Sidama National Regional State Health Bureau

Sidama National Regional State Health Bureau Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Sidama National Regional State Health Bureau, Government Organization, Awassa.

28/05/2026

የሲዳማ ክልል የጤና ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ!

ክልሉ ከመዋቀሩ በፊት የነበረው ዝቅተኛ የጤና ሽፋን እና የነዋሪዎች እንግልት ዛሬ ታሪክ ሆኗል።

በልዩ ትኩረት እና በታላቅ ቅንጅት የተገነቡ ዘመናዊ የጤና መሰረተ ልማቶች፣ የጤና ባለሙያዎች ተነሳሽነት እንዲሁም በጤና ኤክስቴንሽን የተመዘገቡ ስኬቶች የእናቶችና የህጻናትን ህይወት እየታደጉ ይገኛሉ።

ከተግዳሮት ወደ ስኬት የተሻገረውን የሲዳማ ጤና ዘርፍ ጉዞ በቪዲዮው ይመልከቱ!



የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
20/09/2018 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር  አቶ ደስታ ሌዳሞ በሀዋሳ ከተማ ባለ ስምንት ወለል የሆስፒታል ህንፃን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማትን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ። የሲዳማ ክልል መንግ...
27/05/2026

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ በሀዋሳ ከተማ ባለ ስምንት ወለል የሆስፒታል ህንፃን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማትን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ።

የሲዳማ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ግንቦት 19/2018 ዓ.ም

በሀዋሳ ከተማ የሚገኘው የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል፣ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በሚሆን ተጨማሪ በጀት የተከናወነውን ባለ 8 ፎቅ (B+G+8) ዘመናዊ የማስፋፊያ ሕንፃ ዛሬ በይፋ ተመርቆ ወደ አገልግሎት ገብቷል።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ ፕሮጀክቱን በይፋ መርቀው የከፈቱ ሲሆን፣ ግዙፉ የጤና ፕሮጀክት በሲዳማ ክልል የጤና ዘርፍ እየተመዘገበ ያለውን ፈጣን ለውጥ የሚያሳይ ታላቅ የልማት ምልክት መሆኑ ተገልጿል።

ከዘመናዊ የጤና አገልግሎት ባሻገር፣ ሆስፒታሉ የሪፈራል ህክምና አቅምን በማሳደግ ለከተማዋና ለአካባቢው ህብረተሰብ ተደራሽና ጥራት ያለው ህክምና ለመስጠት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወትም ጠቁመዋል።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ፣ በሀዋሳ ከተማ የሚገኘው የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በሚሆን ተጨማሪ በጀት የተገነባው ባለ 8 ፎቅ (B+G+8) ዘመናዊ የማስፋፊያ ሕንፃ፣ የሀዋሳ ከተማን የህክምና ዘርፍ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ፣ የሚሊኒየም ጤና ጣቢያ አዲሱ ባለ (G+3) ሕንፃ ከዚህ ቀደም ሲሰጥ ከነበረው አገልግሎት በተጨማሪ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ተቋም አገልግሎቶችን በስፋት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን አቶ ጥራቱ በየነ ገልጸዋል።

አዲሱ ሕንፃ በዘመናዊ ህክምና መሳሪያዎችና ስፔሻላይዝድ አገልግሎቶች የተደገፈ ሲሆን፣ የውስጥ ደዌ፣ የህፃናት፣ የእናቶችና የወሊድ፣ የቀዶ ሕክምና፣ የድንገተኛ ሕክምና፣ ICU፣ የራዲዮሎጂና የምስል ምርመራ እንዲሁም የላቦራቶሪ አገልግሎቶችን በተሟላ አቅም ለመስጠት የሚያስችል መሆኑ ተጠቁሟል።

ፕሮጀክቱ ከጤና አገልግሎት ማሻሻል ባለፈ፣ ሀዋሳን በጤና ዘርፍ ተመራጭ መዳረሻና የሜዲካል ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የጎላ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።

በተመሳሳይ የሚሊኒየም ጤና ጣቢያ አዲሱ ባለ (G+3) ሕንፃ የእናቶችና ሕፃናት ጤና፣ የድንገተኛ ሕክምና፣ የላቦራቶሪ፣ የፋርማሲ፣ የክትባት እና የተላላፊ በሽታዎች መከላከልና ቁጥጥር አገልግሎቶችን በተሟላ ሁኔታ ለመስጠት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

እነዚህ ዘመናዊ የጤና ፕሮጀክቶች በሀዋሳ ከተማና በሲዳማ ክልል የጤና ዘርፍ ልማትን ከማፋጠን ባለፈ፣ በህብረተሰቡ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖራቸው ተገልጿል።

በሥነ-ምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል አመራሮች፣ የጤና ዘርፍ ኃላፊዎች፣ የሆስፒታሉ ማኔጅመንትና የጤና ባለሙያዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የልማት አጋሮች፣ ኮንትራክተሮች፣ እንግዶችና በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል ::


የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
19/09/2018 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

በጤናው ሴክተር የአገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም  ዙሪያ ለክልሉ ጤና ቢሮ እና ለተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ።የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ግንቦት 18/2018 ዓ.ምየሲዳማ ክ...
26/05/2026

በጤናው ሴክተር የአገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ዙሪያ ለክልሉ ጤና ቢሮ እና ለተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ግንቦት 18/2018 ዓ.ም

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በጤናው ሴክተር የአገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ዝግጅትና ትግበራ ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊ ወ/ሮ እመቤት መኮንን በስልጠና ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት የጤናው ሴክተር ሪፎርም በሴክተሩ ፈጣንና ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው፤

በሪፎርሙ ተግባራዊ የሚደረጉ የአሠራር ስርዓቶችና ሲስተም በዘርፉ ብቁና ተወዳዳሪ ባለሙያዎችን ለመፍጠር እንደሚረዳ፣ ዘርፉን ወደ ዲጂታል ለማሸጋገር ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ባጠቃላይ አመራሩንም ሆነ ባለሙያውን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን በመረዳት ለፎርሙ ስኬት ሁሉም ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል።

ሀላፊዋ አክለውም ሪፎርሙን በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ በጤናው ዘርፍ ለዓመታት ሲንከባለሉ የቆዩ ውዝፍ ችግሮችን ለመፍታትና ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለመሻገር የሚያስችል በመሆኑ የጤናው ሴክተርና ተጠሪ ተቋማት አመራርና ባለሙያዎች ለሪፎርሙ ልዩ ትኩረት መስጠት እንዲችሉ በአፅንኦት ተናግረዋል።

በጤና ሚኒስቴር የብቃትና ሰው ሀብት ልማት አስተዳደር ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሀብታሙ ደምሴ በጤናው ሴክተር የአገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ዙሪያ ባቀረቡት ሰነድ እንዳብራሩት ሀገራዊ ሪፎርም እንዲሰሩ ከተመረጡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ውስጥ ጤና ሚኒስቴር በ"ዌቭ አንድ" (Wave 1) ተመርጦ የሪፎርም ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።

የጤናዉን ዘርፍ የሪፎርም መነሻዎች፣ መዳረሻዎችና ተግዳሮቶችን እንዲሁም አስቻይ ሁኔታዎች እና በክልል ደረጃ የሚሰሩ ስራዎችን በተገቢው በመረዳት ለሪፎርሙ ተግባራዊነት መረባረብ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

ሪፎርሙ በዋናነት በ9 አምዶች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሠራ የገለፁት አቶ ሀብታሙ የተቋም ግንባታን ለማረጋገጥ፣ተደራሽ፣ቀልጣፋና ጥራቱን የጠበቀ የጤና አገልግሎት ስርዓት ለመዘርጋት ዕድል የሚያሰፋ በመሆኑ ክልሎች የሪፎርሙን መነሻ ሐሳብ በመያዝ የትግበራ ፍኖተ-ካርታ (Road map) አስቀምጠው እንዲሠሩ የሚያስችል ነው ብለዋል።

በዝግጅት ምዕራፍ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት የተመላከቱ ሲሆን የሪፎርም ሥራው የጤናውን ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመንና የሰው ሀብት ልማቱን ብቁ ለማድረግ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተብራርቷል።

በግንዛቤ መፍጠሪያ መድረኩ ላይ የጤና ቢሮ የማኔጅመንት አባላት ፣የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የጤና ሚኒስቴር የሪፎርም አማካሪዎች ተገኝተዋል።


የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
18/09/2018 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

''ጤናማና የተማረች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ ብልጽግናን ይምረጡ ! ''የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ሠራተኞች​በሲዳማ ክልል የብልጽግና ፓርቲያችን ዓላማና የለውጥ አጀንዳዎች በመደገፍ ታላቅ ህዝባ...
26/05/2026

''ጤናማና የተማረች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ ብልጽግናን ይምረጡ ! ''

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ሠራተኞች

​በሲዳማ ክልል የብልጽግና ፓርቲያችን ዓላማና የለውጥ አጀንዳዎች በመደገፍ ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

የክልሉ ነዋሪዎች በነቂስ በመዉጣት በከፍተኛ ስሜትና ወኔ ፣ ብልፅግና ፓርቲ የጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ከዳር ለማድረስ ያላቸውን የጸና ዝግጁነትና ቁርጠኝነት በአደባባይ እየገለፁ ነዉ ።

የክልሉ ጤና ቢሮ እና ለቢሮው ተጠሪ የሆኑ መ/ቤቶች ሠራተኞች የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት ድጋፊ እየሰጡ ነው ።

# ብልፅግናን ይምረጡ!
#‎ ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው!

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
18/09/2018 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

የግል ጤና ተቋማት የሪፖርት ቅብብሎሽ ስርዓትን ማጠናከር ለማህበረሰቡ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ወሳኝ ነው።  የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ግንቦት 14/2018 ዓ.ምየሲዳማ ክ...
22/05/2026

የግል ጤና ተቋማት የሪፖርት ቅብብሎሽ ስርዓትን ማጠናከር ለማህበረሰቡ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ወሳኝ ነው።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ግንቦት 14/2018 ዓ.ም

የሲዳማ ክልል ጤናና ጤና ነክ አገልግሎት ግብአት ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በሀዋሳ ከተማ ለሚገኙ የግል ክሊኒክ ባለቤቶች በተቋም ሪፖርት ቅብብሎሽ ስርዓት ላይ ስልጠና ሰጥቷል።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ምክትልና የጤና ፕሮግራም ዘርፍ ሀላፊ አቶ በላይነህ በቀለ በመልዕክታቸው በጤናው ሴክተር ፍትሐዊና ለሁሉም ተደራሽ የሆነ የጤና አገልግሎት ለማድረስ መረጃን መሠረት ያደረገ ውሳኔ እጅግ ወሳኝ ሲሉ ገልፀው፣ የግሉ ዘርፍ በመንግስት የጤና ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያሉ ክፍተቶችን በመሙላት የህብረተሰቡን የጤና ፍላጎት ለማሟላት እያደረጉ ስላለው ጥረት አመስግነዋል።

ተቋማቱ ሙያን መሰረት ባደረገ፣የሙያ ስነ ምግባርን በጠበቀ እና በመንግስት የወጡ የህክምና መመሪያዎችንና ፕሮቶኮሎችን ባከበረ መልኩ እንደ መንግስት ጤና ተቋማት የተሟላና ወቅታዊ ሪፖርት የሚልኩና ግብረ መልስ በተገቢው የሚቀበሉና ተግባራዊ የሚያደርጉ ተቋማት መሆን እንደሚጠበቅባቸው በአፅንኦት ተናግረዋል።

የሲዳማ ክልል ጤናና ጤና ነክ አገልግሎትና ግብአት ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ቡሪሶ ቡላሾ በበኩላቸው የማህበረሰቡን የጤና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በመንግስትም ሆነ በግል ጤና ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶች ጥራታቸውን እና ደረጃቸውን የጠበቁ ሊሆን እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም በክልሉ በርካታ የጤና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መኖራቸውንና ከነዚህ ውስጥ 51 በመቶ ያህሉ የግል ጤና ተቋማቶች መሆናቸውን ጠቁመው ፣ አብዛኞቹ በሀዋሳ ከተማ ውስጥ ቢገኙም የሰሩትን ስራ በተገቢው ሪፖርት በማድረግ ረገድ ክፍተት በመስተዋሉ ክፍተቱን ለመሙላት ስልጠና መዘጋጀቱንና ከስልጠናው በኋላ ግን ሁሉም የግል ጤና ተቋማት 100% የሚጠበቅባቸውን ሪፖርት በወቅቱ ሊልኩ እንደሚገባ አሳስበዋል ።

የግል የጤና ተቋማት ለህብረተሰቡ ቀልጣፋ፣ ጥራት ያለውና ተደራሽ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ተቋማት የሪፖርት ቅብብሎሽ ስርዓታቸው ወጥ በሆነ ስታንዳርድ መሰረት ሊሆን እንደሚገባ የዘርፉ ባለሙያዎች በስልጠናው ላይ ባቀረቡት ሰነዶች ላይ አመላክተዋል።

የግል ተቋማት ባለቤቶች እንደዚህ አይነቱ መሰል ስልጠና በመረጃ አያያዝ ረገድ ያሉትን ውስንነቶች ለመቅረፍ ትልቅ አቅም የሚፈጥር እንደሆነ በመግለጽ በግሉ ጤና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለማረምና የበኩላቸውን አስተዋጾ ለማበርከት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።


የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
14/09/2018 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

22/05/2026

የእናቶችና የህፃናት ጤናን ለመጠበቅ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የትጋት ጉዞ !

የሲዳማ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ በዘመናዊ የህክምና መሣሪያዎች የተደገፉ የጤና ተቋማትን በማጠናከር፣ ብቁ እና ምስጉን የጤና ባለሙያዎችን በማዘጋጀት ፣በቁርጠኛ የአመራር ብቃት የእናቶችና የህፃናት ጤና እንዲጠበቅ ቀን ከሌሊት እየሠራ ይገኛል።

ቢሮው እናቶች ከእርግዝና ክትትል ጀምሮ እስከ ወሊድና ድህረ ወሊድ አገልግሎት ድረስ የተሟላ የጤና እንክብካቤ እንዲያገኙ፣ ህፃናትም ጤናማና ደስተኛ ሕይወት እንዲኖራቸው በትጋት እየሰራ ይገኛል።

“ጤናማ እናት፤ ብሩህ ትውልድ፤ ጠንካራ ማህበረሰብ!”





የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
14/09/2018 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

21/05/2026

የጭንቅ ቀን ጋሻ — ከከባድ ህመም እና ከከፍተኛ ወጪ የታደገው የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን !

የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አባል በመሆናቸው ከድንገተኛ ህክምና ወጪ እንደታደጋቸው የገለጹት አስተያየት ሰጪዎች ፤ እራሳቸውም ሆኑ ቤተሰቦቻቸው ያለምንም የኢኮኖሚ ጫና የነጻ ህክምና አገልግሎት እያገኙ በመሆናቸው የተሰማቸውን ታላቅ ደስታ ገልጸዋል።

የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን — ለጤናችን ዋስትና!

ቪዲዮውን አይተው ለሌሎችም ያጋሩት

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
13/09/2018 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በወንሾ ወረዳ የተለያዩ አገልግሎት ሠጪ ተቋማትን መርቀው ስራ አስጀመሩየሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ወንሾ ወረዳ የ...
20/05/2026

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በወንሾ ወረዳ የተለያዩ አገልግሎት ሠጪ ተቋማትን መርቀው ስራ አስጀመሩ

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ወንሾ ወረዳ የተለያዩ አገልግሎት ሠጪ ተቋማትን መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

በምረቃው የወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ህንፃ፣ፍርድ ቤት ህንፃ፣ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ህንፃና የፖሊስ ጽ/ቤት ህንፃ እንዲሁም የጤና ተቋም ማስፋፊያ ይገኝበታል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በምረቃው ወቅት እንደገለፁት ህዝብ የጠየቃቸውን ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ እየመለስን እንገኛለን በማለት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ነው ብለዋል።

ምንጭ :- የክልሉ ርዐሰ መስተዳድር ጽ/ቤት

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
12/09/2018 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

የመካንነት እና የስነ-ተዋልዶ ጤና ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል ልዩ የሕክምናና የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ በሀዋሳ ከተማ መካሄድ ጀመረ።     የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ግንቦት 12/2018 ዓ.ምየ...
20/05/2026

የመካንነት እና የስነ-ተዋልዶ ጤና ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል ልዩ የሕክምናና የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ በሀዋሳ ከተማ መካሄድ ጀመረ።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ግንቦት 12/2018 ዓ.ም

የመካንነት እና የስነ-ተዋልዶ ጤና ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል ልዩ የሕክምናና የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ፣ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ፣ከሲዳማ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ እና ከአላቲዮን አጠቃላይ ሆስፒታል ጋር በመተባበር በሀዋሳ ከተማ ጀምሯል፡፡

በፕሮግራሙ ማስጀመሪያ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የሕክምና አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙንጣሻ ብርሃኑ በንግግራቸው ፣ የመካንነት ጉዳይ በአገርና በክልል ደረጃ ከፍተኛ የሕዝብ ጤና ችግር (Public Health Problem) እየሆነ መምጣቱን ጠቁመዋል። ዘመቻው በችግሩ ዙሪያ ያሉ የተሳሳቱ አመለካከቶችን ለመቀየርና ግንዛቤን ለማስፋት እንዲሁም የመካንነት ችግር ሊደርስባቸው የሚችል የህብረተሰብ ክፍሎችን ችግር ለመቅረፍ ትልቅ ሚና እንዳለው አስረድተዋል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍጹም ወ/ገብርኤል በበኩላቸው ፤ የሕክምና ቡድኑ ወደ ሀዋሳ መምጣቱን ሲያደንቁ ፦ "ታካሚዎች ባሉበት ቦታ መድረስ መቻል አለበት በሚል የተጀመረው ይህ ንቅናቄ፣ ተደራሽነትን ለማረጋገጥና የተቀናጀ ሕክምናን በዘላቂነት ለመቀጠል ትልቅ መነቃቃት የፈጠረ ነው " ብለዋል።

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የሕክምናና ትምህርት አገልግሎት ዋና ዳይሬክቶሬት ዶ/ር ለሚ በላይ እንደገለጹት ፣ ዘመቻው ተደራሽነትን ማስፋት፣ ማኅበረሰቡ ዘንድ መካንነት እንደማንኛውም በሽታ ታይቶ እንዲታከም ግንዛቤ መፍጠር እና እዚያው መፍትሔ ለሚያገኙት ሕክምና ሰጥቶ ከፍተኛ የላቀ ሕክምና ለሚያስፈልጋቸው ደግሞ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሚመሩበትን የሪፈራል ሥርዓት መዘርጋት የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ዛሬ በሀዋሳ ከተማ በሚገኙ በሀዋሳ ሕክምና ኮሌጅ ኮምፕሬሄንስቪ ሆስፒታል እና በአላቲዮን ጠቅላላ ሆስፒታል የተጀመሩ አገልግሎቶች ፥ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ቡድን ተግባር በዋናው ማዕከል ላይ ብቻ ተወስኖ የቆየውን አገልግሎት ተደራሽነቱን ለማስፋት ታላሚ ያደረገ መሆኑ ተብራርቷል፡፡

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የመካንነትና የሥነ-ተዋልዶ ሕክምና ማዕከል ዋና ኃላፊ ዶክተር መሠረት አንሳባ በመልዕክታቸው ፦በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ሥር የሚገኘው የመካንነትና የሥነ-ተዋልዶ ሕክምና ማዕከል በሀዋሳ ያካሄደው የሕክምና ዘመቻ በማህበረሰቡ ዘንድ የመካንነት ጉዳይ በግልጽ እንዲነሳ እና ተደራሽ የሕክምና አገልግሎት እንዲሰጥ በማለም እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም ከግንቦት 12 እስከ 14 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆየው በዚህ ልዩ የሕክምና ዘመቻ ፤ የአካባቢው ማህበረሰብ እና የሥነ-ተዋልዶ ጤና ችግር ያለባቸው ጥንዶች በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ፣በአላቲዮን አጠቃላይ ሆስፒታል ፣አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል በመገኘት አገልግሎቱ እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል፡፡


የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
12/09/2018 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

Address

Awassa

Telephone

+251462211767

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sidama National Regional State Health Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share