South Ethiopia Region Finance Bureau

South Ethiopia Region Finance Bureau ይህ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ትክክለኛ የፌስቡክ ገጽ ነው!
(2)

የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ከገንዘብ ሚኒስቴርና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ ጋር በሪፎርም ትግበራ ዙሪያ የልምድ ልውውጥ አካሄደነሐሴ 18/2018 ዓ.ምየደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይ...
25/08/2026

የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ከገንዘብ ሚኒስቴርና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ ጋር በሪፎርም ትግበራ ዙሪያ የልምድ ልውውጥ አካሄደ

ነሐሴ 18/2018 ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ፥ የፋይናንስ ሴክተር የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የዝግጅት ምዕራፍ ትግበራን አስመልክቶ ከገንዘብ ሚኒስቴርና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ ጋር የልምድ ልውውጥና የምክክር መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ የሪፎርሙ የዝግጅት ምዕራፍ ትግበራ አፈጻጸም፣ በዕቅድ መሠረት የተከናወኑ ተግባራት፣ የተመዘገቡ ውጤቶችና በትግበራ ሂደቱ የተለዩ ተግዳሮቶች በስፋት ተገምግመዋል።

ከገንዘብ ሚኒስቴርና ከአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ የተገኙ ተሞክሮዎችም ቀርበው፣ በተለይም የሪፎርሙን ትግበራ በተሻለ አቅም ለማስፈጸም የሚያስችሉ የአሠራር አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ምክክር ተደርጓል።

የሪፎርሙን የትግበራ አቅም ማጠናከር፣ የሥራ ሂደቶችን ማሻሻል፣ ተቋማዊ አሠራሮችን ማዘመንና ቀልጣፋና ውጤታማ የመንግሥት አገልግሎትን ማረጋገጥ በሚቻልባቸው አግባቦች ላይም ትኩረት ተሰጥቷል።

የልምድ ልውውጡ በፋይናንስ ሴክተሩ የሚከናወኑ የሪፎርም ሥራዎችን በተቀናጀና በተጠናከረ መልኩ ለማስቀጠል፣ የአሠራር ሥርዓቶችን ለማዘመንና የተቋሙን የአፈጻጸም አቅም ለማሳደግ ጠቃሚ ግብዓት መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም የሪፎርሙ ትግበራ የመንግሥት አሠራርን ይበልጥ ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ተጠያቂ በማድረግ ለዜጎች የሚሰጠውን የመንግሥት አገልግሎት ጥራት ለማሻሻል የሚያግዝ መሆኑ ተመልክቷል።

በመድረኩ የተጋሩ ልምዶችና ተሞክሮዎች፣ እንዲሁም የተነሱ ሀሳቦች፣ የፋይናንስ ሴክተሩን የሪፎርም ሥራ በቀጣይ በተጠናከረ አግባብ ለመምራትና የታቀዱ ውጤቶችን ለማስመዝገብ ወሳኝ ግብዓት እንደሚሆኑ ተጠቁሟል።

23/08/2026
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች “ከተረጂነት ወደ ምርታማነት” በተቀረጸው የአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ ፈንድ ደንብ ላይ ተወያዩ​ነሀሴ 13-2018 ዓ.ም ወላይታ ሶደ የደ...
19/08/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች “ከተረጂነት ወደ ምርታማነት” በተቀረጸው የአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ ፈንድ ደንብ ላይ ተወያዩ​

ነሀሴ 13-2018 ዓ.ም ወላይታ ሶደ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች የክልሉን 3ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ “ለወገን ደራሽ ወገን ነው” በሚል መርህ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር በተዘጋጀው የአደጋ ጊዜ መደጋገፊያ ፈንድ ማሰባሰቢያ ደንብ ቁጥር 112/2018 ዙሪያ ውይይት አካሄዱ።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሶዶ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት፣ የክልሉ መንግስት ከተረጂነት በመላቀቅ ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን እያከናወነ ባለው ተግባር አበረታች ውጤቶች እየተመዘገቡ ይገኛሉ።

አቶ ተፈሪ አክለውም እንደ ሀገር ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን የሚያስችል የአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ ፈንድ ደንብ ቁጥር 112/2018 ወጥቶ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው፣ ምርታማነትን በማሳደግ ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን የሚደረገውን ጥረት ለማሳካት የተቀናጀ አሰራርና የሁሉንም አካላት ተሳትፎ እንደሚጠይቅ አብራርተዋል።​

ይህ እንደ ሀገር የተቀረጸው ደንብ የተለያዩ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ሲከሰቱ ችግሮችን በጽናት በመቋቋም ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን የሚያስችል መሆኑን ያብራሩት አቶ ተፈሪ፣ እንደ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን 3 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብና 698 ሺህ ኩንታል እህል በመጠባበቂያነት ለመያዝ የሚያስችሉ መጠነ-ሰፊ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

መጠባበቂያ ፈንዱ በክልሉ ከሚገኙ አጠቃላይ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከመንግስት ሰራተኞች የሚሰበሰብ በመሆኑ ለስኬታማነቱ ሁሉም በጋራ ሊረባረብ እንደሚገባ አሳስበዋል።​

አክለውም እንደገለጹት፣ በክልሉ ከሚገኙ አጠቃላይ የማህበረሰብ ክፍሎች መካከል 87 ሺህ የሚሆኑ ሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች የተለዩ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ ከ42 ሺህ በላይ የሚሆኑት የዕለት ደራሽ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው መለየታቸውን አስታውቀዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ በምግብ ራስን ለመቻል በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት፣ እንደ ሀገር መንግስት እያከናወናቸው ያሉ ስራዎች፣ እንደ ዜጋ ከሁላችንም የሚጠበቁ ኃላፊነቶችና ተረጂነትን ስለ መጸየፍ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

የቢሮው አመራሮችና ሰራተኞች በበኩላቸው የተጀመረውን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የመሸጋገር ሀገራዊና ክልላዊ ጥረት በመደገፍ፣ የመጠባበቂያ ፈንዱን ለማጠናከርና ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን የሚደረገውን ጥረት በቁርጠኝነት ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን በመግለጽ ውይይቱ ደንቡ ላይ በመስስማማት ተጠናቋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች የክልሉን 3ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በደመቀ ሁኔታ አከበሩ​።ወላይታ ሶዶ —13_2018 ዓ.ምየደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፋይናን...
19/08/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች የክልሉን 3ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በደመቀ ሁኔታ አከበሩ​።

ወላይታ ሶዶ —13_2018 ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ አመራሮችና መላው ሰራተኞች ክልሉ ህገ-መንግስታዊ እውቅና አግኝቶ የተመሰረተበት 3ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን በጋራ በመሆን በደመቀ ሁኔታ አክብረዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ነሀሴ 13 ቀን 2015 ዓ.ም በይፋ የተመሰረተ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት 12 ዞኖችን፣ 65 ወረዳዎችን እና 41 የከተማ አስተዳደሮችን በማቀፍ ከ9.3 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሚኖርበት ከሀገሪቱ 3ኛው ትልቅ ክልል ሆኖ የተደራጀ ህዝባዊና ልማታዊ ክልል ነው።​

በበዓሉ አከባበር ስነ-ስርዓት ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሶዶ ክላስተር አስተባባሪና የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፣ ክልሉ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ባለፉት ሶስት አመታት ውስጥ በህዝቡ ሁለንተናዊ ተሳትፎና በአመራሩ ቁርጠኝነት የተመዘገቡትን ሁለገብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስኬቶች በዝርዝር አቅርበዋል።

አቶ ተፈሪ ባቀረቡት ማብራሪያ፣ ክልሉ ከተመሰረተ ማግስት ጀምሮ ቅድሚያ ተሰጥቶት በተሰራው ህዝብን ያማከለ የሰላም ግንባታ ስራ በሁሉም አካባቢዎች የተረጋጋ ሰላም የሰፈነ ሲሆን፣ ይህም ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች መቃናት ዘላቂ መሠረት ጥሏል።

በተጨማሪም የአገልግሎት አሰጣጥን በማቀላጠፍና የፍትሃዊነትና ግልጸኝነት አሰራሮችን በመዘርጋት ለህዝቡ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ተጨባጭ ምላሽ መስጠት ተችሏል።​

በመሰረተ ልማት ዝርጋታና ተደራሽነት ዘርፍም የዜጎችን ህይወት የሚያሻሽሉ አበይት ስራዎች መከናወናቸውን ኃላፊው ገልጸዋል። በዚህም የመንገድና የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን በማስፋፋት፣ የጤናና የማረሚያ ተቋማትን ደረጃ በማሻሻል፣ ህዝብን ባንድ ማዕከል ፈጣን አገልግሎት የሚሰጠውን "የመሶብ" የአንድ ማዕከል አገልግሎት በመዘርጋት እንዲሁም የአቪዬሽን ዘርፍን የሚያጠናክሩ የአውሮፕላን ማረፊያዎች ግንባታና የማስፋት ስራዎች ውጤታማ ስኬት ተመዝግቦባቸዋል።

ጎን ለጎንም የከተሞችንና የገጠር ማዕከላትን ውበትና ምቾት ለመጠበቅ፣ ለንግድና ለስራ እድል ፈጠራ ተስማሚ ለማድረግ በስፋት የተከናወኑት የኮሪደር ልማት ስራዎች የክልሉን ገጽታ በከፍተኛ ደረጃ መቀየር ችለዋል።​በግብርና፣ በፋይናንስና በሰብአዊ ድጋፍ ዘርፎች የተመዘገቡት ውጤቶችም የዚሁ ስኬት አካል ናቸው።

በአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ አሰራሮች፣ በሰብል ልማትና በእንስሳት ሀብት ላይ በተደረገው ከፍተኛ ጥረት የምርትና ምርታማነት እድገት ተመዝግቧል።

በሌላ በኩል የፋይናንስ ስራን በማጠናከር፣ የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱን በማዘመንና የታክስ መሰረቱን በማስፋት የክልሉን የውስጥ ገቢ አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ተችሏል።

ከሁሉም በላይ ሰብአዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን የተከናወኑት ስራዎች ውጤት አሳይተው፣ የህብረተሰቡን የምግብ ዋስትና በማረጋገጥ ከተረጂነት አስተሳሰብ ወደ ምርታማነት የመሸጋገር ትልቅ እርምጃ ተወስዷል።​

አቶ ተፈሪ አባተ አክለውም፣ በወላይታ ሶዶ በድንገተኛ የእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰበትን የኦቶና ሆስፒታል መልሶ ግንባታ ለማስጀመር አስፈላጊው ቅድመ ሁኔታ መጠናቀቁን ገልጸው፤ የሱማሞ አየር ማረፊያ ግንባታ ስራ በበለጠ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።​

በበዓሉ ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የፋይናንስ ቢሮ ሰራተኞችና አመራሮች ባለፉት ሶስት አመታት በተከናወኑ አበይት የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች የተመዘገቡትን አንጸባራቂ ስኬቶች ያደነቁ ሲሆን፣ አዳዲስ አሰራሮችን በመከተል ክልሉ የጀመረውን ሁለንተናዊ የዕድገት ጉዞ ለማስቀጠል የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ተዘጋጅተዋል።

ሰራተኞቹ አክለውም፣ የተገኙትን ውጤቶች አጠናክሮ ለማስቀጠልና የክልሉን የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓት የበለጠ ግልጽ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ በቀጣይም በላቀ ቁርጠኝነትና ትጋት ጠንክረው ለመስራት በጋራ ቃል ገብተዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለክልል የፀደቀ ጠቅላላ በጀት መረጃ በየገቢ ምንጭ
19/08/2026

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለክልል የፀደቀ ጠቅላላ በጀት መረጃ በየገቢ ምንጭ

19/08/2026

ተረጂነትን መቀነስና የራስን አቅም ማሳደግ ሀገርን ከውጭ ተጽዕኖ ለመጠበቅ ወሳኝ መሆኑን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የክልሉ ሶስተኛ ዓመት ምስረታ በተመለከተ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሶስተኛ ዓመት ምሥረ...
19/08/2026

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የክልሉ ሶስተኛ ዓመት ምስረታ በተመለከተ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሶስተኛ ዓመት ምሥረታ በማስመልከት ለመላው የክልሉ ሕዝቦች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፤ የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

እንኳን ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 3ኛ ዓመት ምሥረታ አደረሰን! አደረሳችሁ!

የኅብረ-ብሔራዊት ኢትዮጵያ ነፀብራቅ፤ ቀዳሚ የብዝኃ ሕዝቦች የጋራ ቤት የሆነው ክልላችን፤ በክልሉ ሕዝቦች ነፃ ፍላጎትና ይሁንታ፤ ፍጹም ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ ሕገ-መንግስታዊ ሂደት፤ ነሐሴ 13 ቀን 2015 ዓ.ም በተካሄደ ታሪካዊ የምስረታ ጉባኤ የፌደረሽኑ 12ኛው ክልል ሆኖ በይፋ ከተመሠረተ እነሆ ዛሬ ሦሥተኛ ዓመቱን ይዟል፡፡

የክልላችንን የ3ኛ ዓመት ምስረታ የምናስበው፤ እንደ ሀገር በረዥሙ የሀገረ-መንግስት ታሪካችን ሲንከባለሉ የመጡ ጥልቅ ፖለቲካዊ ልዩነቶችንና ታሪካዊ ቅራኔዎች በታሪካዊው ሀገራዊ ምክክር ቋጭተን በምክክር የፀናች ተምሳሌታዊ ኢትዮጵያን ለማሻገር ከጫፍ በደረሰንበት አጓጊ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ሆነን መሆኑ ታሪካዊ ያደርገዋል፡፡

ሰላም መገለጫው፤ ብዝኃነት መለያው የሆነው የሰላም ተምሳሌቱ ክልላችን፤ የክልሉን ሕዝቦች አብሮ የመልማት ትልም ዕውን ማድረግ በሚያስችል አግባብ ተደራጅቶ ወደ ስራ በመግባት፤ ባለፉት ሦሥት ዓመታት ለፈተናዎች ያልተበገረ፤ በበርካታ ውጤቶች የታጀበ፤ ቃልን በተግባር ማረጋገጥ የቻለ ስኬታማ ጉዞ ማድረግ ችሏል፡፡

የክልላችን መመስረት፤ ለክልሉ ህዝቦች የአደረጃጀት ጥያቄዎች አሳታፊና ዲሞክራሲያዊ በሆነ አግባብ ታሪካዊ ምላሽ መስጠት ከመቻሉም በላይ የክልሉ ህዝብ ከግጭት አዙሪት ወጥቶ ፍቱን ሙሉ በሙሉ ወደ ልማት በማዞር በጋራ የመልማት ትልሙን ዕውን ለማድረግ በኅብረት በመትጋት ላይ እንዲገኝ አስችሎታል፡፡

መዳረሻውን ዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና ባደረገው ክልላችን፤ ባለፉት ሦሥት ዓመታት በሰላምና በልማት አርበኛው ህዝባችን ግንባር ቀደም ተሳትፎ እና ተደማሪ አቅም፤ ክልሉን የሰላም፤ የመቻቻልና የብልፅግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ በመሰነቅ፤ በሁሉም የልማት አውታሮች አስደናቂ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል፡፡

የክልሉ መገለጫ ለሆነው ሰላም ልዩ ትኩረት በመስጠት አሳታፊ በሆነው የለውጡ የፖለቲካ ባህል እየተመራ፤ ህዝቡን የሰላሙ ባለቤት በማድረግ፤ የህዝብ ለህዝብ ትስስር ስራዎችን በማጠናከር እና ነባር ሀገር በቀል የሰላም ግንባታ ተቋማትን በመጠቀም በተሰሩ የተቀናጁ ስራዎች በክልሉ አስተማማኝ የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

ሀገር በቀሉ የብዝኃ-ዘርፍ የኢኮኖሚ ማሻሻያው የፈጠረውን ምቹ ዕድል እና የክልላችንን እምቅ የመልማት አቅም በአግባቡ በመጠቀም በተሰሩ ዘርፈ ብዙ ስራዎችም፤ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በመደረግ ላይ ያለውን ሽግግር ይበልጥ ያጎለበቱ፤ ለሀገራዊና ክልላዊ ራዕዮች ስኬት መሰረት የጣሉ ውጤቶች መመዝገብ ችለዋል፡፡

በተለይ ብዝኃነትን፤ በጋራ መልማትንና የፍትሀዊ ተጠቃሚነት መርህን በማስቀደም፤ በዋና ዋና የማህበራዊ ልማት እና የኢኮኖሚያዊ ዕድገት ዘርፎች እንዲሁም የውስጥ አቅምን በማጎልበት በራስ አቅም በተሰሩ ውጤታማ ስራዎችና ሰው ተኮር ተግባራት፤ የህዝባችንን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ አመርቂ ውጤቶች ተገኝተዋል፡፡

እንደ ሀገር በወጥነት ለማሳካት በታለሙ የልማት ኢንሸቲቮች ትግበራም፤ የክልሉን ህዝብ በማስተባበር ተጨባጭ ውጤቶች ማስመዝገብ የተቻለ ሲሆን፤ ለአረንጓዴ ልማት ስራዎች ትኩረት በመስጠትም ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታና የተፈጥሮ ሚዛኑን የጠበቀ ከባቢን ለትውልድ ለማሻገር መሰረት የጣለ ውጤታማ ስራ መስራት ተችሏል፡፡

በዚህም ባለፉት ሦሥት የአንድነት፤ የኅብረት፤ የትብብርና የስኬት ዓመታት፤ በገጠርም ሆነ በከተሞች ለህዝብ አዳጊ የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ምላሽ በመስጠት፤ በመደመር መንግስት አሻጋሪ ዕሳቤዎች የተቃኙ ክልላዊ እና ሀገራዊ የልማትና የብልፅግና ትልሞችን ባጭር ጊዜ ዕውን ማድረግ የሚያስችል ስኬታማ ጉዞ ማድረግ ችለናል፡፡

በአጠቃላይ ያለፉ ሦሥት ዓመታት ጉዟችን፤ በጋራ ለሰነቅነው የዘላቂ ሰላምና የሁለንተናዊ ብልፅግና ራዕይ ስኬት እጅ ለእጅ ተያይዘን፤ ኅብረት ትብብራችንን በማጠናከር በጋራ ከሰራን በተደማሪ አቅም የማንሻገረው ፈተና፤ የማናሳካው የልማት ትልም አለመኖሩን በተግባር ያሳየን መሆኑን መገንዘብ ይገባል፡፡

በቀጣይም በተባበረ ክንድ ያቀጣጠልነውን የሰላምና የልማት ችቦ አጠናክረን፤ በጋራ ለሰነቅነው የዘላቂ ሰላምና ብልፅግና ግብ ስኬት፤ በክልሉ ያሉ ፀጋዎችና የመልማት አቅሞች ተጠቅመን በሰላምና በልማት አርበኛው ህዝባችን ግንባር ቀደም ተሳትፎ የተቀናጀ ርብርብ በማድረግ ለላቀ ውጤት የምንተጋ ይሆናል፡፡

በመጨረሻም መላው የክልላችን ሕዝቦች በወንድማማችነት የፀና አንድነታችሁን ጠብቃችሁ የሰላምና የልማት ትብብራችሁን በማጠናከር፤ ፈጣን ዕድገት፤ ዘላቂ ሰላምና ልማት የተረጋገጠበት ተምሳሌታዊ ክልል በማሻገር ለጠንካራዋ ኢትዮጵያ ዕውን መሆን ከፍ ያለ አበርክቶ ማበርከት እንዲንችል እጅ ለእጅ ተያይዛችሁ እንዲትሰሩ ሲል ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።

መጪው ጊዜ የስኬት እንድሆን እመኛለሁ!

ፈጣሪ አገራችንና ህዝቦቿን ይባርክ!

ጥላሁን ከበደ
ርዕሰ መስተዳድር

"የግብርና ሥራን በማዘመን ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን ተቀናጅቶ መሥራት ይገባል"- አቶ ተፈሪ አባተነሐሴ 12/2018 ዓ.ምበደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸ...
18/08/2026

"የግብርና ሥራን በማዘመን ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን ተቀናጅቶ መሥራት ይገባል"- አቶ ተፈሪ አባተ

ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን የሚያስችሉ ዘላቂ መፍትሔዎች ላይ የተቀናጀ ሥራ እንዲሠራ ተገለጸ።

በተለይም የግብርና ሥራን በማዘመን፣ ምርታማነትን በማሳደግና የሕዝቡን የምግብ ራስን መቻል በማረጋገጥ ከተረጂነት ለመላቀቅ አበክሮ መሥራት እንደሚገባ ተጠቁሟል።

በዚህ ዙሪያ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር የአጋርነትና የትብብር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል።

መድረኩ ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን የሚያስችሉ የጋራ የሥራ አቅጣጫዎችን ለመለየትና የተለያዩ አካላትን በትብብር ለማሳተፍ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሶዶ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ፣ ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም መሸፈን የክብርና የራስን አቅም የማሳደግ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው፣ ለዚህም ሁሉም አካላት በተቀናጀ መልኩ አበክረው መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ለዚህ ዓላማ የሚሰበሰበው ፈንድ በክልሉ ከሚገኙ በጀት የሚመደብላቸው መሥሪያ ቤቶች፣ ከመንግሥት ሠራተኞች፣ ከሃይማኖት ተቋማት፣ ከንግዱ ማኅበረሰብ፣ ከመንግሥት የልማት ድርጅቶችና ከሲቪል ማኅበረሰብ ተቋማት በሚደረግ አስተዋጽኦ የሚሰበሰብ መሆኑን አስረድተዋል።

በዚህም ለተጎጂዎች የምግብና የምግብ ነክ ድጋፎች፣ የእርሻ ቁሳቁሶች፣ የማካካሻ ዘር፣ የእንስሳት መኖ እንዲሁም ለመጠለያ ግንባታ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ድጋፍ እንደሚደረግ አቶ ተፈሪ አመላክተዋል።

የሚሰበሰበው ፈንድ ለታለመለት ዓላማ ብቻ በአግባቡ መዋሉን ለማረጋገጥም ጠንካራ የኦዲትና የቁጥጥር ሥርዓት እንደሚዘረጋ ገልጸዋል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊና የፊሲካል ፖሊሲና ትብብር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታምራት ታንጋ በበኩላቸው፣ የመድረኩ ዋና ዓላማ ሰብዓዊነትን ማስፋፋትና በችግር ወቅት የሚደረገውን ድጋፍ በጋራ ማጠናከር መሆኑን ገልጸው፣ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የድርሻቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጠይቀዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎችም በሰጡት አስተያየት፣ ከተረጂነት መላቀቅ እና ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም መሸፈን የጋራ ኃላፊነት መሆኑን ገልጸዋል።

ተረጂነትን መቀነስና የራስን አቅም ማሳደግ ከውጭ ተጽዕኖ ራስን ለመጠበቅና ለተሻለ ራስን መቻል ወሳኝ ጉዳይ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

ተሳታፊዎቹ በተለይም የግብርና ሥራን በማዘመን፣ የግብርና ግብዓቶችንና ቴክኖሎጂዎችን በማስፋፋት እና ምርታማነትን በማሳደግ የሕዝቡን የምግብ ራስን መቻል ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በተጨማሪም የሚሰበሰቡ ሀብቶች በተቀመጠላቸው ዓላማ ብቻ እንዲውሉ ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ ግልጽና ተጠያቂነት ያለው የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

መድረኩ በጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ተጠናቋል።

Address

3F7P+ 533
Awassa
104

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South Ethiopia Region Finance Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share