Bahir Dar Customs Branch - ባሕር ዳር ጉምሩክ ቅርንጫፍ

Bahir Dar Customs Branch - ባሕር ዳር ጉምሩክ ቅርንጫፍ year of excellence!

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት ስር የሚገኘው ወረታ ደረቅ ወደብ ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ  ፕሮግራም አካሄደ፡፡ነሀሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ምበኢ...
21/08/2026

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት ስር የሚገኘው ወረታ ደረቅ ወደብ ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሄደ፡፡

ነሀሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የወረታ ደረቅ ወደብ ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ አመራርና ፈፃሚዎች ደረቅ ወደቡ ባዘጋጀው ቦታ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሂደዋል፡፡

"ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!!
ከደንበኞች ትምህርትና ድጋፍ ቡድን
ባህር ዳር

ጉምሩክ ኮሚሽን ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤትን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/BahirDarCustomsBranch
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/BahirDarCustoms
በኢንታግራም፡https://www.instagram.com/invites/contact/?i=1feknwgnp27tr&utm_content=pbktsa4

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት ስር የሚገኘው ጎንደር መቅረጫ ጣቢያ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ  ፕሮግራም አካሄደ፡፡ነሀሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ምበኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚ...
20/08/2026

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት ስር የሚገኘው ጎንደር መቅረጫ ጣቢያ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሄደ፡፡

ነሀሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የጎንደር መቅረጫ ጣቢያ አመራርና ፈፃሚዎች የጎንደር ከተማ አስተዳደር በሰጣቸው ቦታ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት አካሂደዋል፡፡

"ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!!
ከደንበኞች ትምህርትና ድጋፍ ቡድን
ባህር ዳር

ጉምሩክ ኮሚሽን ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤትን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/BahirDarCustomsBranch
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/BahirDarCustoms
በኢንታግራም፡https://www.instagram.com/invites/contact/?i=1feknwgnp27tr&utm_content=pbktsa4

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት የ2019 በጀት  ዓመት ዕቅድ ትውውቅ አካሄደ፡፡ነሐሴ 08/2019 ዓ.ም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ነሐሴ 08/2018ዓ.ም   ባህር ዳር በሚገኘው ዘ...
14/08/2026

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ አካሄደ፡፡

ነሐሴ 08/2019 ዓ.ም

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ነሐሴ 08/2018ዓ.ም ባህር ዳር በሚገኘው ዘመን ኮንስራክሽን ድርጅት የመሰብሰቢያ አዳራሽ የቅ/ጽ/ቤቱ አመራርና ፈፃሚዎች በአካል እንዲሁም የመቆጣጠሪያ እና የመቅረጫ ጣቢያ አመራርና ፈፃሚዎች በዙም በተገኙበት የ2019 በጀት ዓመት የስራ ዕቅድ ትውውቅ ተዳርጓል፡፡

በመድረኩም የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ አለነ መሐሪ ውይይቱን በንግግር ከከፈቱ በኋላ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን ለማሳካት የ2018 በጀት ዓመት ጠንካራ ጎኖችን እንደ መነሻ በመውሰድ በቀጣይ ለዕቅዱ መሳካት ታሳቢ የተደረጉ የማስፈጸሚያ ስልቶችን ማለትም የውስጥ ቅንጅትን ማጠናከር፣ የቡድን መንፈስ መፍጠር፣ የገቢ እቃዎችን ፍሰትን መጨመር፣ የዕዳ ክትትል የዕቃዎች ሽያጭን ማጠናከር፣ የጉምሩክ ኦፕሬሽን ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል የሚሉትንና ሌሎችንም በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

በመጨረሻም የቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ አለነ መሐሪ አፈጻጸማችን በየጊዜው እያደገና እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም ስልጠናዎችን ከዋና መ/ቤትም ይሁን ከቅ/ጽ/ቤት እስኪሰጠን ድረስ ሳንጠብቅ እርስ በርስ የምናደርገው መደጋገፍ ትልቅ ትርጉም ተሰጥቶት ሁሉም ሰራተኛ የስራ ክፍሉ የተቋቋመበትን ዓላማ መሰረት ያደረገ የተዘጋጀ ዕቅድ በቅንነት ተቀብሎ ስራን በወቅቱ በማከናወን ሁሉም ሰራተኛ ካልተገባ ፍርሃት ነጻ ሆኖ የተሰጠንን ዕቅድ እንድናሳካ አደራ በማለት ሃሳብና አስተያየታቸውን በመግለጽ የ2019 በጀት ዓመት የፍስሐና ውጤት ጊዜ እንዲሆንልን በመመኘት ዕቅዱ 3.98 ቢሊዮን ብር መሆኑን ገልፀው ፕሮግራሙን ዘግተዋል፡፡

"ተቋምን በልህቀት ገቢን በስኬት"
ከደንበኞች ትምህርትና ድጋፍ ቡድን
ባህር ዳር

ጉምሩክ ኮሚሽን ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤትን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/BahirDarCustomsBranch
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/BahirDarCustoms
በኢንታግራም፡https://www.instagram.com/invites/contact/?i=1feknwgnp27tr&utm_content=pbktsa4

13/08/2026
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ  ፕሮግራም ተካሄደ፤ሐምሌ  27 ቀን 2018 ዓ.ም በዛሬው  ዕለት በአንድ  ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን ...
03/08/2026

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ተካሄደ፤

ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም

በዛሬው ዕለት በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብር በመላው ኢትዮጵያ እየተካሄደ ይገኛል።

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህርዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራር፣ ሰራተኞችና የአገር መከላከያ አባላት 101ኛ አየር ወለድ ክፍለ ጦር 2ኛ ንስር ሻለቃ በጋራ በመሆን "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል ልዩ ስሙ ቤዛዊት ማርያም በሚባል ቦታ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተከናውኗል፡፡

በዚህ ፕሮግራም የተገኙት የቅርንጫፉ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ አለነ መሐሪ ባለፉት ዓመታት እና ዘንድሮ የሚተከሉ ችግኞችን ከመትከል ባሻገር በየጊዜው አስፈላጊው እንክብካቤ የእኔ ብሎ መንከባከብ እንደሚገባ እና በቀጣይ ችግኞችን በማረምና በመኮትኮት የተተከሉ ችግኞች የፅድቀት መጠን ከፍ በማድረግ ዓለማችንን እየተፈታተነ ላለው የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ የመፍትሔዉ አካል መሆን እንደሚገባ አሳስበዉ በዚህ ችግኝ ተከላ የተሳተፉ አመራር፣ ሰራተኞችና የአገር መከላከያ አባላትን አመስግነዋል፡፡

"ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!!
ከደንበኞች ትምህርትና ድጋፍ ቡድን
ባህር ዳር

ጉምሩክ ኮሚሽን ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤትን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/BahirDarCustomsBranch
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/BahirDarCustoms
በኢንታግራም፡https://www.instagram.com/invites/contact/?i=1feknwgnp27tr&utm_content=pbktsa4

እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!''የባህርዳር ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የዕውቅና ሽልማት ተበረከተለት''ሐምሌ 25/2018 ዓ.ምየኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ባህርዳር  ቅርንጫፍ ጽ/ቤት  በ2...
03/08/2026

እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!

''የባህርዳር ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የዕውቅና ሽልማት ተበረከተለት''

ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ባህርዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የተቋሙን ዕቅድ በብቃት በመፈጸምና የላቀ የስራ አፈጻጸም በማስመዝገቡ በገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ እና በጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) የዕውቅና ሽልማት ተበርክቶለታል።

ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ በበጀት ዓመቱ የገቢ አሰባሰብን በማሳደግ፣ የጉምሩክ አገልግሎትን በማሻሻል፣ ሕገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችንና ኮንትሮባንድን በብቃት በመከላከል፣ እንዲሁም የንግድ ስርዓቱን በማቀላጠፍ የላቀ የስራ ውጤት አስመዝግቧል። ይህ ስኬት በአመራሩ፣ በሰራተኞቹ እና በባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት፣ ቁርጠኝነትና ኃላፊነት የተገኘ ውጤት ነው።

ለዚህ ታላቅ ዕውቅና መሠረት ለሆናችሁ ክቡራን ደንበኞቻችን፣ አመራርና ሠራተኞች፣ እንዲሁም አጋር አካላት "እንኳን ደስ አላችሁ!" እንላለን።

ቅ/ጽ/ቤቱ ወደፊትም ዘመናዊና ቀልጣፋ የጉምሩክ አገልግሎት በመስጠት፣ ሕጋዊ ንግድን በማበረታታት፣ ኮንትሮባንድን በብቃት በመከላከል እና የተሻለ የስራ አፈጻጸም በማስመዝገብ ለኮሚሽኑና ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገት የበለጠ አስተዋፅኦ ለማበርከት ቁርጠኛ መሆናችንን እንገልፃለን።

"ተቋምን በልህቀት ገቢን በስኬት!"
ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!!
ከደንበኞች ትምህርትና ድጋፍ ቡድን
ባህር ዳር
ጉምሩክ ኮሚሽን ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤትን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/BahirDarCustomsBranch
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et

01/08/2026

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bahir Dar Customs Branch - ባሕር ዳር ጉምሩክ ቅርንጫፍ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share