Prosperity Party Hawassa City Branch Office

Prosperity Party Hawassa City Branch Office Building a brighter future for Hawassa through economic growth, social equity, and community development. Join us in creating prosperity for all residents.

ጳጉሜን 2 “የማንሰራራት ቀን”ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በታዳሽ ሀይል፣ በከተሞች ገጽታ እና በገጠር ኮሪደር ልማት በጣለችው ጠንካራ መሰረት ላይ በመቆም ወደ ተሻለ ከፍታ የተሻገረችበት ድንቅ ስራ ...
06/09/2026

ጳጉሜን 2 “የማንሰራራት ቀን”

ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በታዳሽ ሀይል፣ በከተሞች ገጽታ እና በገጠር ኮሪደር ልማት በጣለችው ጠንካራ መሰረት ላይ በመቆም ወደ ተሻለ ከፍታ የተሻገረችበት ድንቅ ስራ ከኢትዮጵያ ማንሰራራት ምልክቶች ጥቂቶች ናቸው።

#ሀዋሳብልጽግና

በከተማዋ የተመዘገቡ እምርታዎችን በማቀናጀት የሀዋሳን ከፍታ ከዳር ለማድረስ የተከናወኑ አበይት ተግባራትን የሚያስቃኝ "የእመርታ ቀን" በፓናል ውይይት ተከበረ​የዘንድሮው የጳጉሜን ቀናት አከባ...
06/09/2026

በከተማዋ የተመዘገቡ እምርታዎችን በማቀናጀት የሀዋሳን ከፍታ ከዳር ለማድረስ የተከናወኑ አበይት ተግባራትን የሚያስቃኝ "የእመርታ ቀን" በፓናል ውይይት ተከበረ

​የዘንድሮው የጳጉሜን ቀናት አከባበር መርሐ ግብር አካል የሆነው "የእመርታ ቀን" ዛሬ ጳጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ.ም "ከተረጅነት ወደ አምራችነት!" በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ከተማ በድምቀት ተከብሯል።

​በሀዋሳ ከተማ መሠረተ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ አዘጋጅነትና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በተካሄደው በዚህ መድረክ ላይ፤ በሀገር አቀፍ፣ በክልል እና በከተማ ደረጃ የተመዘገቡ ድምቀት ያላቸው የልማት ስኬቶች ተመላክተዋል።

​መድረኩን አስመልክቶ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ ኢንጂነር ቸርነት ፍላቴ ሰነድ አቅርበዋል። በሰነዱም መሠረት እንደ ሀገር እና እንደ ሲዳማ ክልል ከከተማዋ ስኬታማ የለውጥ ጉዞ ጋር የተገኙ ዋና ዋና እመርታዎች ተፈትሸዋል።

​እንደ ሀገር በስንዴ ልማት ከውጭ ገቢ ራስን ችሎ ወደ ውጭ መላክ መጀመሩ፣ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የደን ሽፋን ማደጉ እና እንደ ክልል ራስን በራስ ማስተዳደር ከተጀመረ ወዲህ የቡና ምርትና ጥራትን በቴክኖሎጂ በመደገፍ፣ ለከተሞች መሠረተ ልማት እንዲሟላ በማድረግ እና የሐይቅ ዳርቻ ልማቶችን እውን በማድረግ ረገድ ትልቅ ስኬት እንደተመዘገበ በሰነዱ ተመላክቷል።

​የክልሉ መዲና ሀዋሳ ባለፉት ዓመታት ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ከተማ ነክ ልማቶችን በማፋጠን ረገድ በርካታ ጉልህ እመርታዎችን አስመዝግባለች። ይህ በእንዲህ እንዳለም በከተማዋ በአጭር ጊዜ ውስጥ እውን የተደረጉ ዋና ዋና ስኬቶችም በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

​በቀረበው ሰነድ ማመላከት እንደተቻለው የከተማዋን ውበት እና ጽዳት ለመጠበቅ፣ ለተሽከርካሪዎችና ለእግረኞች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ሰፊ የኮሪደር ልማት፣ የመንገድ ማስፋፊያ እና ዘመናዊ የመብራት ዝርጋታ ሥራዎች በተጨባጭ መከናወናቸው ተመላክቷል።

​ከዚህም ባለፈ የሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትን እውን ከማድረግ ባሻገር፣ በህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ሀዋሳን የቱሪዝም እና የኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል። ለሀገር ውስጥ እንዲሁም ለውጭ ቱሪስቶች ምቹ የሆኑ ዘመናዊ መዝናኛ ስፍራዎች መገንባታቸው ለቱሪዝም ዘርፉ ትልቅ አቅም ስለመፍጠሩ ተመላክቷል።

​ሀዋሳ የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከል እንደ መሆኗ መጠን፣ ከግሉ ዘርፍ ጋር በመተባበር ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን የጠበቁ ሆቴሎች፣ ሎጆች እና የንግድ ማዕከላት እንዲገነፉ መደረጉ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴውን በእጅጉ እንዳነቃቃም ተጠቁሟል።

​በከተማዋ የተገነባው ሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለአካባቢው ወጣቶች ሰፊ የሥራ ዕድል የፈጠረ፣ የሀገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ ረገድ ትልቅ አቅም የሆነ እና የከተማዋን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ያነቃቀረ ዋና ስኬት መሆኑ በመድረኩ ተነስቷል።

​በተያያዘም የህብረተሰቡን ሕይወት ለማሻሻል የከተማን የገቢ አቅም በማሳደግ የተሠሩ ሥራዎች፣ የጤና ተቋማትና የትምህርት ቤቶች ተደራሽነት መስፋፋት፣ ለነዋሪዎች የሚደረጉ የመሠረተ ልማት አቅርቦቶች ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ ተጠናክረው መቀጠላቸው ተመላክቷል።

​እነዚህ እመርታዎች ሀዋሳ የሰላም፣ የቱሪዝም እና የኢንቨስትመንት ማዕከልነቷን ይበልጥ ያጠናከሩ እና የነዋሪዎችን የኑሮ ደረጃ ያሻሻሉ መሆናቸው በመድረኩ ተሳታፊዎች ተገልጿል፤ ስኬቶቹን ይበልጥ በተቀናጀ መልኩ ከዳር ለማድረስም ሁሉም ርብርብ ማድረግ እንዳለበት ተጠቁሟል።

​የቀረበውን ሰነድ ተከትሎ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ታፈሰ ማቲዎስ አወያይነት ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ የሀዋሳ ከተማ ገቢዎች ባለሥልጣን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ መልኩ ማርቆስ እና ኢንጂነር ቸርነት ፍላቴ ከተወያዮች ለተነሱ ሀሳቦች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የድምፅ መጠን ገደብን በማያከብሩ የመዝናኛና የምሽት ክበቦች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ​በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ የምሽት ክበቦችና የድምፅ መሣሪያ ተጠቃሚ ...
06/09/2026

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የድምፅ መጠን ገደብን በማያከብሩ የመዝናኛና የምሽት ክበቦች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ

​በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ የምሽት ክበቦችና የድምፅ መሣሪያ ተጠቃሚ ተቋማት በአካባቢው ማኅበረሰብ ላይ የሚያደርሱትን የድምፅ ብክለት ለመቅረፍ እና የተጣለውን ሕግ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲያከብሩ የሚያስችል አዲስ አቅጣጫ ተቀመጠ።

​ከተማ አስተዳደሩ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ባቋቋመው ግብረ-ኃይል አማካኝነት ከባለቤቶቹ ጋር ሰፊ ውይይት አድርጓል።

​የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ ፍቅሬ በመድረኩ እንደገለጹት፣ ከተማዋ ለቱሪዝም ዘርፉ ምቹ ሆና እንድትቀጥል አስተዳደሩ በትኩረት እየሠራ መሆኑንና በዚህም የቱሪስት ፍሰቱ እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል።

​ይሁን እንጂ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የቱሪስቱንም ሆነ የነዋሪውን ምቾትና ሰላም ሙሉ በሙሉ ባከበረ መልኩ ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ አሳስበዋል።

​ኃላፊው አያይዘውም አብዛኛዎቹ የምሽት መዝናኛ ቤቶች የተቀመጠውን ደንብ አክብረው እየሠሩ ቢሆንም፣ አንዳንዶች ሕጉን በመተላለፍ በነዋሪዎችና በጎብኚዎች ላይ ከፍተኛ የድምፅ ብክለትና ተፅዕኖ እየፈጠሩ መሆኑን ተናግረዋል።

​ችግሩን በዘላቂነት ለማስተካከል ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ ግብረ-ኃይል መቋቋሙንና ሥራ መጀመሩን ገልጸው፤ ከተቀመጠው የሕግ ማዕቀፍ ውጪ በሚንቀሳቀሱ እና የድምፅ ገደቡን በማያከብሩ አካላት ላይ ጥብቅ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አበክረው አሳስበዋል።

​የሀዋሳ ከተማ አካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቁጥጥር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ሹምባሻ በበኩላቸው፣ የከተማው ነዋሪዎች ከመዝናኛ ቤቶች በሚወጣ ሕገወጥና ከፍተኛ ድምፅ ሳቢያ ለተለያዩ ማኅበራዊ ችግሮች እየተጋለጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በዚህም መሠረት ተቋማቱ የተፈቀደውን የድምፅ መጠን በመጠበቅ ወይም ሕጉን የሚያስከብር የድምፅ መከላከያ ቴክኖሎጂ በመዘርጋት ችግሩን እንዲቀርፉ አስረድተዋል። ተቋማቱ የሕጉን ገደብ ሙሉ በሙሉ አክብረው እንዲሠሩም አሳስበዋል።

​ይህንን የምክክር መድረክ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ ፍቅሬ እና የከተማዋ አካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቁጥጥር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ሹምባሻ የመሩት ሲሆን፤ በክፍለ ከተማ ደረጃ የሚገኙ የሥራ ኃላፊዎች፣ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ባለቤቶችና ተወካዮች ተገኝተዋልል።

ከሙያዊ አስተዋፆ ባሻገር በበጎነት ማህበራዊ ኃላፊነትን መወጣት እንደሚገባ ተገለፀይህ የተገለፀው በጤና ተጓዳኝ ዘርፍ ባለሙያዎች የተመሰረተው በጢሌ የበጎ አድራጎት ማህበር የትምህርት ቁሳቁስ ...
05/09/2026

ከሙያዊ አስተዋፆ ባሻገር በበጎነት ማህበራዊ ኃላፊነትን መወጣት እንደሚገባ ተገለፀ

ይህ የተገለፀው በጤና ተጓዳኝ ዘርፍ ባለሙያዎች የተመሰረተው በጢሌ የበጎ አድራጎት ማህበር የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ባደረገበት ወቅት ነው።

በመድረኩ የሀዋሳ ከተማ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ፍሬህይወት ወ/ፃዲቅ ከሙያዊ ኃላፊነት ባሻገር ለማህበረሰቡ በጎ አስተዋፆ ማድረግ የአንድ ባለሙያ ማህበራዊ ኃላፊነት መሆኑን ገልፀው፣ በጢሌ የበጎ አድራጎት ማህበር ለተማሪዎች ያደረገው ድጋፍ ለሌሎችም አርዓያ የሚሆን ተግባር መሆኑን ጠቁመዋል።

የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ እርዳቸው አናቶ በበኩላቸው የማህበሩ አባላት በጤና ዘርፍ ያላቸውን ሙያዊ አስተዋፆ በመጠቀም ተጨማሪ ማህበራዊ ድጋፍ ማድረጋቸው ለማህበረሰቡ የመተጋገዝና የመተባበር ባህልን የሚያጠናክር በመሆኑ ተግባሩ በቀጣይም እንዲጠናከር ጥሪ አቅርበዋል።

የማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ተሽቴ ኬአ በበኩላቸው ማህበሩ ከተመሠረተ 2 ዓመት የሞላው ሲሆን፣ “ባጥሌ” በሲዳሙ አፎ ፍቅር ማለት ነው። ከ80% በላይ አባላቱ በአዳሬ ጀነራል ሆስፒታልና በተለያዩ የመንግስት ተቋማት የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች ሲሆኑ፣ ዓላማው በፍቅርና በመተሳሰብ የተሳሰረ፣ በዕውቀትና በኢኮኖሚ ራሱን የቻለ እና ለወገኑና ለሀገሩ በጎ ተግባር የሚያከናውን ወጣት ማፍራት በማለት ማህበሩ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች እንደሚንቀሳቀስ አመላክተዋል።

የዛሬው የክረምት በጎ አድራጎት መርሀ ግብር እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ነገር ግን በተለያየ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ምክንያት ወደ ትምህርት ገበታ መሄድ ያልቻሉ ህፃናትን የደብተር እና እስክሪፕቶ ድጋፍ ለማድረግ የታሰበ ነው። በዚህ መርሀ ግብር ከ150 በላይ ተማሪዎች የተካተቱ ሲሆን ለነዚህ ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው አንድ ደርዘን ደብተር እና እስክሪፕቶ ተደራሽ መደረጉን የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ ኤልፋዝ ሽታዬ

በዚህም በጢሌ የበጎ አድራጎት ማህበር ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በማበርከት በትምህርት ሂደታቸው ላይ ያለውን ጫና ለማቃለል እና ተማሪዎች በትምህርታቸው እንዲበረታቱ ያለውን ማህበራዊ ድጋፍ አሳይቷል።

የሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ በዲጂታል አደረጃጀት ላይ ያተኮረ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።ስልጠናው የዲጂታል አባላት መረጃ አያያዝን ማሳደግ፣ የአባላት ዲጂታል መታወቂያን በተግ...
05/09/2026

የሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ በዲጂታል አደረጃጀት ላይ ያተኮረ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

ስልጠናው የዲጂታል አባላት መረጃ አያያዝን ማሳደግ፣ የአባላት ዲጂታል መታወቂያን በተግባር ማስፋፋት፣ በኬፒአይ መሰረት የተደገፈ የአንድ እቅድ አንድ ሪፖርት አሰራርን ማጠናከር እና ዲጂታል አደረጃጀቶችን እውን ማድረግ ላይ ያተኮረ ነው።

የሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መስፍን አየለ በመልዕክታቸው የአባላት መረጃ በዘመናዊ ዲጂታል ስርዓት መያዙ የአደረጃጀቱን የስራ ቅልጥፍና፣ ተጠያቂነትና ውጤታማነት ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። የአባላት መረጃ በትክክልና በወቅቱ መመዝገቡና መዘመኑ የዕቅድ አፈጻጸምን በመረጃ ለመደገፍ እና የአደረጃጀቱን አቅም ለማጠናከር የሚያግዝ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

አቶ መስፍን አያይዘውም ስልጠናው በአደረጃጀቱ የሚከናወኑ የመረጃ አያያዝና የሪፖርት ሂደቶችን በአንድ ዲጂታል ስርዓት ለማስተሳሰር የሚያግዝ መሆኑን ጠቁመው፣ የስልጠናው ይዘት በተግባር እንዲውል በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ስልጠናው በዲጂታል መረጃ አያያዝና በመረጃ ላይ የተመሰረተ የአደረጃጀት አሰራርን በማጠናከር፣ የአባላት መረጃ በቀላሉ እንዲደራጅና እንዲጠቀምበት የሚያስችል አሰራር ለመዘርጋት የሚያግዝ ነው።

የሀዋሳ ከተማ የጽዳት እና ውበት ሥራ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ ቀጥሏልበሀዋሳ ከተማ የንፅህናና የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች የነዋሪዎችን፣ የተለያዩ ተቋማትንና የማህበረሰብ አደረጃጀቶችን በማሳ...
05/09/2026

የሀዋሳ ከተማ የጽዳት እና ውበት ሥራ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ ቀጥሏል

በሀዋሳ ከተማ የንፅህናና የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች የነዋሪዎችን፣ የተለያዩ ተቋማትንና የማህበረሰብ አደረጃጀቶችን በማሳተፍ በተቀናጀ መልኩ እየተከናወኑ ነው።

በዚህም ሳምንት በመንገድ ዳርቻዎች፣ በህዝብ መገልገያ ስፍራዎችና በተለያዩ የከተማ አካባቢዎች የጽዳት ሥራዎች ተከናውነዋል። ቆሻሻን መሰብሰብና በአግባቡ ማስወገድ፣ የአካባቢ ጽዳትን ማሻሻልና የከተማ ውበትን ማስጠበቅ ላይም ትኩረት ተሰጥቷል።

የንፅህና ሥራዎቹ በተከታታይ መካሄዳቸው የከተማ ጽዳትን የዘመቻ ሥራ ብቻ ሳይሆን በየዕለቱ ሊተገበር የሚገባው የጋራ ኃላፊነት እንዲሆን እያገዘ ይገኛል። በተለይም የነዋሪዎች ቀጥተኛ ተሳትፎ የጽዳት ሥራውን ከማጠናከር ባለፈ ለአካባቢ ጥበቃ ያለውን ግንዛቤ እንዲያድግ እያደረገ ነው።

ንፁህና የተዋበ ከተማ ለጤናማ ኑሮ እና ለተሻለ የኑሮ ሁኔታ ወሳኝ በመሆኑ፣ የንፅህና ሥራዎች በቀጣይም በተቀጣጣይ መልኩ እንዲቀጥሉ ትኩረት ተሰጥቷል።

በመሆኑም የከተማዋን ንፅህናና ውበት ለማስጠበቅ ነዋሪዎች በተደራጀ የጽዳት ሥራ ብቻ ሳይወሰኑ አካባቢያቸውን በየዕለቱ እንዲጠብቁ፣ ቆሻሻን በአግባቡ እንዲያስወግዱና ለንፅህና የሚያደርጉትን የጋራ ጥረት እንዲያጠናክሩ ጥሪ ቀርቧል።

የሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ የኮማንድ ፖስት አፈጻጸም ገመገመየሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ በዘርፉ ስር ...
05/09/2026

የሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ የኮማንድ ፖስት አፈጻጸም ገመገመ

የሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ በዘርፉ ስር የሚገኙ የተለያዩ መምሪያዎች የኮማንድ ፖስት አፈጻጸምን ገምግሟል።

በግምገማው የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ጤና፣ የእንስሳትና አሳ ሀብት፣ የህብረት ሥራ እና ሌሎች የልማት ዘርፎች ያከናወኗቸው ሥራዎች፣ የተመዘገቡ ውጤቶች፣ ያጋጠሙ ችግሮችና በቀጣይ ሊሻሻሉ የሚገባቸው አፈጻጸሞች በስፋት ተገምግመዋል።

የሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ባቢሶ ባናታ በግምገማው መድረክ እንደገለጹት፣ የኮማንድ ፖስቱ አፈጻጸም በመረጃና በማስረጃ በመመርመር ጠንካራ ጎኖችን ማጠናከርና የአፈጻጸም ክፍተቶችን በጊዜ ለይቶ ማስተካከል ያስፈልጋል። በተለይም የተያዙ የልማት ዕቅዶች በተጨባጭ ውጤት እንዲመዘኑ እና በቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ላይ በጋራ ትኩረት እንዲደረግ አሳስበዋል።

ኃላፊው አክለውም፣ የተመዘገበው ውጤት መሠረት ተደርጎ ያሉ ችግሮችን በመፍታት፣ የተሻለ አፈጻጸም ያሳዩ የሥራ ክፍሎችን በማጠናከርና የተገኙ ልምዶችን በማስፋት የቀጣይ ጊዜ ሥራዎች በተሻለ ውጤት እንዲመሩ አቅጣጫ መቀመጡን ገልጸዋል።

ግምገማው የዘርፉን የሥራ አፈጻጸም በጋራ በመመርመር የተገኙ ውጤቶችን ለማጠናከር፣ የታዩ ክፍተቶችን ለማረምና በቀጣይ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን በተሻለ ውጤታማነት ለመፈጸም የሚያግዝ ነው።


#ሀዋሳብልጽግና

Address

Awassa
0000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Prosperity Party Hawassa City Branch Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share