ባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት/Bahir Dar Zuria Woreda revenue office

  • Home
  • Ethiopia
  • Bahir Dar
  • ባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት/Bahir Dar Zuria Woreda revenue office

ባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ  ገቢዎች ጽ/ቤት/Bahir Dar Zuria Woreda revenue office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት/Bahir Dar Zuria Woreda revenue office, Government Organization, Bahir Dar.

05/09/2026
02/09/2026

ቀን፡-27/12/2018 ዓ/ም
ማስታዎቂያ፣
ለባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ግብር ከፋዮች በሙሉ፣
ጉዳዩ፡-የሚጠበቅባችሁን ግብር እንድትከፍሉ ስለማሳወቅ፣
የባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች የ2018 የግብር ዘመን ግብር አከፋፈልን ስመልክቶ በእጅ ስልካችሁ መልዕክት ሲደርሳችሁ ግብር እንድትከፍሉ በማለት በተቋማችን ድህረ-ገጽ እና በቴሌግራም በመጫን እንዲሁም በስልክ በተደጋጋሚ የቅስቀሳ ስራ ቢሰራም እስካሁን ባለው ሁኔታ መልእክቱን ተቀብሎ ግብሩን አጠቃሎ የከፈል ግብር ከፋይ ቁጥር እጅግ በጣም አነስተኛ እንደሆነ መረጃችን ያሳያል።
በመሆኑም እንደ ገቢ ተቋም የሁሉም ግብር ከፋይ የግብር ውሳኔ ተወስኖ በአብዛኛው በሚባል ደረጃ የምትከፍሉትን የግብር መጠን የሚገልፅ መልዕክት የደረሳችሁ ስለሆነ ነሀሴ 30/2018 ዓ/ም ከመጠናቀቁ በፊት መጥታችሁ የሚጠበቅባችሁን ግብር አጠቃላችሁ በመክፈል ከቅታትና ወለድ ረሳችሁን እንድታድኑ እያሳሰብን ይህንን እድል ባለመጠቀም ለሚደርሰው ቅጣትና ወለድ ተቋማችን የማይጠየቅ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።
ጽ/ቤቱ

04/08/2026

ቀን፡-28/11/2018ዓ.ም
ማስታወቂያ፣
በባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ስር ለምትገኙ ግብር ከፋዮች በሙሉ፣
የባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት እንኳን ለ2018/2019 የግብር ዘመን በሰላም አደረሳችሁ እያለ መጭው ዘመን የሰላምና የደስታ እንዲሆን እየተመኘ ጊዜው የቴክኖሎጅ በመሆኑ ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ባለበት ቦታ ላይ ሆኖ የሚጠበቅበትን ግብር/ታክስ እንዲከፍል የሚያስችል ሲስተም የተዘረጋ በመሆኑ በየደረጃው የምትገኙ ግብር ከፋዮች በእጃችሁ በያዛችሁት ስልክ የሚጠበቅባችሁን የግብር መጠን እና የመክፈያ አካውንት ቁጥር የሚገልጽ መልእክት እንደደረሳችሁ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወይም ዓባይ ባንክ በመሄድ መክፈል እንደምትችሉ እያሳሰብን ቅድሚያ ለከፈላችሁ ግብር ከፋዮች ምስጋናችን የላቀ ነው።


የባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት

20/07/2026

ቀን 13/11/2018 ዓ.ም
ባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት 278.047 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ።በሰሜን ጎጃም ዞን ገቢዎች መምሪያ የባዙወ/ገቢዎች ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከ278.047 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት አስታወቀ።የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ እንዳለ አይነቱ እንደገለፁት በበጀት ዓመቱ 260 ሚሊየን 275 ሺ 822 ብር ለመሰብሰብ እቅድ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ያለ ሲሆን በዓመቱ ማጠቃለያ ብር 278 ሚሊየን 047 ሺ 017 በመሰብሰብ የእቅዱን 106.66% ማሳካት ተችሏል ብለዋል።ይህ የገቢ አሰባሰብ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ 90 ሚሊየን 203ሺህ 951 ብር ብልጫ እንዳለው ገልፀዋል።ለተሰበሰበው ገቢም ከመንግሥት ሰራተኞች፣ከግል ድርጅት ተቀጣሪ ሰራተኞች ፣ከንግድ፣ ከእርሻ፣ከሮያሊት እና ከተለያዩ ገቢ አርዕስቶች የተሰበሰበ መሆኑን ጽ/ቤት ሃላፊው ገልፀዋል።የገቢ አሰባሰቡ ውጤታማ እንዲሆን የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች፣ የወረዳ አመራርና የጋር አካላት ድጋፍና ቅንጅታዊ አሰራር የተጠናከረ እና በየጊዜው እየተገመገመ በመመራቱ የተገኘ ውጤት እንደሆነ ገልፀዋል።የጽ/ቤት ሃላፊው አቶ እንዳለ አይነቱ አያይዘው እንደገለጹት በ2019 በጀት ዓመትም ይህንን አንድነታችንና ተናቦና ተቀናጅቶ መስራት የበለጠ በማጎልበት የሚሰጠንን የገቢ እቅድ ለማሳከት ከወዲሁ የስነልቦና ዝግጅት እንደሚገባ አፅኖት ሰጥተው ገልፀዋል። የሚሰጠውን የገቢ እቅድ ለማሳካት ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባን ገልጸዋል።ሀላፊው አያይዘውም ለገቢ አሰባሰብ እገዛ ላደረጉልን በየደረዳው ላሉ አካላትም ምስጋናችንን እናቀርባለን ብለዋል።ዘገባው የባ/ዙ/ወ/ገቢዎች ጽ/ቤት የግብር ት/ትና ኮሙኒኬሽን ዋና የስራ ሂደት ነው።

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት/Bahir Dar Zuria Woreda revenue office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share