19/06/2020
የጣራሜሳና አከባቢው የገበሬዎች ሁለ/መ/ኅ/ሥ/ ማህበር በሁለገብ ሥራ ዘርፍ ከስድስት ቀበሌ በተወጣጡ አ/አደሮች በ1968 ዓ.ም የቋቋመ ማህበር ነው ::
ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ ከአባላቱ የቡና ምርትን በማሰባሰብና በማዘጋጀት ለውጭ ገበያ በማቅረብ የአ/አደሩ ምርት የተሻለ ገበያ እንድያገኝና ተጠቃሚ እንድሆን ከማድረጉ በተጨማሪ ለሀገር የውጪ ምንዛሪ በማስገኘት ረገድ የራሱን ሚና በመወጣት ላይ የምገኝ ማህበር ነው ። ይህ በእንድህ እንዳለ ሆኖ ማህበሩ ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን የአገልግሎት አድማስ በማስፋት የአባላቱን ተጠቃሚነት ለመጨመር በተወሰነ ሥራ ላይ ብቻ ተንጠልጥሎ ከቆየበት ተጨማሪ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ወደ ሥራ መግባቱ የሚታወስ ነው ። በመሆኑም ማህበሩ እያደረገ ያለውን የዕድገት ግስጋሴ በማጠናከርና እራሱን አስተማማኝ ደረጃ ላይ በማድረስ ለአባላቱና ለአካባቢው ህበረተሰብ እንድሁም ለሀገር የሚያደርገውን አስተዋጽኦ አጠናክሮ ለመቀጠል የተለያዩ ተጨማሪ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ወደ ሥራ መግባት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህንን የነዳጅ ማደያ አቅዶ ወደ ሥራ ተገብቶ የግንባታ ሥራ ተጠናቅቆ ለህብረተሰቡና ለተጠቃሚዎች አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ ሆኖ ይገኛል።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ዓላማ :-
° የህብረተሰቡን ፍላጎትና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ
° በአከባቢው ያለውን የነዳጅ ፍላጎት ማሟላት
° የማህበሩን ሁለንተናዊ ዕድገት በመጠበቅ ሞዴል ማህበር እንድሆን ለማድረግ
° ተጨማሪ የሥራ ዕድል ለመፍጠር
° ማህበረሰብ በቅርበት አስፈላጊ አገልግሎት እንድያገኙ ለማድረግ
° የአባላቱን ገቢ ለማሳደግ ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ራዕይ :-
° ማህበሩ የጀመረውን ሥራ ወደሰፊና ድንበር ዘለል ንግድ ተሻግሮ ማየት።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ተልዕኮ :-
° የማህበረሰቡ ፍላጎትና አቅም እየተከታተለ ምላሽ መስጠት
° ሰፍ የሥራ ዕድል መፍጠር
° ለአካባቢው ማህበረሰብ ጥያቄ መመለስ
° የተወዳዳሪነት መንፈስ ማሳደግ