Guagusa Shikudad Prosperity

Guagusa Shikudad Prosperity Political Party
(1)

እንኳን ደስ አላችሁ!​የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር መንገድ፣ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በክልል ደረጃ በተካሄደው የሥራ አፈጻጸም ምዘና 3ኛ ደረጃን በመያዝ  የዕውቅና ...
03/09/2026

እንኳን ደስ አላችሁ!

​የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር መንገድ፣ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በክልል ደረጃ በተካሄደው የሥራ አፈጻጸም ምዘና 3ኛ ደረጃን በመያዝ የዕውቅና ስርቲፊኬት ተሸላሚ ሆኗል።

​ እንኳን ደስ ደስ አላችሁ!

እንኳን ደስ አላችሁ!​የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት በክልል ደረጃ በተካሄደው የሥራ አፈጻጸም ምዘና 3ኛ ደረጃን ...
02/09/2026

እንኳን ደስ አላችሁ!

​የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት በክልል ደረጃ በተካሄደው የሥራ አፈጻጸም ምዘና 3ኛ ደረጃን በመያዝ የዕውቅና ስርቲፊኬት ተሸላሚ ሆኗል።

​ይህ የተገኘው ውጤት ያለፈውን የሥራ አፈጻጸም የሚያረጋግጥ ብቻ ሳይሆን፣ በቀጣይም በፓርቲው መሪነት የበለጠ ለመሥራትና የተሻለ ስኬት ለማስመዝገብ ትልቅ ጉልበትና አቅም የሚፈጥር ነው።

​ለዚህ ስኬት መመዝገብ አስተዋጽዖ ላበረከታችሁ የአመራርና አባላት በሙሉ እንኳን ደስ ደስ አላችሁ!

Awi prosperity party

‎በዛሬው ዕለት በቲሊሊ ከተማ በስፖርት አፍቃሪያ ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የክረምት የስፖርት ስልጠናና ውድድር የፍፃሜ ጨዋታ በስኬት ተጠናቀቀ።‎‎በቲሊሊ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ምክር...
30/08/2026

‎በዛሬው ዕለት በቲሊሊ ከተማ በስፖርት አፍቃሪያ ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የክረምት የስፖርት ስልጠናና ውድድር የፍፃሜ ጨዋታ በስኬት ተጠናቀቀ።

‎በቲሊሊ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ምክር ቤትና በቲሊሊ አስተዳደር ባህል ቱሪዝም ስፖርት ጽህፈት ቤት አዘጋጅነት በአይነቱና በብዛት የመጀመሪያ የሆነው የ2018 /019 የክረምት ስልጠናና ውድድር በሁሉም የዕድሜ ክልል በእግር ኳስ በ60 ቡድኖች፣በአርት ስፖርት በአራት ማዕከላት ሲካሄድ የቆየው ስልጠናና ውድድር በዛሬው ዕለት ተጠናቀቀ።

‎በፕሮግራሙ የአዊ ብሔረሰብ አስተዳድር ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ተወካይና የስፓርት ዘርፍ ቡድን መሪ አቶ ማርልኝ ሁነኛውን ጨምሮ የከተማ አስተዳድሩ የጽህፈት ቤት አመራሮች፣ጥሪ የተደረገላቸው የስፖርቱ ቤተሰቦችና የክብር እንግዶች የከተማው ወጣቶች እንዲሁም የስፖርት አፍቃሪያን ታድመዋል።

‎የአዊ ብሔረሰብ አስተዳድር ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ተወካይና የስፖርት ዘርፍ ቡድን መሪ አቶ ማርልኝ ሁነኛው በቦታው ተገኝተው እንደተናገሩት የቲሊሊ ከተማ አስተዳደር ህዝብ ለስፖርቱ ያለው ፍቅርና ፍላጎት ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ሆኖ አግኝቸዋለሁ ያሉ ሲሆን ይህም በስፖርቱ እየመጣ ያለውን መነቃቃት የሚያሳይ ነው ብለዋል።
‎ስፖርት የማህበረሰቡን በተለይም የወጣቱን የአካል ፣የጤናና የስብዕና ግንባታ ከማሳደግ ባሻገር ፍቅርንና፣ሰላምን፣አንድነትንና መተባባርን ለማምጣት ሚናው የጎላ ነው ፤ይህንም በዛሬው ዕለት ተመልክተናል ሲሉ ተደምጠዋል።

‎የቲሊሊ ከተማ አስተዳድር ተወካይ ምክትል ከንቲባና የከንቲባ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አማረ ካሴ በከተማ አስተዳድሩ የሚታየውን ከፍተኛ የስፖርት እንቅስቃሴና ፍላጎት የበለጠ ለማሳደግ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ አምስቱም ቀበሌዎች የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች እንዲከለሉና ያሉትም ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ይደረጋል ነው ያሉት።
‎ሰፖርት ከፍተኛ በጀት የሚጠይቅ እንደመሆኑ መጠን በቀጣይ የ2019 በጀት ዓመት ለሚከናወኑ የበጋና የክረምት የስልጠናና ውድድሮች ተገቢ የሆነ በጀት እንዲመደብ እናደርጋለን፤በዘርፉም የተሻለ ውጤት እንዲመጣ ከተቋሙ ጋር አብረን እንሰራለን ብለዋል።
‎አክለውም የሰው ሀይልና በጀት ለተቋሙ እንዲሟላ በቁርጠኝነት እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።

‎የቲሊሊ ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ምስጋናው ያየህ ይህ የክረምት ስልጠናና ውድድር ባለፉት ሁለት ዓመታት ተቀዛቅዞ የነበረውን የስፖርት እንቅስቃሴ ለመመለስና ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ያለመ እንደሆነ አስታውቀዋል።

‎ ስፖርት ተግባቦትን፣ጤናን፣መተማመንና አንድነትን እንዲሁም ሰላምን ያጠናክራል።በቀጣይም የባህል ስፖርቶችን በመጨመር የበለጠ እንደሚሰሩም አስታውቀዋል።

‎በሌላ መልኩም ለስፖርቱ ዕድገት አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትን በተለይም ነጋዴውን ማህበረሰብና የአካባቢውን ነዋሪ አመስግነዋል።
‎የከተማ አስተዳድሩ ባህል ቱሪዝምና ጽህፈት ቤት የስፖርት ዘርፍ ተተኪ ቡድን መሪና ባለሙያ አቶ በእውቀት መኩሪያ የዘንድሮው የክረምት የስፖርት ስልጠናና ውድድር በዓይነቱና በብዛቱ ለየት ያለና የመጀመሪያ ነው ያሉ ሲሆን በቀጣይ የተረሱ የቅርጫት ኳስ ፣የእጅ ኳስ ፣ቴብል ቴኒስና ሌሎችም ባህላዊ የስፖርት አይነቶች በ2019 በጀት ዓመት አካቶ ለመስራት እንዳሰቡ ተናግረዋል።
‎ አክለውም ስፖርት ዘርፍ በጀት ፈላጊና ተጠቃሚ በመሆኑም ከተማ አስተዳድሩ ለዘርፉ የተሻለ በጀትና የሰው ሀይል እንዲያሟላላቸውም ጠይቀዋል።

በጓጉሳ ሸኩዳድ ወረዳ በጅባይታ ቀበሌ የሰላም፥ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በተመለከተ ህዝባዊ ዉይይት ተካሄደ።በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ በጀባይታ ቀበሌ በወ...
30/08/2026

በጓጉሳ ሸኩዳድ ወረዳ በጅባይታ ቀበሌ የሰላም፥ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በተመለከተ ህዝባዊ ዉይይት ተካሄደ።

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ በጀባይታ ቀበሌ በወቅታዊ የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳድር ጉዳዮች ዙሪያ ህዝባዊ ውይይት ማካሄድ ተችሏል።

በውይይቱ የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጅት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ቢተዉ አየሁእንዲሁም የወረዳ አመራሮች፤ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ተገኝተዋል።

29/08/2026
በአዊ ብሔ/አስ የቲሊሊ ከተ/አስ እና የጓ/ሽ/ወረዳ በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ  ከባጃጅ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።ቲሊሊ:- ነሀሴ 21/2018ዓ.ም    " ...
27/08/2026

በአዊ ብሔ/አስ የቲሊሊ ከተ/አስ እና የጓ/ሽ/ወረዳ በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከባጃጅ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።

ቲሊሊ:- ነሀሴ 21/2018ዓ.ም
" በሚል መሪ ሀሳብ ከቲሊሊ ከተማ እና ጓ/ሽ/ወ ከባጃጅ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች ጋር አጋር አካላት በተገኙበት የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

​በውይይቱ ላይ የፅንፈኝነትንና የጥፋት ኃይሎችን እኩይ አላማ በማክሸፍ የሀገርን ብሎም የብሄረሰብ አስተዳደሩን ሰላም መጠበቅ እንደሚገባ ተገልጿል።

የሀገርን ሰላምና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸውም ተጠቁሟል።
~•~•~•~•
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም!!

‎‎" #የውጫዊ የወረራ ስጋትና  #የውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማት እናረጋግጣለን " በሚል መሪ ቃል በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ብልፅግና ፓ...
25/08/2026

‎‎" #የውጫዊ የወረራ ስጋትና #የውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማት እናረጋግጣለን " በሚል መሪ ቃል በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ከወረዳው #ከሐይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ።

መድረኩን የመሩት የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ብልፅግና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሪት አሳቤ አዳነ እና የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አለሙ ሲሆኑ #የሐይማኖት አባቶችና የሀገር #ሽማግሌዎች ለዘላቂ ሰላም መስፈንና ለልማት ስራዎች መፋጠን የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተመልክቷል።

‎‎" #የውጫዊ የወረራ ስጋትና  #የውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማት እናረጋግጣለን " በሚል መሪ ቃል በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ብልፅግና ፓ...
23/08/2026

‎‎" #የውጫዊ የወረራ ስጋትና #የውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማት እናረጋግጣለን " በሚል መሪ ቃል በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ከወረዳው #የነጋዴ ማህበረሰብ ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ።

መድረኩን የመሩት የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አለሙ ሲሆኑ የንግዱ ማህበረሰብ የውስጥ አንድነት እንዲጠናከረና #የውጭ ወራሪዎችን በጋራ ለመመከት በአንድነት መቆም እንደሚጠበቅ በአፅንኦት ተናግረዋል።

"ምንጊዜም በመሣሪያ ያሸነፈ ኃይል የለም" ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያበኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አማካኝነት ባለፉት ሳምንታት ሲካሄድ የቆየው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የመዝጊያ መርሐ ግብር...
22/08/2026

"ምንጊዜም በመሣሪያ ያሸነፈ ኃይል የለም" ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ

በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አማካኝነት ባለፉት ሳምንታት ሲካሄድ የቆየው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የመዝጊያ መርሐ ግብር ዛሬ እየተካሄደ ነው።

በመርሐ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ የሀገራዊ ምክክሩ በከፍተኛ ክርክር፣ ውይይት እና በጠንካራ የእርስ በርስ ግንኙነት ሲካሄድ ቆይቷል ብለዋል።

በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በምክክር ሂደት 4 ሺህ ሰዎችን ማሳተፍ እንደተቻለም ገልጸዋል።

ምክክር ይጀመራል እንጂ በማግስቱ አያልቅም ነው ያሉት ዋና ኮሚሽነሩ። ተመካካሪዎች ብዙ ውሳኔዎች ማሳለፋቸውንም አንስተዋል።

"በመሣሪያ ምን ጊዜም ያሸነፈ ኃይል የለም ነው ያሉት። ማሸነፍ የሚቻለው በጋራ ውይይት እንደኾነም ገልጸዋል።

#አሚኮ #ኢትዮጵያ🇪🇹

" " የአዊ ወጣቶች ተመሙሀገር ጥሪ ስታደርግ ወጣቱ ትውልድ ከፊት ይሰለፋል። የአዊ ወጣቶች  የሀገራችን ህልውና በፅናት የማቆም ታሪካዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ዝግጁ ሁነዋል።
21/08/2026

" " የአዊ ወጣቶች ተመሙ

ሀገር ጥሪ ስታደርግ ወጣቱ ትውልድ ከፊት ይሰለፋል። የአዊ ወጣቶች የሀገራችን ህልውና በፅናት የማቆም ታሪካዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ዝግጁ ሁነዋል።

Address

Bahir Dar_Addis Ababa
Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Guagusa Shikudad Prosperity posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Guagusa Shikudad Prosperity:

Shortcuts

Share