Mershu z great

Mershu z great ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃን እናደርሳለን

ሳምንታዊ መልዕክትምርጫ እና ምክክር የዘላቂ ሰላም፣ ህብረብሔራዊ አንድነት እና ሁለንተናዊ ብልፅግና ራዕያችን የምናሳካበት መንትያ መንገዶች ናቸው፤ከሁሉም ቀድማ በዓለም ሥልጣኔ የመገለጥ ከፍታ...
06/04/2026

ሳምንታዊ መልዕክት

ምርጫ እና ምክክር የዘላቂ ሰላም፣ ህብረብሔራዊ አንድነት እና ሁለንተናዊ ብልፅግና ራዕያችን የምናሳካበት መንትያ መንገዶች ናቸው፤

ከሁሉም ቀድማ በዓለም ሥልጣኔ የመገለጥ ከፍታ የነበራት ሀገራችን ኢትዮጵያ በድህነትና ኋላቀርነት ስሟ መነሳቱ ሊያበቃ ይገባል የሚል ቁጭት የሰነቀዉን የለውጥ መንግሥት እስካሁን አያሌ የሪፎርም ሥራዎች በመሥራት ዝላይ እና ተስተካካይነት የፈጠሩ ሰፋፊ ውጤቶች አስመዝግቧል፡፡

ከነዚህ ሪፎርሞች መካከል ለዘመናት አብሮን የዘለቀና ከፍተኛ ዋጋ ሲያስከፍለን የቆየው የዴሞክራሲ ባህል ስብራታችንን ትርጉም ባለው መልኩ ለመጠገን የተሰራው ሥራ ነው፡፡ በዚህ ረገድ በህገ-መንግሥቱ መሠረት በየአምስት ዓመቱ የሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ጊዜውን ጠብቆ እንዲተገበር ከማድረግ እስከ የዴሞክራሲ ባህላችን መገንባት እና ሀገራዊ ምክክር ማካሄድ የዘለቁ ብስለት፣ ቁርጠኝነትና አሳታፊነት የሚጠይቁ አያሌ ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡

የዴሞክራሲ ባህላችን ላይ የሚታየውን ስብራት ለመጠገን የመግባባት-ዴሞክራሲ እንደ ሁነኛ መፍትሄ እየተተገበረ ሲሆን የዚሀ ጥረት ማዕከል የሆነው ደግሞ የሀገራዊ ምክክሩ ሥራ ነው፡፡ የዛሬ ስድስት ዓመት ገለልተኛ ኮሚሽን ሆኖ በመዋቀር ወደ ሥራ የገባውን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ባለፈው ሳምንት ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ባለድርሻ አካላት አጀንዳዎች የመሰብሰብ ሥራውን ወደ መጨረሻ ምዕራፍ ማሸጋገር ችሏል፡፡

ወደኋላ ቀርቶ የቆየውን የትግራይ ክልል ባለድርሻ አካላት አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ በክልሉ ለማከናወን የተደረጉ በርካታ ጥረቶች እዛ ባለው ጎታች ኃይል ምክንያት አለመሳካቱ ተከትሎ የክልሉ ተወላጆች በብዛት በሚኖሩባት እና የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ቤት በሆነችው አዲስ አበባ ለሦስት ቀናት አጀንዳ የማሰባሰብ መድረክ ተካሂዶ በስኬት ተጠናቅቋል፡፡ መድረኩ ከትግራይ ክልል ለዚሁ ሲባል የመጡ ተሳታፊዎች ያካተተ ከ600 በላይ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት ሲሆን ሂደቱ እጅግ የላቀ የመግባባትና የለውጥ መሻት የታየበት፣ የትግራይ ህዝብ ፍላጎት በምሉዕነት የሚያንጸባርቁ አጀንዳዎች ነጥረው የወጡበት፣ በላቀ የተሳታፊዎች ብስለትና ዲሲፕሊን ታጅቦ እና በነጻነትና በዴሞክራሲያነት ተሞልቶ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ ብልፅግና ፓርቲ ጨምሮ 12 ክልሉ ማዕከል ያደረጉ ክልላዊና ሀገራዊ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች እና ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ተሳታፊዎች ስፋትና ጥልቀት ያለው ምክክር አካሄደው 11 ዋናዋና አጀንዳዎችና 51 ዝርዝር አጀንዳዎች ምክክር እንዲደረግባቸውና መፍትሄ እንዲፈለግላቸው በማለት ለኮሚሽኑ አስረክበዋል፡፡

ይህ ሥራ እንደ ሀገር መፍጠር ለምንሻቸው የመግባባት፣ የዕርቅ እና የዘላቂ ሰላም ዓላማዎች መሳካት አይነተኛ ሚና አለው፡፡ ከዚህም በላይ የኢትዮጵያ ህዝቦች አጀንዳዎች ከሞላ ጎደል የሚመሳሰሉና የሚቀራረቡ መሆናቸው ለመረዳት ተችሏል፡፡ መድረኩ በአዲስ አበባ መካሄዱም የትግራይ ህዝብ እኔ ብቻ አውቅልሀለው ከሚለው የማያግባባና ኋላቀር አስተሳሰብ የመላቀቅ ሂደት ላይ ተስፋ የፈነጠቀ ሆኖ ታይቷል፡፡ የመድረኩ ተሳታፊዎችም አዲስ የለውጥ ምዕራፍ እንዲጀመር ያላቸዉን ከፍተኛ ፍላጎት ባሳየ መልኩ በሙሉ ፍላጎት ሲሳተፉና ሲተባበሩ ተስተዉለዋል፡፡

ባጠቃላይ የሰሙኑ የትግራይ ክልል የባለድርሻ አካላት አጀንዳ የማሰባሰብ መድረክ የምክክር ኮሚሽኑ የዓመታት ጥረት ወደ ወሳኝ ምዕራፍ የደረሰበት፣ ሁሉም አጀንዳዎች በአሳታፊነት፣ እኩልነት እና ፍትሀዊነት መሰብሰብ የተቻለበት እንዲሁም መጻኢው ጊዜ አዎንታዊ ሰላም፣ ሀገራዊ መግባባት እና ሁለንተናዊ ልማት የሚነግስበት መሆኑ ያለንን ተስፋችን ከፍ ያደረገ ታሪካዊ ክስተት ሆኖ ተስተዉሏል፡፡

ይህም እየተሳካ ከሚገኘው ጠቅላላ ምርጫ ጋር በመንትያነት ተደምሮ ሲታይ እንደ ሀገር ምን ያክል ትልቅ ተስፋ እንዳለን በግልፅ የሚያሳይ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ትመርጣለች፤ ትመክራለችም፤ በምርጫና በምክክር የሀገረ-መንግሥት ግንባታዋን ወደ ላቀ ደረጃ ታደርሳለች፤

ብልፅግና ፓርቲ

መጋቢት 28፤ 2018 ዓ/ም

"ሀገር የምትበለጽገው በእድልና በችሮታ ሳይኾን በጥረትና በታታሪ ትውልዶች አቅም ነው!"     ክቡር አረጋ ከበደየአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር
12/11/2025

"ሀገር የምትበለጽገው በእድልና በችሮታ ሳይኾን በጥረትና በታታሪ ትውልዶች አቅም ነው!"

ክቡር አረጋ ከበደ
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከጎንደር ከተማ ሕዝብ የክብር ኒሻን ተሸለሙ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጎንደር አብያተ መንግሥታት እድሳትን መርቀው ሲከፍቱ ከጎንደር ከተማ ሕዝብ የክብር ኒ...
07/11/2025

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከጎንደር ከተማ ሕዝብ የክብር ኒሻን ተሸለሙ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጎንደር አብያተ መንግሥታት እድሳትን መርቀው ሲከፍቱ ከጎንደር ከተማ ሕዝብ የክብር ኒሻን ተሸልመዋል።

አሚኮ

07/11/2025

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

በጎንደር በነበረን ጉብኝት የመገጭ የመስኖ ልማት ፕሮጀክትን የሥራ ሁኔታ ገምግመናል።

ፕሮጀክቱ 870 ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን 17000 ሄክታር መሬት በመስኖ አቅርቦት ይሸፍናል ተብሎ ይጠበቃል።

የፕሮጀክቱ ቁልፍ የሆነው የወንዝ ቅልበሳ ሥራ በተሳካ መልኩ ተጠናቋል።

የቀሩት ሥራዎችም በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ እየተካሄዱ ይገኛሉ።

የመገጭ ግድብም በሚጠናቀቅበት ወቅት የአካባቢውን የግብርና ምርታማነት የሚያሳድግ ይሆናል።

የመገጭ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት የሥራ ሁኔታ በምስል:- 📷 የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት
07/11/2025

የመገጭ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት የሥራ ሁኔታ በምስል:-

📷 የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

ቀን=27/2/2018የሠሜን ሸዋ ግብርና መምሪያ የመስክ ስምሪት ሠጠየመስክ ስምሪቱን በጋራ የተሠጠ ሲሆን አቶ ታደሠ ማሙሻ የዞኑ ግብርና መምሪያ ሀላፊ ;አቶ ንጉሴ የዞኑ መስኖና ቆላማ አካባቢ...
06/11/2025

ቀን=27/2/2018

የሠሜን ሸዋ ግብርና መምሪያ የመስክ ስምሪት ሠጠ

የመስክ ስምሪቱን በጋራ የተሠጠ ሲሆን አቶ ታደሠ ማሙሻ የዞኑ ግብርና መምሪያ ሀላፊ ;አቶ ንጉሴ የዞኑ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች መምሪያ ተወካይና ወ/ሮ ሉባባ መኮንን የዞኑ አደጋ መከላከል ምግብ ዋስት ተጠሪ ተቋም ተወካይ በመሆኑ የመስክ ስምሪቱን በጋራ ሰጥተዋል

የመምሪያዉ ሀላፊ እንዳሉት ወቅቱ የመስኖ ስንዴ በስፋት የሚዘራበትና የተፈጥሮ ሃብት ቅድመ ዝግጅት የሚደረግበት መሆኑን አዉስተዉ የተባይ መከላከል ስራም ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና በፀደይ ወራት የሚተገበሩ አጠቃላይ የግብርና ስራዎች በትኩረት እንዲሠሩ ያሣሠቡ ሲሆን እስከ ታህሣሥ 30/2018 የሚጠቃለሉ የሴፍቲኔት ስራዎችም በትኩረት እንዲሠሩ እና ለዚሁም የሚሆን የባለሙያ ስምሪት እንደተሠጠ አንስተዋል በተጨማሪም በተለዩ 10ወረዳዎች የመስኖናቆላማ አካባቢዎች ተግባር እንዲፈፀም ሀላፊዉ ስምሪት እንደተሠጠ ገልፀዋል

የዚህ ስምሪት ልዩ የሚያደርገዉ ካሉት 23ወረዳዎች በ22ቱ ላይ የተቀናጀ የባለሙያ ስምሪት ለተከታታይ 10ቀናት ስምሪት እንደሚወሰድባቸዉ ገልፀዉ በሪፎርሙ ወደመምሪያዉ የተቀላቀሉ የምግብ ዋስትናና የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች መምሪያ ባለሙያዎችንም የያዘ ስምሪት እንደሆነ ገልፀዋል

@ የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ

በሰሜን ሸዋ ዞን በልማት ድርጅቶች የሚሰሩ የመስኖ ፕሮጀክቶችን ወደ ስራ ለማስገባት  የጋራ ውይይት መድረክ ተካሄደ። ================/////=============ጥቅምት 26/2018...
05/11/2025

በሰሜን ሸዋ ዞን በልማት ድርጅቶች የሚሰሩ የመስኖ ፕሮጀክቶችን ወደ ስራ ለማስገባት የጋራ ውይይት መድረክ ተካሄደ።
================/////=============
ጥቅምት 26/2018
ሰሜን ሸዋ ዞን

በአማራ ልህቀት ዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን አማካሪነት በአባይና ጢስሳት ኮንስትራክሽን የሚገነቡ የመስኖ ፕሮጀክቶችን አስመልክቶ ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር የጋራ ውይይት መካሄዱን የሰሜን ሸዋ ዞን መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት መምሪያ በገፁ አሳውቋል።

የውይይት መድረኩን የመሩት የዞኑ መምሪያ ሀላፊ አቶ ችሮታው አስፋው ሲሆኑ የመስኖ ፕሮጀክቶቹ ያሉበት ሁኔታ የሚመለከት ዝርዝር ሪፖርት ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን በአማራ ልህቀት ማዕከል አማካሪነትም ሆነ በሌሎች ድርጅቶች የተያዙ መስኖ ፕሮጀክቶች በሙሉ አቅም ሳይት ገብተው ስራ እንዲጀምሩ መግባባት ላይ የተደረሰ ሲሆን በየደረጃው ያለ ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርግ የመምሪያው ሀላፊ ጥሪ በማቅረብ መድረኩ ተጠናቋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ በአዲሱ አደረጃጀት ወደ ተቋሙ ለተቀላቀሉ ሰራተኞች የስራ መምሪያ ሰጠ።መምሪያው ከአዲሱ በጀት ጀምሮ ወደ መምሪያው የተቀላቀሉ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች እና ...
03/11/2025

የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ በአዲሱ አደረጃጀት ወደ ተቋሙ ለተቀላቀሉ ሰራተኞች የስራ መምሪያ ሰጠ።

መምሪያው ከአዲሱ በጀት ጀምሮ ወደ መምሪያው የተቀላቀሉ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች እና ከምግብ ዋስትና እና አደጋ መከላከል ፅ/ህፈት ቤት ወደ መምሪያው የመጡ ሰራተኞችን የትውውቅና እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የቀጣይ የስራ መመሪያ ሰጥቷል።

መድረኩን በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር የከፈቱት የመምሪያው ሃላፊ አቶ ታደሰ ማሙሻ እንደተናገሩት የአጋር ተቋማት መቀናጀትን አስመልክቶ ወደ ስራ መግባትና ህዝብን ማገልገል ስለሚገባ ስራችንን በጋራ ለመስራት እንኳን ወደ እናት መስሪያ ቤታችሁ በሰላም መጣችሁ ብለዋል።

ሁላችንም እናት መስሪያቤታችን የሆነው ግብርና ሰፊ በመሆኑ በመተባበራችን ለስራ መሳለጥ ያመች ዘንድ መተዋወቅና የግብርና መዘመን የሁላችንም ነውና ተቀናጅቶ በመስራት በርካታ ተግባራትን በመስራት እና በማስተባበር አርሶ አደራችን የሚጠብቀውን ልማት እንድናፋጥን አደራ እላለሁ ብለዋል።

የዞኑ መስኖና ቆላማ መምሪያ ሃላፊ አቶ ችሮታው አስፋው በበኩላቸው ሸዋ በሁሉም ዘንድ ቀዳሚና ከፍ ያለ ዞን መሆኑን አንስተው ተግባር እንዲሳለጥ ፈጥነን መዋሃዳችን አስፈልጓል፤ይህን የተዋሃደ ሴክተር ፈጥኖ አንድ በማድረግ ወደ ተግባር ለመግባትም ተገናኝተናል ብለዋል።

መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ከግብርና በበርካታ ተግባራት የሚቆራኝ መሆኑ ያነሱት አቶ ችሮታው ከራእይና ተልእኮ አንፃር ተመሳይነቱ የጎላ መሆኑን አንስተዋል።

ስለሆነም የእነኚህ ተቋማት ሰራተኞች በጋራ በመቀናጀትና በመዋሃድ ስራዎችን የበለጠ በማሳለጥ አርሶአደራችን ከልማቱን በአግባቡ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል።

ዋና ዋና የሚባሉ የተቋማቸውን ተግባርና ሃላፊነትም በዝርዝር አቅርበዋል።

ተሳታፊዎችም የተደረገውን አዲስ አደረጃጀት ተከትሎ ፈጥኖ ወደ ስራ ለመግባት የተደረገው የጋራ ንቅናቄ ለስራው ቅልጥፍና እና ቀጣይነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለውና መልካም ነው። የህዝብን አደራ ለመወጣት ተቀናጅቶ ለመስራት ወደእናት መስሪያ ቤት መምጣታቻን ተገቢ ነው ተቀናጅተን ሰርተንም ለአርሶአደራችን እድገት እንሰራለን ሲሉ አረጋግጠዋል።

ሁሉም ወረዳዎች ይህን ፈለግ በመከተል ሰራተኞችን ወደ ስራ ለማስገባት የግብርና ሴክተሩ ሃላፊዎች በሃላፊነት መንፈስ እንዲሰሩ አቶ ታደሰ አሳስበዋል።

@ የሰ/ሸዋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት

በአፍሪካ ልማት ባንክ የበጀት ድጋፍ ለሚገነቡ የመስኖ ፕሮጀክቶች የውሃ ተጠቃሚ ማህበራት አመራሮች የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ፕሮግራም ተጀመረ።ጥቅምት 18/2018 ዓምኮምቦልቻበዋግ ህምራ ብሄ/...
28/10/2025

በአፍሪካ ልማት ባንክ የበጀት ድጋፍ ለሚገነቡ የመስኖ ፕሮጀክቶች የውሃ ተጠቃሚ ማህበራት አመራሮች የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ፕሮግራም ተጀመረ።

ጥቅምት 18/2018 ዓም
ኮምቦልቻ

በዋግ ህምራ ብሄ/አስ/ዞን እና ሰሜን ወሎ ዞኖች በአፍሪካ ልማት ባንክ የበጀት ድጋፍ ለተገነቡና በግንባታ ላይ ላሉ መስኖ ፕሮጀክቶች የሚገኙ የመስኖ ውሀ ተጠቃሚ አመራሮች፣ ከመስኖና ከግብርና ለመጡ ለቀበሌ ባለሙያዎች እንዲሁም የወረዳና የዞን ባለሙያዎች ያካተተ የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና በኮምቦልቻ ከተማ እየተሠጠ ይገኛል።

ስልጠናው የመስኖ ማህበራት አደረጃጀትን ማጠናከር፣ አውታር አያያዝና ውሀ አጠቃቀም ላይ የሚያተኩር ሲሆን ፕሮግራሙን የአብክመ ግብርና ቢሮ ም/ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ መሠሉ ብርሃኑ እና የቢሮው የግንባታ ክትትልና ድጋፍ ዳሬክተር አቶ ጌትነት አያሌው ተገኝተው አስጀምረውታል።

የሹመት መረጃ ፤የአብክመ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ ከጥቅምት 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተለያዩ የክልል ተቋማት አመራሮች ሹመት ሰጥተዋል ።ሹመት የተሰጣቸው አመራሮች የአመራር ...
26/10/2025

የሹመት መረጃ ፤

የአብክመ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ ከጥቅምት 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተለያዩ የክልል ተቋማት አመራሮች ሹመት ሰጥተዋል ።

ሹመት የተሰጣቸው አመራሮች የአመራር ብቃት፣ የስራ ልምድ፣ የትምህርት ዝግጅት እና ስነ ምግባራቸውን መሰረት በማድረግ ነው።

በዚህም መሰረት :-

1. ዶ/ር አማኑኤል ፈረደ ፡ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የአስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ

2. አቶ ደረጀ ማንደፍሮ ዳመነ፡ የግብርና ቢሮ ኃላፊ

3. አቶ ጥላሁን ወርቅነህ ተክሌ፡ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ

4. አቶ አታላይ ጥላሁን፡ የገንዘብ ቢሮ ኃላፊ

5. ዶ/ር ዳኝነት ፈንታ መኮነን፡ የውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ

6. ዶ/ር ጋሻው ሙጨ ፡ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ

7. ዶ/ር ሞላ መልካሙ፡ የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ

8. ዶ/ር መንገሻ ፈንታው፡ የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ

9. አቶ አባይ መንግስቴ፡ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ

10. አቶ አሰፋ ሲሳይ ተሾመ፡ የኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር

11. ዶ/ር ማተቤ ታፈረ፡ የአማራ ስቴት ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት

12. አቶ እሱባለው መሰለ ፀጋየ፡ የአማራ ስቴት ዩኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዚዳንት

13. አቶ እርዚቅ ኢሳ፡ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የርዕሰ መስተዳደር ህዝብ ግንኙነት አማካሪ

14. አቶ ይትባረክ አወቀ፡ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ

15. ዶ/ር ዘላለም ልጃለም፡ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የርዕሰ መስተዳደሩ ፀጥታ ጉዳዮች አማካሪ

16. ዶ/ር ፈንታየ ጥበቡ፡ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የርዕሰ መስተዳድሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ

17. ዶ/ር ወልደትንሳኤ መኮነን ፈለቀ፡ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአብክመ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ አማካሪ

18. ዶ/ር ሰይድ እሸቴ፡ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የመሬት ቢሮ አማካሪ

19. አቶ አብይ አበባው ተስፋሁን፡ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የርዕሰ መስተዳድሩ ስትራቴጂክ ዘርፍ አማካሪ

20. ዶ/ር ምትኩ አለማየሁ፡ የፕላን ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር

21. አቶ ወርቁ ያየህ፡ የህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ

22. አቶ አዲስ በየነ፡ የባህል፣ ኪነ ጥበብና ዝክረ ታሪክ ጽ/ቤት ኃላፊ

23. አቶ አየልኝ መሳፍንት፡ የግብርና ቢሮ መስኖ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

24. ወ/ሮ መሰሉ ብርሃኑ ካሳው፡ የግብርና ቢሮ ተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

25. ወ/ሮ እታገኝ አደመ ገላው፡ የግብርና ቢሮ ምግብ ዋስትና ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

26. አቶ ዘውዱ ማለደ፡ የመንገድ፣ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

27. አቶ ጋሻው ተቀባ፡ የባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

28. አቶ ዘላለም አረጋ ፡ የሴ/ህ/ወጣቶች ቢሮ ወጣት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

29. አቶ ነጋ ይስማው፡ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

30. ዶ/ር ለዓለም ጥላሁን ፡ የፕላንና ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

31. ወ/ሮ ስመኝ ዋሴ፡ የስራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

32. አቶ ጋሻው እሸቱ፡ በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የርዕሰ መስተዳደሩ ህዝብ ግንኙነት ረዳት አማካሪ

33. ዶ/ር ተስፋሁን ተናኘ ፈሩህ፡ የፕላን ኢንስቲቲዩት ምክትል ዳይሬክተር

34. አቶ ገ/ማርያም ይርጋ፡ የባህል፣ ኪነ ጥበብ እና ዝክረ ታሪክ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ

35. ወ/ሮ የሺ ካሴ፡ የባህል፣ ኪነ ጥበብና ዝክረ ታሪክ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ በመሆን ሹመት ተሰጥተዋል ።
•••
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊
•••

አማራ ክልል ርእሰ መዲናዋ ባሕርዳር የጣና ፎረምን ከድምቀቷ በላይ ደምቃ በስኬት አጠናቃለች። በውበቷና በእንግዳ ተቀባይነቷ የተደመሙት እንግዶቿም ቀጣይ ጣና ፎረምን ሳይጠብቁ በውባ ከተማ ሌላ...
24/10/2025

አማራ ክልል ርእሰ መዲናዋ ባሕርዳር የጣና ፎረምን ከድምቀቷ በላይ ደምቃ በስኬት አጠናቃለች። በውበቷና በእንግዳ ተቀባይነቷ የተደመሙት እንግዶቿም
ቀጣይ ጣና ፎረምን ሳይጠብቁ በውባ ከተማ ሌላ ውብ ጊዜ ለማሳለፍ አቅደዋል።

የጣና ፎረም ተሳታፊ እንግዶች በጣና ዳር ያሳለፉት ቆይታ በምስል፦

🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊
•~•~•

"ባሕርዳር ከተማ አፍሪካዊ መድረክ ማዘጋጀት መቀጠሏ ለኮንፈረንስ ቱሪዝም ያላትን ምቹነት የሚያረጋግጥ ነው" ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ባሕርዳር: ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ‎ርእ...
24/10/2025

"ባሕርዳር ከተማ አፍሪካዊ መድረክ ማዘጋጀት መቀጠሏ ለኮንፈረንስ ቱሪዝም ያላትን ምቹነት የሚያረጋግጥ ነው" ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር: ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ‎ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት 11ኛው የጣና ፎረም በባሕርዳር ከተማ አስተናጋጅነት መካሄዱን ገልጸዋል።

ጣና ፎረም ፉክክር በበዛበት ዓለም፣ ከፍተኛ የኾነ የቴክኖሎጂ እድገት በሚታይበትና በርካታ አካባቢያዊ ለውጥ ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ተግዳሮቶች ባሉት ዓለም አፍሪካ እንዴት የሚናዋን መጫወት እንዳለባት ሐሳብ ለመለዋወጥ ያለመ ነው ብለዋል።

አፍሪካ ባለው ተለዋዋጭ ዓለም ውስጥ ተመልካች ሳትኾን ንቁ ተሳትፎ ልታደርግ ይገባል ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ለዚህም ትልቁ መሠረት ሠላም፣ መረጋጋትና ልማት መኾኑን ገልጸዋል።

ባሕርዳር ከተማም ይሕንን አፍሪካዊ መድረክ ማዘጋጀት መቀጠሏ ከተማዋ ለኮንፈረንስ ቱሪዝም ያላትን ምቹነት የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።

11ኛው የጣና ፎረም በድምቀት እና በስኬት እንዲጠናቀቅ የበኩላችሁን ሚና ለተወጣችሁ መሪዎች ፣ የጸጥታ አካላት እና ለከተማችን ነዋሪዎች ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ ነው ያሉት በመልዕክታቸው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ

Address

Bahir Dar

Telephone

+251911974850

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mershu z great posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Mershu z great:

Share