02/12/2025
****የሴት ልጅ****
በሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን
የሴት ልጅ ይሉኛል
የማንስ መስሎአቸው
ከፍ እንዳደረጉኝ ማን በነገራቸው
እስኪ ተመልከቱኝ
የሴቷ ልጅ ሆኜ
ከቶ ምን ጎደለኝ
ኧረ ጥያቄ አለኝ
የሴት ልጅ ያልሆነ
በሉኝ ደጋግሙና
የሴት ልጅ በሉና
በሴት መጠራቴ
ነውና ኩራቴ
አዋ ነኝ የሴት ልጅ
አዋ ነኝ የእናቴ
የእርስዋን አለም ትታ
ለምትሞት ለሞቴ
ትኑርልኝ እማ በስምዋ እንድጠራ
የሴት ልጅ ተብዬ ሁሌ እንድኮራ
በሴት መጠራቴ ነውና ኩራቴ
ስሜን ቀይራችሁ ጥሩኝ በእናቴ