Amhara National Regional Sate Plan And Development Bureau

Amhara National Regional Sate Plan And Development Bureau Gevernment Service

19/05/2025

ግንቦት 11/2017 ዓ.ም ባሕር ዳር

ሰላም ውድ የተከበራችሁ የገፃችን ተከታዮች!

ይህ የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ በአዲስ መልኩ የከፈተው ኦፊሻል የፌስቡክ ገፅ ሲሆን ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን ትወዳጁን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቀለን።

Note;-ከዚህ በኋላ የቢሮው የስራ ተግባራት እና ልዩ ልዩ መረጃወች በአዲሱ ኦፊሻል ገፅ ብቻ የሚለቀቁ ይሆናል።
👇

https://www.facebook.com/profile.php?id=61576561109939

Government organization

የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ አመራሮችና ሠራተኞች “ የጥፋት ክንዶች እና መዘዞቹ " በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀ ዶክመነታሪ ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡ +++ፕላንና ልማት ቢሮ (ሚያዚያ 28/2018 ...
06/05/2025

የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ አመራሮችና ሠራተኞች “ የጥፋት ክንዶች እና መዘዞቹ " በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀ ዶክመነታሪ ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡
+++
ፕላንና ልማት ቢሮ (ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም)
በክልሉ ውስጥ እየተስተዋለ ያለውን የጸጥታ ቸግርና፤ ችግሩ እያስከተለው ያለውን ሰብአዊ፤ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራዎች በየደረጃው ያለው የመንግስት አመራርና ሠራተኛ አንዲረዳውና መንግስት በሚያደርገው ሠላም የማስፈን ሂደት አካል አንዲሆን ለማስቻል ታስቦ “የጥፋት ክንዶችና መዘዞቹ" በሚል ርእሥ የተዘጋጀውን ዶክመንታሪ ፊልም ሁሉም የቢሮው ሠራተኞች እንዲመለከቱት ተደርጓል፡፡
ዶክመንታሪው ታይቶ አንዳለቀ አመራሮችና ሠራተኞና ጥያቄና አስተያየት ካላቸው እንዲያቀርቡ በሠብሳቢው እድል ተሰጥቶ፤ የቀረበውን አስተያየት መነሻ በማድረግ ሠፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡
ሠራተኞቹ በሰጡት አስተያየት “በዶክመንታሪው የቀረቡት ትእይንቶች በየአካባቢያችን የሚስተዋሉ መሠረታዊ ችግሮች ናቸው፡፡ በቀጣይ መንግስት ሠላም የማስከበር ህገ-መንግስታዊ ሀላፊነቱን ባግባቡ አንዲወጣና ክልላችን ሠላም የሠፈነበት አንዲሆን ማድረግ አለበት ብለዋል፡፡
ሠራተኞቹ አክለውም “ጥያቄ አለን በሚል ምክንያት ወደ ጦርነት የገቡ ወገኖችም ቢሆኑ ጥያቄቸውን ሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንግድ በማቅረብ እንዲፈታላቸው በጠረንጴዛ ዙሪያ መታገል አንጂ በጦርነት መልስ ለማግኘት የሚሄዱት አካሄድ ክልሉንና ህዝቡን ዋጋ እያስከፈለው በመሆኑ ከድርጊታቸው ቢቆጠቡና ወደ ሰላማዊ ውይይት ቢመጡ ጥሩ ነው” ብለዋል፡፡
መድረኩ የመሩት የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር) እንደተናገሩት በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭት እያስከተለው ያለው ሠብአዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ ሠፊና ክልሉን በልማት ወደ ኋላ እየመለሠው መሆኑን ገልጸው፤ አንዳንዶቹ ድርጊቶች ዘግናኝና አሠቃቂ በመሆናቸው ምክንያት በዶክመንታሪው ያልተካተቱ በመሆናቸው ነው አንጂ ችግሩ ከዚህም በላይ አሳዛኝ ነው ብለዋል፡፡
“የመንግስት ሰራተኛው በክልሉ ውሥጥ የእየተከሠተ ያለውን ችግር በውል በመረዳት፤ መንግስት ችግሩን ለመቅረፍ የሚያደርገውን ጥረት መደገፍ ይጠበቅበታል” ያሉት የቢሮ ኃላፊው የተከበሩ ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር) “ጠበንጃ አንግበው ወደ ጫካ የገቡ ወንድሞቻችን ከተሳሳተ ድርጊታቸው ተመልሰው አለን የሚሉትን ጥያቄ በሠላማዊ መንገድ በማቅረብ የክልሉን ሠላም ወደ ነበረበት ለመመለስና ልማቱን ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ አንዲያደርጉ” ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
Website:-http://anrsbopd.gov.et
Telegram:-https://t.me/planpdb2014
Facebook:-https://www.facebook.com/ANRSPADB
YouTube channel: - https://www.youtube.com/-2014
Instagram :- https://www.instagram.com/plan_and_development_bureau/
x-account:- https://x.com/logout
tiktok:- https://www.tiktok.com/?lang=en-GB
gmail address:- [email protected]

የአማራ በሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ልማት ቢሮ ከቢሮዎችና ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን የክልሉን የ2017 በጀት አመት የ9 ወራት የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈጻጸም ሪፖ...
01/05/2025

የአማራ በሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ልማት ቢሮ ከቢሮዎችና ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን የክልሉን የ2017 በጀት አመት የ9 ወራት የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት መገምገም ጀመረ፡፡

+++

ሚያዚያ 23/2017 ዓ.ም (ፕላንና ልማት ቢሮ)

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ ከክልሉ ቢሮዎችና ተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን የክልሉን የ2017 በጀት አመት የ9 ወራት የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በዛሬው እለት መገምገም ጀምሯል፡፡

የግምገማ መድረኩን በመክፈቻ ንግግር የከፈቱት የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር) እንደተናገሩት ክልላዊ የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅዶቻችንን በምን ደረጃ ፈጽመናቸዋል? ጥንካሬወቻችንና ድክመቶቻችን ምን ምን ነበሩ? በአፈጻጸም ሂደት ምን ችግሮች ገጠሙን? እንዴትስ ተሻገርናቸው? በቀጣይ ምን እንማራለን? የሚሉትን የግምገማ ጥያቀዎች በሚመልስ መልኩ አፈጻጸሙን መገምገም እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

ሪፓርቱ ክልላዊ ይዘት እንዲኖረው ተደርጎ ፣ የየቢሮዎችን የአፈጻጸም ሪፖርት መሰረት አድርጎ የተዘጋጀ መሆኑን የገለጹት ቢሮ ሀላፊው ሁሉም ተሳታፊ ለግምገማው ትኩረት ሰጥቶ በመገምገም እንደ ክልል ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል፤ ድክመቶችን ደግሞ ለይተን አውቀን በማረም በቀጣይ ቀሪ ወራት እቅዳችንን በሚገባ ለመፈፀም የሚያስችል ግብአት ማግኘት የመድረኩ ትኩረት ይሆናል
ብለዋል።

ግምገማው በቀጣይ ቀናት እንደሚቀጥል የሚጠበቅ ሲሆን አጠቃላይ የግምገማ ሂደቱን በተመለከተ ስብሰባው እንደተጠናቀቀ ለክቡራን አንባቢዎቻችን የምናቀርብ ይሆናል።

Website:-http://anrsbopd.gov.et
Telegram:-https://t.me/planpdb2014
Facebook:-https://www.facebook.com/ANRSPADB
YouTube channel: - https://www.youtube.com/-2014
Instagram :- https://www.instagram.com/plan_and_development_bureau/
x-account:- https://x.com/logout
tiktok:- https://www.tiktok.com/?lang=en-GB
gmail address:- [email protected]

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሻሻለው የአስፈጻሚ አካላት እንደገና ማቋቋሚያና ሥልጣንና ተግባራት መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 280/2014 ዓ.ም መሠረት ለአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ የተሠጡ ተ...
30/04/2025

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሻሻለው የአስፈጻሚ አካላት እንደገና ማቋቋሚያና ሥልጣንና ተግባራት መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 280/2014 ዓ.ም መሠረት ለአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ የተሠጡ ተግባርና ኃላፊነት
1. የክልላዊ መንግሥቱን ረቂቅ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ከአቻ የፌደራል መንግሥት ማዕቀፎች ጋር በማገናዘብና በማስተሳሰር ይነድፋል፣ ያበለጽጋል፣ ያስጸድቃል፤
2. የኢኮኖሚና የልማት ፖሊሲ ትንተናና ጥናቶችን ያካዳል፣ ስትራቴጅካዊ የሶሾ-ኢኮኖሚ ጉዳዮችን ይለያል፣ በትንተናና ጥናቶች በሚገኙ ውጤቶች መሠረት የፖሊሲ ምክረ ሐሳቦችን ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ሥራዎችን ያካሒዳል፤
3. የክልሉን የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ የልማት ዕቅዶችን ለማዘጋጀት የሚረዱ የኢኮኖሚ ጥናትና ምርምሮችን ያካሂዳል፣ አጠቃላይ የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሁኔታ መለኪያዎችንና መመዘኛዎችን ያዘጋጃል
4. በሀገሪቱ የልማት ስትራቴጂዎች ላይ የተመሠረተና በክልሉ መንግሥት የሚፈጸም የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ የልማት ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤
5. ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የክልሉን ሕዝብ ፍትሐዊ የመልማትና የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያግዝ ስርዓት ይዘረጋል፣ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፤
6. ለክልሉ መንግሥት አካላት በተለይም ለክልሉ ከፍተኛ አስፈጻሚና አስተዳደራዊ አካል የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅዶች ዝግጅት፣ ክትትል፣ አተገባበርና ግምገማ ማዕከል ሆኖ ይሠራል፤
7. የብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ተቋማትን የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ዕቅዶችን አተገባበር፣ ውጤታማነትና ጥረት በላቀ ሙያዊ ኃላፊነትና በሀቀኝነት ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ለዚህም ያመቸው ዘንድ በስትራቴጅካዊ የትኩረት መሥኮች ከፋፍሎ የየዘርፉን ዕቅዶችና ሪፖርቶች ይቀበላል፣ ለበላይ አመራሩ የሚቀርበውን የተጠቃለለ ሪፖርት ያዘጋጅል፤
8. በክትትልና በግምገማው የተገኙትን ውጤቶች በጥልቀት በመመርመርና በመተንተን ከተገማች እንድምታዎቻቸው ጋር ለበላይ አመራሩ እናአግባብ ላላቸው ፈጻሚ አካላት በወቅቱ ያስተላልፋል፤
9. የእርስ በርስ ግንኙነቶችን በማጠናከር በክልሉ ውስጥ የተደራጁትን ልዩ ልዩ መንግሥታዊ ተቋማት፣ የግል ተቋማትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በሰፊው የሚያሳትፉበት ተጠያቂነትን ያሰፈነ የክትትልና ግምገማ ሥርዓት ይዘርጋል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተል፤
10. የክትትልና ግምገማ ሥርዓቱን ለማስተዋወቅና በክልሉ መንግሥታዊ ተቋማት ዘንድ ለማስረፅ የሚያግዙ የሕዝብ ግንኙነት ሥራዎችን ያከናውናል፣ ሥርዓቱን በማላመድና በማስተግበር ረገድ የየደረጃው ፈጻሚ አካላት ክህሎት ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚገነባበትን ስልት ይቀይሳል፤
11. የልማት ዕቅድን ለማሳካት እንዲሁም የመንግሥትን የማስፈጸም አቅም ለማጠናከርና ቀጣይነት ያለው ተቋማዊ አቅም እንዲፈጠር የሥርዓት ማሻሻያ ጥናት ያካሂዳል፣ በጥናቱ ላይ ተመሥርቶ የተቋማትን አደረጃጀት በተመለከተ የውሳኔ ሐሳብ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤
12. በመንግሥት በጀት፣ በመንግሥት ዋስትና ብድር እንዲሁም በሌሎች ተመሳሳይ የበጀት ምንጮች እንዲከናወኑ የታቀዱ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ የአዋጭነትና አስፈላጊነት ግምገማ በማከናወን ወጤቱን ለሚመለከተው አካል ያሳውቃል፤
13. የልማት ፕላን ፕሮግራምና ፕሮጀክቶች አዘገጃጀት ሥርዓት በመዘርጋት በሥራ ላይ እዲውል ያደርጋል፣ የቴክኒካል ምክር አገልግሎትና የአቅም ግንባታ ድጋፍ ይሰጣል፤
14. ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የክልሉ መንግሥት አካላት ጋር በመመካከር በአጭር፣ በመካከለኛና በረዥም ጊዜ የልማት ዕቅዶች ውስጥ ሊንፀባረቁ የሚገባቸውና በክልሉ መንግሥት የሚከናወኑ ፕሮጀክቶች እንዲጠኑና እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ይገመግማል፤
15. በክልሉ የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ የልማት ዕቅዶችን ለማሳካት የሚከናወኑ ፕሮጀክቶችን አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ሪፖርት ያዘጋጃል፤
16. አለም ዓቀፍና ሀገራዊ የስታትስቲክስና የጅኦ ስፓሻል መረጃ ስታንዳርዶችን መሠረት በማድረግ መረጃዎች በክልሉ እንዲሰበሰቡ ሥርዓት ይዘረጋል፣ ይከታተላል፣ ያሰፈጽማል፤
17. የክልሉን የተፈጥሮ ሀብት፣ የጂኦ-ስፓሻል፣ የግብርና፣ የኢንዱስትሪ፣ የምርት፣ የአገልግሎትና የመሳሰሉትን መረጃዎች ያሰባስባል፣ ያጠናቅራል፣ ለሚመለከታቸው ያስተላልፋል፤
18. ለክልሉ ዘላቂ ልማትና ዕድገት ፋይዳ ያላቸው የቅየሳ፣ የካርታና የጂኦግራፊ ጥናት ሥራዎችን ያከናውናል፣ እንዲከናወን ያስተባብራል፣ ይከታተላል፤
19. የተቋማትን የመረጃ የመሰብሰብ ተግባራት ይቆጣጠራል፣ የአሠራር ስታንዳርድ እና የናሙና ዘዴዎችን ያጸድቃል፣ የትክክለኛነት ማረጋገጫ ይሰጣል፤ 2
20. በክልሉ ውስጥ በወሰን ተለይተው ለሚቋቋሙ የከተማና የገጠር አስተዳደራዊ እርከኖች የአስተዳደር ወሰን ይሠራል፣ መለያ ኮዶችን በመስጠት የካርታ ሥራ ይሠራል፣ የሥነ ሕዝብ መረጃዎችን ለተጠቃሚዎችም ያሰራጫል፤ ያደራጃል፣
21. በክልሉ ውስጥ የማክሮ ኢኮኖሚ መረጃዎችን ያመነጫል፣ ለተጠቃሚዎችም ያሰራጫል፤
22. የሥነ-ሕዝብ ጉዳዩችን አስመልክቶ ጥናትና ምርምር ያካሒዳል፣ መረጃዎችን ያደራጃል፣ ለተጠቃሚዎችም ያሰራጫል፤
23. መንግሥታዊም ሆነ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በብሔራዊው የሥነ-ሕዝብ ፖሊሲ አፈጻጸም ረገድ የሚያደርጓቸውን እንቅስቃሴዎች ያስተባብራል፣ ይመራል፣ ከነዚሁ አካላት ጋር በመቀናጀት ይሠራል፤
24. በክልሉ መንግሥት አካላት እየተዘጋጁ የሚቀርቡትን የመደበኛና የካፒታል በጀት ጥያቄዎች ከክልሉ የልማት እቅድ ጋር ተገናዝበው እዲዘጋጁና ፍትሐዊ የሆነ የበጀት ቀመር እንዲኖር የሚያስችል መረጃዎችን ያሰባስባል፣ ከአስተያየት ጋር ለገንዘብ ቢሮ ያስተላልፋል፤
25. ከሀገር ውስጥና ከውጭ በመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም ሆነ በበይነ መንግሥታት የሚቀርቡ የልማት ፕሮግራሞችንና ፕሮጀክቶችን ከክልሉ የልማት እቅድ ጋር ተመጋጋቢ እዲሆኑ ያደርጋል፤ እንዲሁም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን በመሰብሰብ ከአጠቃላይ የክልሉ ሪፖርት ጋር በማገናዘብ ጥቅል ሪፖርት በማዘጋጀት ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፡፡
26. የአየር ንብረት ለውጥን የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት ጉዳዩ የሚመለከታቸውን አካላት ያስተባብራል፣ ይደግፋል፣ ይከታተላል፡፡

Website:-http://anrsbopd.gov.et
Telegram:-https://t.me/planpdb2014
Facebook:-https://www.facebook.com/ANRSPADB
YouTube channel: - https://www.youtube.com/-2014
Instagram :- https://www.instagram.com/plan_and_development_bureau/
x-account:- https://x.com/logout
tiktok:- https://www.tiktok.com/?lang=en-GB
gmail address:- [email protected]

 Welcome to the official website of the Amhara National Regional State Plan and Development Bureau! The Plan and Development Bureau plays a major role in drafting and enriching the regional state’s draft policies and strategies, conducting economic studies and research to help prepare development...

ሚያዚያ10/2017 ዓ/ም######የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመደሃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል ...
18/04/2025

ሚያዚያ10/2017 ዓ/ም
######
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመደሃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በአሉ የፍቅር የደስታ የመከባበርና የሰላም እንዲሆን መልካም ምኞቱን ይገልፃል ።
መልካም የትንሳኤ በዓል

የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ
👇👇👇
Website:-http://anrsbopd.gov.et
Telegram:-https://t.me/planpdb2014
Facebook:-https://www.facebook.com/ANRSPADB share, like, comment and follow

የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወር የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ፡፡ +++ ሚያዚያ 04/2017 ዓ.ም (ፕላንና ልማት ቢሮ) የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላን...
13/04/2025

የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወር የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ፡፡
+++

ሚያዚያ 04/2017 ዓ.ም (ፕላንና ልማት ቢሮ)

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ ዛሬ ሚያዚያ 04/2017 የቢሮው አማራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል።

የግመገማ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የቢሮው አማካሪና የጽ/ቤት ዘርፍ ተወካይ ኃላፊ የሆኑት የተከበሩ ሙሉቀን አዳነ (ዶ/ር) ሲሆኑ "በዚህ የግምገማ መድረክ በእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት አማካኝነት የሚቀርበውን ሪፖርት መነሻ በማድረግ አፈጻጸማችንን ስንገመግም ባለፉት ዘጠኝ ወራት የነበሩን አፈጻጸሞች ጥንካሬና በድክመት ሲገለጹ ምን ይመስሉ ነበር? ያላሳካናቸው ግቦች የትኞቹ ናቸው? ያጋጠሙን ችግሮች ምን ነበሩ? እንዴትስ ተሻገርናቸው? የሚሉትን ነጥቦች በጥልቀት መገምገምና ለቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ ይጠበቀል" ብለዋል።

በዚህም መሰረት በተቋሙ የእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ባለሙያ በወ/ሮ አረጋሽ ሽፈራው አማካኝነት ሪፖርቱ በጽሁፍ የቀረበ ሲሆን በእቅድ አፈጻጸም ሂደቱ የነበሩ ድክመትና ጥንካሪወች፥ የተፈጸሙና ያልተፈጸሙ ተግባራት፥ እንዲሁም በአፈጻጸም ሂደት ያጋጠሙ ችግሮች በዝርዝር ቀርበዋል።

በተሳታፊወች በኩልም ሪፖርቱን መሰረት በማድረግ ድክመቶችና ጥንካሪወች፣ ያጋጠሙ ችግሮችና መፍትሄወቻቸው እንዲሁም በቀጣይ መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በግምገማው የቢሮው አጠቃላይ የመፈፀም አቅም እየጎለበተ በመምጣቱ የሩብ አመቱ አፈጻጸሙ በጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኝ መሆኑ ታይቷል። በተለይም የክልሉን የእስፓሻል ፕላን በማዘጋጀት፥ የቀጣይ 25 አመት የልማትና መልካም አስተዳደር ፍኖተ ካርታና የቀጣይ 5 አመት አሻጋሪና ዘላቂ ልማት እቅድን በተመለከተ ቀሪ ስራወችን በማጠናቀቅ በኩል፣ የክልሉን የልማትና የመልካም አስተዳደር ስትራቴጂወች አስተባብሮ በማዘጋጀት፥ ክልላዊ መዋቅራዊ አደረጃጀትን በማዘጋጀት፣ የቀጣይ በጀት አመት የክልሉንና የቢሮውን አመታዊ እቅዶች በማዘጋጀት፣ የቢሮውን የኤርጎኖሚክስ አፈጻጸም በማሳደግ አካባቢው ለባለሙያዎችና ለባለጉዳዮች ምቹና ማራኪ በማድረግ እንዲሁም የፈጻሚውን አቅም በማሳደግ በኩል ሰፊና ውጤታማ ስራ የተሰራ መሆኑ ተገምግሟል።

በቀጣይ ታቅደው ባልተፈጸሙ ተግባራት ላይ የበለጠ ትኩረት አድርጎ በመስራት የተቋሙን አፈጻጸም የተሟላ ማደረግ እንደሚጠበቅ መግባባት ላይ ተደርሷል።

ከዚህም በተጨማሪ የክልላችን ማህበረሰብ ሁለንተናዊ የመልማት ፍላጎትን ለማረጋገጥ ቢሮው እያከናወነ ያለው ተግባር ትልቅ መሆኑን በመገንዘብ በእቅድ የተሰጡንን ተግባራት በትኩረት በመለየት መፈፀም እንደሚገባም ተገምግሟል።

በመጨረሻም በቀጣይ ወራት በትኩረት ሊሰሩ የሚገባቸው የስራ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ግምገማው ተጠናቋል፡፡

👇👇👇
Website:-http://anrsbopd.gov.et
Telegram:-https://t.me/planpdb2014
Facebook:-https://www.facebook.com/ANRSPADB share, like, comment and follow

የፕላንና ልማት ቢሮ ሰራተኞች በዲሲፕሊን አፈፃፀም መመሪያ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፥ +++ ሚያዚያ 03/2017 ዓ.ም (ፕላንና ልማት ቢሮ)የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ለአመራሮች፤ ለባለሙያዎችና ...
11/04/2025

የፕላንና ልማት ቢሮ ሰራተኞች በዲሲፕሊን አፈፃፀም መመሪያ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፥

+++
ሚያዚያ 03/2017 ዓ.ም (ፕላንና ልማት ቢሮ)
የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ለአመራሮች፤ ለባለሙያዎችና ለሰራተኞች በተሻሻለው የመንግስት ሰራተኞች የዲሲፕሊን አፈፃፀም መመሪያ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በዛሬው እለት ሰጥቷል፡፡

ስልጠናውን በመክፈቻ ንግግር የከፈቱት የፕላንና ልማት ቢሮ አማካሪና የጽ/ቤት ዘርፍ ተወካይ ኃላፊ የተከበሩ ሙሉቀን አዳነ (ዶ/ር) እንደተናገሩት "የስልጠናው አስፈላጊነት የቢሮው የመንግስት ሰራተኞች መንግስት ያወጣውን የዲሲፕሊን መመሪያ አውቀውና ተገንዝበው በአመለካከትና በሥነ-ምግባራቸው የታረሙ እንዲሆኑ ፥መመሪያውን ባለማወቅ በራሳቸውም ሆነ በመስሪያ ቤቱ ላይ ችግር እንዳይፈጥሩ፥ ህግና ስርአትን አክብረው የተቀላጠፈና ፍትሐዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ማስቻል ነው" ብለዋል።

በዚህም መሰረት የተቋሙ ባለሙያ በሆኑት በአቶ በቀለ ሀይሉ አማካኝነት ሰነድ ተዘጋጅቶ ስልጠናው የተሰጠ ሲሆን የስልጠናው ተሳታፊዎች ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አቅርበው ስፊ ውይይት ተካሂዷል።

በመጨረሻም በስራ ሂደት የሚፈጠሩ የዲሲፐሊን ጉድለቶች በመመሪያው መሰረት ለሚመለከተው አካል ቀርበው፥ ተጣርተውና ተመርምረው ውሳኔ እንደሚያገኙ የጋራ ግንዛቤ ተወስዷል፡፡

👇👇👇
Website:-http://anrsbopd.gov.et
Telegram:-https://t.me/planpdb2014
Facebook:-https://www.facebook.com/ANRSPADB share, like, comment and follow

የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ በችግር ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ አደረገ፡፡+++መጋቢት 26/2017 ዓ.ምየአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ በባህር ዳር ከተማ ፋሲሎ ክፍል ከተማ በማህበ...
05/04/2025

የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ በችግር ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ አደረገ፡፡
+++
መጋቢት 26/2017 ዓ.ም
የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ በባህር ዳር ከተማ ፋሲሎ ክፍል ከተማ በማህበረሰብ ቀውስ እና በሌሎች የተለያዩ ችግሮች ምክንያት ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ድጋፍ የተደረገላቸው አንድ በማህበራዊ ቀውስ ምክንያት ከሌላ አካባቢ ተፈናቅሎ የመጣና አካል ጉዳት የደረሰበት ግለሰብ እና አንዲት ወላጆቿ አቅመ ደካማ የሆኑ ተማሪ ሲሆኑ ለእያንዳንዳቸው 5000 ብር ድጋፍ ተደርጎላቸዋል፡፡
በእለቱ ቢሮውን ወክለው ተገኝተው ድጋፉን ያደረጉት የፕላንና ልማት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሞገስ እያሌው “ቢሮዎች በአዋጅ የተሰጣቸውን ተግባርና ኃላፊነት ከመወጣት በተጨማሪ ለከፋ ማህበራዊ ችግር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመለየት የተቻላቸውን ድጋፍ ማድረግ አንደሚገባቸው ቢሮአችን ያምናል፡፡ ይህን አምነቱን በተግባር ለመግጽና ከማህበረሰቡ ጋር ያለውን አብሮነት ለማሳየት ሠራተኛው አስተባብሮ ያሰባሰበውን ይህንን ድጋፍ አድርጓል” ብለዋል፡፡
የፋሲሎ ክፍለ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይበልጣል አለም “ቢሮው በዚህ ልክ እስከ ቀበሌ ድረስ በመውረድ ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች ድጋፍ ማድረጉ መንግስት ለማህበረሰብ ያለውን ትኩረት ያሳያል፡፡ ዋናው ነገር የድጋፉ መብዛትና ማነስ ሳይሆን አመለካከቱ ነው፡፡ ሌሎች ቢሮዎችን የፕላንና ልማት ቢሮን አርአያነት ተከትለው በተለያዩ ማህበራዊ ቀውስ ምክንያት የተጎዱ ሰዎችን ቢረዱ መልካም ነው” ብለዋል፡፡
የክፍለ ከተማው ማህበራዊ ዘርፍ ሀላፊም “ፕላንና ልማት ቢሮ በአሁኑ ጊዜ ለህዝብና ለክልል ጠቃሚ የሆኑ ተግባራትን እየፈጸመ ወደ ፊት በመውጣት ላይ ያለ ቢሮ መሆኑን አንስተው ይን ድጋፍ ለማድረግ በመምጣቱ ላቅ ያለ ምስጋናችንን በክፍለከተማው ስም እናቀርባለን ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ድጋፍ የተደረገላቸው አካላት ስለድጋፉ አመስግነው ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ከሳምንት በፊት የጀመረውን ስልጠና ዛሬ አጠናቀቀ። -----መጋቢት 06/2017------ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ  መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ  ከክልሉ ቢሮዎ...
15/03/2025

የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ከሳምንት በፊት የጀመረውን ስልጠና ዛሬ አጠናቀቀ።

-----መጋቢት 06/2017------

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ ከክልሉ ቢሮዎች ለተውጣጡ የእቅድና በጀት ዳይሬክተሮች፣ ከስራ አመራር ተቋም እና ከፕላንና ልማት ቢሮ ለመጡ ባለሙያዎች፣ እንዲሁም ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽንና ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን/አሚኮ/ ለተውጣጡ ጋዜጠኞች ከ01/07/2017 አ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ሲሰጠው የቆየውን የአሻጋሪ እድገትና የዘላቂ ልማት እቅድ ስልጠና ዛሬ መጋቢት 06/2017 አ.ም አጠናቋል።

ስልጠናውን የሰጡት በሙያው በቂ እውቀት ባላቸውና ከመጀመሪያው ጅምሮ የእቅድ ዝግጅት ሂደቱን ሲመሩት የነበሩት የፕላንና ልማት ቢሮ ሀላፊ በሆኑት የተከበሩ ደመቀ ቦሩ(ዶ/ር) እና እውቅ የኢኮኖሚክስ ባለሙያ የሆኑት የርእሰ መስተዳድሩ የቴክኒክ አማካሪ ሰይድ ኑሩ (ዶ/ር) እንዲሁም የፕላንና ልማት ቢሮ የማክሮ ፕላን ባለሙያ የሆኑት አቶ ምትኩ መኩሪያው ናቸው።

ስልጠናው በተለያዩ ርእሶች ማለትም፥
1. ጥቅል የኢኮኖሚ ማእቀፍ
2. የዘርፍ ልማት እቅድ
3. የልማት አቅሞችና የልማት ፋይናንስ
4. የስርአታት ልማት
5. የማስፈጸሚያ ስልቶች
6. የአሻጋሪ እድገትና የዘላቂ ልማት እቅድ የተግባቦት ስትራቴጂ በሚሉ ርእሶች ላይ ትኩረት አደርጎ የቀረበ ነው።
በስልጠናው ይዘትና አቀራረብ ደስተኞች መሆናቸውን፣ እንዲሁም በቀጣይ በሚኖረው የእቅድ አፈጻጸም ሂደት የበኩላቸውን አስተዋጸኦ ለማበርከት የሚያስችላቸውን ግንዛቤ ማግኘታቸውንም ስልጣኞች ገልጸዋል።

በቀጣይ ከክልል ጅምሮ እስከታችኛው የመንግስት መዋቅር ለሚገኘውን አመራርና ፈጻሚ ተመሳሳይ ይዘት ያለው ስልጠና ለመስጠት እቅድ መያዙን ቢሮው ገልጿል።

👇👇👇
Website:-http://anrsbopd.gov.et Telegram:-https://t.me/planpdb2014 please join and share it.
Facebook:-https://www.facebook.com/ANRSPADB share, like, comment and follow

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ  በአሻጋሪ እድገትና ዘላቂ ልማት እቅድ ዙሪያ ለአስፈፃሚ ተቋማት ስልጠና መስጠት ጀመረ::+++++መጋቢት 1/2017 ዓ.ም የአብክመ ፕላንና...
10/03/2025

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ በአሻጋሪ እድገትና ዘላቂ ልማት እቅድ ዙሪያ ለአስፈፃሚ ተቋማት ስልጠና መስጠት ጀመረ::
+++++
መጋቢት 1/2017 ዓ.ም

የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ በክልሉ አሻጋሪ እድገትና ዘላቂ ልማት እቅድ ዙሪያ በክልሉ አስፈፃሚ ተቋማት ለተውጣጡ አመራሮችና ባለሙያዎች ከዛሬ መጋቢት 01 - 07/2017 አ.ም ድረስ የሚቆይ ስልጠና መሰጠት ጀምሯል::

የስልጠናው አላማ በቀጣይ አመት ጅምሮ ተግባራዊ የሚሆነውን የ5 አመት (2018 - 2022) የአሻጋር እድገትና የ25 አመት (2018 - 2042) የዘላቂ ልማት እቅድ በተሳካ ሁኔታ እንዲፈጸም በማድረግ በኩል ከፍተኛ ሚና ያላቸው አስፈጻሚ አካላት እቅዱን እንዲረዱትና ተገቢውን አመለካከት እንዲይዙ በማድረግ በመፈጸምና በማስፈጸም በኩል የራሳቸውን ሚና እንዲጫዎቱ ማስቻል መሆኑን ስልጠናውን በመክፈቻ ንግግር የከፈቱት የፕላንና ልማት ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቅነህ ገልጸዋል።

ለረጅም አመታት ሲቀነቀኑ የኖሩ አሉታዊ/አፍራሽ/ የሀሰት ትርክቶች እያደጉና እየሰፉ መጥተው ክልላችን የተረጋጋና ሰላማዊ እንዳይሆን በማደረግ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገቱ በታሰበው ፍጥነት እንዳያድግ አድርገውታል ያሉት አቶ ጥላሁን ለዚህ ችግር መፍትሄው በጥናት ላይ የተመሰረተ ክልላዊ አሻጋሪና ዘላቂ ልማት እቅድ ማዘጋጀትና ወደ ስራ መግባት ነው ያሉ ሲሆን ፥ ይህም እቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ትግበራ ለመግባት ፈጻሚን በማብቃት ሂደት ላይ ይገኛል ብለዋል።

በረጅምና በመካከለኛ ጊዜ ተግባራዊ እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀው ክልላዊ እቅድ ያስቀመጣቸው ግቦች እንዲሳኩ የተግባቦት ስትራቴጅውን ተከትሎ ከላይ እስከታች የሚገኙትን ፈጻሚና አስፈጻሚ አካላት በተለያዩ ዙሮች ስልጠናውን እንዲያገኙ ማድረግ የስትራቴጂው አካል ሲሆን በዚህ ዙር ከፕላንና ልማት ቢሮ፣ ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ፤ ከስራ አመራር ኢንስቲትዩት እና ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን/አሚኮ/ የተውጣጡ 265 አማራሮችና ባለሙያዎች የስልጠናው ተሳታፊዎች እንዲሆኑ ተደርጓል።

ስልጠናው ለ7 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በነዚህ ቀናት ወስጥ ዛሬ የተጀመረውን የአሻጋሪ እድገትና ዘላቂ ልማት የተግባቦት ስትራቴጂን ጭምሮ ሌሎች የስልጠና ርእሶች ማለትም የጥቅል ኢኮኖሚ ገለጻ፣ የዘርፍ ልማት ገለጻ 1፣ የዘርፍ ልማት ገለጻ 2፣ የልማት አቅሞችና የልማት ፋይናንስ፣ እንዲሁም የስርአታት ልማት የሚሉ ርእሶች ለሰልጣኞች የሚሰጡ የሆናል።

👇👇👇
Website:-http://anrsbopd.gov.et Telegram:-https://t.me/planpdb2014 please join and share it.
Facebook:-https://www.facebook.com/ANRSPADB share, like, comment and follow

ለፕላንና ልማት ቢሮ ለአመራሮችና ሠራተኞች በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ፓሊሲ  ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፤  የካቲት 25/2017 ዓ.ም  +++++ለአብክመ ፕላንና ላማት ቢሮ አመራሮችና ሰራተ...
05/03/2025

ለፕላንና ልማት ቢሮ ለአመራሮችና ሠራተኞች በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ፓሊሲ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፤
የካቲት 25/2017 ዓ.ም
+++++
ለአብክመ ፕላንና ላማት ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች በመንግሥት የአገልግሎትና አስተዳደር ፓሊሲ እንዲሁም በቅሬታ አቀራረብ ስርአት ዙሪያ የካቲት 25/2017ዓ.ም በቢሮው ባዘጋጀው መድረክ ሰፊ የሆነ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ስልጠናውን በመክፍቻ ንግግር ያስጀመሩት የቢሮው ኃላፊ የተከበሩ ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር) በንግግራቸው “ማንኛውም የመንግስት አገልገሎት በጥራትና በፍጥነት መቅረብ የሚችለው አገልግሎት አቅራቢው መንግስት ያስቀመጠውን አሰራር በተመለከተ በቂ ግንዛቤ ሲኖረው ነው” ብለዋል፡፡ “የአገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን የኢኮኖሚውን እድገት ለማፋጠን፣ አዳዲስ አሠራሮችን የሚቀበል ትውልድ ለመፍጠር የፈጻሚው ሁለንተናዊ አቅም ማሳደግ ላይ መሥራት ይገባል” ያሉት ደመቀ ቦሩ(ዶ/ር) ይህ ስልጠና እጅጉን አስፈላጊ ስልጠና በመሆኑ ሰልጣኞች ትኩረት ሰጥተው እንዲከታተሉና በቂ ግንዛቤ ይዘው ወደ ስራ እንዲገቡ አሳስበዋል፡፡

ባለሙያዎችና ሰራተኞችም በስራቸው ላይ የሚደርስባቸው የመብት ጥሰት ካለ የቅሬታ አቀራረብ ስርዓቱን በመከተል መብታቸውን ማስከበር እንዲችሉ የዛሬው ስልጠና ግንዛቤ ይሰጣል ብለዋል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎችም በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት የሚደርሱ አስተዳደራዊ በደሎችን ፈጥኖ ለማረምና የሚደርሱ የመብት ጥሰቶችንም ለመከላከል ስልጠናው አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

ከስልጠናው በኋላም ስልጠናው ስለ ቅሬታ አቀራረብና ሰለመንግስት የአገልግሎት የአስተዳደር ፖሊሲ ምንነት የነበራቸውን እውቀት፣ አመለካከት እና ክህሎት እንዳሳደገላቸው ገልጸዋል፡፡

Website:-http://anrsbopd.gov.et Telegram:-https://t.me/planpdb2014 please join and share it
Facebook:-https://www.facebook.com/ANRSPADB share, like, comment and foll

ፕላንና ልማት ቢሮ ሰራትኞች  በመንግስት የቀጣይ አገራዊ የልማትና የመልካም አስትዳደር አቅጣጫወችና ውሳኔዎችን ዙሪያ የውይይት አደረጉ። ++++የካቲት 23/2017 ዓ.ም የአማራ ክልል ፕላንና...
02/03/2025

ፕላንና ልማት ቢሮ ሰራትኞች በመንግስት የቀጣይ አገራዊ የልማትና የመልካም አስትዳደር አቅጣጫወችና ውሳኔዎችን ዙሪያ የውይይት አደረጉ።
++++
የካቲት 23/2017 ዓ.ም

የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ በቀጣይ በፓርቲና በመንግስት የሚከናወኑ ተግባራትን በሚመለከት የቢሮው አመራሮችና ሰራተኛች በተገኙበት በዛሬው ዕለት ዉይይት አካሂዷል።

ውይይቱን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የቢሮው ኃላፊ የተከበሩ ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር) እንደተናገሩት በ2ተኛው የብልፅግና ፓርቲ መደበኛ ጉባዔ የተላለፉ አበይት ውሳኔዎችን በሚቀጥሉት ዓመታት በመተግበር የህዝባችን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ በትጋትና በጊዜ የለኝም መንፈስ ልንሰራ ይገባል ብለዋል::

እንደ ክልል ያሉትን ፀጋዎች መሠረት በማድረግ ወቅቱን የሚመጥን የረጅም እና የአጭር ጊዜ እቅድ በማቀድና የአሰራር ስርዓቱን በማስተካከል ወጥ የሆነ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ላይ እንገኛለን ያሉት ኃላፊው በጉባዔ የተቀመጡ አበይት ውሳኔዎች የመፈፀም አቅማችንን ከፍ ለማድረግ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ ስለሆኑ በትኩረት መፈፀም ተገቢ መሆኑን አስገንዝበዋል::

በዕለቱ ለውይይት መነሻ የሚሆን ሰነድ ቀርቧል። በቀረበው ሰነድ እስካሁን በአፈጻጸም የነበሩብን ችግሮች ተለይተው የቀረቡ ሲሆን ችግሮቹን ለመፍታት በቀጣይ ትኩረት ሰጥቼ እሰራቸዋለሁ ያላቸው፦
1. የብሄራዊ ገዥ ትርክት ግንባታን ማጠናከር
2. ውጤታማ የሰላም ግንባታ ስራ መስራት
3. የፍትህ ዘርፍ ውጤታማነትን ማሳደግ
4. የአገር ግንባታ/Nation bulding / ስራን ማጠናከር
5. የኢኮኖሚ ልማትን ማፋጠን
6. ማህበራዊ ብልጽግናን የሚያረጋግጡ ስራዎችን በውጤታማነት ማስቀጠል።
7. ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራዎችን መስራት
8. የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ውጤታማነትን ማረጋገጥ
9. ጠንካራ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራዎችን መስራት የሚሉ ሲሆኑ እነዚህን የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ውጤታማ አፈጻጸም እንዲኖራቸው ማድረግና መልካም አፈፃፀሞችን በመቀመርና በማስፋት ክልላዊና አገራዊ ብልጽግናን በማረጋገጥ ሂደቱ የበኩላችንን ሚና መጫዎት እንደሚገባን ስራትኞቹ በውይይታቸው ገልፀዋል።

በ2ተኛው የብልፅግና ፓርቲ መደበኛ ጉባዔ የተላለፉ አበይት ውሳኔዎችን በሚቀጥሉት ዓመታት በመተግበር የህዝቡን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ በትጋት እንሰራለን ሲሉ የውይይቱ ተሳታፊዎች ጨምረው ተናግዋል።
Website:-http://anrsbopd.gov.et Telegram:-https://t.me/planpdb2014 please join and share it
Facebook:-https://www.facebook.com/ANRSPADB share, like, comment and foll

Address

Bahir Dar

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 02:00 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Telephone

+2510583209566

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara National Regional Sate Plan And Development Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Amhara National Regional Sate Plan And Development Bureau:

Share