Amhara Occupational Competence Assessment and Certification Authority

Amhara Occupational Competence Assessment and Certification Authority Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Amhara Occupational Competence Assessment and Certification Authority, Government Organization, Ethiopia, Bahir Dar.

ተልዕኮ፡-
በመደበኛ፣ መደበኛ ባልሆኑ የሥልጠና ፕሮግራሞች እና በኢ-መደበኛ መንገድ በዝቅተኛና መካከለኛ ደረጃ ሙያው የሚጠይቀውን ዕውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ላካበቱ ባለሙያዎች በአገር አቀፍ የሙያ ደረጃዎች ላይ የተመሠረተ የሙያ ብቃት ምዘና እና ብቁ ለሆኑት የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በመስጠት ብቃቱ የተረጋገጠ ባለሙያ ለገበያው እንዲቀርብ በማድረግ የኢንዱስትሪውን ምርትና ምርታማነት ማሳደግ፣

ራዕይ፡-

በ2022 ብቃቱ የተረጋገጠና በገበያ ተወዳዳሪ የሆነ ባለሙያ በኢንዱስትሪው ተገንብቶ ማየት፣

እሴቶች፡-

· ቅንነት፣

· ታማኝነት፣

· በቡድን የመስራት ባህል፣

· አዳዲስ እውቀቶችንና ክህሎቶችን መማር፣

· ኪራይ ሰብሳቢነትን መታገል፣

· ጥራትና ተወዳዳሪነት፣

· በሥነምግባር መረሆዎች መመራት፣

· በብቃት ማመን፣

29/05/2026
29/05/2026

ኢትዮጵያ ትመርጣለች!

28/05/2026

ምርጫው ነጻ፣ ፍትሃዊ እና ገለልተኛ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በርካታ ስራ ተሰርቷል - ቦርዱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ክርክር ማጠናቀቂያና የጥሞና ግዜ ማብሰሪያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በዚህ ወቅት÷ ምርጫው ነጻ፣ ፍትሃዊ እና ገለልተኛ ሆኖ በስኬት እንዲጠናቀቅ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቁመዋል፡፡

በዚህም የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ለመራጩ ህዝብ ራሳቸውን እንዳዲያስተዋውቁ የማድረግ ስራ በሰፊው መሰራቱን አንስተዋል፡፡

በፖሊሲ ጥናት በመታገዝ እና ፓርቲዎች ሊወያዩ የሚችሉባቸው ጉዳዮችን በመለየት ገለልተኛ ተቋማት እንዲሳተፉ ተደርጓልም ነው ያሉት።

የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ተስፋዬ ንዋይ በበኩላቸው÷ አንጋፋ የሆኑ 22 ሙያተኞችን በምርጫ ክርክር አስተባባሪነት እና በጥናት እንዲሳተፉ መደረጉን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም ገለልተኛነታቸው የተመሰከረላቸው 32 ጋዜጠኞች መሳተፋቸውን ተናግረዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ምርጫው ነጻ፣ ፍትሃዊ እና ገለልተኛ እንዲሆን የሚያስችሉ ስራዎች መሰራታቸውን ነው የገለጹት፡፡

በምርጫ ክርክር ሂደቱ ፍላጎት እንደሌላቸው ካሳወቁት ውጪ 33 የፖለቲካ ፓርቲዎች መሳተፋቸው ተመላክቷል።

ተደራሽነትን ለማስፋት በአምስት ቋንቋዎች ክርክሩ የተካሄደ ሲሆን፤ ይህም የዲጂታል አማራጭን ጨምሮ በሚዲያዎች ለህብረተሰቡ መተላለፉ ተገልጿል።

አካታችነት ላይ በተገቢው መንገድ የተሰራ ሲሆን፤ ውጤታማነቱን ለመመዘን መጠየቅ ከተሰጣቸው ውስጥ 70 በመቶ የሚሆኑት መራጮች ግንዛቤ ማግኘታቸውን እና ክርክሩም ድምፅ ለመስጠት እንዳነሳሳቸው መግለጻቸው ተጠቁሟል፡፡

ከ4 ቀናት በኋላ የሚካሄደው ምርጫ የተሳካ እንዲሆን ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

በማህሌት ካሳሁን

ምርጫና የሴቶች ተሳትፎየኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ሴቶች በማናቸውም ሕገ መንግሥቱ ባረጋገጣቸው መብቶችና ጥበቃዎች ከወንዶች እኩል መብት እንዳላቸው ይደነግጋል፡፡በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 25 ሁሉም...
28/05/2026

ምርጫና የሴቶች ተሳትፎ
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ሴቶች በማናቸውም ሕገ መንግሥቱ ባረጋገጣቸው መብቶችና ጥበቃዎች ከወንዶች እኩል መብት እንዳላቸው ይደነግጋል፡፡
በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 25 ሁሉም ሰዎች በሕግ ፊት እኩል መሆናቸውን ያስቀምጣል፡፡ በአንቀጽ 35 ላይ ደግሞ ሴቶች ከወንዶች እኩል መብት እንዳላቸው እና በፖለቲካ ተሳትፎ ላይ ልዩ ድጋፍ ማግኘት እንደሚችሉ ያነሳል፡፡ በተጨማሪም አንቀጽ 38 ላይ ሁሉም ዜጎች የመምረጥና የመመረጥ መብት እንዳላቸው ይገልጻል።
በዚሁ መሠረት ሕጋዊ ማዕቀፎች የሴቶችን ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ ማሳደግ በሚያስችሉ መልኩ ይቀረጻሉ ማለት ነው፡፡
ለምሳሌ የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩ ሲያቀርቡ ተገቢው የሴቶች ውክልና እንዲኖራቸው የሕግ ግፊትና ማበረታቻ ይደረጋል፡፡
በዚህ ረገድ ፓርቲዎች ባቀረቡት የሴቶች እጩ ብዛት ላይ የተመሠረተ የምርጫ ወጪ መሸፈኛ ድጎማ ያገኛሉ፡፡
በተጨማሪም የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 የፖለቲካ ፓርቲዎች በየደረጃው ያሉትን አመራሮች ሲመርጡ የጾታ ውክልና እንዲኖራቸው የሕግ ግፊትና ማበረታቻ ማድረግ የሚያስችሉ ድንጋጌዎችን አካቷል፡፡
ኢትዮጵያ ትመርጣለች! See less

በአራቱ የጥሞና ቀናት ...
28/05/2026

በአራቱ የጥሞና ቀናት ...

28/05/2026
28/05/2026
28/05/2026

ዛሬ መተግበር የጀመረው እና ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚቆየው የጥሞና ጊዜ መራጩ ያለ ምንም ውጫዊ ተፅዕኖ፣ ግርግርና ቅስቀሳ በሰላም አስቦ እንዲወስን ይረዳል።

ኢትዮጵያ ትመርጣለች

25/05/2026
25/05/2026

Address

Ethiopia
Bahir Dar
6000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Occupational Competence Assessment and Certification Authority posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Amhara Occupational Competence Assessment and Certification Authority:

Share