02/09/2026
የክረምት በጎ አድራጎት ስፖርታዊ ስልጠና
በአሶሳ
ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም
የክረምት በጎ አድራጎት እንቅስቃሴ አካል የሆነዉ በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች ለታዳጊ ህፃናት እየተሰጠ ያለው ስልጠና በአሶሳ ከተማ ሻንጉል ስቴዲየም ምልከታ ተደረገ።
በምልከታው የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሙያዎች፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስፖርት ኮሚሽን የውድድርና ስልጠና ዳይሬክቶሬት አቶ አጠይብ መሀመድ እና በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች ታዳጊዎችን በማሰልጠን ላይ የሚገኙ አሰልጣኞች ተገኝተዋል።
በወቅቱም የስልጠናው አፈጻጸም፣ የታዳጊ ህፃናት ተሳትፎ እና የስፖርት ችሎታ እድገት ተመልክቷል።
የክረምት ስፖርታዊ ስልጠናው ታዳጊዎች ክረምታቸውን በአግባቡ እንዲያሳልፉ፣ የስፖርት ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ እና ለወደፊት የሀገር ስፖርት ልማት የሚያገለግሉ ተስፋ ያላቸው ስፖርተኞችን ለማፍራት የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።