West Bellessa Woreda Court

West Bellessa Woreda Court Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from West Bellessa Woreda Court, Public & Government Service, Bahir Dar.

03/02/2026
የምዕራብ በለሳ ወረዳ ፍርድ ቤት የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የስራ አፈፃፀሙን በዛሬው ዕለት ገምግሟል።በመድረኩም  የተቋሙ እና ሁሉም የሂደቶች የ6 ወር የስራ አፈፃፀም ቀርቦ በጥንካሬና...
02/02/2026

የምዕራብ በለሳ ወረዳ ፍርድ ቤት የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የስራ አፈፃፀሙን በዛሬው ዕለት ገምግሟል።
በመድረኩም የተቋሙ እና ሁሉም የሂደቶች የ6 ወር የስራ አፈፃፀም ቀርቦ በጥንካሬና በድክመት ከተገመገመ በኋላ የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ውይይቱን አጠናቋል።
ጥር 25/2018 ዓ/ም

31/12/2025
የምዕራብ በለሳ ወረዳ ፍርድ ቤት የህዝብ የምክክር መድረክ አካሄደ።ታህሣሥ 21/2018 ዓ/ምፍርድ ቤቱ የአምስት ወር የስራ አፈፃፀሙን አስመልክቶ ከአጋር አካላት እና ከወረዳዉ ማህበረሰብ እን...
30/12/2025

የምዕራብ በለሳ ወረዳ ፍርድ ቤት የህዝብ የምክክር መድረክ አካሄደ።
ታህሣሥ 21/2018 ዓ/ም
ፍርድ ቤቱ የአምስት ወር የስራ አፈፃፀሙን አስመልክቶ ከአጋር አካላት እና ከወረዳዉ ማህበረሰብ እንዲሁም ከሀይይማኖት አባቶች ጋር የመጀመሪያውን ዙር የህዝብ የምክክር መድረክ አካሂዷል። በመድረኩም
የፍ/ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት የ5 ወር የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት በተቋሙ ዕቅድ ባለሙያ ከቀረበ በኋላ ሠፊ ዉይይት ተደርጎበታል፡፡በውይይቱም የቀረበውን የስራ አፈፃፀም ሪፖርት መነሻ በማድረግና አጠቃላይ የፍርድ ቤቱን አገልግሎት አሰጣጥ አስመልክቶ በጥንካሬና በደክመት የተለያዩ ሀሳቦች በተሳታፊዎቹ ተነስተው ለተነሱት ሀሳቦችም በፍ/ቤቱ ፕሬዚዳንት አቶ ሀብተማርያም ወ/ዮሀንስ አማካኝነት ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡
ታህሳስ 21/2018 ዓ/ም

ማሥተካከያ ሥለመሥጠት፣================በፍርድ ቤታችን ድህረ ገፅ ለባህል ፍርድ ቤት ሽማግሌዎች ሥልጠና ተሠጠ በሚል የተዘገበው ዘገባ በሥህተት መሆኑን በትልቅ ይቅርታ እየገለፅን የተ...
28/12/2025

ማሥተካከያ ሥለመሥጠት፣
================
በፍርድ ቤታችን ድህረ ገፅ ለባህል ፍርድ ቤት ሽማግሌዎች ሥልጠና ተሠጠ በሚል የተዘገበው ዘገባ በሥህተት መሆኑን በትልቅ ይቅርታ እየገለፅን የተሰጠው ሥልጠና እና የተደረገው ውይይት በፍ/ቤት መር ስምምነት፣ በጉዳዮች ፍሰትና በፍርድ ቤት የሪፎርም ስራዎች ላይ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን።

16/12/2025

ሰው በመጥለፍ ወንጀል ክስ የቀረበባቸው በ11 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጡ

ባህር ዳር ፣ ታህሳስ 06/2018 (አብክመ ጠ/ፍ/ቤት)

ሰው በመጥለፍ ወንጀል ክስ የቀረበባቸው ኤርሚያስ (ዲበኩሉ) አለነ፣ አይነኩሉ (ኪሩቤል) ማሩ እና በለጠ አለባቸው በአስራ አንድ (11) ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተፈርዶባቸዋል።

ተከሳሾች በ1ኛ ክስ የወ/ህ/ቁ/32/1/ሀ/ እና 590/1/ሀ/ ና 2/ሐ/ ላይ የተመለከተውን ሕግ በመተላለፍ ለጊዜው ካልተያዙ ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን ጥቅምት 27/2016 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 1 ሰዓት ሲሆን ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 16 A ዞን ግሮሰሪ ከተባለው ቦታ የግል ተበዳይ ሃይማኖት መርሻን 1ኛ ተከሳሽ ጠላፊዎችን በማገናኘት እና በማመቻቸት 2ኛ ተከሳሽ ከመጀመሪያውም የግል ተበዳይ እንዲጠለፍ ወይም እንዲታገት ሃሳብ በማመንጨት እና ከግል ተበዳይ ጋርም አብሮ መጠጥ ቤት በማምሸት እና ሲወጡም መልዕክት ለ3ኛ ተከሳሽ በመላክ እና በኋላም አብሮ ተጠላፊ /ታጋች/ በመምሰል አብሮ የሄደ 3ኛ ተከሳሽ 2ኛ ተከሳሽ የሚጽፍለትን መልዕክት እና ስልክ ለሌሎች ጠላፊዎች በማሳየት እና በማመቻቸት የግል ተበዳይን ከነመኪናው ጠልፈው /አግተው/ ይባብ ቀበሌ ከወሰዱት በኋላ ተበዳይን 3,000,000/ሶስት ሚሊዮን ብር/ አምጣ በማለት በኋላም በድርድር 700,000/ሰባት መቶሺ ብር/ ከግል ተበዳይ ቤተሰቦች በህዳር 03/2016 ዓ.ም ከተቀበሉ በኋላ የግል ተበዳይ ከነመኪናው የተለቀቀ ሲሆን ፣ ተከሳሾች በመላ ሃሳባቸው እና ፍላጎታቸው የድርጊቱ ተካፋይ እና ዋና ወንጀል አድራጊ በመሆን ሰውን ጠልፎ ገንዘብ መቀበል ወንጀል ፈፅመዋል በሚል በዐ/ህግ በኩል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡

እንዲሁም በ2ኛ ክስ የወ/ህ/ቁ/ 671/1/ ላይ የተመለከተውን ህግ በመተላለፍ በ1ኛ ክስ በተጠቀሰው ቀን ፣ ሰዓት እና ቦታ እንዲሁም የግል ተበዳይ ሃይማኖት መርሻን በጦር መሳሪያ በመታገዝ የተለያየ ንብረት የወሰዱ በመሆኑ ከባድ ውንብድና ወንጀል ፈፅመዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡

ተከሳሾች የወንጀል ድርጊቱን አልፈጸምንም በማለት ክደው የተከራከሩ ሲሆን፣ በግራ ቀኙ በኩል ማስረጃዎች ቀርበው ተደምጠዋል፡፡

ጉዳዩ በመጀመሪያ ደረጃ የቀረበለት የባህር ዳር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዲሁም በይግባኝ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ ውሳኔ የተሰጠበት ሲሆን፣ ደረጃውን ጠብቆ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቀርቦ ተከሳሾች በተከሰሱበት 1ኛ ክስ ጥፋተኛ ተብለው በአስራ አንድ አመት (11 ዓመት) ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል፡፡

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when West Bellessa Woreda Court posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share