20/08/2026
በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት ከ3 መቶ በላይ ለሚሆኑ ለአዲስ እና ለነባር ምዘና ማዕከላት እውቅናና ፈቃድ እድሳት መሰጠቱ ተገለጸ
========================
ባህርዳር፣ ነሃሴ 15 2018 ዓ.ም (የሙ/ብ/ም/ማ/ባ) በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት ከ3 መቶ በላይ ለሚሆኑ አዲስ የምዘና ማዕከላት ፍቃድ እና ለነባር ምዘና ማዕከላት አዉቅና አድሳት መሰጠቱን የአብክመ የ ሙያ ብቃትና ምዘናና ማረጋገጫ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
የባለስልጣኑ የሙያ ደረጃ ምደባ፣ ጥናትና አውቅና አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ባያሌው መነሻ እንደገለጹት አምስቱን ካላስተር ማዕከላትን ጨምሮ ለ150 የምዘና ማዕከላት አዲስ አውቅና ለመስጠት ታቅዶ ከመካከለኛና ከፍተኛ እንዱስትሪዎች 25 እና ከጥቃቅንና አንስተኛ ኢንተርፕራይዞች 131 በድምሩ ለ156 ኢንዲስትሪዎች አዲስ የምዘና ፍቃድ ተሰጥቷቸዋል ብለዋል ፡፡
ለ36 ነባር ምዘና ማዕከላት በ70 ሙያወች ተጨማሪ የምዘና ማዕከላት ፈቀድ መሰጠቱንም ተናግረዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ለ243 ለነባር ምዘና ማዕከላት እዉቅና ለማደስ ታቅዶ አስከ በጀት ዓመቱ ማጠቃልያ ድረስ በተደረገዉ እንቅስቃሴ የቅዱን 170 /70 በመቶ ባቻ ማከናዎን እንደተቻለም አቶ ባያሌዉ ተናግረዋል፡፡
የነባር ምዘና ማዕከላት እዉቅና ማደስ አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆን በክልላችን በአንዳንድ አካባቢዎች የፀጥታ ችግር ምክንያት በየደረጃዉ የሚገኙ ባለድርሻ አካለት እና ባለሙያወች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ ለመስራት አለመቻል መሆኑን የተናገሩት ዳይሬክተሩ እውቅና ያገኙ ምዘና ማዕከላትም አንዳንድ ሙያዎች ላይ ለምዘና የሚወጣው ወጭ ተመዛኞች ከሚከፍሉት የምዘና ክፍያ አዋጭ አይደለም በሚሉና በሌሎች ተያያዥ ችግሮች ወደ ምዘናው አለመግባት በበጀት አመቱ ያጋጠሙ ችግሮች እንደነበሩ አቶ ባያለው ተናግረዋል፡፡
የሙያ ብቃት ምዘና መስጫ ማዕከላትና መዛኞችን እና ተያያዥነት ያለቸውን ጉዳዮች በውጤታመነት ለማከናወን በአንድ ተቋም ብቻ ሊሳካ ስለማይችል የአጋር አካላት ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ በቀጣይ በጀት ዓመት ሁሉም አካል የበኩሉን ሚና ሊወጣ ይገባል ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡