17/03/2021
ለግንዛቤዎ
በጥላሁን ጀንበሩ
ከታክስ ከፋይ ግዴታዎች ውስጥ፡-
በግብር ከፋይነት የመመዝገብ ግዴታ፣
በባለሥልጣኑ የተፈቀደ ደረሰኝ የማሳተምና የመጠቀም ግዴታ፣
የሒሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ደረጃ ሀ እና ለ፣
ለተጨማሪ እሴት ታክስ የመመዝገብ ግዴታ ዓመታዊ ሽያጩ ከ 1 ሚሊዮን
ብር በላይ፣
ግብይትን በደረሰኝ ብቻ የማከናወን ግዴታ፣
በህግ በተመለከተው ጊዜ ገቢውን ወይም ሽያጩን አሳውቆ ትክክለኛ ታክሱን
የመክፈል ግዴታ፣
ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ግብርን ቀንሶ የማስቀረትና ለባለስልጣኑ ገቢ ማድረግ
ግዴታ፣
ህጋዊና ትክክለኛ ደረሰኞችንና ሰነዶችን ብቻ የመጠቀም ግዴታ፣
በታክስ ደረሰኝና ሌሎች የግብይት ሰነዶች ላይ የገዥውን ወይም
የአገልግሎት ተቀባዩን የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የመፃፍ ግዴታ፣
አስተዳደራዊ ቅጣቶች
በታክስ ከፋይነት ያልተመዘገበ እንደሆነ የግብሩን 25% መቀጮ ይቀጣል፡፡
የሚከፈል ግብር ከሌለ በየወሩ 1,000 ብር ይቀጣል፡፡
ከግብር ከፋይነት እንዲሰረዝ ያልጠየቀ በየወሩ 1,000 ብር መቀጫ
ይከፍላል፡፡
የሒሳብ መዝገብ ያልያዘ እንደሆነ የግብሩን 20% መቀጮ ይከፍላል፡፡
የሚከፈል ታክስ እንኳን ባይኖር ለገቢ ግብር በዓመት 20,000 ብር ለሌሎች
ታክሶች በየወሩ 2,000 ብር ይቀጣል፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በደረሰኝ ላይ አለመጻፍ ቁጥሩ ባልተጻፈበት
በእያንዳንዱ ደረሰኝ ብር 3,000 ያስቀጣል፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tax Identification Number/TIN) ለሌላ
ሰው የሰጠ ብር 10,000 ይቀጣል፣
የሌላ ሰው TIN የተጠቀመ ብር 10,000 ይቀጣል፣
የግብር ማስታወቂያ ማዘግየት 5% ያስቀጣል (25% እስኪሞላ ድረስ)
ግብር/ታክስ ሳይከፈል ማዘግየት ለአንድ ወር 5% ከዚያ በላይ ለሆነው ጊዜ
ተጨማሪ 2% መቀጫ ያስከፍላል፡፡
ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ግብር ያልቀነሰ ወይም ቀንሶ ገቢ ያላደረገ
ያልተቀነሰውን ወይም ገቢ ያልተደረገውን ግብር 10% ይቀጣል፡፡
እንዲሁም ሥራ አስኪያጁና የሂሳብ ሹሙ እና ግብሩን ተቀናሽ ያላደረጉ
ሠራተኞች እያንዳንዳቸው ብር 2,000 ይቀጣሉ፡፡
ለተጨማሪ እሴት ታክስ አለመመዝገብ በየወሩ 2,000 ብር ያስቀጣል፡፡
ባልተመዘገበበት ጊዜ ላከናወነው ግብይት ሊከፈል የሚገባውን ታክስ 100%
ይቀጣል፡፡
ታክስን ለማሳነስ ወይም ተመላሽ እንዲጨምር ለማድረግ ትክክለኛ ያልሆነ
ደረሰኝ የሰጠ ሰው ብር 50,000 ይቀጣል፡፡
ደረሰኛ መስጠት ሲገባው ያልሰጠ ባልሰጠው በእያንዳንዱ ደረሰኝ ብር
50,000 ይቀጣል፡፡
ታክስ አሳንሶ ማሳወቅ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን 10% ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን
30% ለሦስተኛ ጊዜ ሲሆን 40% መቀጮ ያስከትላል፡፡
ታክስ ላለመክፈል የሚደረጉ ጥረቶች ያልተከፈለውን ታክስ እጥፍ መቀጫ
ያስቀጣል፡፡
የኤሌክትሮኒክስ ሥርዓት አለመከተል
ታክሱን በኤሌክትሮኒስ ሥርዓት አሳውቆ እንዲከፍል የተጠየቀ ግብር ከፋይ
በዚሁ መሠረት ያልፈጸመ እንደሆነ ብር 5ዐ,ዐዐዐ ይቀጣል፡፡
በታክስ ወኪል ላይ የሚጣል መቀጫ
የታክስ ወኪል ለደንበኛው የምስክር ወረቀት ወይም መግለጫ ከልሰጠ
ወይም እነዚህን መረጃዎች በህግ ለተወሰነው ጊዜ ይዞ ያልቆየ እንደሆነ፣
ሥራ ማቆሙን ለባለሥልጣኑ ካላሳወቀ ብር 1ዐ,ዐዐዐ ይቀጣል፡፡
ከሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ
የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ የመጠቀም ግዴታ ያለበት ማንኛውም ግብር
ከፋይ፤
እውቅና ያልተሰጠውን መሣሪያ ተጠቅሞ ከተገኘ ለእያንዳንዱ መሣሪያ
5ዐ,ዐዐዐ ብር፣
በሸያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ከታተመ ደረሰኝ ውጪ ሌላ ደረሰኝ
ከተጠቀመ ብር 5ዐ,ዐዐዐ፣
በመሣሪያው ላይ ጉዳት ያደረሰ ወይም የፊሲካል ማስታወሻው እንዲቀየር
ያደረገ ወይም ይህን ለማድረግ ሙከራ ያደረገ ብር 1ዐዐ,ዐዐዐ፣
በመሣሪያው ላይ ፍተሻ (ኦዲት) እንዳይደረግ የተከላከለ ወይም የቴክኒክ
ምርመራ በየዓመቱ ያላደረገ ብር 25,ዐዐዐ፣
ከአገልግሎት ማዕከል ጋር ውል ካልፈጸመ ወይም መሣሪያውን ከተርሚናል
ጋር ሳያያይዝ ከተጠቀመ ወይም የመሣሪያው ምርመራ መዝገብ ከመሣሪያው
ጐን እንዲቀመጥ ካላደረገ ወይም በተመላሽ መዝገብ ሳይመዘገብ የተመላሽ
ደረሰኝ ከሰጠ ብር 25ዐዐዐ፣
መሣሪያው አገልግሎት መስጠት ሲያቋርጥ (ሲሰረቅ ወይም ሲጐዳ)
በሦስት ቀናት ውስጥ ወይም ሲበላሽ በአራት ሰዓት ውስጥ ለአገልግሎት
ማዕከሉና ለባለሥልጣኑ ካላሳወቀ ብር 1ዐ,ዐዐዐ፣
መሣሪያው ያለበትን ትክክለኛ አድራሻ ለባለሥልጣኑ ያላሳወቀ እንደሆነ ብር
5ዐ,ዐዐዐ፣
የአድራሻ ወይም የስም ለውጥ ሲያደርግ ወይም የንግድ ሥራውን ሲያቋርጥ
ከሦስት ቀናት አስቀድሞ ለአገልግሎት ማዕከሉና ለባለሥለጣኑ ያላሳወቀ
እንደሆነ ብር 25,ዐዐዐ፣
መሣሪያው ባለበት የንግድ ሥራ ቦታ በህጉ የተዘረዘሩ አስፈላጊ መረጃዎችና
ማስታወቂያዎች ካልተቀመጡ ብር 1ዐ,ዐዐዐ፣
የሽያጭ ነቁጣ ሶፍት ዌር ዕውቅና ባልተሰጠው ሰው አስቀይሮ ወይም
እንዲሻሻል አድርጐ ከተገኘ ብር 3ዐ,ዐዐዐ ይቀጣል፡፡
የማይሰራ፣ የተበላሸ (የተጐዳ) መሣሪያ ለአገልግሎት ማዕከላት በሦስት
ቀናት ውስጥ አቅርቦ ማስቀየር (መተካት) አለመቻሉን ለባለሥልጣኑ አስቀድሞ
ካላሳወቀ ብር 5ዐ,ዐዐዐ፣
ስለተዋዋለባቸው አገልግሎት ማዕከላት መረጃ ካልያዘ ወይም
ለባለሥልጣኑ ካላሳወቀ ብር 5ዐ,ዐዐዐ፣
የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያዎች አገልግሎት ማዕከል፣
የፊሲካል ማስታወሻ በተተካ በሁለት ቀናት ውስጥ ለባለሥልጣኑ ካላሳወቀ
ብር 25,ዐዐዐ፣
ውል የገባባቸውን መሣሪያዎች በዓመት አንድ ጊዜ የቴክኒክ ምርመራ
ካላደረገ ብር 25,ዐዐዐ፣
ዕውቅና ያልተሰጠውንና በባለሥልጣኑ ያልተመዘገበ ሠራተኛ ለሥራ
አሰማርቶ ከተገኝ ብር 5ዐ,ዐዐዐ ይቀጣል፡፡
ስለ ታክስ እውቀት ያለው ትውልድ እንዲኖር እንትጋ