Sedie Muja Woreda Revenue Office 2014

Sedie Muja Woreda Revenue Office 2014 Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Sedie Muja Woreda Revenue Office 2014, Government Organization, Bahir Dar.

16/03/2022

በሰዴ ሙጃ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት

በግብር ትምህት ኮሙኑኬሽን

ዋና የስራ ሂደት

ለግብር ከፋዮች እና ለተለያዩ

የማህበረሰብ ክፍሎች የተዘጋጀ
የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ
መጋቢት/2014 ዓ.ም
ሮቢት

የገቢ ሰንጠረዥ
አምስት አይነት የገቢ ሰንጠረዦች አሉ፡፡ እነሱም፡-
1. ሰንጠረዥ ”ሀ” ከመቅጠር የሚገኝ ገቢ (Personal Income Tax)
 ከመንግስት መስሪያቤቶች እና ከግል ድርጅቶች ተቀጥረው ከሚሰሩ የሚቆረጥ ግብር ነው፡፡
 ከ600 ብር በታች የወር ደመዎዝ ያላቸውን አይጨምርም፡፡
1.ከመ ቅጠር የሚገኝ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ ምጣኔዎች
የወር ደመወዝ ገቢ የግብር መክፈያ ምጣኔ ተቀናሽ
ብር
ከብር እስከ ብር
0 600 0% 0
601 1,650 10% 60
1,651 3,200 15% 142.50
3,201 5,250 20% 302.50
5,251 7,800 25% 565
7,801
10,900 30% 955
ከ10,900 በላይ 35% 1500
ለምሳሌ አቶ ሮቤል የሰዴ ሙጃ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ሰራተኛ ሲሆን በወር 9014 ብር ይከፈላቸዋል፡፡ አቶ ሮቤል በወር እና በዓመት ምን ያህል ብር ይከፈላሉ፡፡
የተሰጠ
ጠቅላላ የወር ደመዎዝ =9014
የግብር መክፈያ ምጣኔ =30%
ተቀናሽ ብር=955
የተጠየቀ
በየወሩ የሚከፍለው ግብር ስንት ነው?
ቤዓመቱ የሚከፍለው ግብር ስንት ነው?
መፍትሔ/አሰራር
የሚከፈል ግብር ጠቅላላ ደመወዝ= (ጠቅላላ የወር ደመዎዝ×የግብር መክፈያ ምጣኔ)- ተቀናሽ ብር
 የአቶ ሮቤል የወር ደመወዝ የስራ ግብር ስኬል ከወር ደመወዝ 7,801 እሰከ 10,900 ብር መካከል ስለሚገኝ ምጣኔዉ 30% ነዉ፡፡
 አቶ ሮቤል የሚከፍሉት ግብር በወር =(9014×30%)-955 = 2704.2 ብር በወር ይከፍላሉ፡፡
 አቶ ሮቤል የሚከፍሉት ግብር በዓመት =2704.2 ×12 = 32,450.4 ብር በዓመት ይከፍላሉ፡፡
2. ሰንጠረዥ “ለ” ከቤት ኪራይ የሚገኝ ገቢ (Rental Income Tax)
• የመኖሪያ እና
• የድርጅት ቤት
ከኪራይ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ ምጣኔዎች
የዓመት ገቢ የግብር መክፈያ ምጣኔ ተቀናሽ
ብር
ከብር እስከ ብር
0 7,200 0% 0
7,201 19,800 10% 720
19,801 38,400 15% 1,710
38,401 63,000 20% 3,630
63,001 93,600 25% 6,780
93,601
130,800 30% 11,460
ከ130,800 በላይ 35% 18,000
ለምሳሌ፡- አንድ የመኖሪያ ህንፃ የሚከራይ ግብር ከፋይ በየወሩ ብር 200,000.00 ቢያከራይ ዓመታዊ ገቢው ብር 200,000.00×12=ብር 240,000.00
ግብር የሚከፈልበት ገቢ ብር 240,000.00×50%=ብር 120,000.00
 ዓመታዊ ግብር ብር 120,000.00×30%=ብር 36,000.00
36,000.00-11,460.00=24,540
 ዓመታዊ ግብር ብር=24,540
3. ሰንጠረዥ “ሐ” ከንግድ ትረፍ የሚገኝ ገቢ (Business Income Tax)
 ከመቀጠር የሚገኝ ገቢን አይጨምርም፡፡
 ዓመታዊ ገቢያቸው ከ7200 ብር እና በታች የሆነን አይጨምርም፡፡
 ድርጅት ላይ ተፈፃሚ የሚሆነው የንግድ ስራ ገቢ የግብር ምጣኔ 30% ነው፡፡



ከንግድ ስራ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ ምጣኔዎች
የዓመት ገቢ የግብር መክፈያ ምጣኔ ተቀናሽ
ብር
ከብር እስከ ብር
0 7,200 0% 0
7,201 19,800 10% 720
19,801 38,400 15% 1,710
38,401 63,000 20% 3,630
63,001 93,600 25% 6,780
93,601
130,800 30% 11,460
ከ130,800 በላይ 35% 18,000
ለምሳሌ፡- XYZ ተቋራጪ ድርጅት በዓመት የተጣራ ትርፍ 280,000 ብር ቢያገኝ ሚከፍለው ግብር 280,000×30%=84,000
4. ሰንጠረዥ “መ” ሌሎች ገቢዎች (Other Income Tax)
o ሮያሊቲ
o ትርፍ ድርሻ ክፍፍል
o የስራ አመራር ክፍያ
o የቴክኒክ አገልግሎት ክፍያ
o ንፋስ አመጣሽ ትርፍ
o ያልተከፋፈለ ትርፍ
o ወለድ ወዘተ…..ናቸው፡፡
5. ሰንጠረዥ “ሠ” ከገቢ ግብር ነጻ የሆኑ ገቢዎች (Free From Income Tax)
• የውሎ አበል
• የወር ደመወዛቸው ከ600 ብር በታች የሆነ
• የማበረታቻ ሽልማት
• የአየር ጸባይ አበል እሰከ 30% የሚከፈል
• ስጦታ የመሳሰሉት ናቸው፡፡

15/02/2022

ከሀምሌ 01/11/2013 ዓ.ም እስከ ጥር 30/05/2014 ዓ.ም የተከናወኑ ዋናዋና ተግባራት
1. ከግብር ትምህርት ኮምኒኬሽን አኳያ
 ለግብር ከፋይ ነጋዴዎች ቤት ለቤት/በብሎክ ግንዛቤ ተፈጥሯል፡፡
 የደረጃ “ሐ” ነጋዴዎች ግብራቸዉን በወቅቱ እንዲከፍሉ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ ተሰርቷል፡፡
 ለግብር ከፋዮች እና ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ በፈስቡክ ፔጅ መሰረት መላክ ተችሏል፡፡
2. ከደንኞች አገልግሎት አኳያ
 ለ951 ነጋዴዎች የእድሳት ደብዳቤ ተሰጥቷል፡፡
 ለ69 ነጋዴዎች የጣት አሻራ ፎርም ተሞልቶ ተሰጥቷል፡፡
 ለ16 ደረጃ “ሀ “እና “ለ” ነጋዴዎች ደረሰኝ ህትመት እንዲያሳትሙ ተደርጓል፡፡
 ለ01 ነጋዴዎች ንግዳቸዉን እንዲቀይሩ ደብዳቤ ተሰጥቷል፡፡
 ለ10 ነጋዴዎች የመዝጊያ ክሊራንስ ተሰጥቷቸዋል፡፡
3. ከገቢ አሰባሰብ አኳያ
ጥረት በሚጠይቁ ገቢዎች ላይ የተከናወኑ ተግባራት
በወረዳዉ ዉስጥ ካሉ የመንግስት መ/ቤቶች ሰራተኞች በበጀት ዓመቱ ሊሰበሰብ የታቀደ ብር 19,738,521.00 ሲሆን እስከዚህ ወር የተሰበሰበ ብር 11,185,598.38 በማከናወን የእቅዱን 56.67% መፈፀም ተችሏል፡፡
በወረዳዉ ዉስጥ ካሉ 7 የግል ድርጅቶች በበጀት ዓመቱ ሊሰበሰብ የታቀደ ብር 4,861,085.00 ሲሆን እስከዚህ ወር የተሰበሰበ ብር 2,572,059.69 በማከናወን የእቅዱን 52.91% መፈፀም ተችሏል፡፡
ከአከራይ ተከራይ ገቢ በበጀት ዓመቱ ሊሰበሰብ የታቀደ ብር 28,747.00 ሲሆን እስከዚህ ወር የተሰበሰበ ብር 28,045.00 በማከናወን የእቅዱን 97.56% መፈፀም ተችሏል፡፡
ከእርሻ ስራ ገቢ ግብር በበጀት ዓመቱ ሊሰበሰብ የታቀደ ብር 666,667.00 ሲሆን እስከዚህ ወር የተሰበሰበ ብር 283,367.00 በማከናወን የእቅዱን 42.51% መፈፀም ተችሏል፡፡
ከገጠር መሬት መጠቀሚያ ክፍያ በበጀት ዓመቱ ሊሰበሰብ የታቀደ ብር 333,333.00 ሲሆን እስከዚህ ወር የተሰበሰበ ብር 141,508.00 በማከናወን የእቅዱን 42.45% መፈፀም ተችሏል፡፡የቲኦቲ አሰባሰብ በተመለከተ የታቀደ 1434993 ሲሆን የተሰበሰበ ገቢ 921264.18 አፈጻጸሙ 64.2% ነዉ፡፡
ከሮያሊቲ ገቢ ግብር በበጀት ዓመቱ ሊሰበሰብ የታቀደ ብር 97,816.00 ሲሆን እስከዚህ ወር የተሰበሰበ ብር 25,785.00 በማከናወን የእቅዱን 26.36% መፈፀም ተችሏል፡፡የቲኦቲ አሰባሰብ በተመለከተ የታቀደ 1434993 ሲሆን የተሰበሰበ ገቢ 921264.18 አፈጻጸሙ 64.2% ነዉ፡፡
ከተጨማሪ እሴት ታክስ በበጀት ዓመቱ ሊሰበሰብ የታቀደ ብር 438,924.00 ሲሆን እስከዚህ ወር የተሰበሰበ ብር 30,086.16 በማከናወን የእቅዱን 6.85% መፈፀም ተችሏል፡፡
ከተርን ኦቨር ታክስ በበጀት ዓመቱ ሊሰበሰብ የታቀደ ብር 1,441,000 ሲሆን እስከዚህ ወር የተሰበሰበ ብር 739,714.56 በማከናወን የእቅዱን 51.33% መፈፀም ተችሏል፡፡
ከገጠር መሬት መጠቀሚያ ክፍያ በበጀት ዓመቱ ሊሰበሰብ የታቀደ ብር 333,333.00 ሲሆን እስከዚህ ወር የተሰበሰበ ብር 141,508.00 በማከናወን የእቅዱን 42.45% መፈፀም ተችሏል፡፡

ተ/ቁ የተሰበሰበ ገቢ በታከስ አይነት የዓመቱ ዕቅድ እስካሁን የተሰበሰበ አፈጻጸም ምርመራ
1 ቀጥታ ታከስ 28,152,995.00 16,985,071.78 60.33%
2 ቀጥታ ያልሆነ ታክስ 2,584,924.00 1,054,668.36 40.80%
3 ታክስ ያልሆ ገቢዎች 2,471,209.00 349,483.29 14.14%
መደበኛ ገቢ 33,209,128.00 18.389,223.43 55.37%
ጠቅላላ ድምር 33,209,128.00 18.389,223.43 55.37%
ጠቅላላ ለወረዳዉ የታቀደ መደበኛ ገቢ 33,209,128.00 ሲሆን እስካሁን የተሰበሰበ ጠቅላላ መደበኛ ገቢ ብር 18.389,223.43 ሲሆን 55.37% መድረስ ተችሏል፡፡

09/02/2022

በሰዴ ሙጃ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት
በግብር ትምህርት ኮምኒኬሽን ዋና የስራሂደት

ለግብር ከፋዮች እና ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች
የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ
ሰነድ
የካቲት/2014 ዓ.ም
ሮቢት



1. የግብር ከፋይ ደረጃዎች
የግብር ከፋይ ደረጃዎች በ3 ይከፈላሉ ፡፡ እነሱም ደረጃ “ሀ”፣ ደረጃ “ለ”፣ደረጃ “ሐ” ናቸዉ፡፡
ሀ. ደረጃ “ሀ” ግብር ከፋዮች
 ድርጅት
 ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢያቸዉ ከ1000,000 ብር በላይ የሆነ
 ሂሳብ መዝገብ የማቅረብ ግዴታ ያለባቸዉ ግብር ከፋዮች ናቸው፡፡
 ሪፖርት የማድረግ ግዴታ ያለባቸዉ ግብር ከፋዮች ናቸው፡፡
 ከፍተኛ ግብር ከፋይ በመባል ይታወቃል፡፡
 ግብራቸዉን ከሃምሌ1-ጥቅምት 30 የመክፈል ግዴታ ያለባቸዉ ግብር ከፋዮች ናቸው፡፡
 የድርጅት ላይ ተፈጻሚ የሚሆነዉን የንግድ ስራ ገቢ ግብር ተፈጻሚ የሚሆነዉ 30% ነዉ፡፡
 ግብር የሚከፈለዉ ከተጣራ ትርፍ ላይ ነዉ፡፡
ለ. ደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች
 ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢያቸዉ ከ500,000-1000,000 የሆነ
 ድርጅቶችን አይጨምርም፡፡
 ሂሳብ መዝገብ የማቅረብ ግዴታ ያለባቸዉ ግብር ከፋዮች ናቸው፡፡
 ደረሰኝ የመጠቀም ግዴታ ያለባቸዉ ግብር ከፋዮች ናቸው፡፡
 ግብር የሚከፍሉት ከሃምሌ1- ጳጉሚት 5/6 የመክፈል ግዴታ ያለባቸዉ ግብር ከፋዮች ናቸው፡፡
 በየሩብ አመቱ ሪፖርት ለገቢ ተቋሙ የማሳወቅ ግዴታ ያለባቸዉ ግብር ከፋዮች ናቸው፡፡
 መካከለኛ ግብር ከፋዮች በመባል ይታወቃሉ፡፡
ሐ. ደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች
 እስከ 500,000 ብር ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢ ያለባቸዉ ግብር ከፋዮች ናቸው፡፡
 ድርጅቶችን አይጨምርም፡፡
 ሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ የለባቸዉም፤ነገር ግን በፍቃደኝነት ሂሳብ መዝገብ መያዝ ይችላሉ፡፡
 ደረሰኝ የማሳተም ግዴታ የሌለባቸው ግብር ከፋዮች ናቸው፡፡፡፡
 ግብራቸዉን ከሃምሌ1-ሃምሌ 30 የመክፈል ግዴታ ያለባቸዉ ግብር ከፋዮች ናቸው፡፡
 ዝቅተኛ ግብር ከፋዮች በመባል ይታወቃሉ፡፡

2. የገቢ ሰንጠረዥ
አምስት አይነት የገቢ ሰንጠረዦች አሉ፡፡ እነሱም
1. ሰንጠረዥ ”ሀ” ከመቅጠር የሚገኝ ገቢ (Personal Income Tax)
 ከመንግስት መስሪያቤቶች እና ከግል ድርጅቶች ተቀጥረው ከሚሰሩ የሚቆረጥ ግብር ነው፡፡
 ከ600 ብር በታች የወር ደመዎዝ ያላቸውን አይጨምርም፡፡
1.ከመ ቅጠር የሚገኝ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ ምጣኔዎች
የወር ደመወዝ ገቢ የግብር መክፈያ ምጣኔ ተቀናሽ
ብር
ከብር እስከ ብር
0 600 0% 0
601 1,650 10% 60
1,651 3,200 15% 142.50
3,201 5,250 20% 302.50
5,251 7,800 25% 565
7,801
10,900 30% 955
ከ10,900 በላይ 35% 1500
ለምሳሌ አቶ ሮቤል የሰዴ ሙጃ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ሰራተኛ ሲሆን በወር 9014 ብር ይከፈላቸዋል፡፡ አቶ ሮቤል በወር እና በዓመት ምን ያህል ብር ይከፈላሉ፡፡
የተሰጠ
ጠቅላላ የወር ደመዎዝ =9014
የግብር መክፈያ ምጣኔ =30%
ተቀናሽ ብር=955
የተጠየቀ
በየወሩ የሚከፍለው ግብር ስንት ነው?
ቤዓመቱ የሚከፍለው ግብር ስንት ነው?

መፍትሔ/አሰራር
የሚከፈል ግብር ጠቅላላ ደመወዝ= (ጠቅላላ የወር ደመዎዝ×የግብር መክፈያ ምጣኔ)- ተቀናሽ ብር
 የአቶ ሮቤል የወር ደመወዝ የስራ ግብር ስኬል ከወር ደመወዝ 7,801 እሰከ 10,900 ብር መካከል ስለሚገኝ ምጣኔዉ 30% ነዉ፡፡
 አቶ ሮቤል የሚከፍሉት ግብር በወር =(9014×30%)-955 = 2704.2 ብር በወር ይከፍላሉ፡፡
 አቶ ሮቤል የሚከፍሉት ግብር በዓመት =2704.2 ×12 = 32,450.4 ብር በዓመት ይከፍላሉ፡፡
2. ሰንጠረዥ “ለ” ከቤት ኪራይ የሚገኝ ገቢ (Rental Income Tax)
• የመኖሪያ እና
• የድርጅት ቤት
ከኪራይ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ ምጣኔዎች
የዓመት ገቢ የግብር መክፈያ ምጣኔ ተቀናሽ
ብር
ከብር እስከ ብር
0 7,200 0% 0
7,201 19,800 10% 720
19,801 38,400 15% 1,710
38,401 63,000 20% 3,630
63,001 93,600 25% 6,780
93,601
130,800 30% 11,460
ከ130,800 በላይ 35% 18,000
ለምሳሌ፡- አንድ የመኖሪያ ህንፃ የሚከራይ ግብር ከፋይ በየወሩ ብር 200,000.00 ቢያከራይ ዓመታዊ ገቢው ብር 200,000.00×12=ብር 240,000.00
ግብር የሚከፈልበት ገቢ ብር 240,000.00×50%=ብር 120,000.00
 ዓመታዊ ግብር ብር 120,000.00×30%=ብር 36,000.00
36,000.00-11,460.00=24,540
 ዓመታዊ ግብር ብር=24,540
3. ሰንጠረዥ “ሐ” ከንግድ ትረፍ የሚገኝ ገቢ (Business Income Tax
 ከመቀጠር የሚገኝ ገቢን አይጨምርም፡፡
 ዓመታዊ ገቢያቸው ከ7200 ብር እና በታች የሆነን አይጨምርም፡፡
 ድርጅት ላይ ተፈፃሚ የሚሆነው የንግድ ስራ ገቢ የግብር ምጣኔ 30% ነው፡፡
ከንግድ ስራ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ ምጣኔዎች
የዓመት ገቢ የግብር መክፈያ ምጣኔ ተቀናሽ
ብር
ከብር እስከ ብር
0 7,200 0% 0
7,201 19,800 10% 720
19,801 38,400 15% 1,710
38,401 63,000 20% 3,630
63,001 93,600 25% 6,780
93,601
130,800 30% 11,460
ከ130,800 በላይ 35% 18,000
ለምሳሌ፡- XYZ ተቋራጪ ድርጅት በዓመት የተጣራ ትርፍ 280,000 ብር ቢያገኝ ሚከፍለው ግብር 280,000×30%=84,000
4. ሰንጠረዥ “መ” ሌሎች ገቢዎች (Other Income Tax)
o ሮያሊቲ
o ወለድ ወዘተ…..
5. ሰንጠረዥ “ሠ” ከገቢ ግብር ነጻ የሆኑ ገቢዎች (Free From Income Tax)
• የውሎ አበል
• የወር ደመወዛቸው ከ600 ብር በታች የሆነ
• የማበረታቻ ሽልማት
• ስጦታ

20/01/2022

በሰዴ ሙጃ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በግብር ትምህት ኮሙኑኬሽን ዋና የስራ ሂደት

ለግብር ከፋዮች እና ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ
ጥር/2014 ዓ.ም
ሮቢ

1. የመንግስት የገቢ ምጮች
የመንግስት የገቢ ምጮች ከምንላቸው መካከል የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
እርዳታ
ብድር
ከሀገር ውስጥ መንግስት ግምጃ ቤት
የመንግስት ዋነኛው እና አስተማማኙ የመንግስት የገቢ ምንጭ ከሀገር ውስጥ የሚሰበሰበው ገቢ
ነው፡፡
1.1. የመንግስት ግምጃ ቤት የገቢ ምንጭ
የመንግስት ግምጃ ቤት የገቢ ምንጭ በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላሉ፡፡ እነርሱም፡-
1. ታክስ ነክ ገቢዎች/Taxable Income/
2. ታክስ ነክ ያልሆኑ ገቢዎች /Non Taxable Income/
1. ታክስ ነክ ገቢዎች/Taxable Income
ታክስ ነክ ገቢዎች በሁለት ይከፈላሉ፡፡
እነሱም፡- ሀ. ቀጥታ ታክስ /Direct tax/
ለ. ቀጥታ ያልሆነ ታክስ/Indirect tax/

ሀ. ቀጥታ ታክስ /Direct tax/
ቀጥታ ታክስ ማንኛዉም ሰዉ በሚያገኘዉ ገቢ ወይም ከያዘዉ ሀብት ጋር በተያያዘ በቀጥታ ባገኘዉ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ላይ በታክስ ሥርዓቱ በተደነገገዉ ምጣኔ መሠረት የሚጣል የታክስ ዓይነት ነው፡፡ የታክሱ ቀጥተኛ ከፋይ ገቢዉን ወይም ጥቅሙን ያገኘዉ ሰው/ድርጅት በመሆኑ ግዴታውን ወደ ሌላዉ አካል በፍፁም ማሸጋገር አይችልም።
በቀጥታ ታክስ ስር ከሚመደቡት የመንግስት የገቢ ግብር ዓይነቶች ውስጥ
 ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ (ሠንጠረዥ “ሀ”)
 ቤትን ከማከራየት የሚገኝ ገቢ (ሠንጠረዥ “ለ”)
 ከንግድ ትርፍ የሚገኝ ገቢ(ሠንጠረዥ “ሐ”)
 ሌሎች ገቢዎቸ የሚገኝ ገቢ(ሠንጠረዥ “መ”) ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
ለ. ቀጥታ ያልሆነ ታክስ/Indirect tax/
ቀጥታ ያልሆነ ታክስ ግብር ከፋዩ በታክስ ህጉ መሠረት ከመንግስት ባገኘው ውክልና በሚሸጠዉ ዕቃ / በሚሰጠው/ አገልግሎት ላይ ታክሱን በማሰብ /በመጨመር/ የሚሰበሰበዉና ለመንግስት ገቢ የሚያደርገዉ የታክስ ዓይነት ነዉ፡፡
ቀጥታ ያልሆነ ታክስ በቀጥታ የሻጩን/ የአገልግሎት ሰጪውን ጥቅም የማይነካና በቀላሉ ወደ ተጠቃሚዎች የሚሸጋገር ወይም የሚያርፍ በመሆኑ ትክክለኛው የታክሱ ከፋዮች ሸማቾች ወይም ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡

በሀገራችን በሥራ ላይ የዋሉ ቀጥተኛ ያልሆኑ ታክሶች /Indirect tax/
1. ተጨማሪ እሴት ታክስ (Value Added Tax)
2. ተርን ኦቨር ታክስ (Turn Over Tax)
3. ኤክሳይዝ ታክስ (Excise Tax)
4. የጉምሩክ ቀረጥ (Customs Duty)
5. የቴምብር ቀረጥ (Stamp Duty) እና
6. ሱር ታክስ (Sur Tax) ሲሆኑ በወረዳችን በአብዛኛው አገልግሎት ላይ እየዋሉ ያሉ ታክሶች የተጨማሪ እሴት ታክስና የተርን ኦቨር ታክስ ናቸው፡፡
1. የተጨማሪ እሴት ታከስ /Value Added Tax (VAT)/ ምንነት
 የተጨማሪ እሴት ታክስ (value added tax ወይንም በምህጻረ ቃሉ VAT) መሠረቱ ሰፊ የሆነ በፍጆታ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ወይም በተጠቃሚው ወጪ ላይ ተመስርቶ የሚጣል ቀጥተኛ ያልሆነ የታክስ አይነት ነው፡፡
 ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚሰበሰበው በምርት ማምረት፣ ማከፋፈልና በስርጭት ሂደት ውስጥ በሚፈጠረው እሴት እና በአገልግሎት ወቅት በተጨመረው እሴት ላይ ሆኖ ምርቱ ወደ ሀገር ውስጥ ሲገባ ወይም ማንኛውም ታክሱ የሚከፈልበት ዕቃ እና አገልግሎት ግብይት ሲፈጸም ነው።
የተጨማሪ እሴት ታክስ መርሆዎች
የተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከተላቸው መርሆዎች ሁለት ናቸው፡፡ እነርሱም፡-
ሀ. የመነሻ እና
ለ. መድረሻን መሠረት ተደርጎ የሚጣል ታክስ ነው።
ሀ. የመነሻ /Origin Principle/ የሚባለው መርህ ትኩረት የሚያደርገው ከሀገር ውስጥ ወደ ውጭ የሚላኩ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ላይ ነው፡፡
የተጨማሪ እሴት ታክስ ሸክሙ የሚወድቅበት ሰው የውጭ ሀገር ዕቃውን ወይም አገልግሎቱን የሚገዛው ሰው ይሆናል። ይህ መርህ ተፈፃሚ የሚሆነው ከፍተኛ ኤክስፖርት አቅም ባላቸው ሀገሮች ይሆናል።
ለ. የመድረሻ /Destination Principle/ ትኩረት የሚያደርገው በሀገር ውስጥ በሚገቡ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ላይ ነው፡፡
የተጨማሪ እሴት ታክስ ሸክም የሚያርፈው ዕቃና አገልግሎት ወደ አገር ውስጥ በሚያስገባው ሰው ላይ ይሆናል። ይህ መርህ የታክስ ወደ አገር ውስጥ በሚያገቡ እና የታክስ መሠረታቸው በአገር ውስጥ ለማስፋት የሚሹ አገሮች የሚጠቀሙበት አሠራር ነው።

በአለም ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ በመጀመሪያ በፈረንሳይ አገር በ1948 ዓ.ም በስራ ላይ የዋለ ሲሆን ሌሎችም አገሮች የገቢ ማመንጨት አቅም እና የታክስ አስተዳደሩን ሚዛናዊነት በማዬት 150 አገሮች በላይ ስራ ላይ አውለውታል።
ለምሳሌ፡- ኬንያ 16% በ1990፣
ደቡብ አፍሪካ 14% 1991፣
ናይጀሪያ 5% በ1994፣
አልጀሪያ 17%፣ ተግባራዊ አድርገውታል፡፡
በኢትዮጵያ ከታህሳስ 23/1995 ጀምሮ ስራ ላይ የዋለ የታክስ ዓይነት ነው፡፡
2. ተርን ኦቨር ታክስ (Turn Over Tax) ምንነት
የተርን ኦቨር ታክስ (Turn Over Tax ወይንም በምህጻረ ቃሉ TOT) በአገር ውስጥ በሚከናወን የዕቃ ወይም የአገልግሎት ሽያጭ ወቅት የአቅርቦት ሰንሰለቱን ተከትሎ በየደረጃው የሚጣል ቀጥተኛ ያልሆነ የታክስ ዓይነት ነው።
የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የተርን ኦቨር ታክስ ተመሳሳይነት
 የተጨማሪ እሴት ታክስም ሆነ የተርን ኦቨር ታክስ በቀጥታ ከግብር/ ታክስ ከፋዩ ካዝና / ቋት ወይም ሰርቶ ካገኘዉ ገቢ የሚከፈሉ ሳይሆን በመንግስት ዉክልና በተሰጠዉ መሠረት ታክስ ከፋዮች ከተጠቃሚዉ ህብረተሰብ የሚሰበሰቡ በመሆናቸዉ ቀጥተኛ ያልሆኑ ታክሶች ከሚባሉት ይመደባሉ። ከዚህም ባህሪያቸዉ ማረፊያ ቀያሪነት(shift) የማድረግ ባህሪ ይታይባቸዋል።
 ሁለቱም የታክስ አይነቶች በተጠቃሚዉ የፍጆታ ወጪ ላይ ተመስርተዉ የሚጣሉ የታክስ ዓይነቶች ናቸዉ። ይህም ባህሪያቸዉ የሽያጭ ታክስን ተክተዉ ከመምጣታቸዉ ጋር የሚመነጭ ነዉ።
 ሁለቱም የታክስ ዓይነቶች በመተካካት ወይንም አንዱ በሌለበት ሌላኛዉ ከመምጣቱ ጋር ተቆራኝተዉ በመሠረታዊ ፍላጎትነት ከሚፈረጁ ግብይቶች ላይ ባለመጣላቸዉም (ለህብረተሰቡ መሠረታዊ የሚባሉትን ግብይቶች ከታክሱ ነጻ ናቸዉ) ይመሳሰላሉ።
 ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ሆነ ግብይት ከተርን ኦቨር ታክስም በተመሳሳይ መንገድ ነጻ ሆኖ ተደንግጎ ይገኛል። መሰረታዊ ፍላጎታችንን ከታክሱ ነጻ በማድረግ የዋጋ ተመጣጣኝነትን ከማረጋገጥ ባለፈ የሁለቱም ታክሶች በተመሳሳይ ግብይቶች ላይ ያለመጣል ለታክስ አስተዳደሩ አመቺነትም ጉልህ ሚና አለዉ ለማለት ያስችላል።
የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የተርን ኦቨር ታክስ ልዩነት
ተ.ቁ መለያ ባህሪያት ተጨማሪ እሴት ታክስ (ተእታ) ተርን ኦቨር ታክስ (ተኦታ)
1. የታክሶቹን
አጣጣል ተከትለው  የተጨማሪ እሴት ታክስ የሚጣለው በምርት ወይም በአቅርቦት ላይ በሚጨመረዉ እሴት ላይ ነው፡፡  የተርን ኦቨር ታክስ የሚጣለው የአቅርቦት ሰንሰለቱን ተከትሎ ነዉ።
 የተጨማሪ እሴት ታክስ በምርት ሂደት ወይም በአቅርቦት ሰንሰለት ቀድሞ የተከፈለን የግብዓት ታክስ የማቀናነስ ሂደትን የሚከተል ነው፡፡  የተርን ኦቨር ታክስ ግን አጠቃላይ የሽያጭ ዋጋዉ ላይ እየተከተለ ቀድሞ የተከፈለን ታክስ ሳያቀናንስ ተሰልቶ ይሰበሰባል።
2.
የታክሶቹን
ስሌት ተከትለው  የተጨማሪ እሴት ታክስ የተቀናናሽ ስሌት አለው፡፡  የተርን ኦቨር ታክስ የተንከባላይነት
(cascading effect) የሚንጸባረቅበት ነዉ።
3.

የታክሶቹን
ምጣኔ
ተከትለው
 የተጨማሪ እሴት ታክስ በመርህ ደረጃ አገልግሎትን እና የዕቃን አቅርቦትን ሳይለይ አስራ አምስት በመቶ (15%) ታክስ እንዲሰበሰብበት ምጣኔ ( rate) የተቀመጠለት ነው፡፡  የተርን ኦቨር ታክስ አገልግሎትንና ዕቃን በተለያየ መጣኔ የሚያሳይ የታክስ አይነት ነዉ።
 ለአገልግሎት የተደነገገዉ የተርን ኦቨር ታክስ ምጣኔ አስር በመቶ (10%) ነዉ።

 የዉጪ ንግድን ለማበረታታት በዜሮ ምጣኔ (zero rate) ታክሱ የሚጣልባቸዉን አቅርቦቶችን አስቀምጧል።  ለዕቃ ሽያጭ የተደነገገዉ የተርን ኦቨር ታክስ ምጣኔ ሁለት በመቶ (2%) ነዉ።
4.

የታክሶቹን
አመዘጋገብ
ተከትሎ የተጨማሪ ታክስን ለመሰብሰብ ተመዝጋቢ መሆን ያስፈልጋል፡፡
የተርን ኦቨር ታክስን ለመሰብሰብ ግን የተለየ ምዝገባ ሳያስፈልገዉ በግብር ከፋይነት ተመዝግቦ በንግድ ስራ ላይ መሠማራት እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ያለመመዝገብ በቂ ነዉ።
3. ኤክሳይዝ ታክስ (Excise Tax)
o በቅንጦት እቃዎችና ጤና ሊጎዱ በሚችሉ ምርቶች ላይ የሚጣል የታክስ አይነት ነው፡፡
4. የጉምሩክ ቀረጥ (Customs Duty)
ከውጭ ሀገር ወደ ሀገር ውስጥ ገቢ በሚሆንና ከሀገር ውስጥ ወደ ውጭ ሀገር ወጭ በሚሆኑ ምርቶች እና ጥሬ እቃዎች ላይ የሚጣል የታክስ አይነት ነው፡፡
5. የቴምብር ቀረጥ (Stamp Duty)
• በልዩ ልዩ ሰነዶች ላይ የተጣለ ቀጥተኛ ያልሆነ የታክስ አይነት ነው፡፡
6. ሱር ታክስ (Sur Tax
ሱር ታክስ ማለት በአንድ ሀገር ውስጥ የመንግስትን የፋይናንስ ድጋፍ የሚፈልጉ ሁኔታዎች ሲከሰቱ በተወሰኑ ሸቀጦች ወይም የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ የሚጣል የታክስ ዓይነት ነው፡፡ በኛ ሀገር ተጨባጭ ሁኔታ ሱር ታክስ ተግባራዊ የተደረገው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመንግስት ለመደጎም ታስቦ ነው፡፡
ሱር ታክስ ለምንና መቼ ይጣላል?
መንግስት ሱር ታክስ ለመጣል ከሚገደድባቸው ሁኔታዎች መካከል፡-
o የሀገርን ሉአላዊነት ከአደጋ ለመከላከል
o ለሚካሄድ ጦርነት መከላከያውን በገንዘብ አቅም ለማጠናከር፤
o የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ሲከሰቱ መልሶ ለማቋቋሚያ፤
o በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኘው የህብረተሰብ ክፍል የመንግስት ቀጥተኛ ድጎማ የሚፈልግበት ወቅት ሲከሰት የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡
ለምሳሌ፡- በ1999 ዓ/ም የኢፌዲሪ መንግሰት በከተሞች ውስጥ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ዜጎች ድጎማ የሚውል ገንዘብ ለማሰባሰብ ወደብ በሚገቡ ሸቀጦች የተጣለውን የ10 በመቶ ሱር ታክስ፡፡
2. ታክስ ነክ ያልሆኑ ገቢዎች /Non Taxable Income/
የንግድ ፍቃድ እድሳት
የዳኝነት
የፍርድ ቤት መቀጫ
የአገልግሎት ምርት ሽያጭ
ልዩ ል ገቢ እና
የጡሬታ መዋጮ ናቸው፡፡

07/01/2022

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አያለ በዓሉ የሰላም፣የተስፋ፣የፍቅርና የመተሳሰብ እንዲሆን ምኞቱን ይገልፃል!!!
የሰዴ ሙጃ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት
ታህሳስ 28/2014 ዓ.ም

24/12/2021

በሰዴ ሙጃ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በግብር ትምህት ኮሙኑኬሽን ዋና የስራ ሂደት
ለግብር ከፋዮች እና ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ
ታህሳስ/2014 ዓ.ም ሮቢት
መግቢያ
• የግብር ክስተት ከመንግሥት ክስተት ጋር የተገናኘ እንደሆነ የታሪክ ድርሳናት
• ያስረዳሉ፡፡
• በሃገራችን በጥንት ጊዜ በተለያዩ መንግስታት የተለያዩ የግብር አጣጣሎች ነበሩ፡፡
• የጹሁፍ ማስረጃ የተገኘው በ15ኛው ክፍለ ዘመን በአፄ ዘርዓይ ያዕቆብ ዘመነ መንግስት ስለነበረው የግብር ስርዓት ነው፡፡
• ዘመናዊ መንግስት ቅርጽ እየያዘ እስከመጣበት 20ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ግብር ይከፈል የነበረውም በዓይነትና በአገልግሎት ነበር፡፡
• በዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ በ1885ዓ.ም. የታወጀው የግብር ሕግ ለዘመናዊ የግብር ሥርዓት በር ከፋች እንደሆነ ይነገራል፡፡
• ከ1983 ዓ.ም. ወዲህ የሽግግር መንግሥት ሲቋቋም በአገሪቱ አስተዳደራዊ መዋቅርና የኢኮኖሚ ፖሊሲ ላይ ለውጥ በመደረጉ በታክስ ሥርዓቱ ላይ አበይት ለውጦች ተከስተዋል፡፡
• ከፌዴራላዊ የመንግስት አወቃቀር ጋር የክልል መንግስታት በአዋጅ ቁጥር 7/1985 ሲመሰረቱ አሃዳዊ የነበረው የታክስ አስተዳደር ወደ አልተማከለ የታክስ አስተዳደር ተቀይሯል፡፡
• ሕገ-መንግስቱ ሕዳር 29 ቀን 1987 ዓ.ም. የታወጀ ሲሆን በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 96 እና 97 የፌዴራልና የክልል መስተዳድሮች የታክስና የግብር ሥልጣኖች ተደንግገዋል፡፡
1. የግብር/ታክስ ምንነት እና አስፈላጊነት
1.1 የግብር/ታክስ ምንነት
ግብር የመዝገበ ቃላት ፍችው ሲታይ መንግስት በህግና ደንብ ላይ ተመስርቶ ከህዝብና ከድርጅቶች ገንዘብ የሚያገኝበት መሳሪያ ነው፡፡
1.2 የግብር/ታክስ አስፈላጊነት /ጥቅም
ግብር ከእያንዳንዱ ግለሰብ የየእለት እንቅስቃሴ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ሲሆን ጠቀሜታዎቹም አያሌና ዘርፈ ብዙ ናቸው፡፡ የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል፡-
 ለኢኮኖሚ ልማት፣
 ለማህበራዊ አገልግሎቶች መስፋፋት፣
 ለባህል እድገት፣
 ለሀገር ደህንነት፣
 ለፍትህና መልካም አስተዳደር መስፈን፣
 ለአከባቢ ጥበቃ፣
 ሀገርን ከጠላት ለመከላከል፣
 ዜጎች በሰላም ወጥተው በሰላም ሰርተውና ውለው ለመግባት፣
 ደህንነታቸውና ሰላማቸውን ለመጠበቅ፣
 ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣ መንገዶች፣የሀይል አቅርቦቶችን ለመስፋፋት
 ኢኮኖሚን ለመነቃቃት፣
 ንግድና ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት፣
 ልማትን ለማፋጠን፣የሕ/ሰቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል፣
 ኢኮኖሚን ለማረጋጋት፣
 በዜጎች መካከል ፍትሃዊ የሆነ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር ለማድረግ እና የመሳሰሉት ስራዎችን ለማከናወን የሚውል ገንዘብ ነው፡፡
1.3 የግብር መርሆች
አንድ የግብር ስርአት ሊከተላቸው ከሚገባ ዋና ዋና መርሆች መካከል የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
1.ፍትሃዊነትን (እኩልነትንና ገለልተኝነት) መጠበቅ:- ሰዎች ከሚያገኙት ገቢ ተመጣጣኝ የሆነ ግብር ልዩነት ሳይፈጥር ያለ አድሎአዊነት እንደየዘርፉ መክፈል እንዳለባቸው የሚያመለክት ነው፡፡
2.የታክስ ስርአቱ አስተዳደራዊ ወጪ ቆጣቢ መሆን፡- የታክስ ማስከፈያ ምጣኔው እና የታክስ ማዕቀፎቹ ይዘት ለመገንዘብና ለማስተዳደር ግለጽና ቀላል እንዲሆኑ በማድረግ የታክስ አከፋፈሉና ግዜው አመቺና በከፋዩ ላይ ውጣ ውረድ የማያስከትል እንዲሆን በማስቻል የታክስ አወሳሰኑና አሰባሰቡ የሚያስከትለው አስተዳደራዊ ወጪ ዝቅተኛ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡
3. ምርታማነት /ውጤታማነት፡- የታከስ ስርዐቱ የመንግስትን የወጪ ፍላጎት ለመሸፈን በቂ ገቢ ማስገኘት እንደሚገባውና በሂደት ከራስ በሚሰበሰበው ገቢ የመንግሰትን አገልግሎቶችና መሰረተ ልማቶች ለመቅረብ የሚያስችለው መሆኑ ነው፡፡
4. እርግጠኛና ምቹ መሆን፡- የአገሪቱ የታክስ ስርአት የግብር ከፋዩ አጠቃላይ ገቢ፣ ግብር የሚከፈለበት ገቢ እንዲሁም ከግብር ከፋዩ የሚፈለግ የግብርና የታክስ መጠን ላይ ለመድረስ የሚሰላበት አሰራር ወጥና በሁሉም ዘንድ በትክክል የሚታወቅ እንዲሆን ማድረግን የሚያመለክት ነው፡፡

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sedie Muja Woreda Revenue Office 2014 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share