩ።

በውይይታቸውም በክልሉ በዩኒሴፍ ድጋፍ የተሰሩ ፕሮጀክቶች የስራ አፈጻጸም ያለበት ሁኔታና የክልሉን ህዝብ የልማት ፍላጎቶች ከማሟላት አንጻር እያደረገ ያለውን አበርክቶ እንዲሁም በቀጣይ ድጋፍና እገዛ የሚፈልጉ ወሳኝ ጉዳዮችን የሚያመላክት ሰነድ በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዚያድ አብዱላሂ በኩል ቀርቧል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻደሊ ሀሰን ዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ለክልሉ ህዝብ እያደረገ ላለው ዘርፈ ብዙ አበርክቶ አመስግነዋል።

አቶ አሻድሊ አክለውም ክልሉ በርካታ ስደተኞችን ተቀብሎ እያስተናገደ መሆኑን በመግለጽ በዚህም ምክንያት የጤና ተቋማትን፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፣ የትምህርትና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን ተጋርቶ እየተጠቀመ በመሆኑ በክልሉ እና በተቃባዩ ማህበረሰብ ዘንድ ተጽዕኖ እያሳደረ እንደሚገኝ በመጠቆም የአጋር አካላትን ትኩረትና ያልተቋረጠ እገዛ እንደሚፈልግ ተናግረዋል።

የዩኒሴፍ ኢትዮጵያ የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል ተወካይ ሚስተር አርጃን ደ ዋግት በበኩላቸው ለተደረገላቸው አቀባበልና ስለቀረበላቸው አጠቃላይ ገለጻ አመስግነው በተለይ የክልሉ መንግስትና ህዝብ ስደተኞችን ተቀብሎ እያስተናገደበት ያለውን መንገድ አድንቀዋል።

ዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ለክልሉ ህዝብ የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍና እገዛ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

መረጃው፦ የክልሉ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ነው

‎የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ የዶሮ ልማትን ወደ ዘመናዊ አሠራር እያሸጋገረ ነው ፦ አቶ አዲሱ አረጋ‎***********‎‎የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ የዶሮ ልማትን ወደ ዘመናዊ አሠራር እያሸጋገረ ...
31/08/2026

‎የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ የዶሮ ልማትን ወደ ዘመናዊ አሠራር እያሸጋገረ ነው ፦ አቶ አዲሱ አረጋ
‎***********

‎የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ የዶሮ ልማትን ወደ ዘመናዊ አሠራር እያሸጋገረ እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስትር አቶ አዲሱ አረጋ ተናገሩ።

‎አቶ አዲሱ አረጋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ የዶሮ ሥጋና እንቁላል ምርትን በማሳደግ ዘመናዊ የዶሮ እርባታን እያስፋፋ ነው ብለዋል።

‎የተሻሻሉ ዝርያዎችን ማስፋፋት፣ ዘመናዊ ማባዣና ማስፈልፈያ ማዕከላትን ማጠናከር፣ የጫጩት እንክብካቤና የባዮ-ሴኩሪቲ ሥርዓትን ማሻሻል እንዲሁም የግል ባለሀብቶችን ማሳተፍ የኢኒሼቲቩ ዋና ትኩረቶች መሆናቸውንም ገልጸዋል።

‎የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ የዶሮ ልማትን ወደ ዘመናዊ አሠራር እያሸጋገረ እንደሚገኝም ነው አቶ አዲሱ የተናገሩት።

‎በዚህም አርቢዎችን ከአነስተኛ እርባታ ወደ ገበያ ተኮርና ምርታማ የዶሮ ልማት በማሸጋገር ለምግብ ዋስትና፣ ለገቢ ምንጭ እና ለዜጎች የሥራ ዕድል ፈጠራ የሚያበረክት ዘርፍ እየሆነ መምጣቱን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

‎በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ኡራ ወረዳ በሚገኘው “ጼጼ” የዶሮ ልማትና መኖ ማደራጃ ማዕከል የሚካሄደው የዶሮ እርባታ ሥራ የዚህ አንዱ ማሣያ ነው ብለዋል።

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ8 ሺህ 985 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቀረበ***********የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት ከ8 ሺህ 985 ኪሎ ግራም በ...
31/08/2026

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ8 ሺህ 985 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቀረበ
***********

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት ከ8 ሺህ 985 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማቅረቡን አስታውቋል።

"የማዕድን ሀብታችን ለዘላቂ ብልፅግናችን" በሚል መሪ ሐሳብ የማዕድን ዘርፉን ምርታማነት ከማሳደግ ባለፈ፣ በዘርፉ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን ለመፍታት ያለመ ንቅናቄ መድረክ በአሶሳ ከተማ ተካሂዷል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በዘርፉ የሚታዩ ህገ-ወጥ ተግባራትን ለመከላከልና የሀገርን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሠራ ተናግረዋል።

የማዕድን ዘርፉ የሀገር ኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፣ ዘርፉን በከፍተኛ ጥንቃቄና ትኩረት መምራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

በክልሉ የሚገኙ የወርቅ አምራች ፋብሪካዎች ዘርፉን ለማጠናከር ትልቅ አቅም እየሆኑ መምጣታቸውን የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ እንደ ሀገርና እንደ ክልል የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የንቅናቄው ፋይዳ የጎላ መሆኑን አብራርተዋል።

የክልሉ ማዕድን ቢሮ ኃላፊ አቶ ቲጃኒ አደም በበኩላቸው በበጀት ዓመቱ 8 ሺህ 985 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ መላኩን ገልጸዋል። ቢሮው ከወርቅ ምርት በተጨማሪ የከሰል ድንጋይና የእምነበረድ ምርትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገርና የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን ለማሳደግ በትኩረት እየሠራ መሆኑን ጠቁመዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 5 ዓመታት ከ1.18 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማስመዝቡንና ይህም ለሀገር ኢኮኖሚ እያበረከተ ያለውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያሳይ መሆኑን አንስተዋል።

ይሁን እንጂ በዘርፉ የሚስተዋሉ ህገ-ወጥ የማዕድን ግብይቶችና የአደገኛ ኬሚካሎች አጠቃቀም ክፍተቶች ተግዳሮቶች መሆናቸውን ገልጸው፣ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና ከዘርፉ የሚገኘውን ሀገራዊ ጥቅም ለማሳደግ የተቀናጀ አሠራርና የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ቁርጠኝነት እንደሚጠይቅ አመላክተዋል።

ኢቢሲ

31/08/2026
31/08/2026
የጉሙዝ ብሔረሰብ የአዲስ ዓመት ማብሰሪያ የሆነው የ"ጓንዷ" በዓል በአዲስ አበባ ከተማ እየተከበረ ነው‎************‎‎(አሶሳ፣ ነሐሴ 23/2018 ዓ.ም) የጉሙዝ ብሔረሰብ የአዲስ ዓመ...
29/08/2026

የጉሙዝ ብሔረሰብ የአዲስ ዓመት ማብሰሪያ የሆነው የ"ጓንዷ" በዓል በአዲስ አበባ ከተማ እየተከበረ ነው
‎************

‎(አሶሳ፣ ነሐሴ 23/2018 ዓ.ም) የጉሙዝ ብሔረሰብ የአዲስ ዓመት ማብሰሪያ የሆነው የ"ጓንዷ" በዓል በአዲስ አበባ ከተማ እየተከበረ መከበር ጀምሯል።

‎የዘንድሮው የጓንዷ በዓል "ጓንዷ ለዘላቂ ሠላምና ለሁለንተናዊ ዕድገት" በሚል መሪ ቃል ነው እየተከበረ የሚገኘው።

‎በአዲስ አበባ እየተከበረ በሚገኘው የጓንዷ በዓል ላይ የተለያዩ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች የብሔረሰቡ ተወላጆች እና የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች በአብሮነት ተገኝተዋል።


የ2018 ዓ/ም የጳጉሜን ቀናት አከባበር ማስፈጸሚያ ዕቅድ ላይ የተቋቋመ ኮሚቴ ውይይት አካሄደ​“የኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የሚከበረው ይህ የጳጉሜን ቀናት፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ በ...
28/08/2026

የ2018 ዓ/ም የጳጉሜን ቀናት አከባበር ማስፈጸሚያ ዕቅድ ላይ የተቋቋመ ኮሚቴ ውይይት አካሄደ

​“የኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የሚከበረው ይህ የጳጉሜን ቀናት፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በህዝብ ይሁንታ ያገኘው ፓርቲ መንግስት በሚመራበት፣ የብሔራዊ ምክር ቤት ውጤቶች ወደ ተግባር በሚሸጋገሩበት እና ዘርፈ-ብዙ ሀገራዊ ስኬቶች በተመዘገቡበት ታሪካዊ ወቅት የሚከናወን መሆኑ ተገልጿል።

​አከባበሩ ሀገራችንን ከችግርና ተቃርኖዎች የመቋቋም ምዕራፍ ተሻግራ ወደ ላቀ የክፍታ እና የልማት ምዕራፍ መሸጋገሯን ለህዝባችንና ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ ለማብሰር የታለመ ነው። በዚህም መሰረት በዕቅዱ የተካተቱት የጳጉሜን ቀናት በየዕለቱ በሚከተሉት መሪ ሐሳቦች እንደሚከበሩ ታውቋል፦
✅️ጳጉሜን 1: የእመርታ ቀን
✅️ጳጉሜን 2: የማንሠራራት ቀን
✅️ጳጉሜን 3: የጽናት ቀን
✅️ጳጉሜን 4: የኀብር ቀን
✅️ጳጉሜን 5: የነገ ቀን
​በዕለታዊ መርሃ-ግብሮቹ የኢኮኖሚ አበርክቶን፣ የሜጋ ፕሮጀክቶችን ስኬት፣ የተቋማትን ዘመናዊ ቁመና፣ የጀግኖችን መስዋዕትነት፣ ሕብረ-ብሔራዊ አንድነትና አብሮነት እንዲሁም የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አቅሞችን የሚያጎሉ እና የነገን ተስፋ የሚያነሳሱ ኩነቶች የሚከናወኑ ይሆናሉ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኡሱማን አህመድ የማስፈጸሚያ ዕቅድ ሰነዱን አቅርበው ውይይት ተደርጓል።

​የዘንድሮው የጳጉሜን ቀናት አከባበር ዋና ዓላማ ኢትዮጵያ ከአግድሞሽና ከዝቅታ ጉዞ ተላቃ በሁሉም ዘርፎች ወደ ላቀ የክፍታ ጉዞ መሸጋገሯን፣ ሀገር-መንግሥቱን በፅናት እያነፀች መሆኑን፣ እንዲሁም ከጥገኝነት ነፃ የሆነች እና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እውን እያደረገች ያለች የነገዋን ኢትዮጵያ የመገንባት መሠረት መጣሏን ለህዝቦችና ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በማብሰር ለበለጠ ሀገራዊ ውጤት ከፍተኛ መነሳሳትና የተስፋ መንፈስ መፍጠር መሆኑ በውይይቱ ላይ ተመላክቷል።

መረጃው የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ነው

‎የአለም አቀፉ የህፃናት ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ የህፃናት መበት ጥበቃ ስርዓትን ለማጠናከር ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ‎*******‎የህፃናት ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴ...
28/08/2026

‎የአለም አቀፉ የህፃናት ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ የህፃናት መበት ጥበቃ ስርዓትን ለማጠናከር ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ
‎*******
‎የህፃናት ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ የህፃናት ያለዕድሜ ጋብቻን ለመከላከልና የህፃናት ጥበቃ ስርዓትን ማጠናከር ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጿል።

‎የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ከህፃናት ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን ዋና መስራች ሰር ክሪስ ሆን እና ልዑካቸው ጋር አጋርነትን ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ በሰፊው ተወያይተዋል።

‎በውይይታቸውም፥ በዋነኝነት በኢትዮጵያ የህፃናት ያለዕድሜ ጋብቻ፣ ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችንና መሰል ተግባራትን ከማስቆምና የህፃናት ጥበቃን ከማጠናከር አኳያ የህፃናት የልደትና የክትባት ምዝገባ ስርዓትን ከዲጂታል መታወቂያ ጋር ማስተሳሰር በሚቻልበት አግባብ ላይ መክረዋል።

‎በተጨማሪም እስከታችኛው መዋቅር በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቋቋሙ የሴቶች የልማት ህብረቶችን በማጠናከር ያለዕድሜ ጋብቻንና የሴት ልጅ ግርዛትን በመከላከል እንዲሁም የህፃናት ጥበቃን ስርዓትን በማሻሻል ረገድ የድርሻቸውን እንዲወጡ የሚያስችሉ ተግባራትን ውጤታማ ለማድረግ በጋራ እንደሚሰሩ የስራ ሃላፊዎቹ አስታውቀዋል።

‎የፋውንዴሽኑ ዋና መስራችና ስራ አስፈፃሚ ሰር ክሪስ ሆን፥ ህፃናትን ከ 5 አመት እድሜ አንስቶ የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ውስጥ በማካተት መብትና ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ኢትዮጵያ ፈር ቀዳጅ ሀገር በመሆኗ የተሰማቸውን ኩራት ገልፀዋል።

በቀጣይም ‎የሴቶች የልማት ህብረትን ማጠናከር፣ የህፃናት የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ፣ የልደት ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የህፃናት ክትባት፣ የCPIMS+ ማጠናከር፣ የህፃናት ጥበቃ ስራ፣ ለሴቶችና ህፃናት የሚሰጥ የፍትህ ስርዓትን ማጠናከርና መሰል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በትኩረት እያከናወናቸው ለሚገኙ ተግባራት ውጤታማነት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ነው።

Address

Asdoss
Asosa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ BG.Bureau of Women and Social Affairs posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ BG.Bureau of Women and Social Affairs:

Shortcuts

Share