Sidama National Regional State Road Development &Transport Bureau

Sidama National Regional State Road Development &Transport Bureau RD&TB

‎Sidaamu Qoqqowira Mootimmate Owaante Woyyeessate Uurrinshuwate Riforme Assinanni Gede Qoqqowu Kaabine Gumultu‎‎Sidaamu ...
28/08/2026

‎Sidaamu Qoqqowira Mootimmate Owaante Woyyeessate Uurrinshuwate Riforme Assinanni Gede Qoqqowu Kaabine Gumultu

‎Sidaamu Qoqqowira deerra deerranko mootimmatenni uynanni owaante rakkinota, lifixanna owaatamaanote orao ajishshannota hattono, qansootu kasseenya luphi assitannota ikkitanno gede uurrinshuwate riforme assinanni gede qoqqowu kaabine gumultino.

‎Qoqqowoho dagate fakkana owaante uytanno uurrinshuwa giddonni Hawaasi Quchuminna Sidaamu Qoqqowi Hodhishshu Biiro uytanno owaante lainohunni noo mitiimma bande xiinxallo assinoonni.

‎Hatte uurrinshuwa sooreeyye mitiimma baddenna malu doorshuwa xiinxallatenni shiqishshino ripoorteno qoqqowu kaabine hajo la'annonsa bissa ledo seekkite keentino.

‎Kaabine keenotenni bandoonni hajubba la'e; taalannore taashsh*te; shiqqino riformete doorshuwa loosu aana hossanno gede gumultino.

‎Uurrinshuwate riformeti qara mixono mootimma uytanno owaante lifixanna baalanko iillitannota assatenni owaatamaanote yannanna fulo ajishatenninna ragiweelo orao hoolatenni qansootu kasseenna luphi assate.

በሲዳማ ክልል የመንግሥት አገልግሎቶችን ለማሻሻል የተቋማት ሪፎርም እንዲካሄድ በክልሉ ካቢኔ ተወሰነ

በሲዳማ ክልል በየደረጃው በመንግሥት የሚሰጡ አገልግሎቶች ፈጣን፣ ቀልጣፋና የተገልጋዮችን እንግልት የሚቀንሱ እንዲሁም የዜጎችን እርካታ የሚያሳድጉ እንዲሆኑ የተቋማት ሪፎርም እንዲካሄድ በክልሉ ካቢኔ ተወስኗል።

በክልሉ ሰፊ የሕዝብ ተጠቃሚነት ካላቸው ተቋማት መካከል የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር እና የሲዳማ ክልል ትራንስፖርት ቢሮ የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች በተመለከተ ያሉ ችግሮች ተለይተው ጥናት ተካሂዷል።

የተቋማቱ ኃላፊዎች ችግሮቹን በመለየት እና የመፍትሔ አማራጮችን በማጥናት ያቀረቡት ሪፖርትም በክልሉ ካቢኔ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በጥልቀት ተገምግሟል።
ካቢኔው በግምገማው የተለዩ ጉዳዮችን በመመልከት ተጨማሪ ማሻሻያዎችን በማከል የቀረቡት የሪፎርም አማራጮች ተግባራዊ እንዲሆኑ አጽድቋል።

የተቋማት ሪፎርሙ ዋና ዓላማም የመንግሥት አገልግሎቶችን ቀልጣፋና ተደራሽ በማድረግ፤ የተገልጋዮችን ጊዜና ወጪ በመቀነስ እና አላስፈላጊ እንግልትን በማስወገድ የዜጎችን እርካታ ማሳደግ ነው።

የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ከክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጋር በመቀናጀት በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን የመንገድ ደህንነት ቁጥጥር ሥራ መከናውኑ ተገለፀ::=======================...
28/08/2026

የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ከክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጋር በመቀናጀት በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን የመንገድ ደህንነት ቁጥጥር ሥራ መከናውኑ ተገለፀ::
===============================

የተቀናጀ ድንገተኛ ቁጥጥር ቡድን በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ዳሌ ወረዳ መሰንቀላና ይርጋአለም ከተማ አስተዳደር ; አዎዳ ካምፖስና አቦስቶ ፖሊስ ማሰልጠኛ አካባቢ በተመረጡ የቁጥጥር ቀጠናዎች የቁጥጥር ስራዎች መከናውኑ ተገልፆዋል::

በየደረጃው ካለው አካላት ጋር በመቀናጀት የመንገድ ደህንነት ትራፊክ ፍስትን በመቆጣጠር በዋናነት ላልተፈቀደ አገልግሎት ፣ትርፍ ተሳፋሪ መጫን፣ሶስተኛ ወገን፣የጭነት ብቃት ማረጋገጫ ፣የቴክኒክ ምርመራ ቦሎ፣የትራፊክ ተቆጣጣሪ ትዕዛዝ አለማክበር መጣስ፤መንጃ ፍቃድና ሌሎች ደንብ መተላለፎች ላይ ትኩረት በመስጠት የተቀናጀ የቁጥጥር ሥራ ተሰርቷል::


በተቀናጀ ቁጥጥር ሥራ በአጠቃላይ 302 ተሽከርካሪዎች የታዩ ሲሆን 11 አሽከርካሪዎች ደንብ ተላልፈው በመገኘታቸው 28,800 (ሃያ ስምንት ሺህ ስምንት መቶ ብር) እንዲቀጡ ተደርጎ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ተደርጓል::

በዕለቱም በይርጋለም ከተማ አስተዳደር በመናኸሪያ ዉስጥ ለአሽከርካሪዎች፣ለረዳቶች፣ተሳፉሪዎችና ለተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች በቁጥር 108 ለሚሆኑት የትራፊክ አደጋንና ሕግ ማስከበርን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ ተሠርቷል።

የ3ኛ ወገን ያላሟሉ 3 ተሽከርካሪዎች በህጉ መሠረት እርምጃ እንዲወሰድባቸው ተደርጓል።

የተቀናጀ የቁጥጥር ቡድን ሥራ በሌሎች ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የቁጥጥር ሥራ ተጠናክሮ የሚቀጥል እንደሆነ ታውቋል::

================================
የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይረክቶሬት
ነሐሴ, 2018 ዓ.ም

የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ከክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጋር በመቀናጀት የሚደረገው የመንገድ ቁጥጥር ሥራ በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ተጠናክሮ ቀጥሏል::=======================...
28/08/2026

የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ከክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጋር በመቀናጀት የሚደረገው የመንገድ ቁጥጥር ሥራ በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ተጠናክሮ ቀጥሏል::
==============================

በክልል ደረጃ የተቋቋመው የድንገተኛ የመንገድ ትራፊክ የቁጥጥር ቡድን በደቡባዊ ሲዳማ ዞን አለታ ወንዶ ወረዳ ፣አለታ ወንዶ ከተማ አስተዳደር፣ አለታ ጩኮ ወረዳ፣ አለታ ጩኮ ከተማ አስተዳደርና ዳራ ቀባዶ ወረዳዎች በተመረጡ የቁጥጥር ቀጠናዎች የቁጥጥር ስራዎች ተሰርቷል::

በየደረጃው ካለው አካላት ጋር በመቀናጀት የመንገድ ደህንነት ትራፊክ ፍሰት በዋናነት ላልተፈቀደ አገልግሎት ፣ትርፍ ተሳፋሪ መጫን፣የ3ኛ ወገን፣የብቃት ሜረጋገጫ ቦሎ፣የትራፊክ ተቆጣጣሪ ትዕዛዝ አለማክበር መጣስ፤መንጃ ፍቃድና ሌሎች ደንብ መተላለፎችን መነሻ በማድረግ ቁጥጥር ተደርጓል::

ደንብ መተላላፎችን መሠረት ያደረገ የተቀናጀ የቁጥጥር ሥራ የተሠራ ሲሆን በዕለቱ አጠቃላይ 3
479 ተሽከርካሪዎች የተዩ ሲሆን 46 አሽከርካሪዎች ደንብ ተላልፈው በመገኘታቸው 87,500 (ሰማኒያ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር) ለመንግስት ገቢ እንዲሆን መደረጉ ተገልፆዋል::

በዕለቱም በአለታ ወንዶ መናኸሪያ ለአሽከርካሪዎች፣ለረዳቶች፣ተሳፉሪዎችና ለተለያዩ ሕብረተሰብ 193 ለሚሆኑት የትራፊክ አደጋንና ሕግ ማስከበርን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ ተሠርቷል።

በየደረጃው ካለው መዋቅር ጋር የተሠሩ ተግባራትን በመገምገም ግብረመልስ በመስጠት የህግ ማስከበር ሥራው ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አቅጣጫ ተቀምጧል።

በቀጣይም የክልሉ የተቀናጀ የቁጥጥር ቡድን ሥራ በሌሎች ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የቁጥጥር ሥራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡===============================
የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ነሐሴ, 2018 ዓ.ም

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ማሰልጠኛ ማዕከል ግንባታ 85 በመቶ ደርሷልአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21/2018 ዓ.ም. (ትሎሚ) – በቃሊቲ እየተገነባ የሚገኘው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ...
28/08/2026

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ማሰልጠኛ ማዕከል ግንባታ 85 በመቶ ደርሷል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21/2018 ዓ.ም. (ትሎሚ) – በቃሊቲ እየተገነባ የሚገኘው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ማሰልጠኛ ማዕከል ግንባታ 85 በመቶ አፈጻጸም ላይ መድረሱ ተገለጸ።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ደንጌ ቦሩ ዛሬ በግንባታ ሥፍራው ተገኝተው የማዕከሉን የግንባታ ሂደት ተመልክተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው በጉብኝታቸው ወቅት የግንባታው አፈጻጸም አበረታች መሆኑን ገልጸው፣ ቀሪ ሥራዎች በአጭር ጊዜ ተጠናቀው ማዕከሉ ለአገልግሎት ዝግጁ እንዲሆን አቅጣጫ ሰጥተዋል።

ማዕከሉ ሲጠናቀቅ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የሥልጠና የልህቀት ማዕከል በመሆን፣ የዘርፉን የሰው ኃይል በማብቃት ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ የሚያስፈልገውን የሙያ ብቃት ለማሳደግ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው አቶ ደንጌ ገልጸዋል።

ማዕከሉ 22 የሥልጠና ክፍሎች፣ 39 የሰልጣኞች ማደሪያ ክፍሎች እንዲሁም ለኦንላይን ሥልጠናና ለቪዲዮ ኮንፈረንስ የሚያገለግሉ አራት ስማርት ክፍሎች ያካተተ ነው።

በተጨማሪም 34 ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚችል የቤዝመንት ማቆሚያ ሥፍራ ያለው ሲሆን፣ በምድረ ግቢው ውስጥ ደግሞ እስከ 89 ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚያስችል ሥፍራ ተዘጋጅቷል።

ማዕከሉ እስከ 200 ሰዎችን የሚይዙ ሁለት ዘመናዊ አዳራሾችንም ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የመሠረተ ልማት ማስፋፊያ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ መቅደም ማቴዎስ እንደገለጹት፣ ማዕከሉ ቤዝመንትና ግራውንድ ወለልን ጨምሮ ባለ 10 ወለል ዘመናዊ ሕንፃ ሲሆን፣ የሰልጣኞች ማደሪያ ክፍሎችንና የአስተዳደር ሕንፃንም ያካትታል።

የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ባህራይ ታደሰ በበኩላቸው፣ ማዕከሉ ዘመናዊና ዌብ ቤዝድ በሆነ የቪዲዮ ኮንፈረንስና የሥልጠና ሥርዓት እንዲገለገል ታስቦ እየተገነባ መሆኑን ገልጸዋል።

አሁን ላይ የፕሮጀክቱ የማጠናቀቂያ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውንም አቶ ባይራይ ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን የፕሮጀክቱ አማካሪና ዋና ተቆጣጣሪ አቶ አቡበከር ሰይድ እንዳስረዱት፣ ሕንፃው የግንባታ ጥራቱን ጠብቆ እንዲገነባ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱና በአማካሪ ድርጅቱ በኩል ጥብቅ ክትትል እየተደረገ ይገኛል።

የማሰልጠኛ ማዕከሉ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የሰው ኃይል ልማትን በማጠናከር፣ የዘርፉን የሙያ ብቃትና የሥልጠና ጥራት ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚያግዝ ይጠበቃል።

የማሰልጠኛ ማዕከሉ ቤዝመንት እና ግራውንድ ጨምሮ ባለ አስር ወለል ዘመናዊ ህንፃ መሆኑን በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የመሠረተ ልማት ማስፋፊያ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ መቅድም ማቴዎስ ገልፀዋል።

የማሰልጠኛ ማዕከሉ የሰልጣኞች ማደሪያ ክፍሎች እና የአስተዳደር ህንፃ አካቶ የያዘ ስለመሆኑ አቶ መቅድም ማቴዎስ ጨምሮ ገልፀዋል።

ማዕከሉ ዌብ ቤዝድ የሆነ ስማርት የቪዲዮ ኮንፈረንስ እና የስልጠና ክፍሎች እንዲኖሩት ተደርጎ የተገነባ መሆኑን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኬያጅ አቶ ባይራይ ታደሠ ያስረዱ ሲሆን አሁን ላይ የማጠናቀቂያ ስራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ ብለዋል።

ህንፃው ጥራቱን ጠብቆ እንዲገነባ በሚኒስቴር መሥራያቤቱ እና በአማካሪ ድርጅት ጥብቅ ክትትል ስደረግ መቀየቱን በኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን የፕሮጀክቱ አማካሪ እና ዋና ተቆጣጣሪ አቶ አቡበከር ሰይድ ገልጿል።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚንስቴር

የሲዳማ ክልል የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን በማልጋ ወረዳ ለሁለት የአቅሜ ዉስንነት ላላቸው ዜጎች ገንብቶ ለማስረከብ የማስጀመሪያ መረሃ ግብር ተካደሄደ::=======...
27/08/2026

የሲዳማ ክልል የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን በማልጋ ወረዳ ለሁለት የአቅሜ ዉስንነት ላላቸው ዜጎች ገንብቶ ለማስረከብ የማስጀመሪያ መረሃ ግብር ተካደሄደ::
=============================

በማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የቢሮ ኃላፊ ክቡር ጎሳዬ ጎዳና እንደተናገሩት በሴክተር ደረጃ የማህበራዊ ዘርፍ ግቦችን ለማሳካት የታቀዱ ዕቅዶችን መነሻ በማድረግ ለሁለት ቤተሰቦች ሁለት ቤቶች አጠናቆ ለማስረከብ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ድጋፍ ለማድረግ እንደሆነ ገልፆዋል::

ከቤቶች ግንባታ ጎን ለጎን በአከባቢው ለሚገኙ የ lአቅም ዉስንነት ላላቸው ለ50 ተማሪዎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶችን ድጋፍ እንደሚደረግ ተናግሯል::

የማልጋ ወረዳ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ ድግሶ ህዝቅኤል በቢሮ በኩል ለአቅሜ ደካሞች እንዲሁም ለተማሪዎች መማሪያ ቁሳቁሶች ድጋፍ በቢሮ በኩል በመደረጉ ምስጋናውን አቅርቧል:: በመንግስት የተቀመጡ አቅጣጫዎችን ለማሳካት በሴክተር ደረጃ እየተሰራ ያለው ተግባርን እጅግ አበረታች መሆኑን አብራርቷል::

በአብዬ ጅሩ ቀበሌ ላይ ድጋፍ የተደረገላቸው ቤተሰቦች 6 ሲሆኑ 3 ውንድና 1 ሴት በድምሩ 4 ልጆችን በማሳደግ ላይ ሆኖ በችግር ዉስጥ እያለን መጥታችሁ ድጋፍ በማድረጋችሁ ተስፋችን እንድለመል አድርጋችሁናል በማለት የልጆቹ እና ወ/ሮ አማራጭ ባሪሶ ተግራለች::

በማልጋ ወረዳ ወተራረሳ ትምህርት ቤት እንዲሁም በወጅግራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ63 ተማሪዎች የደብተርና እስክርብቶና የቦርሳ ድጋፍ የማድረግ ሥራ ተከናውኗል::

በቆቾ ቀበሌ ለወ/ሮ ማኒቱ ኪኔሳ ቤተሰብ የቤት ግንባታን የማስጀመርና የማአድ ማጋራት ሥራም ድጋፍ የማድረግ ሥራ ተሰርቷል::

የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎች በትምህርት ዘመኑ ለትምህርት እንቅስቃሴያቸው እጅግ ወሳኝ መሆኑን ተናግሯል::

የቢሮ ኃላፊ ክቡር ጎሳዬ ጎዳና በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ እንደተናገሩት በክልል ደረጃ የተጀመረው የክረምት በጎ ፍቃድ አካል የሆነው የበጎ ሥራ ትክረት ተሰጥተው እየተሰራ እንደሆነ ገልፆዎ በቀጣይ ቤቶቹን በአጭር ጊዜ ዉስጥ በማጠናቀቅ ለማስረከብ ጠንካራ ክትትል በማድረግ እንደሚሰራ ገልፆዋል::

በመጨረሻም በቢሮ በኩል የማህበራዊ ኃላፊነትን በሚገባ በመወጣት ለዜጎች የቤት; የማዕድ ማጋራት የም ልገሳ እንዲሁም የትምህርት ቤት ቁሳቁሶችን ድጋፍ የማድረጉ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የቢሮ ኃላፊ ክቡር ጎሳዬ ጎዳና ተናግረዋል::

በፕሮግራሙ ላይ የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ የማናጅመንት አባላት ;ዳይረክቴሮች የማልጋ ወረዳ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል ::

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ነሐሴ, 21/12/2018 ዓ.ም

የሲዳማ ክልል የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ከክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጋር በመቀናጀት ድንገተኛ የቁጥጥር ሥራ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ:: ============================...
26/08/2026

የሲዳማ ክልል የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ከክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጋር በመቀናጀት ድንገተኛ የቁጥጥር ሥራ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ::

============================
የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ሥራ ዛሬ በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በንሳ ወረዳ ፣ዳዬ ከተማ አስተዳደርና ቦና ዙሪያ ወረዳዎች በተመረጡ የቁጥጥር ቀጠናዎች በየደረጃው ካለው አካላት ጋር በመቀናጀት የመንገድ ደህንነት ትራፊክ ፍስትን በተመለከተ ቁጥጥር ተደርጓል::

የቁጥጥር ቡዱኑ በዋናነት ከታሪፍ በላይ ማስከፈል፣ትርፍ ተሳፋሪ መጫን፣ የትራፊክ ተቆጣጣሪ ትዕዛዝ አለማክበር መጣስ፤መንጃ ፍቃድና ሌሎች ደንብ መተላለፎች በዕለቱ የታዩ ሲሆንና ሌሎች ደንብ መተላላፎችን መሠረት ያደረገ የተቀናጀ የቁጥጥር ሥራ ተሰርቷል::

በተሰራው የተቀናጀ ቁጥጥር ሥራ በዕለቱ አጠቃላይ 312 ተሽከርካሪዎች የተዩ ሲሆን 14 አሽከርካሪዎች ደንብ ተላልፈው በመገኘታቸው 35,500 (ሰለሳ አምስት ሺህ አምስት መቶ ብር) ለመንግስት ገቢ የሆነ ሲሆን በዕለቱም በዳዬ መናኸሪያ ለአሽከርካሪዎች፣ለተሳፋ ሪዎችና ለተለያዩ ሕብረተሰብ 125 ለሚሆኑት ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ መከናውኑ ተጠቅሷል።

በየደረጃው ካለው መዋቅር ጋር የተሠሩ ተግባራትን በመገምገም ግብረመልስ በመስጠት የህግ ማስከበር ሥራው ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አቅጣጫ ተቀምጧል።

በዕለቱም የምሽት የተቀናጀ ቁጥጥር ሥራ በደቡባዊ ሲዳማ ዞን በአለታ ወንዶ ከተማ አስተዳደር በተደጋጋሚ የትራፊክ አደጋ የሚደርስበት ቦታ አካባቢ ተሠርቷል።

በቀጣይም የክልሉ የተቀናጀ የቁጥጥር ቡድን ሥራ በሌሎች ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የቁጥጥር ሥራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

================================
የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ነሐሴ, 20/2018 ዓ. ም

ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ በአረንጓዴ ሎጂስቲክስና ስማርት ሞቢሊቲ ዘርፍ በጋራ ለመሥራት ተወያዩአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም. (ትሎሚ) – የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዲኤታ ክ...
26/08/2026

ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ በአረንጓዴ ሎጂስቲክስና ስማርት ሞቢሊቲ ዘርፍ በጋራ ለመሥራት ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም. (ትሎሚ) – የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ ደንጌ ቦሩ ከደቡብ ኮሪያ የመጣ የጥናት ቡድንን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ከቡድኑ ጋር በስማርት ሎጂስቲክስና ሞቢሊቲ ዘርፍ በጋራ መሥራት በሚቻልበት አግባብ ላይ ተወያይተዋል።

የውይይቱ ዋና ትኩረት “Ethiopost Green Logistics Transition Package ODA Project” በተሰኘው ፕሮጀክት ላይ ሲሆን፣ የደቡብ ኮሪያ የጥናት ቡድኑ መሪ ፕሮፌሰር ያንግ ሆ ሊ እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ ከታቀዱ ዘርፎች መካከል አረንጓዴ ሎጂስቲክስና ሞቢሊቲ ዋነኛው ነው።

ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ደንጌ ቦሩ በበኩላቸው፣ ፕሮጀክቱ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፉ በተያዘው ዕቅድ መሠረት እየተሠራበት መሆኑን ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱ ከመንግሥት ፖሊሲና ስትራቴጂ ጋር በቀጥታ የሚጣጣም በመሆኑም መንግሥት ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርግለት ጠቁመዋል።

ክቡር አቶ ደንጌ የሎጂስቲክስ አገልግሎትን ቅልጥፍናና ውጤታማነት ለማሳደግ ዘርፉን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማስደገፍ አስፈላጊ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

በዚህ ረገድ የደቡብ ኮሪያ ያላት ልምድና የቴክኖሎጂ አቅም ለኢትዮጵያ ጠቃሚ እንደሚሆን ገልጸዋል።

ፕሮፌሰር ያንግ ሆ ሊ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ትራንስፖርትና በአካባቢ ጥበቃ ዘርፎች እያስመዘገበች ያለው እድገት ለደቡብ ኮሪያ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ እንድትመርጥ ካደረጓት ምክንያቶች መካከል ዋነኛው መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም ሁለቱ ወገኖች በአረንጓዴ ሎጂስቲክስ፣ በስማርት ሞቢሊቲና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ዘርፎች ያላቸውን ልምድና እውቀት በመለዋወጥ የጋራ ትብብርን ለማጠናከር ያለውን ዕድል መወያየታቸው ተገልጿል።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር

የትራንስፖርት ዘርፍ አገልግሎትን ዘመኑ የሚዋጀውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ማቅለልና ማዘመን ይገባል::                 አቶ ጎሳዬ ጎዳና                      ( ቢሮ ኃላፊ )...
21/08/2026

የትራንስፖርት ዘርፍ አገልግሎትን ዘመኑ የሚዋጀውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ማቅለልና ማዘመን ይገባል::
አቶ ጎሳዬ ጎዳና
( ቢሮ ኃላፊ )

የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
ነሀሴ- 15/2018 ዓ.ም
ሀዋሳ
በክልሉ እንዲሁም በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የሚሰጠውን የትራንስፖርት ዘርፍ አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሙሉ በሙሉ ማስገባት የሚያስችል በሀገሪቱ ከሚገኙ የተለያዩ የሶፍትዌር አበልፃጊ ድርጅቶች ጋር የተግባር አፈፃፀም ልምዳቸውን የሚያሳይ መድረክ ተካሄዷል::

መድረኩን የከፈቱት የቢሮ ኃላፊ ክቡር ጎሳዬ ጎዳና በንግግራቸው:- ይህን መድረክ ያዘጋጀነው በክልላችን የምንሰጠው የትራንስፖርት ዘርፍ አገልግሎቶችን በማዘመን ረገድ ትኩረት በማድረግ እየተሰራ ያለው የሲዳማ ድጅታል ትራንስፖርት ስራዎች አካል እንደሆነ ተናግሯል::

በትራንስፖርት ዘርፍ በኩል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በፌዴራል ተቋማትና በሌሎች ክልሎች ሶፍትዌር ያበለፀጉና የተከሉ ድርጅቶችን ልምዳቸውንና አፍፃፀማቸውን በመፈተሽ የተሻለውን በመምረጥ የክልላችንን የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን የምንጠቀምበት መድረክ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል::

በመድረኩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በኦሮሚያ ክልልና በሌሎች ክልሎች በትራንስፖርት ዘርፍ ማለትም በተሽከርካሪና በእሽከርካሪ መስኮች እንደ ከስተመር ኮምቲንግ፣ ጥበብ ቴክኖሎጂ ሶሉሹንና ዳፍ ቴክ ሶሻል አይሲቲ ሶሉሽን የተባሉ ድርጅቶች ልምዳቸውንና የተግባር አፈፃፀማቸውን በሰነድ አቅርበዋል::

ድርጅቶቹ በአሽከርካሪ መንጃ ፈቃድ አስጣጣና እድሳትን ቅጣትን፣ የትራፊኮች የክትትልና የአደጋ መረጃ ልውውጥን፣ የተሽከርካሪን የሶስተኛ ወገን ፣ የቦሎ ክፍያና እድሳት እንዲሁም የቴክኒክ ፍተሻ መረጃዎችንና ክፍያዎችን የቴሌ ብርና በሌሎች የክፍያ ስርዓቶችን ባለንበት ሆነን በእጅ ስልካችን የምንጠቀመምባቸውን ስርዓቾች በዝርዝር ማስቀመጥ ችለዋል::

ድርጅቶቹ ባቀሩቡዎቸው የሶፍትዌር ትግበራ አፈፃፀሞች ላይ ተሳታፊዎች ጥያቄዎችንና አስተያየቶች አንስተው ምላሽ ከሚመለከታችሁ አካላት ተሠጥቶ በጥልቀት ውይይት ተደርጎባቸው በፍጥነት ወደ ተግባር መግባት ብንችል የሚሉ ሀሳቦች ተጠቁመዋል::

በመድረኩ የተገኙት የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ በመልዕክታቸው:- በክልሉ ትኩረት ከተሰጣቸው መስኮች አንዱ የትራንስፓርት ዘርፍ መሆኑን አንስተው የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን ቁርጠኛ እንደሆኑ አስምረውበታል::

አክለውም ከንቲባው ትኩረት በመስጠት ወደ አንድ መሶብ አገልግሎት አሰጣጥ ከሚገቡና ከተመረጡት 7 ሴክተሮች አንዱ የትራንስፖርት ዘርፍ እንደሆነም አስታውሰዋል::

በመጨረሻም ድርጅቶቹን የሚፈትሽና ይሁንታ የሚሰጥ የቴክኒክ ኮሚቴ ተደራጅቶ ከክልልና ከሀዋሳ ከተማ ተውጣጥቶ በቀጣይ ሂደቱ የሚገመገምበት አቅጣጫ ተቀምጦ መድረኩ ተጠናቋል::

በመድረኩ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ; የቢሮና የክልል የባለድርሻ ተቋማት አመራሮች ፣ የክልሉ ፓሊስ ጠቅላይ መምሪያ የትራፊክ ፓሊስ አስተባባሪዎች ፣ የክልልና የሀዋሳ ከተማ ትራንስፖርትና መንገድ ደህነነት ከፍተኛ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል::

መዘመን ግዴታ ነው!

20/08/2026
የትራፊክ አደጋን ለመከላከል መፍትሄ የሚያበጅ አስቸኳይ ምክክር መካሄዱ ተጠቆመ::የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ኮሙኒኬሽን      ነሀሴ - 11 / 2018 ዓ.ም                ...
17/08/2026

የትራፊክ አደጋን ለመከላከል መፍትሄ የሚያበጅ አስቸኳይ ምክክር መካሄዱ ተጠቆመ::

የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ኮሙኒኬሽን
ነሀሴ - 11 / 2018 ዓ.ም
ሀዋሳ

የቢሮው የመንገድ ደህንነትና የመድህን ፈንድ አገልግሎት ዘርፍ ከክልሉ ፓሊስ ጠቅላይ መምሪያ የትራፊክ ዘርፍ ጋር በመቀናጀት በክልሉ እየተከሰተ ያለውን ተከታታይ የትራፊክ አደጋን ለመከላከል የሚያስችል የምክክር መድረክ ተካህዷል::

መድረኩን የመሩት የቢሮ ምክትል ሀላፊና የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ዘርፍ ሀላፊ ኮሮነል ሮዳሞ ኪአ በንግግራቸው:- የዚህ አስቸኳይ ውይይት ዋና ዓላማ እየደረሰ ያለውን የትራፊክ አደጋ ለማስቆምና ለመቀነስ ፈጣን የመፍትሄ አአቅጣጫ በማበጀት በቀጥታ ወደ ጠንካራ የቁጥጥርና የክትትል ሥራ እንድገባ ነው ብለዋል::

በመድረኩም ከሰሞኑ በክልሉ የተከሰቱትን አደጋዎች ታሳቢ በማድረግ ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን ሠንዝረዋል::

ለአደጋው መንስዔ የሆኑትን ነጥቦችንም ሲያነሱ:- በአብዛኛው በክልሉ የተከሰቱት አደጋዎች በከባድ የጭነት መኪናዎች በተለይም በሲኖ ትራክ መኪና መሆኑን ገልጸዋል::

ለዚህም ክስተት የአሽከርካዎች ብቃት ማነስና የተሽክርካሪዎች በወቅቱ የቴክኒክ ብቃታቸው አለመፈተሽ መሆኑን አንስተዋል::

በተጨማሪ የመንገዶች ወቅታዊ ጥገና ማጣት፣ የፍጥነት መቀነሻዎች አለመኖር፣ የመንገድ አቅጣጫ ጠቋሚ ታፔላዎች አለመተከላቸው መሆኑን አስረድተዋል::

ከመድረኩ በሳል የሆነ ምክክር በኃላ እንደ መፍትሄ ከተቀመጡት ሀሳቦች ለአብነት :- የአሽከርካሪዎች መንጃ ፈቃድ ትክክለኛነት የሚረጋገጥበት እስትራቴጂ መንደፍና ተሽከርካሪዎች ከመነኃሪያዎች ከመውጣታቸው በፊት ብቃታቸው በባለሙያዎች የሚፈተሽበትን ሂደት ከማህበራት በቅንጅት መስራት እንዲሁም ድንገተኛ የቁጥጥር ሥራዎችንም በምሽት ማካሄድ የተወሰኑት ናቸው::

ይህን ገዳይ፣ አካል አጉዳይና ንብረት አውዳሚ አደጋን ለመከላከል የሚረዳ ከሁለቱም ተቋማት በተውጣጡ አመራርና ባለሙያዎች መርሀ- ግብር ተዘጋጅቶ ወደ ስራ የሚገባበትን አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል::

በመድረኩ የቢሮ የመንገድ ደህነትና የትራንስፖርት ዘርፍ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ የክልሉ ፓሊስ ጠቅላይ መምሪያ ; የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ቁጥጥር አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል::

የትራፊክ አደጋን በጋራ እንከላከል!

Address

Hawassa
Awassa

Telephone

+251989059666

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sidama National Regional State Road Development &Transport Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share