Benishangul Gumuz Education Bureau

Benishangul Gumuz Education Bureau የትምህርት ጥራት ተጠብቆ የተማሪዎቻችን ውጤትና ስነ-ምግባር እንዲሻሻል እንሰራለን !!! Equity

አጋርነቱ ያልተቋረጠው ኢቲዮ ቴሌኮም ለ2019 የትምህርት ዘመን "ለነገ ተስፋዎች" በሚል መሪ ሀሳብ  2,300 ደርዘን ደብተር ስርጭት በአሶሳ ከተማ አስተዳደር አጤጦ 1ኛና መካከለኛ ደረጃ ት...
06/09/2026

አጋርነቱ ያልተቋረጠው ኢቲዮ ቴሌኮም ለ2019 የትምህርት ዘመን "ለነገ ተስፋዎች" በሚል መሪ ሀሳብ 2,300 ደርዘን ደብተር ስርጭት በአሶሳ ከተማ አስተዳደር አጤጦ 1ኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ድጋፍ ማድረጉን ጀምሯል
------------- ------------- ------------- ---------------
(ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም ፤ አሶሳ) አጋርነቱ ያልተቋረጠው ኢቲዮ ቴሌኮም ለ2019 የትምህርት ዘመን "ለነገ ተስፋዎች" በሚል መሪ ሀሳብ 2,300 ደርዘን ደብተር ስርጭት በአሶሳ ከተማ አስተዳደር አጤጦ 1ኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ድጋፍ ማድረጉን ጀምሯል

27,600 ደብተር ለተማሪዎቾ ድጋፍ በዚህ ዓመት ኢቲዮ ቴሌኮም ድጋፍ ሲያደርግ ትውልድን በዕውቀት በክህሎትና በአመለካከት ለማብቃት ሃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ሲሉ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኢቲዮ ቴሌኮም ምዕራብ ምዕራብ ሪጅን ሃላፊ አቶ ጥላሁን እጅጉ ገልጸዋል።

2,4 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የተማሪዎች መማሪያ ደብተር በክልሉ በሶስቱም ዞኖች ፣ በአሶሳ ከተማ አስተዳደርና በማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳ ለሰባት ትምህርት ቤቶች ከ2,300 ተማሪዎች በላይ ድጋፍ ይደረጋል ተብሏል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ተወካዮች ፣ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ የወረደ ሁለት ዋና አስተዳዳሪ በደረዲን አህመድ ፣ የትምህርት መምሪያ ሃላፊ ወ/ሮ ጎጃም አያናና የአጤጦ ቀበሌ አመራሮችና መምህራን ተገኝተዋል።

በዛሬውም ዕለትም በአሶሳ ከተማ አስተዳደር በአጤጦ ትምህርት ቤት ለ350 ተማሪዎች የመማሪያ ደብተር ኢቲዮ ቴሌኮም ምዕራብ ምዕራብ ሪጅን ድጋፍ አድርጓል።

ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሰ ሁሉም ህጻናት በትምህርት ገበታ ላይ እንዲገኙ ብቻ አይደለም ፤ የዓመቱንም ትምህርት ተምረው እንዲያጠናቅቁ አቶ በደረዲን መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ፤ የኢቲዮ ቴሌኮም ምዕራብ ምዕራብ ሪጅን ለዳረገው ድጋፍ አመስግነዋል።

ተማሪዎች መስከረም 5/2019 ዓ.ም ትምህርት እንደሚጀመር አውቀው በትምህርት ገበታ ተገኝተው እንዲማሩ ያሳሰቡት የትምህርት መምሪያ ሃላፊ ወ/ሮ ጎጃም አያና የኢቲዮ ቴሌኮም ምዕራብ ምዕራብ ሪጅን ሁል ጊዜ አጋራችን ነው እናመሰግናለን ብለዋል።

ያልተቋረጠ የሰባት ዓመት የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍና መሰል ጊዜውን የዋጀ የዲጂታል ቴክኖሎጂና የ2018 ዓ.ም የሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተናና በቅርበት በማገዝ ትምህርቱን ለማዘመን ኩባኒያቸው በጉልህ እየተሳተፈ መሆኑን የገለፁት የኢቲዮ ቴሌኮም ምዕራብ ምዕራብ ሪጅን ሃላፊ አቶ ጥላሁን እጅጉ ሲሆኑ "የነገ ተስፋዎች" በሚል መሪ ሀሳብ የተደረገው መማሪያ ደብተር አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።

10,000 ደብተር "ለህብር ቀን" ከወዲሁ ተጀምሯል። የቀበሌው ዋና አስተዳዳሪና የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል። የዘገበው የቢሮው ኮሙኒኬሽን ዳሬክቶሬት ነው።

ክቡር ርዕሰ መስተዳድር እናመሰግናለን 👏👏👏‎የመደመር መንግሥት የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት እውነተኛ እና ሁለንተናዊ ብልጽግናን እያረጋገጡ ነው ፦ አቶ አሻድሊ ሀሰን‎************‎‎...
05/09/2026

ክቡር ርዕሰ መስተዳድር እናመሰግናለን 👏👏👏‎የመደመር መንግሥት የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት እውነተኛ እና ሁለንተናዊ ብልጽግናን እያረጋገጡ ነው ፦ አቶ አሻድሊ ሀሰን
‎************

‎(አሶሳ፣ ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም) የመደመር መንግሥት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚያከናውናቸው ተግባራት እውነተኛ እና ሁለንተናዊ ብልጽግናን እያረጋግጡ መሆና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ተናገሩ።

‎የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በቡልድግሉ የተለያዩ የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራዎችን አካሂደዋል።

‎አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ በክልሉ መስተዳድር በተያዘው ክረምት የሚገነቡ ቤቶችን ያስጀመሩ ሲሆን፣ ለአቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት እና ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።

‎ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በዚሁ ወቅት፣ የመደመር መንግሥት ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ ውጤታማ ኢኒሼቲቮችን እየተገበረ መሆኑን ገልጸዋል።

‎በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እየተከናወነ ያለው ተግባር እንደሀገር እውነተኛ እና ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚደረውን ጉዞ እውን የሚያደርግ ነው ብለዋል።

‎በክልሉ በተያዘው ክረምት የተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች እየተከናወኑ መሆኑን አቶ አሻድሊ ተናግረዋል።

‎በክልሉ በተያዘው ክረምት ብቻ በሁሉም ወረዳዎች የ200 አቅመ ደካማ ዜጎች አዳዲስ ቤቶች ግንባታ እና የ50 ቤቶች ጥገና፣ ለአቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት፣ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

‎የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት በቡልድግሉ ወረዳ የ5 ቤቶችን ግንባታ ከማስጀመር በተጨማሪ ለ200 አቅመ ደካሞች የምግብ እና ምግብ ነክ ድጋፍ እና ለ200 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ጠቁመዋል።

‎የጀመርነው ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚሳከው ስንደመር እና ስንተሳሰብ ነው ያሉት አቶ አሻድሊ፣ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የዚህ ትልቅ ማሣያዎች ናቸው ብለዋል።

‎ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራዎች ከቁሳዊ ድጋፍ ባለፈ እያመጡት ያለው የአመለካከት ለወጥ ከፍተኛ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

‎የዘገበው የቤኒሻንጉል_ጉሙዝ_ክልል_የመንግሥት_ኮሙኒኬሽን_ጉዳዮች_ቢሮ ነው።

እናመሰግናለን 👏👏👏ቢሮው የትምህርትና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡  የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ አባላት ድጋፍ...
04/09/2026

እናመሰግናለን 👏👏👏
ቢሮው የትምህርትና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ አባላት ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች ሊውል የሚችል የንፅህና መጠበቂያና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉ ከተቋሙና ከቢሮው የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ አባላት የተገኘ ሲሆን፤ ድጋፉን የቢሮው የፍቃድ አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና በተቋሙ የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ሰብሳቢ ወ/ሮ ኑራ አሻድሊ አስረክበዋል፡፡

ወ/ሮ ኑራ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክትም መሰል ድጋፎች የሴቶችን የኢኮኖሚ ጫና ለማቃለል ታስቦ የተከናወነና በቀጣይ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የሚደረገው መሰል ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የብልፅግና ፓርቲ የኢኮኖሚ ዘርፍ የሴቶች ክንፍ አስተባባሪዎች በድሪያ አበደላ እና ሙሉሰው አለሙ ተቋሙና የተቋሙ የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ያደረጉት ድጋፍ ለሌሎች አርዓያ የሚሆንና መቀጠል ያለበት መልካም ተግባር መሆኑን ጠቁመው፤ አመስግናዋል ፡፡

የተቋሙ የሪፎርም ስራዎችን አስመልክቶ ለባለድርሻ አካላት ገለጻ ተደርጓል ---------    ------------    -------------     ----------- -------------(ነ...
04/09/2026

የተቋሙ የሪፎርም ስራዎችን አስመልክቶ ለባለድርሻ አካላት ገለጻ ተደርጓል
--------- ------------ ------------- ----------- -------------
(ነሃሴ 29/2018 ዓ.ም ፤ አሶሳ) የቤኒሻንጉል -ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ የተቋሙ የሪፎርም ስራዎችን አስመልክቶ ለባለድርሻ አካላት ገለጻ ተደርጓል።

በተቋሙ በሪፎርም ስራ የተከናወኑ ተግባራት በቢሮው የዕቅድ ዝግጅት ባለሙያና የሪፎርሙ ቴክኒካል ኮሚቴ አባል በአቶ ሙሃዲን ከድር በኩል ቀርቧል።

የባለድርሻ አካላት ሚና ፣ ተሳትፎና ልየታ ፣ ትንተና የሚጠበቁ ውጤቶች በተመለከተ በዝርዝር በአቶ ሙሃዲን በኩል ቀርቧል።

ሪፎርሙ ከቢሮ አልፎ እስከ ወረዳና ትምህርት ቤቶች ድረስ እንደሚወርድና እንደሚተገበር ከቀረበው የባለድርሻ አካለት ሚና ሰነድ ተመልክቷል።

የለውጥ ሥራዎችን በተመለከተ ለግልገል በለስ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ አባላት መግለጫ ተሰጠ----------    -----------    -------------     ------==-=----(ነ...
04/09/2026

የለውጥ ሥራዎችን በተመለከተ ለግልገል በለስ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ አባላት መግለጫ ተሰጠ
---------- ----------- ------------- ------==-=----
(ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም ፤ አሶሳ)በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ተግባራዊ እየኾነ የሚገኘውን የለውጥ ሥራዎች የማከናወን ትግበራን በተመለከተ፤ ለግልገል በለስ መምህራን ኮሌጅ አባላት ገለጻ ተደረገ፡፡

የነገሩን፤ ገለጻውን በተመለከተ የያብራሩልን፤በትምህርት ቢሮ ተቋቁሞ የለውጥ ሥራዎችን እያከናወነ የሚገኘው ቡድን መሪ አቶ ሸምሰዲን መሐመድ ሲኾኑ፤በግልገል በለስ የመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ አባላት የተነሱትን የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በተመለከተ የትምህርት ቢሮ አባላት ተገቢውን ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ለኮሌጁ አባላት በተለይም በመሠረታዊና አስተዳዳራዊ የለውጥ ሥራዎች አወቃቀርና አተገባባር ዙሪያ ሰፋ ያለ ማብራሪያ መሰጠቱን አቶ ሸምሰዲን ነግረውናል፡፡
በተጨማሪም በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ተግባራዊ የሚኾኑትን ሰባቱ የለውጥ ሥራዎች ዓዕማድ ምንነትና አፈጻጸማቸውን በተመለከተም ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

ሰባቱ የለውጥሥራዎች አዕማድ የሚባሉት፤
ቀልጣፋና ተደራሽ የመንግሥት አልግሎት አቅርቦት ሥርዓት መዘርጋት፣ የመንግሥት አስተዳደርና አደረጃጃት ሥርዓትን ማሳለጥ፣ የመንግሥት ሠራተኞች የብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ሥርዓት መገንባትና የማስፈጸም አቅምን ማሳደግ፣
የዲጂታል ሲቪል ሰርቪስ በመገንባት ቅቡልነት ያላቸውን አገልግሎቶችንና ውሳኔዎችን ማሳለጥ፣ ነጻና ገለልተኛ ሲቪል ሰርቪስ ግንባታን ማሳለጥ፣ ብዝኃነትና አካታችነትን ያረጋገጠ ሲቪል ሰርቪስ መገንባትና፤ የሲቪል ሰርቪስ ገቢር ነበብ አመራርና ተቋም ግባታን ማፋጠን እንደኾኑ ይታወቃል፡፡

ዘገባው የትምህርት ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው

ዕውቅናና ሽልማት 👏👏👏 በ28ኛው ክልል አቀፍ የትምህርት ጉባኤ------   👏👏👏----------------------👏👏👏_______________ በ2018 የትምህርት ስራ አፈጻጸም የተሻለ ው...
04/09/2026

ዕውቅናና ሽልማት 👏👏👏 በ28ኛው ክልል አቀፍ የትምህርት ጉባኤ
------ 👏👏👏----------------------👏👏👏_______________
በ2018 የትምህርት ስራ አፈጻጸም የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ የዞን ፣ የልዩ ወረዳና የከተማ አስተዳደርና ወረዳዎች ፣ በ2018 ዓ.ም ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የብር የታብሌትና ሰርቲፊኬት ተሰጥቷቸዋል።

ተሸላሚዎችም ሽልማታቸውንና የምስጋና ሰርተፊኬት ከክቡር እንግዶች ከክቡር አቶ አሻሊ ሀሰን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና ከክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ተቀብለዋል።

የትምህርት ልማት አጋሮች በትምህርት ዘርፍ ላበረከቱት ጉልህ አስተዋጽኦ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ተመስገን ዲሳሳ (ዶ/ር) ፣ ከምክትል ቢሮ ሃላፊዎች ከአቶ በሺር አብዱራሂምና ከአቶ መሀመድ ኡስማን እጅ ተቀብለዋል።

28ኛው ክልል አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በፎቶ  "ጥራትና ፍትሃዊነቱ የተረጋገጠ ትምህርት ለተሻለ የመማር  ውጤት !! " በአሶሳ ህዳሴ ኤርፖርት የክብር እንግዳ አቀባበል ፤ ፎቶ በከፊል።
04/09/2026

28ኛው ክልል አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በፎቶ "ጥራትና ፍትሃዊነቱ የተረጋገጠ ትምህርት ለተሻለ የመማር ውጤት !! " በአሶሳ ህዳሴ ኤርፖርት የክብር እንግዳ አቀባበል ፤ ፎቶ በከፊል።

04/09/2026

ጥራትና ፍትሃዊነቱ የተረጋገጠ ትምህርት ለተሻለ የመማር ውጤት !!
28ኛው ክልል አቀፍ የትምህርት ጉባኤ
የቤ/ጉ/ ክ/መ/ ትምህርት ቢሮ

እናመሰግናለን !👏👏👏👏የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ  በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በክልሉ መተከል ዞን ወንበራ ወረዳ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።...
04/09/2026

እናመሰግናለን !👏👏👏👏
የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በክልሉ መተከል ዞን ወንበራ ወረዳ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

(አሶሳ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም)የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትበክልሉ መተከል ዞን ወንበራ ወረዳ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፋን ያበረከቱት የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዚያድ አብዱላሂ ቢሮው ላለፉት አመታትና በዚህ ዓመት በተለያዩ አካባቢዎች የተለያዩ የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ገልፀዋል ።

በ2019 ዓመት የክልሉ መንግስት በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እያተደረገ ሲሆን የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ የክልሉ መንግስት ባደረገው ድልድል መሰረት በክልሉ መተከል ዞን ወንበራ ወረዳ የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎችን ''በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ'' በሚል መሪ ሀሳብ ለማከናወን ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም የቢሮው የበጀትና ፋይናንስ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ትዕግስት ዲቢሳ እና የወረዳው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በይፋ ማስጀመራቸው አስታውሰዋል።

በዛሬው ዕለትም ቢሮው በወዳዋ አንድም ተማሪ በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታው እንዳይቀር' የተቻለውን አስተዋፅኦ ለማበርከት ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺ ብር/ በላይ የተገዙ የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን አመላክተው ቢሮው ቀሪ የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል ተናግረዋል።

ድጋፋን ከክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዚያድ አብዱላሂ እና የግ/ንብ/አስ/ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ማህድያ አልበሽር የወንበራ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ካሳሁን በላቸው የተረከቡ ሲሆን ስለተደረገላቸው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል ። ዘገባው የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ነው።

የተገኙ ውጤቶችን የሚያስቀጥል ፤ የዘርፉን ችግሮች መፍታት የሚያስችል ዕቅድ ማዘጋጀት ይኖርብናል ፤ አቶ በሺር አብዱረሂም------------     ------------     ----------...
04/09/2026

የተገኙ ውጤቶችን የሚያስቀጥል ፤ የዘርፉን ችግሮች መፍታት የሚያስችል ዕቅድ ማዘጋጀት ይኖርብናል ፤ አቶ በሺር አብዱረሂም
------------ ------------ -------------- --------------------
(ነሃሴ 29/2018 ዓ.ም ፤ አሶሳ) በ2018 የትምህርት ዘመን የተገኙ ውጤቶችን የሚያስቀጥል ፤ የዘርፉን ችግሮች መፍታት የሚያስችል ዕቅድ ማዘጋጀት ይኖርብናል ሲሉ በክልሉ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ፕሮግራሞች ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ በሺር አብዱረሂም ገልጸዋል።

በትምህርት ተሳትፎ ፣ በተደራሽነትና ከዓመት ዓመት እየተሻሻለ የመጣውን የተማሪዎች ውጤት ለማስቀጠል ከቢሮው እስከ ወረዳ የሚዘጋጀው ዕቅድ ወሳኝ ነው ያሉት አቶ በሺር የሚዘጋጀው ዕቅድ በውጤት ተኮር አግባብ በመሆኑ ተጠያቂነትም ያካተተ ነው ብለዋል።

የ2019 የትምህርት ዘመን የትምህርት ስራችን ሁሉንም የወረዳ የዕቅድ ባለሙያዎች ተወዳዳሪና ተጠቃሚ የሚያደርጉ አሰራሮች ቢሮው እንደሚከተል የገለጹት በቢሮው የዕቅድ ዝግጅት ዳሬክተር አቶ ቴዎድሮስ አበራ ሲሆኑ ግልጽና አሰራሮችን የጋራ የሚደረግበት ዲጂታል የግንኙነት አግባብ ይፈጠራልም ብለዋል።

የክልሉ የ2019 የትምህርት ዘርፍ ዕቅድ በቢሮው የዕቅድ ዝግጅት ባለሙያ አቶ ደረጄ አብዲሳ ቀርቧል። በዚህ የዕቅድ ማናበብ ፕሮግራም ከክልል ፣ ከዞንና ከወረዳ የትምህርት ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል። ዘገባው የቢሮው ኮሙኒኬሽን ዳሬክቶሬት ነው።

Address

Asosa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Benishangul Gumuz Education Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share