02/09/2026
በሎማ ቦሳ ወረዳ የዳውሮ ብሄር ዘመን መለወጫ ''ቶኪ በኣ'' በዓል በቀበሌ ደረጃ ተከበረ
የዳውሮ ብሄር ዘመን መለወጫ ቶኪ በኣ በዓል በሎማ ቦሳ ወረዳ በቀበሌ ደረጃ በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች በድምቀት ተከብሯል።
ቶኪ በኣ ከጥንት ጀምሮ እየተከበረ የመጣ በዳውሮ ብሄር ዘንድ ከሌሎች በዓላት ልዩ ትርጉም ያለው በዓል መሆኑን የባህል ሽማግሌዎቹ ተናግራዋል።
በብሄሩ ዘንድ በዚህ በዓል ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲስ ዓመት መሻገርን፣ አዲስ ተስፋና ሀሳብ ማስጀመሪያ፣ ተራርቀው የነበሩ አንድ የሚሆኑበት፣ የተጣሉ የሚታረቁበት፣ አቅመ ደካሞች የሚረዱበት፣ የዘመን መለወጫና ሌሎች በርካታ ማህበራዊና ባህላዊ ዕሴቶችን የሚያንጸባርቅ መሆኑን ተናግረዋል።
ለበዓሉ ድምቀት ከጥንትም በተለመደ ስርዓት አባቶች፣ እናቶች፣ ሴትና ወንድ ወጣቶች እያንዳንዳቸው ለረጅም ጊዜ የበኩላቸውን የተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚያደርጉም በመግለጽ።
በዓሉ በውስጡ በርካታ ባህላዊ፣ ታሪካዊና ማህበራዊ ዕሴቶችን የያዘ በመሆኑ በዓለም የሳይንስና ትምህርት ድርጅት ዩኔስኮ ላይ ለማስመዝገብ እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ከግብ እንዲደርስ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም ተናግረዋል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉን 👇
Follows us via👇
page https://www.facebook.com/profile.php?id=100064822177806
Telegram channel https://t.me/lomabosaworedgovtcomnctnaffairs/email [email protected]//
https://www.youtube.com/
http://twitter.com/
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!