የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

  • Home
  • Ethiopia
  • Awassa
  • የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

14/08/2026

እናት ደህና፣ ልጅም ጤና!

የሲዳማ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ በእናቶችና ሕፃናት ጤና ያስመዘገበውን ለውጥና ውጤት የሚያሳይ ይህንን አጭር ዶክመንተሪ ቪዲዮውን ይመልከቱ፣ ሀሳብዎን በኮሜንት ያካፍሉን፣ ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር ያድርጉ !

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
ነሀሴ 8/2018 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

100 barri fayyimmate loossa handaari mixo lifixxinota ikkite dagooma horaameette assitannota xawinsi. Woxawaajje 6/2018 ...
12/08/2026

100 barri fayyimmate loossa handaari mixo lifixxinota ikkite dagooma horaameette assitannota xawinsi.

Woxawaajje 6/2018 M.D Fayyimmate Biiro

Qoqqowoho Ayr/ Paartete Sooreessinni Kalaa Abraami Marshaalonni massagantinoti 100 barri millimmote kakkayishshi barera shiqqinoti Fayyimmate Biiro mixo loosu aana hosse dagoomu horaamimma buuxissannota kulloonni.

Konnirano Qoqqowu Fayyimmate Biiro gede aananno 100 barrira konni woroonni noo bixxilluwa loosu aana hosiisate mixi’noonni .

👉 Taraabbannonna taraabbannokki dhiwanna ittisatenna gargarate loossa
Fayyimmanna fayyimma labbanno owaantena udiinnu qorqorsha assatenni hattono fayyimmate gawajjo abbitara dandiitanno dhiwanna xiinxallotenni irkisatenninna badatenni horrote ikkito ittisatenni lifixxino owaante aate akata injiino garinni jeefisate illacha tunge loonsoonni.

👉 Co'itte ikkitino fayyimmate uurrinshuwa yaano fayyimmate xaawubbanna hospitaaluwa kalaqa

👉 Owaante woyyitinota assa

👉 Gibiaatete qorqorshanna shiqo woyyeessa

👉 Dijitaale teknolooje horoonsi'ratenni woyyinore loosa

👉 Kuri loossa deerra deerraho afantanno tantanubba loosonsa loossanno gede assa
Gobbate deerrinni worroonni wodho bikkaasinchinni keenneenna qaddo ikkitinno woraada kiirotenni 5 kalaqa

👉 Luphiima guma maareekkisiisse qaddo ikkitinno fayyimmate uurrinshubba kiirotenni 31 ikkitannota kalaqa

👉 Qaddo ikkitinno oluubba fayyimmate ekistenshiine pakeejjubba ikkadimmatenni gumulinore 60 kalaqa.

👉 Fayyimmate uurrinshara qajeeltino fayyimmate ogeeyyenni uuynanni ilate owaante 93% ikkanno amuwi mixotenni illanno gede assa.

👉 Maatete jireenyi qaacha kaalaqa
Fayyimmate uurrinshubbara xagichunna looso harisate ikkado woxi gaamme egensiisa umi bocira hasiisannoha 100% dirrisa.

👉 Dagate Xagichi Mine fantinokki woradda ikkado baajeette amadde fantanno assa
Fayyimmate xaawubbaranna hospitaalubbate qara qara hasiissanno xagicho uurrinshubbate afirate bikka 90% iillisha.

👉 Fayyimmate Xaawanna Fayyimmate Keellubba (110) gatamarsha hasirannoha dagate millimillo assatenni 100% mucci asse guda hattono xaphooma Fayyimmate keella mittu mittunku woradi mitticho mixire dagate millimillonni hanafanno assa

👉 Amubulaansubba uurritinota baalante woraddara 100% gatamarante loosu aana hossanno assa .

👉 Dagooma hanqaffino fayyimmate woowe buxichu buxichira amandanni woxe woraddatenna qoqqowu qeecha amada hattono Dagooma hanqaffino fayyimmate woowe miilla kalaqate assinannita balaxote qixxaawo gudatenni loosu giddora ea

👉 Fayyimmate uurrinshubbara looso harisate ikkanno woxe mitte hospitaalera 1 miloone hattono mittu fayyimmate xaawira 600 kume birra mixote amada

👉 Fayyimmate uurinshubbara heedhanota laabratoorete owaante deerrase agadhitinota assate hasiissanno irko assa
Fayyimmate haandari hawadi dancha fajjo owaante loossa gumulate amandoonni mixo garinni baalantanni haja jeefisa hattono Hawadi yanna mundee gamba assa

👉 Hawaasi Quchumira hedhanota fayyimmate xaawubbanna hospitaalla womunni woma dijitaale assa hattono Hawaasi Quchumira heerano xagicho dagoomu fayyimanke/teninete ጤንነት/ yinannita dijitaale appe horoonsire afiranno assa/ baalantinni uurrinsha loosu giddora eanno gede kaajjisha

👉 Dillaloote gadi soorro ha'runsite kalaqama dandiitannota fayyimmate mitiimmuba balaxe huwatatenni dagate huwanyoote baalante woraddara kalaqa.

👉 Shoolu woradira shekkeere luphi yite leeltannowa hasiissanno irko assatenni kemikaalete kiifatto harinsanni
Hooro akaata affidhinno fayya 1 bari gido reporte assatenni 7 bari gido urisate loonsanni hajo balauku huwanyte afire gumulanno assa

👉 Halallaho shumate ofolatenni wolaphino (74) olla kalanqe waajo baandeera qasa

👉 HIV/ADIS 0.5% baalanti woradda wodhote garinni murtanno assanna harunsite baanke muramino woxe 100% eessitanno assanna horaameeyye mommoddo nookkiha horoonsidhanno assa hattono HIV/ADIS 0.5% konni albaanni murroonniha hafanfarre kalaqantinowa harunsine qorqorsha assa


የሲዳማ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ
ነሀሴ 6/2018 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

የ2018 በጀት ዓመት የጤና ስኬትን ወደ ሞዴል ደረጃ ማሸጋገር የ2019 በጀት ዓመት ዋነኛ ትኩረት ነው — አቶ በላይነህ በቀለሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ — ነሐሴ 5/2018 ዓ.ም. በሲዳማ ክልል...
11/08/2026

የ2018 በጀት ዓመት የጤና ስኬትን ወደ ሞዴል ደረጃ ማሸጋገር የ2019 በጀት ዓመት ዋነኛ ትኩረት ነው — አቶ በላይነህ በቀለ

ሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ — ነሐሴ 5/2018 ዓ.ም.

በሲዳማ ክልል በእናቶችና ሕፃናት፣ በአፍላ ወጣቶችና ወጣቶች ጤና እንዲሁም በሥርዓተ ምግብ ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት የተመዘገበውን ስኬት ማስቀጠልና ወደ ሞዴል ደረጃ ማሸጋገር የ2019 በጀት ዓመት ዋነኛ የሥራ አቅጣጫ መሆኑን የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይነህ በቀለ ገለጹ።

አቶ በላይነህ ይህን ያሉት የቢሮው የእናቶችና ሕፃናት፣ የአፍላ ወጣቶችና ወጣቶች ጤና እንዲሁም የሥርዓተ ምግብ ዳይሬክቶሬቶች የ2018 በጀት ዓመት ዓመታዊ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅት መድረክ ላይ ነው።

እንደ አቶ በላይነህ ገለጻ፣ በ2018 በጀት ዓመት በእናቶች፣ በሕፃናት፣ በአፍላ ወጣቶችና በሥርዓተ ምግብ ጤና ዘርፎች ከቀደመው ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ተመዝግቧል። ይሁን እንጂ የተገኘው ውጤት መድረሻ ሳይሆን ለቀጣይ ስኬት መነሻ መሆኑን ጠቁመዋል።

የተመዘገበውን ለውጥ ለማስቀጠልና ወደ ሞዴል ደረጃ ለማሸጋገር በተቀናጀ አሠራር፣ በተጠናከረ ክትትልና በሁሉም አካላት የጋራ ርብርብ መሥራት እንደሚገባ ገልጸዋል። በ2018 በጀት ዓመት የተጀመረው ቅንጅታዊ አሠራርም በ2019 ይበልጥ እንደሚጠናከር አስታውቀዋል።

በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት የአፈጻጸም ሰነዶችና የድጋፍ ክትትል ሪፖርቶች ቀርበው ተገምግመዋል። የቀጣይ ዓመት አቅጣጫዎችም በሰነድና በባነር ኤግዚቢሽን ቀርበዋል።

በተጨማሪም በ2018 በጀት ዓመት በእናቶችና ሕፃናት፣ በአፍላ ወጣቶችና ወጣቶች ጤና እንዲሁም በሥርዓተ ምግብ የተመዘገቡ ውጤቶችና ተሞክሮዎች በዶክመንታሪ ቀርበዋል።

በ2018 በጀት ዓመት ለተመዘገበው የጤና ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጉ ወረዳዎች፣ የጤና ልማት አጋሮች፣ የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች፣ የግል የጤና ተቋማትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በሜዳሊያና በሰርተፍኬት እውቅና ተሰጥቷል።

በተለይም ለእናቶችና ሕፃናት ጤና በግል ተነሳሽነትና በልዩ ትጋት ላበረከቱ ግለሰቦች ልዩ እውቅና ተሰጥቷል። ከእነዚህም የእናቶች፣ ሕፃናት፣ ወጣቶችና ሥርዓተ ምግብ ጤና አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ኢመላ ላሜቻ፣ ዳይሬክቶሬቱን በተሳትፎና ቅንጅት በመምራታቸው በዳይሬክቶሬታቸው እውቅና አግኝተዋል።

አቶ በላይነህ በቀለ በማጠቃለያ ንግግራቸው በበጀት ዓመቱ የተሰጠው እውቅና በእናቶችና ሕፃናት፣ በአፍላ ወጣቶችና ወጣቶች ጤና እንዲሁም በሥርዓተ ምግብ የተመዘገቡ ውጤቶችን መሠረት ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

በቀጣይም እንደ ሴክተር አጠቃላይ ግብ በቀደሙት ዓመታት የተሞከሩ ኢኒሼቲቮችና የተመዘገቡ ስኬቶች በመነሻነት፣ በአራተኛው ምዕራፍ ጥራት ያለውና ሞዴል የሆነ ተደራሽና ዘመናዊ የጤና አገልግሎትን የሚያረጋግጥ ሞዴል የጤና ሥርዓት መገንባት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

በመጨረሻም የ2018 በጀት ዓመት ስኬቶችን በማጠናከር፣ የታዩ ክፍተቶችን በተግባራዊ መፍትሔ በመሙላትና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዶችን በውጤታማነት በመፈጸም የተሻለ የጤና ውጤት ለማስመዝገብ በቅንጅት ለመሥራት ተስማምተው መድረኩን አጠናቀዋል።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
ነሀሴ 5/2018 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ  በእናቶች፣ ሕፃናት፣ አፍላ ወጣቶችና ወጣቶች እንዲሁም በሥርዓተ ምግብ  አገልግሎት የ2018 አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የውይይት...
11/08/2026

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ በእናቶች፣ ሕፃናት፣ አፍላ ወጣቶችና ወጣቶች እንዲሁም በሥርዓተ ምግብ አገልግሎት የ2018 አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተጀመረ።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ | ነሐሴ 5/2018 ዓ.ም.

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ የ2018 ዓ.ም. የእናቶች፣ ሕፃናት፣ አፍላ ወጣቶችና ወጣቶች እንዲሁም የሥርዓተ ምግብ ጤና አገልግሎት አፈጻጸምን ገምግሟል።

በግምገማው የዓመቱ ዋና ዋና ስኬቶችና የአፈጻጸም ክፍተቶች በመለየት፣ ከተሳካ ተሞክሮዎች በመማር ለ2019 ዓ.ም. የጋራ የትኩረት አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ እንደገለጹት፣ በቢሮ ደረጃ እየተተገበሩ ያሉት “ለውጤት እንስራ” እና “ለላቀ ውጤትና ለጥራት እንስራ” ኢኒሼቲቮች በጤና ዘርፉ የሚታዩ ለውጦችን ለማፋጠን ወሳኝ አቅም ናቸው።

በተለይም የእናቶችንና የሕፃናትን ሕመምና ሞት መቀነስ፣ የሥርዓተ ምግብ ሥራዎችን ማጠናከርና የጤና አገልግሎቱን ውጤታማነት ማሳደግ በቅንጅት በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት መመዝገቡን ዶ/ር ሰላማዊት ገልጸዋል።

እንደ ዶ/ር ሰላማዊት ገለጻ፣ የእናቶችና የሕፃናት ጤና ላይ የሚታየውን ለውጥ የበለጠ ለማፋጠን የተቀናጀና የጋራ ሥራ ያስፈልጋል።

ለዚህም በቀጣዮቹ ዓመታት የጤና ዘርፉን ለመምራት ከተዘጋጀው ሁለተኛው የጤና ዘርፍ መካከለኛ ዘመን ልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድ (HSDIP-II) ጋር በማጣመር መሥራት ይገባል ብለዋል።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የጤና ፕሮግራም ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይነህ በቀለ በበኩላቸው፣ በክልሉ ለአፍላ ወጣቶችና ወጣቶች ተደራሽ፣ ጥራት ያለውና ምቹ የጤና አገልግሎት ለማቅረብ በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመዋል።

የእናቶች፣ ሕፃናት፣ ወጣቶችና ሥርዓተ ምግብ ጤና አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ኢመላ ላሜቻ ያቀረቡት የ2018 ዓ.ም. ዓመታዊ ሪፖርት የዓመቱን ዋና ዋና ስኬቶች፣ የአፈጻጸም ክፍተቶችንና በቀጣይ የጤና አገልግሎቱን ውጤታማነት ለማሳደግ የተቀመጡ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች በዝርዝር አካቷል።

በ2018 ዓ.ም. በእናቶችና ሕፃናት ጤና ላይ የተመዘገቡ ውጤቶችን ወደ ቀጣይ የለውጥ ምዕራፍ ለማሸጋገር የተቀመጡት የ2019 ዓ.ም. የጋራ የትኩረት አቅጣጫዎችም የአገልግሎቱን ጥራት፣ ተደራሽነትና ውጤታማነት ይበልጥ ለማሻሻል ያለሙ ናቸው።

የግምገማና የዕቅድ መድረኩ በ2018 ዓ.ም. የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማጠናከር፣ የታዩ ክፍተቶችን ለመቅረፍና በ2019 ዓ.ም. የተሻለ የጤና ውጤት ለማስመዝገብ የጋራ የሥራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ታላሚ ያደረገ መሆኑ ተብራርቷል።

በመድረኩ የሲዳማ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ፣ የሆስፒታል ሥራ አስኪያጆች፣ የጤና ቢሮ የማኔጅመንት አባላት፣ የግል ጤና ተቋማት ተወካዮች፣ የአፍላ ወጣቶችና ወጣቶች ማኅበራት፣ የዞንና ወረዳ ጤና ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም የጤና ልማት አጋር ድርጅቶች ተወካዮች ተሳትፈዋል።

የሲዳማ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ


የሲዳማ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ
ነሀሴ 5/2018 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

የሲዳማ ጤና ቢሮ በ2018 ዓ.ም. በእናቶች፣ ሕፃናት፣ ወጣቶችና ሥርዓተ ምግብ አገልግሎት የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገቡን ገለጸ የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ነሐሴ 4/2018 ዓ.ም.የሲዳማ ክልል ጤ...
10/08/2026

የሲዳማ ጤና ቢሮ በ2018 ዓ.ም. በእናቶች፣ ሕፃናት፣ ወጣቶችና ሥርዓተ ምግብ አገልግሎት የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገቡን ገለጸ

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ነሐሴ 4/2018 ዓ.ም.

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ በ2018 ዓ.ም. በእናቶች፣ ሕፃናት፣ ወጣቶችና ሥርዓተ ምግብ አገልግሎት አበረታች አፈጻጸም ማስመዝገቡን ገለጸ።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የጤና ፕሮግራም ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይነህ በቀለ፣ 2018 ዓ.ም. ለጤናው ዘርፍ፣ በተለይም ለእናቶች፣ ሕፃናት፣ ወጣቶችና ሥርዓተ ምግብ ጤና አገልግሎት፣ የተሻለ አፈጻጸም የተመዘገበበት ስኬታማ ዓመት መሆኑን ገልጸዋል።

በዓመቱ ከተመዘገቡ ዋና ዋና ውጤቶች መካከል፣ የቅድመ ወሊድ ክትትልና የአልትራሳውንድ አገልግሎት መስፋፋት፣ የእናቶች ማቆያ ቤቶችን ማጠናከር፣ የሕፃናት ክትባት አፈጻጸምን ማሻሻልና የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎትን ማስፋፋት ይገኙበታል።

አቶ በላይነህ እንደገለጹት፣ በክልሉ የሚታየውን የጤና አገልግሎት ስኬት ለማረጋገጥና በ2030 የተቀመጡ የጤና ግቦችን ለማሳካት የተጀመረው ጥረት መጠናከርና መቀጠል እንደሚገባ አፅንዖት ሰጥተዋል።

ይህንንም ለማሳካት የተዘጋጀው የመማሪያ ጉብኝት፣ አንዱ የጤና ተቋም ከሌላው የተሻለ አሠራርና ተሞክሮ እንዲቀስም፣ በመሬት ላይ የተሳኩ ተሞክሮዎች ወደ ሌሎች ተቋማት እንዲስፋፉና የአገልግሎት ጥራት እንዲሻሻል እንደሚያግዝ ገልጸዋል።

የመድረኩ ዋና ዓላማ የ2018 ዓ.ም. አፈጻጸምን በመገምገም የተገኙ ውጤቶችንና ክፍተቶችን መለየት፣ ከተሳካ ተሞክሮ መማርና ለ2019 ዓ.ም. የጋራ የትኩረት አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ ነው።

በመማሪያ ጉብኝቱ ተሳታፊዎች በ11 ቡድኖች ተከፍለው በተለያዩ የጤና ተቋማት የመስክ ምልከታ አድርገዋል። በጉብኝቱም የተመለከቷቸውን ጠንካራ አሠራሮች፣ ምርጥ ተሞክሮዎችና የአገልግሎት ክፍተቶች በመለየት ግብረ መልስ አቅርበዋል።

በቀጣዩ ቀን በይፋ በሚጀመረው መድረክ፣ የቢሮው የእናቶች፣ ሕፃናት፣ ወጣቶችና ሥርዓተ ምግብ ጤና አገልግሎት የ2018 ዓ.ም. አፈጻጸም፣ የተመዘገቡ ስኬቶችና ያሉ ክፍተቶች በጥልቀት ይገመገማሉ። በተጨማሪም ከተሳካ ተሞክሮዎች በመማር ለ2019 ዓ.ም. የጋራ የትኩረት አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በመድረኩ የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ፣ ከፌዴራል ጤና ሚኒስቴር የተወከሉ አካላት፣ የክልሉ ጤና ቢሮ የማኔጅመንት አባላት፣ የዞንና የወረዳ ጤና ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች፣ የጤና ተቋማት ባለሙያዎችና የጤና ልማት አጋር ድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተዋል።


የሲዳማ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ
ነሀሴ 4/2018 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

10/08/2026

3
Fayyimmate uurrinshubba dhuka bowirsanna qorqorsha kaajjishatenni isilanchonna yannitte fayyimmate owaante buuxisiinsanni he'noonnita xawinsi

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ መድሀኒት ቸርቻሪ ተቋማት ያላቸውን መድሐኒት ለይተው ጤንነቴ(Teninete) ወደተሰኘው የሞባይል መተግበሪያ የማስገባት ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል።        አቶ ቡሪሶ ...
08/08/2026

በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ መድሀኒት ቸርቻሪ ተቋማት ያላቸውን መድሐኒት ለይተው ጤንነቴ(Teninete) ወደተሰኘው የሞባይል መተግበሪያ የማስገባት ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል።
አቶ ቡሪሶ ቡላሾ

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ነሀሴ 02/2018 ዓ.ም

የሲዳማ ክልል ጤናና ጤና ነክ አገልግሎት ግብዓት ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ጤንነቴ (Teninete) የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችለውን አሰራር በመዘርጋት፣በሀዋሳ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ የፋርማሲ እና የመድኃኒት መደብር አገልግሎት ሰጪ አካላት ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት በማድረግና ስልጠና በመስጠት ወደ ተግባር መግባቱ ይታወቃል።

ይህንኑ ተከትሎ ባለስልጣኑ አስር ቡድኖችን በሀዋሳ ከተማ በሚገኙ ክፍለ ከተሞች በሙሉ በማሰማራት መድሀኒት ቸርቻሪ ተቋማት ያላቸውን መድሀኒት ዝርዝር ወደ ሲስተም ሲያስገቡ ቆይተዋል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቡርሶ ቡላሾ እና ቡድናቸው የእስካሁኑን ሂደት በቅርበት በመከታተልና በመገምገም በጥሩ ሂደት ላይ ያሉትን ያበረታቱ ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ኋላ የቀሩ መድሀኒት መደብሮችና ፋርማሲዎች በፍጥነት የኮምፒውተር ምዝገባውን አጠናቀው አገልግሎቱ እንዲጀመር እንዲያደርጉ አሳስበው እስከቀጣይ ሳምንት በማያጠናቅቁ ተቋማት ላይ ባልስልጣኑ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቀዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም "ጤንነቴ" የሞባይል መተግበርያው የፋርማሲና መድኃኒት መደብሮች የያዙትን መድኃኒት ከነዋጋው የሚያሳይና አድራሻቸውን የሚጠቁም በመሆኑ ተገልጋዮች በፍለጋ የሚያባክኑትን ጉልበትና ጊዜ የሚቆጥብ የዘመነ አሰራር ስርዓት በመሆኑ ሁሉም በወጥነት ሊተገብረው ይገባል ሲሉ በአፅንኦት ተናግረዋል።

በዛሬው ዕለት በሁሉም ክፍለ ከተሞች የተሰማሩ ቡድኖች በፋርማሲና መድኃኒት መደብሮች እስካሁን የተከናወኑ ዝርዝር ተግባራትን አፈፃፀም በማቅረብ ውይይት ተደርጎበታል፤ቀጣይ የስራ አቅጣጫም በባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ተቀምጦ ውይይቱ ተጠናቋል።


የሲዳማ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ
ነሀሴ 2/2018 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

ለቆልማማ እግር /Club Foot/ የተዳረጉ ህፃናት በጊዜ የህክምና ክትትል ካልተደረገላቸው ለዘላቂ አካል ጉዳተኝነት እንደሚዳረጉ ተገለፀ። የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ነሀሴ 02/2018 ዓ.ም ቆ...
08/08/2026

ለቆልማማ እግር /Club Foot/ የተዳረጉ ህፃናት በጊዜ የህክምና ክትትል ካልተደረገላቸው ለዘላቂ አካል ጉዳተኝነት እንደሚዳረጉ ተገለፀ።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ነሀሴ 02/2018 ዓ.ም

ቆልማማ እግር /Club Foot/ በወሊድ ወቅት የሚፈጠር፣ በጊዜ ህክምና ካላገኘ ለከፋ የአካል ጉዳተኝነት የሚዳርግ ችግር መሆኑን የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ hope walks ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በትብብር ባካሄዱት የአፈፃፀም ግምገማ መድረክ ላይ ተገልጿል።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ምክትልና የህክምና አገልግሎት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሙንጣሻ ብርሀኑ ባስተላለፉት መልዕክት ቆልማማ እግር የሚባለው ህፃናት በሚወለዱበት ጊዜ አንድ ወይም ሁለት እግራቸው ወደ ውስጥ የመዞር ችግር መሆኑን ጠቁመው ህፃናቱ ሮጠው እንዳይቦርቁ እና እንደ ዕድሜ እኩዮቻቸው እንዳይጫወቱ የሚገድብ፣ ማህበራዊና ስነልቦናዊ ጫናን የሚያሳድር ችግር መሆኑን አስገንዝበዋል።

ም/ሀላፊው አያይዘውም ችግሩ ከቤተሰብ ጀምሮ በሀገር ሁለንተናዊ እድገት ላይ አሉታዊ ጫና የሚያሳድር በመሆኑ በክልሉም ሆነ በሌሎች አጎራባች ክልሎች ባሉ ተቋማት ውስጥ አገልግሎቱን አጠናክሮ በመቀጠል የህፃናቱን የወደፊት እጣ ፈንታ ማስተካከል እንደሚገባ አሳስበዋል።

እንደ ሲዳማ ክልል ዝቅተኛ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ሆስፒታሎች አሰራራቸውን ለማሻሻል፣በውልደትና በክትባት አገልግሎት ወቅት የአፈጣጠር ችግር መኖር አለመኖሩን ባለሙያዎች በመደበኛነት እንዲፈትሹ ማድረግ ፣ስለቆልማማ እግር ምንነትና ስለህክምና አገልግሎቱ ለማህበረሰቡ ተገቢውን መረጃ ተደራሽ ማድረግ፣ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከርና ባለቤትነትን መፍጠር ተጠባቂ መሆኑን አቶ ሙንጣሻ በአፅንኦት ተናግረዋል።

የHope Walks ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ እዳሻው አበራ በበኩላቸው ቆልማማ እግር ወይንም ክለብ ፉት በህይወት ከሚወለዱ 1000 ህፃናት መካከል በአንዱ ላይ ሊከሰት የሚችል፣በጊዜ ተለይቶ ህክምና ከተጀመረ ግን በቀላሉ ሊስተካከል የሚችል መሆኑን አስረድተው፤ በተለይም ህፃናት በተወለዱ በ15 ቀናት ውስጥ ችግሩ ከተለየላቸው ታክሞ ለመዳን እጅግ ቀላል መሆኑን ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ ህፃናት ከፍ ሲሉ ከ6 ወር እስከ 12 ወር ድረስ የመመለስና እንደ ልብ የመራመድ እድል እንደሚኖረው ከዛ ዕድሜ በላይ ከፍ እያለ በሄደ ቁጥር ግን ህክምናውን እንደሚያከብደው ብሎም ለዘላቂ የአካል ጉዳት እንደሚያዳርግ አቶ እንዳሻው ተናግረዋል።

የዞረ እግር(clubfoot) ህክምና ሁለት ደረጃዎች ሲኖሩት የዞረውን እግር ማቃናት እና የተቃናውን እግር አስጠብቆ ማቆየት መሆኑን ያብራሩት አቶ እንዳሻው የመጀመሪያው ደረጃ የጄሶ ህክምና ሲሆን እሱም በጥቂት ሳምንታት እግሩን ማቃናት፣ ሁለተኛው ልዩ ጫማ(brace) በጄሶ የተቃናውን እግር ባለበት ማስቀጠል እንደሆነ አስረድተዋል።

ማህበረሰቡ ስለ ቆልማማ እግር (club foot) ያለው አመለካከት የተዛባ እንደሆነ በተለይም ከእርግማን፣ ከሀጢያትና ከዘር ጋር በማያያዝ ወደ ህክምና ከማምጣት ይልቅ ቤት ውስጥ በመደበቅ የጉልበት ስራ እንደሚያሰሯቸው፣ህክምና ጀምረው የሚያቋርጡም ስለመኖራቸው በመድረኩ ተነስቷል፡፡

አገልግሎቱን እየሰጡ ካሉ ሆስፒታሎች አንዳንዶች ባነሱት ሀሳብ የቆልማማ እግር /Club Foot/ ህክምና የበርካታ ህፃናትን እግር ያቃና ብቻ ሳይሆን ተስፋቸውንም ያቃና እንደሆነም ገልፀው ህክምናው ከተለያዩ ዘመቻዎች ጋር እየተቀናጀ መሰራቱም ከጊዜ ወደ ጊዜ ውጤት እያመጣ መሆኑን አስረድተዋል ።

በአፈፃፀም ግምገማ መድረኩ ላይ የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ የማኔጅመንት አካላትና ፎካሎች፣የጤና ሚኒስቴር ተወካዮች ፣አገልግሎቱን እየሰጡ ያሉ ሆስፒታሎች ማለትም የሀዋሳ ሪፈራል ሆ/ል፣ አዳሬ፣ይርጋለም፣ቦና ሻሸመኔ፣ቡሌሆራ፣አዶላ፣ዲላ፣ የሆስፒታል አመራሮችና የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
ነሀሴ 2/2018 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

የጡት ማጥባት አስፈላጊነት እና ጥቅሞች ─── የጡት ማጥባት ለሕፃናት ጤናማ እድገትና የበሽታ መከላከል አቅም እንዲሁም ለእናቲቱ ጤና እጅግ አስፈላጊ የሆነ ተፈጥሯዊ ሂደት ነው። ህጻናት በመጀ...
05/08/2026

የጡት ማጥባት አስፈላጊነት እና ጥቅሞች

───

የጡት ማጥባት ለሕፃናት ጤናማ እድገትና የበሽታ መከላከል አቅም እንዲሁም ለእናቲቱ ጤና እጅግ አስፈላጊ የሆነ ተፈጥሯዊ ሂደት ነው። ህጻናት በመጀመሪያዎቹ 6 ወራት የእናት ጡት ወተት ብቻ (Exclusive Breastfeeding) ማግኘት አለባቸው።

👉በጡት ማጥባት ወቅት ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ፦

▪️የመጀመሪያውን ወተት (እንገር / Colostrum) ለህጻኑ ይስጡ:- እንገር የመጀመሪያው የእናት ወተት ሲሆን ሕፃኑን ከበሽታዎች የሚጠብቅ በጣም ከፍተኛ የመከላከያ ኃይል ያለው ነው። ይህ ወተት ከፍተኛ የበሽታ መከላከል አቅም ያላቸውን ንጥረ ነገሮች ይዟል።

▪️ጡት ማጥባትን በመጀመሪያው 1 ሰዓት ውስጥ ይጀምሩ:- ሕፃኑ ከተወለደ በኋላ በመጀመሪያው 1 ሰዓት ውስጥ ጡት ማጥባት መጀመር ለሕፃኑ ሕይወት ማዳን፣ ለእናቱም ፈጣን ማገገም ይረዳል። እንዲሁም የጡት ወተት ምርት በቶሎ እንዲጀምር እና በቂ የሆነ ወተት እንዲመነጭ ያደርጋል።

▪️ህጻኑ/ኗ በፈለገ/ች ጊዜ ያጥኑ:- ሕፃኑ/ኗ በፈለገ/ች ጊዜ በቀንና በሌሊት በተደጋጋሚ ጡት ያጥቡ። ይህ የወተት ምርትን ያበረታታል።

▪️ትክክለኛ የማጥባት ሁኔታን ይጠቀሙ (Positioning & Latching)፦ በአግባቡ ለማጥባት እናቲቱ በተመች ሁኔታ ተቀማጣ ማጥባት አለባት። ሕፃኑ አፉን በደንብ ከፍቶ ጠቆር ያለዉን የጡትዎን ክፍል አብዛኛዉን በመጉረስ፣ ጉንጮቹ ሞላ በመድረግና በመሀል ትንሽ እያረፈ በደንብ መሳቡን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

▪️ሙሉ በሙሉ በጡት ወተት ብቻ ማሳደግ፦ በመጀመሪያዎቹ 6 ወራት ውስጥ ውሃን ጨምሮ ምንም አይነት ተጨማሪ ምግብ ወይም ፈሳሽ ሳይሰጥ በጡት ወተት ብቻ ህጻናትን ማሳደግ ይገባል። ይህም የጡት ወተት በመጀመሪያዎቹ 6 ወራት ለህጻናት እድገት የሚያስፈልጉትን ንጥረ ምግቦች እንዲሁም ውሃን ስለሚይዝ ነው።

▪️የበሽታ መከላከል ጥቅሞች፦ የጡት ወተት ሕፃናትን ከተቅማጥ፣ ከሳንባ ነቀርሳ (Pneumonia) እና ከጆሮ ኢንፌክሽን የሚከላከል ሲሆን እናቶችንም ከጡት እና ከማህፀን ካንሰር ተጋላጭነት ይከላከላል።

▪️በህመም ወቅት ጨምረው ጡት ያጥቡ:- ከ 6 ወር በታች የሆኑ ህጻናት በተለያየ ህመም በሚጠቁበት ወቅት ከሌላ ጊዜ አብልጠው/ጨምረው ያጥቡ። ይህም በህመም ወቅት በሽታን ለመቋቋም እንዲሁም በቶሎ ለማገገም ይረዳቸዋል።

▪️ከ6 ወር ጀምሮ(181 ቀን) ከተጨማሪ ምግብ ጎን ለጎን ጡት ማጥባትን ይቀጥሉ:- ከ 181ኛ ቀን ጀምሮ እድሜውን የሚመጥን፣ የተመጣጠነና የተሰባጠረ ተጨማሪ ምግብ በመጀመር ጡት ማጥባቱን እስከ 2 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ ይቀጥሉ።

▪️የበቂነት ምልክቶች፦ ሕፃኑ በቀን ቢያንስ ከ6-8 ጊዜ የሚሸና ከሆነ እና በቂ የክብደት እድገት የሚያሳይ ከሆነ፥ ህጻኑ በቂ ወተት ማግኘቱን ማረጋገጥ ይቻላል።

▪️የእናቶች ስነ-ምግብ ሁኔታ፦ የሚያጠቡ እናቶች ከሌላው ጊዜ ተጨማሪ ሁለት ጊዜ የተሰባጠረ ምግብ ማገኘት የሚገባዘው ሲሆን፣ በቂ ፈሳሽ (ውሃ፣ ሾርባ) እና አትክልትና ፍራፍሬዎችንም አብዝተው መመገብ ይኖርባቸዋል።

👉 የአባቶች እና የቤተሰብ ሚና፦

▪️የቤት ውስጥ ስራዎችን ማገዝ፦ አባቶችና ቤተሰብ የሚያጠቡ እናቶችን በቤት ውስጥ ስራ በማገዝ በቂ የእረፍት ጊዜ እንዲኖራቸው ማድረግ አለባቸው።

▪️ስነ-ልቦናዊ ድጋፍ መስጠት፦ በእናቶች ላይ የሚፈጠረውን ድካም እና ጭንቀት ለመቀነስ አዎንታዊ እና ስነ-ልቦናዊ ድጋፍ ማድረግ ወሳኝ ነው።

▪️የተመጣጠነ ምግብ ማቅረብ፦ እናቲቱ በቂ እና የተመጣጠነ ምግብ ማግኘቷን ማረጋገጥ እና ማበረታታት።



የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአንድ ወቅት ተግባር ብቻ ሳይሆን በደስታ የምናስቀጥለው ትልቅ አሻራ መሆኑ ተገለፀ። የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ሀምሌ 28/2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ የመድሀኒት አ...
04/08/2026

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአንድ ወቅት ተግባር ብቻ ሳይሆን በደስታ የምናስቀጥለው ትልቅ አሻራ መሆኑ ተገለፀ።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ሀምሌ 28/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ የመድሀኒት አቅራቢ አገልግሎት ሀዋሳ ቅርንጫፍ ከሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ፣ ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ እንዲሁም ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር የ2018 ዓ/ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል አስጀምሯል።

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ሀላፊና የእለቱ የክብር እንግዳ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ መርሀ-ግብሩን በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት በጤናው ሴክተር ውስጥ ለሚሰራ አካል የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የዕለት ተዕለት ተግባሩ መሆኑን ገልፀው፣ በ2018 ዓ.ም በተያዘው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ14 በላይ ትኩረት የሚሹ ተግባራት፣ ነፃ የምርመራና የህክምና አገልግሎት ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።

ሀላፊዋ አክለውም የኢትዮጵያ የመድሀኒት አቅራቢ አገልግሎት ሀዋሳ ቅርንጫፍ ከሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ጋር በመቀናጀት ለኩላሊት ችግር የተጋለጡ ወገኖች የኩላሊት እጥበት አገልግሎት እንዲያገኙ እያደረጉ ላሉት ያላሰለሰ ጥረት በማመስገንና እውቅና በመስጠት እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ በመደጋገፍ ስቃይ ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን ህይወት እንታደግ ሲሉ አሳስበዋል ።

መርሀ-ግብሩ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ፣ ቃልኪዳን ማደሻ እንደመሆኑና የጉዳዩን አሳሳቢነት በመረዳት በተቋማቱ 50ሺህ አባላት ለማፍራት ከተያዘው ዕቅድ እንደ ክልል ጤና ቢሮ 1000 ያህል አባላትን በማፍራት እውን እናደርጋለን ሲሉ የቢሮ ሀላፊዋ ቃል ገብተዋል።

የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ፍፁም ወ/ገብርኤል በበኩላቸው የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብሩ በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ጤና ተቋማት መምጣት ያልቻሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ወርደን የምናገለግልበት መልካም አጋጣሚ ነው ሲሉ ገልፀው የዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት በቅንጅት ቢሰሩ ውጤታማ እንደሚያደርጉ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።

ዶ/ር ፍፁም አያይዘውም እጅግ አሳሳቢ እየሆነ የመጣውን የኩላሊት ችግር ለመቅረፍና ወገኖችን ከስቃይ ለመታደግ በ2019 ዓ.ም የሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህክምና ለመጀመር ቅድመ ዝግጅቱን እያደረገ መሆኑን አብስረዋል።

የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ አገልግሎት የደቡብ ክላስተር አስተባበሪና የሀዋሳ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ስራ አስኪያጅ እንዲሁም የሜሪ ጆይ አምባሳደር አቶ ዘመን ለገሰ በመልዕክታቸው የኩላሊት ህመም ለበርካታ ወገኖች ሞት መንስኤ እየሆነ የመጣ፣ነገር ግን ህክምናው እንደሀገር በበቂ ሁኔታ ተደራሽ ያልሆነ መሆኑን አብራርተዋል ።

አቶ ዘመን አያይዘውም የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ አገልግሎት የመድሀኒት አቅርቦት ስርዓቱን ከማሻሻል ጎን ለጎን የማህበራዊ አገልግሎትን በማስፋፋት በተለይም ለኩላሊት ህመም ልዩ ትኩረት በመስጠት የተቋሙን ሰራተኞች በሙሉ ቋሚ አባል በማድረግ ሀላፊነታቸውን እየተወጡ መሆኑን ተናግረዋል።

የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ በስፋት ከሚያከናውነው ማህበራዊ አገልግሎት በተጨማሪ በሀዋሳ ከተማ ተቋቁሞ ለበርካታ የኩላሊት ታካሚዎች የዲያሊስስ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው የኩላሊት እጥበት ማዕከሉ በዝቅተኛ ክፍያ አገልግሎት እየሰጠ ቢሆንም እየመጣ ካለው የታካሚ ቁጥር አንፃር አገልግሎቱ እንዳይስተጓጎል ማህበረሰቡ የአላማው ደጋፊ በመሆን ወርሀዊ 200 ብር ብቻ በመክፈል አባል እንዲሆኑና የተቸገሩ ወገኖቻቸውን ህይወት እንዲታደጉ ጥሪ አቅርበዋል።

በመድረኩ በማዕከሉ የዲያሊስስ አገልግሎት እያገኙ ካሉ ታካሚዎች ውስጥ አንዳንዶች ቀርበው ባስተላለፉት መልዕክት ከዚህ ቀደም የግል ሆስፒታል ላይ የጀመሩትን አገልግሎት በአቅም ውስንነት ምክንያት በማቋረጥ ከሞት አፋፍ ላይ ሆነው የሜሪ ጆይ ሀዋሳ የኩላሊት እጥበት ማዕከል እንደደረሰላቸው በመግለፅ ነገር ግን ውስን ክፍያውም ቢሆን ያለማህበረሰቡ እገዛ የማይቻል በመሆኑ ለወገን ደራሽ የሆነው ህዝብ በጥቂት መዋጮ አባል በመሆን ከፈጣሪ በታች ህይወታቸውን እንዲያስቀጥሉላቸው ተማፅነዋል።

በተቋሙ የተጀመረው የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በርካታ የጤና ችግሮች ነፃ ምርመራና ህክምና አገልግሎት፣ የደም ልገሳ ተግባራትና የጤና የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች የተካተተበት መሆኑ ተገልጿል።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

Address

Awassa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share