SERS Women and Social affairs Bureau በደ/ኢ/ክ/መንግስት ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ

  • Home
  • Ethiopia
  • Awassa
  • SERS Women and Social affairs Bureau በደ/ኢ/ክ/መንግስት ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ

SERS Women and Social affairs Bureau በደ/ኢ/ክ/መንግስት ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from SERS Women and Social affairs Bureau በደ/ኢ/ክ/መንግስት ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ, Government Organization, Meskel Square, Awassa.

የበጎ ፈቃድ ልማዳችንን በማስቀጠል የነገዋን የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ሁላችንም የጋራ ኃላፊነታችንን እንወጣ!‎****************‎የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የኢትዮጵያን ታሪካ...
05/09/2026

የበጎ ፈቃድ ልማዳችንን በማስቀጠል የነገዋን የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ሁላችንም የጋራ ኃላፊነታችንን እንወጣ!
‎****************
‎የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የኢትዮጵያን ታሪካዊ የጋራ መከባበር፣ መተጋገዝና አብሮነት መንፈስ ከዘመናዊ የልማት ፍላጎት ጋር የሚያገናኝ ጠንካራ ድልድይ ነው።

‎ዜጎች ጊዜያቸውን፣ ጉልበታቸውን እና እውቀታቸውን ለሀገራቸው በፈቃደኝነት ሲለግሱ፣ ኢትዮጵያ በብሩህ ተስፋ ከፈተናዎች ተነስታ የከፍታ አድማሷን ታሰፋለች፤ ካሰበችበትም ትደርሳለች።

‎የኢትዮጵያ የማንሰራራት ጉዞ እንዲፋጠንና እንዲሳካ ዜጎች በቀና ልብ እና በፈቃደኝነት የሚያሳዩት ተነሳሽነትና የሚሰጡት ተግባራዊ ምላሽ እጅግ ወሳኝ ነው።

‎ስለሆነም የበጎ ፈቃድ ልማዳችንን በማስቀጠል የነገዋን የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ሁላችንም የጋራ ኃላፊነታችንን እንወጣ።

‎ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ
‎የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከ“ሆፕ ፎር ጃስቲስ” ግብረ-ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር የሕፃናትን መብት ለማስከበርና ሕገ-ወጥ ዝውውርን ለመግታት ያለመ የሥልጠና እና ...
04/09/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከ“ሆፕ ፎር ጃስቲስ” ግብረ-ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር የሕፃናትን መብት ለማስከበርና ሕገ-ወጥ ዝውውርን ለመግታት ያለመ የሥልጠና እና የቁሳቁስ ድጋፍ ለክልሉ የሕፃናት ፓርላማ ተወካዮች ሰጠ።

ነሐሴ 29/2018 ወላይታ ሶዶ፤

በመድረኩ ላይ የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ የመንግስትን የሕፃናት ደህንነት ትኩረት በማንሳት፣ የክልሉን የሕፃናት ፓርላማ አቅም ለመገንባት “ሆፕ ፎር ጃስቲስ” እያደረገ ላለው ዘላቂ ድጋፍ የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።

ሁለቱ ተቋማት በቅንጅት ባዘጋጁት በዚህ መድረክ ላይ በሕፃናት ጉልበት ብዝበዛና በሕገ-ወጥ ፍልሰት ዙሪያ ለክልሉ የሕፃናት ፓርላማ ተወካዮች ሰፊ የግንዛቤ ማሳደጊያ ስልጠና ተሰጥቷል።

የሕፃናትን ፍልሰትና የጉልበት ብዝበዛን ሙሉ በሙሉ ለመከላከል በማህበረሰቡ ውስጥ የሚገኝ እያንዳንዱ ግለሰብ የበኩሉን አወንታዊ ድርሻ መወጣት እንዳለበትና ሁለተኛው ዙር የሕፃናት ፓርላማም ለሕፃናት ድምፅ መሆን እንደሚገባው ተጠቁሟል።

የድርጅቱ ካንትሪ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሶሲና ይርጋ በበኩላቸው፣ ነገ ሀገርን የሚረከቡ ሕፃናት የራሳቸውን ችግር ራሳቸው መፍታት የሚችሉበትን ብቃት እንዲያዳብሩ ሰፊ ዕድል ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ም/ኃላፊ ወ/ሮ ገነት በለጠ ስልጠናው የህጻናት ፖርላማ አባላት ለጥቃት ተጋላጭ ለሆኑ ህጻናት መብት እንዲሟገቱ አቅም የሚፈጥር ነው ብለው መሰል ድጋፎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ጠይቀዋል።

በስልጠናው ተየተሳተፉ ሕፃናትም በአቅም ውስንነት ምክንያት ለጉልበት ብዝበዛ እንዳይዳረጉ የበኩላቸውን ሚና ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ገልጸው፤ ወላጆች፣ መንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

“ሆፕ ፎር ጃስቲስ” በክልሉ እያደገ ለመጣው ማህበራዊ ችግር ሕፃናቱ ራሳቸው መፍትሔ እንዲሆኑ መልዕክት ያስተላለፈ ሲሆን፣ የኢኮኖሚ አቅም ውስንነት ላላቸው ሕፃናትም የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

‹‹ሰዎች ለሰዎች - Menschen fur Menschen›› የተሰኘ አጋር ድርጅት በክልሉ እየተገበረ ያለው የልማት ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡አጋር ድርጅቱ በጤና...
01/09/2026

‹‹ሰዎች ለሰዎች - Menschen fur Menschen›› የተሰኘ አጋር ድርጅት በክልሉ እየተገበረ ያለው የልማት ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡

አጋር ድርጅቱ በጤና፣ በትምህርትና በሴቶች ጤና ዙሪያ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ታውቋል፡፡

ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም

የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና ጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ መና መኩሪያ እንደተናገሩት ‹‹ሰዎች ለሰዎች›› የተሰኘ አጋር ድርጅት ለህብረተሰቡ የሰራውና እየሰራ ላሌው ልዩ ልዩ ማህበራዊ ተቋማት ግንባታ አመስግነዋል፡፡

በቀጣይም በክልሉ የተለያዩ አከባቢዎች ለሚተገበሩ ማህበራዊ መሠረተ ልማቶች መሳለጥ ሥራ አስፈፃሚ ግብረኃይል በመሰየም ‹‹ከሰዎች ለሰዎች-Menschen fur Menschen›› አጋር ድርጅት ጋር እንደሚሰሩ ቢሮዎቹ አስታውቀዋል፡፡

አጋር ድርጅቱ ከክልሉ ጤና ቢሮ፣ ትምህርት ቢሮ እና ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር በመቀናጀት በክልሉ 5 ዞኖች ስር በሚገኙ ወረዳዎች ላይ ፕሮግራማቸውን ተፈፃሚ እንደሚያደርጉ የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ተወካይ ወ/ሮ ሀያት መሀመድ አስታውቀዋል፡፡

ድርጅቱ በጤናው ዘርፍ የማህፀን ውልቃት ልየታና ህክምና፣ ኤች አይቪ መከላከልና ቁጥጥር፣ ለጤና ተቋማት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ፣ ትምህርት ቤት ግንባታ፣ ንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ አቅም ግንባታ ሥልጠና እና ልዩ ልዩ ድጋፎችን እንደሚያደርጉ ወ/ሮ ሀያት አስታውቀዋል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎች ሀሳብ አስተያየት በመስጠት ድርጅቱ ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ አረጋግጠው፤ ፕሮግራሙ ተደራሽ ወዳልሆነባቸው መዋቅሮች ዕቅዳቸውን እንዲያሰፉ ጠይቀዋል፡፡

ለሴቶች ጤና ድጋፍ እየተሰራ ያለውን አገልግሎትን አድንቀው፤ በቀጣይ የበለጠ ተስፋፍቶ እንዲሰራ የክልሉ ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ በዛብህ በላይነህ ተናግረዋል፡፡

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢሳያስ እንድሪያስ በበኩላቸው አጋር ድርጅቱ በትምህርቱ ዘርፍ በግንባታ እያደረገ ያለውን እገዛ አድንቀው፤ የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲያጠናክሩም ጭምር ጠይቀዋል፡፡

የጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና ጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ መና መኩሪያ እስካሁን ለተሰሩ ግንባታዎች፣ ቁሳቁስ ድጋፍና አቅም ግንባታ ሥራዎች አመስግነው፤ ከክልል ጀምሮ እስከ ወረዳ ተግባራትን በማገዝና በመከታተል የሚደግፍ ግብረኃይል በማቋቋም በቅንጅት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡

"የሴቶችን ሁል አቀፍ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ "፦የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም የክልሉ ሴቶች ማህበር የ201...
01/09/2026

"የሴቶችን ሁል አቀፍ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ "፦የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ

ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም

የክልሉ ሴቶች ማህበር የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀምና በ2019 ዕቅድ ላይ ያተኮረ መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሂዷል።

ሴቶችን በልማት ህብረት ማደራጀት ለሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ጉልህ ድርሻ እንዳለውም ተጠቁሟል።

የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ካሰች ኤሊያስ እንደገለፁት፣ቢሮው ሴቶችን በማደራጀትና በተለያዩ የልማት ስራዎች በማሳተፍ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገልጸዋል ።

ሴቶችም የተሰጣቸውን ዕድል በአግባቡ መጠቀም እንዳለባቸውም ኃላፊዋ አስገንዝበዋል ።

በመተጋገዝና በመቀናጀት ለሚፈለገው ውጤት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው ፣በሚያቀራርቡን ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል ።

የህብረቱ አባላት ቁጥርን ማሳደግ መዋጮን በማጠናከር ሀብት የማሰባሰብ ተግባር ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚያስፈልግ የገለፁት ወ/ሮ ካሰች ለህብረቱ ውጤታማነት ይበልጥ መትጋት ይገባል ብለዋል። ።

የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ወ/ሮ ካሰች አጽንኦት ሰጥተዋል።

የክልሉ ሴቶች ማህበር ሰብሳቢ ወ/ሮ መነን ዘውዱ በበኩላቸው፣ሴቶችን በልማት ህብረት ማደራጀት ለሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ጉልህ ድርሻ እንዳለው ገልጸዋል ።

በወቅቱ አስተያየታቸውን የሰጡት የመድረኩ ተሳታፊዎች ሴቶች በሁሉም ዘርፍ ተጠቃሚ እንዲሆን የተቀናጀ ጥረት ያስፈልጋል ብለዋል።

የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በልማት ህብረት ማደራጀትና የተደራጁትን ማብቃት እንዲሁም አባላቱን የማሳደግ ተግባር የሁሉም ኃላፊነት እንደሆነም አስተያየት ሰጪዎች አበክረዋል ።

የብድር አቅርቦት ማመቻቸት እንዲሁም ብድሩን ወስደው በአግባቡ በመጠቀም ውጤታማ እንዲሆኑ የተጠናከረ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል ።

በቀጣይ አደረጃጀቱን የተሻለ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት በመፍጠር መድረኩ ተጠናቋል ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶች አደረጃጀትን በማጠናከር ሁለንተናዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለፀ ነሐሴ 26/2018 ...
01/09/2026

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶች አደረጃጀትን በማጠናከር ሁለንተናዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለፀ

ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም

የክልሉ ሴቶች ማህበር በ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል

በክልሉ ከ748 ሺህ በላይ የሴቶች አደረጃጀት ህብረት አባላት መኖራቸውም ተጠቁሟል

የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የሴቶቸና ህፃናት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት በለጠ በመድረኩ መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ሴቶች በስራ እድል ፈጠራ እንዲሳተፉ በማድረግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

መንግስት ሴቶች በማህበር ተደራጅተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ልዩ ትኩረት መስጠቱን የገለፁት ወ/ሮ ገነት በክልሉ ይህንኑ ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት መመዝገቡንም አብራርተዋል።

የክልሉ ሴቶች ማህበር ሰብሳቢ ወ/ሮ መነን ዘዉዱ በበኩላቸው በክልሉ ሴቶች በማህበር ተደራጅተው ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሚገኝ ገልጸዋል ።

ሴቶች በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በፖለቲካ ዘርፍ ግንባር ቀደም ተሳታፊ መሆናቸውን ጠቁመው፣ በቀጣዩ አደረጃጀቱን በማጠናከር ተጠቃሚነታቸውን ይበልጥ ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የሴቶች ልማት ህብረት ለማጠናከር የተካሄደበት ሂደት አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን የገለፁት ወ/ሮ መነን፣በክልሉ የሴቶች አደረጃጀት ህብረት አባላት ከ748 ሺህ በላይ መሻገሩንም አመላክተዋል።

በጉባኤው የሴቶች አደረጃጀትና ተጠቃሚነትን ለማጠናከር በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ስኬቶች እና በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳይ ላይ ስነድ ቀርቦ ውይይት የሚደረግ ይሆናል ።

በመድረኩ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሴቶች ክንፊ ኃላፊ ወ/ሮ እቴነሽ በየነን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛል።

"የበጎ ተግባራት ስራዎች የተወሰነ ወቅት ብቻ ሳይሆን የሁልጊዜ ተግባር ሊሆኑ ይገባል "የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶች ማህበር፣በወ...
01/09/2026

"የበጎ ተግባራት ስራዎች የተወሰነ ወቅት ብቻ ሳይሆን የሁልጊዜ ተግባር ሊሆኑ ይገባል "የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ

ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶች ማህበር፣በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ድል በጌሬራ ቀበሌ የአረጋውያን ቤት ግንባታ አስጀምረዋል ።

በጎ ተግባራት ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ከምንም በላይ እርካታ የሚሰጥ በመሆኑ ተግባሩ በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥልም ተጠቁሟል ።

የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ካሰች ኤሊያስ፣በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ በሚል መሪ ቃል የተጀመረው ኢንሼቲቭ በክልሉ ውጤት እያስመዘገበ እንደሆነ ገልጸዋል ።

የለውጡ መንግስት ለበጎ ተግባር ልዩ ትኩረት መስጠቱን የገለፁት ወ/ሮ ካሰች ይህም የብዙዎች እንባ በማበስ ተጠቃሚነታቸውን እያረጋገጠ ነው ብለዋል።

ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን መደገፍ የሚሰጠው እርካታ ከምንም በላይ መሆኑን ጠቁመው አረጋዊያንን በዘላቂነት መደገፍ የሁልጊዜ ተግባር መሆን እንዳለበትም አስገንዝበዋል ።

ብልጽግና ፓርቲ ሰው ተኮር ተግባርን የሚያስቀድም ፓርቲ መሆኑን በተጨባጭ እያሳየ ነው ያሉት ወ/ሮ ካሳች ፣መንግስት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠቱ በክልሉ የሚከናወነው ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አስታውቋል ።

የክልሉ ሴቶች ማህበር ሰብሳቢ ወ/ሮ መነን ዘዉዱ በበኩላቸው የክልሉ ሴቶች ማህበር በተለያዩ አካባቢዎች የበጎ ፈቃድ አገሌግሎት ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ አመላክተዋል።

በጎነትን ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ከምንም በላይ እርካታ የሚሰጥ ጉዳይ መሆኑን ገልፀው፣ተግባሩ ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የተጀመሩ ስራዎች ይጠናከራሉ ብለዋል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ እቴነሽ ኤሊያስ በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ በሚል መሪ ቃል የተጀመረው ኢንሼቲቭ፣ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ አካል ችግሮችን መቅረፉን ጠቁመዋል።

ወ/ሮ በለጠቸ ባልቻ የወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ድል በጌሬራ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ ከዚህ በፊት መኖሪያ ቤት ባለመኖሩ በከፍተኛ ችግር ውስጥ ሆነው ያሳልፉ እንደነበር በመግለጽ አሁን የቤት ግንባታ በመጀመሩ መደሰታቸውን ተናግረዋል ።

በመርሃ ግብሩ የክልሉ የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ካሰች ኤሊያስ ጨምሮ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሴቶች ክንፊ ኃላፊ ወ/ሮ እቴነሽ በየነ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል ።

ሴት ልጅ ስትበቃ ሀገር ትበለፅጋለች!የብልፅግና ፓርቲ የመደመር ፍልስፍና የሰውን ልጅ ሁለንተናዊ ክብር ማስከበርና ማበልፀግ ነው።የነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ  ማዕከል በታሪ...
30/08/2026

ሴት ልጅ ስትበቃ ሀገር ትበለፅጋለች!

የብልፅግና ፓርቲ የመደመር ፍልስፍና የሰውን ልጅ ሁለንተናዊ ክብር ማስከበርና ማበልፀግ ነው።

የነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል በታሪክ አጋጣሚ ለተለያዩ የስነ-ልቦና ተፅዕኖዎች ለጎዳና ህይወት የተጋላጡ ሴቶችን በዕውቀት፣ በክህሎትና በስብዕና በመገንባት አዲስ ህይወት እንዲጀምሩ ያደርጋል።

የነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የተገነባና በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ውስጥ የነበሩ ሴቶችን መልሶ ለማቋቋም የተቋቋመ ግዙፍ ሰው ተኮር ፕሮጀክት ነው።

ማዕከሉ በበርካታ ውስብስብ ማህበራዊና ሥነ-ልቦናዊ ቀውስ ውስጥ የነበሩ ሴቶችን ሕይወት በአዲስ የለውጥ ምዕራፍ እንዲሸጋገሩ እያደረገ ይገኛል ።

የዚሁ ታላቅ ራዕይ አካል የሆነው የነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ሴቶች በልዩ ልዩ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፈተናዎች ውስጥ አልፈው ተስፋ እንዳይቆርጡ፣ አዲስ የህይወት ምዕራፍ እንዲጀምሩ እያደረገ ይገኛል።

ማዕከሉ ሴቶችን በስነ-ልቦና ተሃድሶ ከመደገፍ ባሻገር፣ ከወቅቱ የገበያ ፍላጎት ጋር የተጣጣሙ የሙያና የስራ ፈጠራ ክህሎቶችን በማሰልጠንም ወደ ስራ እንዲሰማሩ መንገድ ይጠርጋል።

በማኅበረሰቡ ውስጥ ያሉ በርካታ ችግሮች፣ መድልኦ እና መገለል በሴቶች ላይ የሚያደርሰው ተፅዕኖ የጎላ ነው ይሄን ማዕከል በቀጣይ ከዚህ በበለጠ በማጠናከር የብዙ ሴቶችን ሕይወት ለመቀየር በትጋት እየሰራ ይገኛል ።

በተቋሙ የሙያ ስልጠናዎችን በመስጠት በባህል አልባሳት ስራ በኮስሞቶሎጂ እና ውበት ሳሎን ሙያዎች ስልጠናዎችን ፣ የስነ_ልቦና እና የጤና ክብካቤ ሰልጣናና ድጋፍ በማድረግ የትላንት ማህበራዊ ስብራታቸውን አክመው የነገ ማንነታቸውን እንዲያሳምሩ የስነ-ልቦና ምክርና የህክምና ድጋፍ የሚያገኙ ሲሆን የስራ ዕድል ፈጠራ ሰልጣኞች ሰልጥነው ሲመረቁ በግልም ሆነ በቡድን ተደራጅተው የራሳቸውን ገቢ እንዲፈጥሩ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል ።

የእህቶችን ህይወት ለመቀየር፣ ለነገዋ የሴቶች የተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል በ2016 ዓ.ም ጀምረው በ5 ዙር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች 3 ሺህ 259 ሰልጣኞችን በክህሎት እና በስብዕና ግንባታ ሰልጥነው ወደ ስራ ገብተዋል።

ለ”ለነገዋ የተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል” የሰነቅነው ራዕይ፣ በዓመት እስከ 10 ሺህ ሴቶችን የሚያበቃ፣ እንዲሁም አካታች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ልምድ የሚቀሰምበት የልህቀት ማዕከል እየሆነ ይገኛል ።

ማዕከሉ የሴቶችን ክብር ከመመለስ ባለፈ፣ በሙያና በክህሎት ኮትኩቶ ለራሳቸው፣ ለቤተሰባቸውና ለሀገራቸው የሚተርፉ አምራች ዜጎችን የሚያፈራ ትልቅ ተቋም ነው ።

ምንጭ

‎ተጋላጭ የሆኑ ህጻናትን፣ ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችንና አረጋዊያንን ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ለመጠበቅ ማህበረሰብ አቀፍ ድጋፍና ክብካቤ ጥምረት ሚናው የጎላ ነው፦ወ/ሮ ዝናቧ በየነ ‎‎ነ...
29/08/2026

‎ተጋላጭ የሆኑ ህጻናትን፣ ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችንና አረጋዊያንን ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ለመጠበቅ ማህበረሰብ አቀፍ ድጋፍና ክብካቤ ጥምረት ሚናው የጎላ ነው፦ወ/ሮ ዝናቧ በየነ

‎ነሐሴ 23/2018

የወላይታ ዞን ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ማህበረሰብ አቀፍ ድጋፍና ክብካቤ ጥምረት(CCC) እና ተጋላጭ ልየታ ዙሪያ ኦሬንቴሽን መድረክ በጉኑኖ ከተማ እና ዳሞት ሶሬ ወረዳ አስተዳደር እያካሄደ ነው።

‎መድረኩን በይፋ ከፍተው ያስጀመሩት የወላይታ ዞን ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ዝናቧ በየነ ተጋላጭ የሆኑ ህጻናትን፣ ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችንና አረጋዊያንን ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ለመጠበቅ ማህበረሰብ አቀፍ ድጋፍና ክብካቤ ጥምረት ሚናው የጎላ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

‎ጥምረቱ በአካባቢው የሚገኙ የድጋፍና እንክብካቤ ሀብቶችን ማስተባበር፣ ተጋላጭ የሆኑ ዜጎችን በመለየት ተገቢውን ድጋፍ እንዲያገኙ ማገናኘት እና ችግሮችን ከመባባሳቸው በፊት በማህበረሰብ ደረጃ መፍታት ነውም ብለዋል።

‎አያይዘውም ወ/ሮ ዝናቧ ለተጋላጭ ዜጎች የሚደረገውን ድጋፍ በተቀናጀና በሰብዓዊ መልኩ ለማጠናከር በቁርጠኝነት ልንሰራ ይገባል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

‎ማህበራዊ ጥበቃ የተጋላጭነት ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት መጠበቅ፣ የኑሮ ደህንነታቸውን ማረጋገጥና በማህበረሰቡ ውስጥ በክብርና በእኩልነት እንዲኖሩ ማስቻል ነውም ሲሉ አስገንዝበዋል።

‎የCCC ስራ ውጤታማ እንዲሆን አደረጃጀቱ ብቻ በቂ አለመሆኑን ገልጸው፥ ግልጽ የሆነ የስራ ድርሻ፣ የተቀናጀ አሰራር፣ የመረጃ ልውውጥ፣ የክትትል ስርዓት፣ እንዲሁም የባለድርሻዎች ቁርጠኝነት ያስፈልጋል።

‎የዳሞት ሶሬ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ከበቡሽ አፋቶ የማህበራዊ ጥበቃ ስራ የአንድ ተቋም ወይም የአንድ ግለሰብ ኃላፊነት ሳይሆን የሁላችንም የጋራ ኃላፊነት መሆኑንን አስገንዝበዋል።

‎ጥምረቱ ውጤታማ እንዲሆን አደረጃጀቶችን ማጠናከር እና መደገፍ አለብን ሲሉም አሳስበዋል።

‎ሁሉም ባለድርሻዎች “እኔ ምን አደርጋለሁ?” “ተቋሜ ምን ሚና አለው?” እና “በጋራ እንዴት ውጤታማ እንሆናለን?” የሚሉ ጥያቄዎችን በመመለስ ተጨባጭ የስራ አቅጣጫ ማስቀመጥ ይገባናል ሲሉ ገልጸዋል።

የአካል ጉዳተኞችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና ብሔራዊ ማኅበራት በጋራ መሥራታቸውን እንደሚቀጥሉ አረጋገጡየሴቶችን ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከብሔራዊ የአካል ጉ...
28/08/2026

የአካል ጉዳተኞችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና ብሔራዊ ማኅበራት በጋራ መሥራታቸውን እንደሚቀጥሉ አረጋገጡ

የሴቶችን ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከብሔራዊ የአካል ጉዳተኞች ማኅበራት ጋር ባካሄደው የዕቅድ ማዋሀድ እና ውይይት፣ የአካል ጉዳተኞችን መብትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ዋና ዋና የትኩረት መስኮች ላይ በመወያየት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን መግባባት ፈጥረዋል፡፡

የሚኒስቴሩ የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስቴር ድኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ ከብሔራዊ የአካል ጉዳተኞች ማኅበራት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ እንደገለጹት የጤና መድህንና ማህበራዊ ጥበቃ፦ በድህነት ውስጥ የሚገኙ አካል ጉዳተኞች በማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን (CBHI) ሙሉ የህክምና ወጪ ሽፋን እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የቀረጥ ነፃ አገልግሎትን በተመለከተ አሰራሩን ይበልጥ በማዘመንና በማቀላጠፍ ወደ "መሶብ" (Masob) ዲጂታል ኢ-ሰርቪስ ተሸጋግሯል። እንዲሁም የመረጃ ክፍተቶችን ለመቅረፍ "ብሔራዊ የማህበራዊ መዝገብ" (National Social Registry) እየተዘረጋ እንደሚገኝ ተቁመው የአካል ድጋፍ መሳሪያዎችን ተደራሽ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ድጋፍ ሰጪ መሳሪያዎችን በሀገር ውስጥ የማምረት ስራ ትኩረት በመስጠት ወደ ምርት መገባቱን ገልፀዋል።

ፖሊሲና የሕግ ማእቀፎችን በተመለከተ አገራዊ የተጠቃለለ የአካል ጉዳተኞች ፖሊሲና የ10 ዓመት ድርጊት መርሃ ግብር እንዲፀድቁ ለማድረግ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ የበኩሉን ጥረት በማድረግ ላይ እንደሆነ ጠቁመዋል ሲል የዘገበው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ነው።

በዲላ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፈ ጥምረት (ccc) የማጠናከሪያ መድረክ ተካሄደ‎ነሐሴ ‎19/2018ዓ.ም ‎በዲላ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ማህበራዊ ጉ...
25/08/2026

በዲላ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፈ ጥምረት (ccc) የማጠናከሪያ መድረክ ተካሄደ

ነሐሴ ‎19/2018ዓ.ም

‎በዲላ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፈ ጥምረት (ccc) የማጠናከሪያ መድረክ አካሂዷል።

‎በመድረኩም ላይ የተገኙት የዲላ ከተማ ምክር ቤት ም/ ም ሰብሳብ ወ/ሮ አዳነች ኤዴማ እንደገለፁት የማህበረሰብ አቀፍ ጥምረት(ccc)ጉዳይ የአንድ መምሪያ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሁላችንም ጉዳይ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል ፡፡

‎ተግባሩ ሰው የመሆን ጉዳይ እንደመሆኑ መጠን የማጠናከሩ ሥራ በየቀበሌዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልፀዋል፡፡

‎የዲላ ከተማ ሴቶችና ማህበራዊ መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ ዜና ክፍሌ እንደገፁት የማህበረሰብ አቀፍ ጥምረት(ccc) ጉዳይ ብልጽግና ፓርቲያችን ሰው ተኮር ተግባራት በስፋት እየሰራ እንደሆነ ይታወቃል ለዚህም ሁሉም አካላት በርብርብ መሥራት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

‎ተጋላጮችን ከመለየትና ዘላቅ ድጋፍ ከማድረግ አንፃር በሪካታ ጉዳዮችን መሥራትና ‎ለዚም ተግባር ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ማስተባበር ያስፈልጋል ብለዋል።

‎በመድረኩ የከተማዉ ምክርቤት አፈ-ጉባኤን ጨምሮ የማህበራዊ ክላስተር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳብ እና ከክፍሌከተማ የተወጣጡ ሥራ አስፈፃሚ እና ማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪዎች ከተለያዩ ቀበሌያት የተወጣጡ የቀበሌ አስተዳዳርዎችና አፈ-ጉባየዎችና የዲላ ከተማ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

Address

Meskel Square
Awassa
251

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when SERS Women and Social affairs Bureau በደ/ኢ/ክ/መንግስት ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to SERS Women and Social affairs Bureau በደ/ኢ/ክ/መንግስት ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ:

Shortcuts

Share