Benishangul Gumuz Ethics and Anti-Corruption Commission /ቤ/ጉ/ ፀረ-ሙስና/

  • Home
  • Ethiopia
  • Asosa
  • Benishangul Gumuz Ethics and Anti-Corruption Commission /ቤ/ጉ/ ፀረ-ሙስና/

Benishangul Gumuz Ethics and Anti-Corruption Commission /ቤ/ጉ/ ፀረ-ሙስና/ በክልሉ ሙስናና ብልሹ አሠራር ለመልካም አስተዳደር እና ለልማት ማነቆ እንዳይሆን እንሰራለን!!!

የሰዎች መጥፎ አድራጎቶች ዋና ምንጭ፤         **********************የሰውን ልጅ መንፈስ ወደ ውድቀት እና ማህበራዊ ቀውስ ከሚነዱ ነገሮች መካከል የክፉዎች ሦስት መሠረቶች በ...
04/09/2026

የሰዎች መጥፎ አድራጎቶች ዋና ምንጭ፤
**********************
የሰውን ልጅ መንፈስ ወደ ውድቀት እና ማህበራዊ ቀውስ ከሚነዱ ነገሮች መካከል የክፉዎች ሦስት መሠረቶች በመባል የሚታወቁት አጥፊ ባሕርያት እጅግ ጎልተው ይታያሉ። በቡድሂስት አስተምሮት ውስጥ የሰዎች መጥፎ አድራጎቶች እና የዕለት ተዕለት ስቃዮች ዋና ምንጭ ተደርገው የሚወሰዱት ስግብግብነት፣ ቁጣ እና ማታለል ናቸው። እነዚህ አዝማሚያዎች የግለሰቡን አዕምሮ በመቆጣጠር የሞራል እሴቶችን እንዲያጣ እና ህብረተሰቡን ለከፍተኛ መከራ እንዲዳርግ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።

ከመጠን ያለፈ የቁሳቁስ ፍላጎት፣ የገንዘብ ጥማት እና የሥልጣን ፍቅር ከሚያስከትሏቸው አጥፊ ባሕርያት መካከል ስግብግብነት ዋነኛው ነው። ይህ ባሕርይ የተጠናወተው ግለሰብ ምንጊዜም አልበቃኝም በሚል መንፈስ በመነዳት ሁልጊዜ አዳዲስ ሀብቶችን ለማከማቸት ይተጋል። እንዲህ ዓይነቱ ከልክ ያለፈ ራስ ወዳድነት ሰዎችን ወደ ሌብነት፣ የሙስና አዘቅት እና የሌሎችን መብት ያለ አግባብ ወደ መጋፋት ይመራቸዋል። የቁሳቁስ ፍቅር የሰው ልጅን ሕሊና በማጨለም የሕይወትን እውነተኛ ትርጉም እንዲስት ያደርገዋል።

ነገሮች እንደ ፈቃዱ ሳይሆኑ ሲቀሩ ወይም ሲቃወሙት የሚፈነዳው ቁጣ ሌላው የሰው ልጅ መሠረታዊ ፈተና ነው። ጥላቻ፣ ምሬት እና ጠላትነት የተሞላበት ይህ አጥፊ ስሜት የግለሰቡን የአእምሮ ሰላም በመንጠቅ ለከፍተኛ የጤና እክል ይዳርጋል። በቤተሰብ አባላት፣ በቅርብ ወዳጆች እና በሰፊው ማህበረሰብ መካከል የሚፈጠሩ ግጭቶች፣ ጥልና የደም ግፊት መነሳት በቀጥታ ከዚህ አጥፊ ስሜት ጋር የተያያዙ ናቸው። ሰብአዊ መስተጋብርን ከንጹህ ፍቅር ይልቅ በመንፈስ ጭንቀት እንዲጠለፍ ያደርጋል።

እውነታውን በአግባቡ አለመረዳት እና ራስን ማታለል ደግሞ ሦስተኛው ጉዳይ ነው። ትክክለኛውን ከስሕተት፣ መጥፎውን ከጥሩ መለየት የማይቻልበት አእምሮዊ መዛነፍ ለጥፋቶች እንደ ነዳጅ ሆኖ ያገለግላል። ይህ የተሳሳተ አመለካከት የተዛቡ ውሳኔዎች እንዲወሰኑ በማድረግ ሕይወትን ትርጉም በሌለው ጎዳና እንዲመራ ያደርጋል።

እነዚህ ሦስት አጥፊ ባሕርያት እርስ በርስ የተሳሰሩ እና የሰውን አእምሮ የሚቆጣጠሩ የሰንሰለት ኃይሎች ናቸው። ከእነዚህ አስከፊ መረቦች ሙሉ በሙሉ ለመላቀቅ ራስን ማወቅ፣ ጥልቅ ማሰላሰል እና የርኅራኄ ስሜትን ማዳበር እጅግ ወሳኝ ነው። የሰው ልጅ ውስጣዊ ሰላሙን አስጠብቆ ለመኖር የነዚህን መርዞች ተፅዕኖ በንቃት መቃወም ይጠበቅበታል።

ዛዲግ አብርሀ (የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝደንት)

የሙስና ተጋላጭነት ዋነኛ ምክንያቶች፤        ********************የሙስና ተጋላጭነት ማለት አንድ ተቋም፣ የሥራ ሂደት ወይም ሰው ለሙስና ድርጊት በቀላሉ ሊጋለጥ የሚችልበት ሁኔ...
31/08/2026

የሙስና ተጋላጭነት ዋነኛ ምክንያቶች፤
********************
የሙስና ተጋላጭነት ማለት አንድ ተቋም፣ የሥራ ሂደት ወይም ሰው ለሙስና ድርጊት በቀላሉ ሊጋለጥ የሚችልበት ሁኔታ ነው። የሙስና ተጋላጭነትን መለየት ቀድሞ የመከላከያ አሠራሮችንና ቁጥጥሮችን በመዘርጋት ሙስናን ለመከላከል ያስችላል።

☞ ለሙስና ተጋላጭነት ዋነኛ ምክንያቶች

☞ የአሠራር ግልጽነት ማነስ፤
☞ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ለህዝብ ወይም ለተገልጋይ ክፍት አለመሆን፤
☞ ግልጽ ያልሆኑ ህጎች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች፤
☞ የቁጥጥር እና የተጠያቂነት ማነስ፤
☞ የውስጥ እና የውጭ ኦዲት/ቁጥጥር ስርአት መዳከም፤
☞ በስልጣን አለአግባብ መጠቀም ላይ እርምጃ አለመውሰድ (የቅጣት ማነስ)፤
☞ የስልጣን ስብስብነት እና ያልተገደበ ስልጣን፤
☞ አንድ አካል ወይም ግለሰብ ያለ ምንም ጠንካራ ተቆጣጣሪ ብቻውን ውሳኔ የሚሰጥበት አሰራር መኖር፤
☞ የሰራተኞች ዝቅተኛ ጥቅም እና የስራ ተነሳሽነት ማነስ፤
☞ ከኑሮ ውድነት ጋር የማይመጣጠን ክፍያ እና ጥቅማጥቅም አለመኖር።
☞ በህብረተሰቡ ወይም በተቋሙ ውስጥ የነበረው የሥነ-ምግባር እሴት መዳከም እና ለሙስና ታጋሽ የመሆን ባህል መዳበር የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ።

“ትውልድን በሥነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሠራር!”

የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን በተለያዩ አማራጮች ይከታተሉ !!!

page ☞ https://web.facebook.com/bgrseacc/

Telegram Channel ☞ https://t.me/bgrseaccpr

YouTube ☞ https://www.youtube.com/

ለጥቆማ ☞ Web.☞https://www.bgrseacc.gov.et/

Email: ☞ [email protected]

የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በከማሺ ዞን፣ ዛይ ወረዳ የአቅመ ደካማ ቤቶችን ለመገንባት ርክክብ አደረገ።ኮሚሽኑ እንደ ክልል የተጀመረውን የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎ...
30/08/2026

የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በከማሺ ዞን፣ ዛይ ወረዳ የአቅመ ደካማ ቤቶችን ለመገንባት ርክክብ አደረገ።

ኮሚሽኑ እንደ ክልል የተጀመረውን የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራዊ ለማድረግ በከማሺ ዞን፣ ዛይ ወረዳ የ ሁለት አቅመ-ደካማ ቤቶች አዲስ ግንባታ ለማከናወን የቦታ ርክክብ አደረገ።

ኮሚሽኑን ወክለው ርክክቡን ያካሄዱት፣ አቶ ኤሊያስ ወዲሻ እና አቶ ለሜሳ ዲነግዴ፣ ግንባታው በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለነዋሪዎች ለማስረከብ ከፍተኛ ርብርብ እንደሚደረግ ጠቁመዋል፡፡

የበጎ ፈቃድ ሥራዎች የመረዳዳት፣ የመተባበር እና የሰብዓዊነት እሴቶችን የሚያጠናክሩ የመልካም ሥነ-ምግባር ተግባራዊ መገለጫዎች ናቸው ።

ኮሚሽኑ ዝቅተኛ አቅም ላላቸው ተማሪዎች የት/ት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡ድጋፉ ሁሌም በየዓመቱ አንድ ጊዜ የሚደረግ ሲሆን፣ ይህም በዕቅድ ተይዞ ከሚከናውኑ ዓመታዊ የበጎ-ፈቃድ አገልግሎቶች ተጨ...
27/08/2026

ኮሚሽኑ ዝቅተኛ አቅም ላላቸው ተማሪዎች የት/ት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

ድጋፉ ሁሌም በየዓመቱ አንድ ጊዜ የሚደረግ ሲሆን፣ ይህም በዕቅድ ተይዞ ከሚከናውኑ ዓመታዊ የበጎ-ፈቃድ አገልግሎቶች ተጨማሪ ለዚሁ በጎ ዓላማ እንዲውል ታስቦ ከኮሚሽኑ ሰራተኞች ከሚሰበሰብ መዋጮ መሆኑ በድጋፍ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡

ድጋፉን ማድረግ ያስፈለገበት ዋናው ዓላማ፣ ተማሪዎቹ በት/ት ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩ ከማድረጉ በተጨማሪ፣ ለተማሪዎቹ ደጋፊ ማሕበረሰብ ከጎናቸው እንዳለ በማሳየት ማሕበራዊ መስተጋብርን ለማጠናከር እንደሚያግዝ በዝግጅቱ ላይ ተጠቁሟል፡፡

“ትውልድን በሥነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሠራር!”

የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን በተለያዩ አማራጮች ይከታተሉ !!!

page ☞ https://web.facebook.com/bgrseacc/

Telegram Channel ☞ https://t.me/bgrseaccpr

YouTube ☞ https://www.youtube.com/

ለጥቆማ ☞ Web.☞https://www.bgrseacc.gov.et/

Email: ☞ [email protected]

24/08/2026

‎ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
‎*****

‎(አሶሳ፣ ነሐሴ 18/2018 ዓ/ም) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ለ1501ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሰዐወ) የመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

‎አቶ አሻድሊ ሀሰን በመልዕክታቸውም ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለነቢዩ መሐመድ የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።

‎የነቢዩ መሐመድን የመውሊድ በዓል ስናከብር የነብዩን አስተምህሮዎች በመተግበር ሊሆን ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ በዓሉን በመፈቃቀር፣ ተካፍሎ በመብላት፣ ለሌሎች በማዘንና በማካፈል ማክበር እንደሚገባ ገልጸዋል።

‎መላው ህዝበ ሙስሊም ይህንን በዓል ሲያከብር አንድነቱን በማጠናከር፣ በመደጋገፍ፣ ያለውን በማካፈል እና ከአላህ በረከት የሚያስገኝ መልካም ሥራን በመሥራት እንዲሆንም መልዕክት አስተላልፈዋል።

‎አቶ አሻድሊ በዓሉ የሰላም፣ የአብሮነት፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

24/08/2026
ሹመት/ ስልጣን/ የግል ጥቅም የሚገኝበት ዕድል ሳይሆን፤ ሕዝብን ለማገልገል የሚወሰድ ኃላፊነት ነው፡፡ በሕጋዊና ሥነ-ምግባራዊ መንገድ የሠራ ሰው ከሹመት ቢነሳም የሚቆጨው ያልበላው ጥቅም ሳይ...
21/08/2026

ሹመት/ ስልጣን/ የግል ጥቅም የሚገኝበት ዕድል ሳይሆን፤ ሕዝብን ለማገልገል የሚወሰድ ኃላፊነት ነው፡፡ በሕጋዊና ሥነ-ምግባራዊ መንገድ የሠራ ሰው ከሹመት ቢነሳም የሚቆጨው ያልበላው ጥቅም ሳይሆን፣ ለሕዝብ መሥራት የነበረበትን ሥራ አላጠናቀኩም ብሎ ነው፡፡ እውነተኛ ኃላፊ/ ሠራተኛ/ ከስልጣን ሲወርድ እራሱን መጠየቅ ያለበት ‘‘ ምን በላሁʔ'' ብሎ ሳይሆን፤‘‘ምን ሠራሁ፣ ምን አስቀረሁ፣ ለሕዝብ ምን ጥቅም አመጣሁʔ'' ብሎ መሆን አለበት!

“ትውልድን በሥነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሠራር!”

የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን በተለያዩ አማራጮች ይከታተሉ !!!

page ☞ https://web.facebook.com/bgrseacc/

Telegram Channel ☞ https://t.me/bgrseaccpr

YouTube ☞ https://www.youtube.com/

ለጥቆማ ☞ Web.☞https://www.bgrseacc.gov.et/

Email: ☞ [email protected]

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 4ኛው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሥራ ጀመረ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 4ኛው የበለስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በዛሬው ዕለት ተመርቆ ሥራ ጀምሯል።የክልሉ...
19/08/2026

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 4ኛው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሥራ ጀመረ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 4ኛው የበለስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በዛሬው ዕለት ተመርቆ ሥራ ጀምሯል።

የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድር ጌታሁን አብዲሳ ማዕከሉን በመረቁበት ወቅት እንዳሉት፥ መሶብ የአንድ ማዕከል የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን በማሻሻል የዜጎችን እንግልት የሚያስቀር ምቹ ሁኔታን የፈጠረ ነው።

‎የበለስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በክልሉ አራተኛው ማዕከል መሆኑን ገልጸው፤ የቤጉ መሶብ፣ የአሶሳ እና የባምባሲ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎቶች ቀደም ሲል ወደ ሥራ መግባታቸውን አስታውሰዋል።

በክልሉ በተዘረጋው ዘመናዊ የአገልግሎት ስርዓት እስካሁን በ124 የአገልግሎት ዘርፎች ከ53 ሺህ 900 በላይ ዜጎች የዲጂታል አገልግሎት ማግኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህም የእርካታ ደረጃውን 99 ነጥብ 2 ከመቶ ማድረስ ተችሏል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

የመንግሥት ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጣቸውን በቴክኖሎጂ በሥርዓት ወደሚመራ ተቋማዊ ብቃት ለመሸጋገር መሶብ አንዱ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል።

FBC እንደዘገበው

"የተንዛዛ አሰራር ጉቦ ሰጪን፤ ጉቦ ሰጪ ደግሞ ጉቦ ተቀባይን ይፈጥራል፤ ሙስናን የምንሸፋፍንበት ባሕላችን ዛሬውኑ መለወጥ አለበት፤ የተጀመሩ የዲጂታል ሥራዎችም ይበልጥ መጠናከር አለባቸው" -...
19/08/2026

"የተንዛዛ አሰራር ጉቦ ሰጪን፤ ጉቦ ሰጪ ደግሞ ጉቦ ተቀባይን ይፈጥራል፤ ሙስናን የምንሸፋፍንበት ባሕላችን ዛሬውኑ መለወጥ አለበት፤ የተጀመሩ የዲጂታል ሥራዎችም ይበልጥ መጠናከር አለባቸው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Via፡FBC

Address

Asosa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Benishangul Gumuz Ethics and Anti-Corruption Commission /ቤ/ጉ/ ፀረ-ሙስና/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Benishangul Gumuz Ethics and Anti-Corruption Commission /ቤ/ጉ/ ፀረ-ሙስና/:

Shortcuts

Share