Anteneh Elmeneh

Anteneh Elmeneh መድኃኔዓለም!

ዓለምን ያዳነ የዓለም መድኃኒት ነው።
ጥበቃው አይለየን 🙏

28/08/2026

I'm in the top 12% of Derbew Ameshe fans. I earned 49 points on their weekly engagement list last week.

ብዙ ባወቅን ቁጥር ገና ብዙ የማናውቀው እውነት እንዳለ እንረዳለን!«ያወቅነው የአንዲት ጠብታ ያህል ሲሆን፤ያላወቅነው ግን የውቅያኖስ ያህል ነው» ይህ አስተቆማሪ አባባል በ ሰር አይዛክ ኒውተ...
27/08/2026

ብዙ ባወቅን ቁጥር ገና ብዙ የማናውቀው እውነት እንዳለ እንረዳለን!

«ያወቅነው የአንዲት ጠብታ ያህል ሲሆን፤
ያላወቅነው ግን የውቅያኖስ ያህል ነው» ይህ አስተቆማሪ አባባል በ ሰር አይዛክ ኒውተን የተነገረ ሲሆን የሰውን ልጅ የዕውቀት ወሰን እና የተፈጥሮን ማለቂያ የሌለው ጥልቀት በግልጽ የሚያሳይ እጅግ ጥልቅ ፍልስፍናዊ ሐሳብ ነው።

በታሪክ ውስጥ ከታላላቅ አእምሮዎች አንዱ ተደርጎ የሚወሰደው ኒውተን ራሱ የደረሰበት ሳይንሳዊም ሆነ ዓለማዊ ዕውቀት ከባሕር ጠብታ ጋር ሲነጻጸር ምን ያህል አነስተኛ መሆኑን መገንዘቡ እውነተኛ ዕድገት ሁልጊዜም ከከፍተኛ ትሕትና ጋር አብሮ እንደሚጓዝ ያስተምረናል።

ገና ያልተደረሰባቸው፣ ያልተመረመሩ እና ከግንዛቤያችን ባሻገር ያሉት ማለቂያ የሌላቸው እውነታዎች ልክ እንደ ማለቂያ የለሽ ውቅያኖስ ይሰፋሉ። እውቀት ሲጨምር ስንሰበስበው የነበረው መረጃ ከሰፊው ዓለም ጋር ሲወዳደር አነስተኛ መሆኑ ይፋ ይሆናል፤ ብዙ ባወቅን ቁጥር ገና ብዙ የማናውቀው እውነት እንዳለ በመረዳት አእምሮአችንን ለክስተቶች እና ለቀጣይ ጥናቶች ክፍት እናደርጋለን።

ይህ ድንቅ ፍልስፍና በግል ሕይወትም ሆነ በተቋማት አስተዳደር ውስጥ ምንጊዜም ለአዳዲስ እውነታዎች ክፍት መሆንን፣ ያለማቋረጥ መማርን እና በታላቅ ትሕትና ማገልገልን ይጋብዘናል።

እብሪት የአስተሳሰብ አድማስን ሲያጠብ ትሕትና ግን አዳዲስ አድማሶችን ለማሰስ የውስጥ ድፍረት ይሰጠናል። እውነተኛው ጥበብ የሚጀምረው የዕውቀትን ስፋት እና የአለማወቃችንን ገደብ በሰከነ መንፈስ በመቀበል ነው።

➧ብዙ ባወቁ ቁጥር የበለጠ ትሁት መሆን እንደሚገባ በሕይወትዎ የተገነዘቡበት አጋጣሚ አለ?

~ ዛዲግ አብርሀ ~
(የአፍሌክስ ፕሬዝደንት)

 #የልብህን ሰዎች ሁሉ ለአደባባይ አታቅርብ ወዳጀ #ውድ ነገሮች ጫጫታን አይወዱም። ወርቅ በመሬት ውስጥ ይገኛል፤ ዕንቁ በባሕር ጥልቀት ይበቅላል፤ እውነተኛ ፍቅርም በልብ ውስጥ ይኖራል። #ዘ...
25/08/2026

#የልብህን ሰዎች ሁሉ ለአደባባይ አታቅርብ ወዳጀ

#ውድ ነገሮች ጫጫታን አይወዱም። ወርቅ በመሬት ውስጥ ይገኛል፤ ዕንቁ በባሕር ጥልቀት ይበቅላል፤ እውነተኛ ፍቅርም በልብ ውስጥ ይኖራል።

#ዘመኑ ግን ሁሉን ነገር ለአደባባይ ማቅረብን እንደ ድፍረት እያስተማረን ነው፤ ሁሉን መናገርን እንደ ታማኝነት፣ ሁሉን ማሳየትን እንደ ፍቅር እያስለመደን ነው ። እውነቱ ግን ይለያል።

#የምትወደው ሰው የሚታይ ወይም የሚሸጥ ዕቃ አይደለም፤ የነፍስህ ክፍል ነው። የነፍስ ክፍል ደግሞ በየመንገዱ ለሚያልፍ ሰው አይታይም፤ በክብር ይጠበቃል።

#አስታውስ... የሚጠላህ ሰው በጥንካሬህ ላይ አያተኩርም፤ ልብህ በሚያምበት ቦታ ላይ ያነጣጥራል። የሰው ትልቁ ድክመቱ ገንዘቡ ወይም ሥልጣኑ ሳይሆን፣ ከልቡ የሚወዳቸው ሰዎች ናቸው።

#ሁሉም ፈገግ የሚልልህ ወዳጅህ አይደለም፤ ሁሉም የሚያጨበጭብልህ በደስታህ የተደሰተ አይደለም። አንዳንዶች የሚቀርቡት የልብህን በር ለመክፈት ሳይሆን፣ የሚያቆስሉህን መስኮት ለማግኘት ነው።

#ስለዚህ ጸጥ ብለህ ውደድ። በጥልቅ ጠብቅ። ለሁሉም ሰው የልብህን ካርታ አትስጥ፤ የቤትህን በር ቁልፍ ለማንኛውም ሰው እንደማትሰጥ ሁሉ፣ የነፍስህን ቁልፍም በጥንቃቄ ጠብቅ።

#አንዳንድ ፍቅሮች የሚያምሩት በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ስለተለጠፉ አይደለም፤ ከክፉ ዓይን ተጠብቀው ስለኖሩ ነው። አንዳንድ ግንኙነቶች የሚጸኑት በብዙ ምስክሮች ፊት ሳይሆን፣ በጸጥታ ውስጥ ስለተገነቡ ነው።

#ሰው ሁሉ የደስታህን ምንጭ ማወቅ አያስፈልገውም፤ ሰው ሁሉ የእንባህን ምክንያት ማወቅም አያስፈልገውም። የልብህን ቅዱስ ስፍራ ለሚያከብሩት ብቻ ክፈተው።

#ምክንያቱም የምትወዳቸውን ሰዎች መደበቅ ፍቅርን መንፈግ አይደለም፤ ፍቅርን መጠበቅ ነው። የሚያምረው ነገር ሁሉ ለአደባባይ አይወጣም፤ አንዳንድ ውበቶች በዝምታ ውስጥ እንጂ በጩኸት ውስጥ አያብቡም።

ይሔው ነው❗

"...  #ከብዙ ሀሳብ ትንሽ ስራ ይበልጣል ። ኢትዮጵያ አሁን የምትፈልገው የሚሰራ እጅ ነው ። የኔ ጥሪ ስራ ነው መናገር አላውቅም ።Ⓜ️ከማፍረስ መገንባት ፣ ከብዙ ምላስ ትንሽ ስራን ፣ ከ...
24/08/2026

"... #ከብዙ ሀሳብ ትንሽ ስራ ይበልጣል ። ኢትዮጵያ አሁን የምትፈልገው የሚሰራ እጅ ነው ። የኔ ጥሪ ስራ ነው መናገር አላውቅም ።

Ⓜ️ከማፍረስ መገንባት ፣ ከብዙ ምላስ ትንሽ ስራን ፣ ከበቀል ይቅርታን ፣ ከጥላቻ ፍቅርን ፣ ከመሃይምነት እውቀትን እመርጣለሁ ። ቂል ነኝ ግን አንድ ነገር አውቃለሁ

Ⓜ️በሁሉም ነገር ላይ እምነት ከማጣት የበለጠ ሀገርን የሚያጠፋ ቦንብ የለም ..

📚📚

📢 ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ልዩ መረጃ! 🎓የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤታችሁን ለማየት የEAES ኦፊሴላዊ የውጤት መመልከቻ አማራጮችን ብቻ ይጠቀሙ።🌐 result.eaes.et🌐 result.n...
24/08/2026

📢 ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ልዩ መረጃ! 🎓
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤታችሁን ለማየት የEAES ኦፊሴላዊ የውጤት መመልከቻ አማራጮችን ብቻ ይጠቀሙ።
🌐 result.eaes.et
🌐 result.neaea.gov.et
📱 SMS: 6284
🙏 ይህን መረጃ ውጤታቸውን ለሚጠባበቁ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እንዲደርስ Share ያድርጉ! 📲
🎓 መልካም ውጤት ለሁላችሁም! ❤️

24/08/2026

With Derbew Ameshe – I just got recognised as one of their top fans!

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ይፋ ይደረጋል።ትምህርት ሚኒስቴር በላከልን መረጃ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል የሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን በተመለከተ ከሰዓት በኋላ መግለጫ እንደሚሰጥ ...
22/08/2026

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ይፋ ይደረጋል።

ትምህርት ሚኒስቴር በላከልን መረጃ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል የሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን በተመለከተ ከሰዓት በኋላ መግለጫ እንደሚሰጥ ጠቅሷል።

በዓመቱ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 62 በመቶ የሚሆኑት በኦንላይን ፈተናውን ወስደዋል።

በ2018 የትምህርት ዘመን አጠቃላይ 563 ሺህ 501 ተማሪዎች በ607 የፈተና ማዕከላት ውስጥ የተፈተኑ ሲሆን ፈተናው በ6 ዙሮች ተሰጥቷል።

ከዘንድሮ ጠቅላላ ተፈታኞች መካከል 306 ሺህ 456 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሲሆኑ፣ 257 ሺህ 45 ደግሞ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ነበሩ፡፡

ውጤቱን በተመለከትም ትምህርት ሚኒስቴር በ9 ሰዓት መግለጫ እሰጣለሁ ብሏል፡፡

 #እሳትና ዉሀ ተባብረዉ አንድ በሬ ገዙ ። #የዕለቱ ለት በሬያቸዉን ሌባ ሰረቀባቸዉ። #በዚህ ግዜ አቶ እሳት እንዲህ አለ። #ባለንጀራየ ሆይ ያዉ እንደምታዉቀዉ ካንተ በስተቀር ሁሉንም አሸን...
21/08/2026

#እሳትና ዉሀ ተባብረዉ አንድ በሬ ገዙ ።

#የዕለቱ ለት በሬያቸዉን ሌባ ሰረቀባቸዉ።

#በዚህ ግዜ አቶ እሳት እንዲህ አለ።

#ባለንጀራየ ሆይ ያዉ እንደምታዉቀዉ ካንተ በስተቀር ሁሉንም አሸንፋለሁ።

#ስለዚህ አሁን በአፋጣኝ ተነስቼ ቤቱ ንም፣ሳሩንም፣ ደኑንም አቃጥየ የበሪያችንን ሌባ ላግኝዉ አለዉ።

#ዉሃ በበኩሉ ወንድም ጋሸ እሳት ምነዉ እንደዚህ ማለትህ የሰረቀዉንም ያልሰረቀዉንም አንድላይ ማቃጠል አይገባም።

#ሌባዉን ለመያዝ የምንቸገረዉ ነገር አይኖርም፤አሁን እናገኝዋለን ብሎ ያፅናናዋል። "እንዴት አርገን "ሲለዉ

#"እጠብስ ያለ ካንተ ፤አጥብ ያለ ከኔ ብቅ ይላል። ያን ግዜ እንይዘዋለን"።አለዉ ይሄን ከተባባሉ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ አንዱ ቅልጥም ይዞ ሊጠብስ እሳቱ ጋር መጣ አንዱ ደግሞ ጨጎራ ሊያጥብ ዉሀ ጋ መጣ።በዚህ ሰአት ሌቦቹ ስለታወቁ ተያዙ።

#አንድ ወይም ሁለት ሌባ ለመያዝ አገር ማቃጠል አይጠበቅብንም ብልሀት እንጅ።

#ምንጭ:-ካነበብኩት።
✍️

➧"መከረኞች ከመከራቸው ነፃ የሚወጡት ለመብታቸው ሲጥሩ ወይም ሲሞቱ ነው፡፡”💚✔➧“ሞት! ሞት! ሞት! ሞት!➧አንተ ስመ - ክፉ ሥራህ ግን ደግነት!የድሆች ነፃ አውጪ የእውነት ነፃነት፣ የንቅል...
21/08/2026

➧"መከረኞች ከመከራቸው ነፃ የሚወጡት ለመብታቸው ሲጥሩ ወይም ሲሞቱ ነው፡፡”💚✔

➧“ሞት! ሞት! ሞት! ሞት!

➧አንተ ስመ - ክፉ ሥራህ ግን ደግነት!
የድሆች ነፃ አውጪ የእውነት ነፃነት፣
የንቅልፍ ታላቅ ወንድም የዘለዓለም ዕረፍት፣
ፍጡራን በሐሰት ስለሚደለሉ፣
ደሀም እንደ ሀብታም አንተን ጠላህ አሉ።

12ቱ የሥነ ምግባር እሴቶች🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿በኢትዮጵያ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና የሕዝብ አገልግሎት ዘርፍ በስፋት የሚሠሩባቸውና የሚታወቁት 12ቱ መሠረታዊ የሥነ ምግባር እሴቶች የሚከተሉት ናቸው፡...
20/08/2026

12ቱ የሥነ ምግባር እሴቶች
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

በኢትዮጵያ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና የሕዝብ አገልግሎት ዘርፍ በስፋት የሚሠሩባቸውና የሚታወቁት 12ቱ መሠረታዊ የሥነ ምግባር እሴቶች የሚከተሉት ናቸው፡

➣ታማኝነት፦
እውነትን መሠረት በማድረግ መሥራትና ከማንኛውም ዓይነት ማታለልና ሙስና የጸዳ መሆን።

➣ቅንነት ፦
ሰዎችንና አገልግሎት ፈላጊዎችን በበጎ መንፈስ፣ በቅን ልቦናና ያለ ክፍያ ወይም ጥቅም አሳቦ ማገልገል።

➣ፍትሐዊነት፦
ማናቸውንም አድሎአዊ አሠራሮች አስወግዶ ሰዎችን በእኩልነትና በፍትህ ማስተናገድ።

➣ግልጽነት ፦
አሠራርና ውሳኔዎች ለሕዝብና ለሚመለከታቸው አካላት ግልጽና ክፍት እንዲሆኑ ማድረግ።

➣ተጠያቂነት ፦
ለሚሰጥ የሥራ ውሳኔና ለሚከናወን ተግባር ሙሉ ኃላፊነት መውሰድና ለመጠየቅ ዝግጁ መሆን።

➣ሚስጥር ጠባቂነት ፦
የሕዝብና የመሥሪያ ቤትን ምስጢራዊ መረጃዎች በአግባቡና በኃላፊነት መጠበቅ።

➣አድሎአዊ አለመሆን፦
በዘር፣ በሃይማኖት፣ በጾታ ወይም በሌላ ማንኛውም ልዩነት ሳይወሰኑ አግልግሎትን በገለልተኝነት መስጠት።

➣ሕግን ማክበር፦
ሕጎችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን በጥብቅ መከተልና ማስከበር።

➣ለሕዝብ ጥቅም ቅድሚያ መስጠት፦
የግል ጥቅምን አስወግዶ ሁልጊዜ ለሕዝብና ለሀገር ጥቅም ቅድሚያ መስጠት።

➣ኃላፊነትን በአግባቡ መወጣት፦
የተሰጠን የሥራ ድርሻ በከፍተኛ ትጋት፣ በጥራትና በጊዜው ማከናወን።

➣አርአያነት፦
በሥነ ምግባር፣ በሥራ ወዳድነትና በባህርይ ለሌሎች መልካም አርአያ ሆኖ መገኘት።

➣የሕዝብን ንብረት በአግባቡ መያዝ፦
የመንግሥትና የሕዝብ ሀብትና ንብረትን ያለ ብክነት ለታለመለት ዓላማ ብቻ በቁጠባና በጥንቃቄ መጠቀም።

Address

01
Bahir Dar
LIFE

Telephone

+251920258618

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Anteneh Elmeneh posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Anteneh Elmeneh:

Shortcuts

Share

Category