ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር
እናሻግራት ሁላችንም በመደመር
መድረሻችን ጫፍ እስከ ጫፍ እንዲሰማ
እንለኩሰው ይቀጣጠል የድል ሻማ።

"ለጋራ ርዕይ የሚታትር፣ በዓላማ የተግባባ እና የጋራ ግብ ያለው አመራር ማረጋገጥ ተችሏል"  ርእሰ መሥተዳድር ክቡር አቶ አረጋ ከበደArega  Kebede Legas/አረጋ ከበደ ለጋስ
26/08/2026

"ለጋራ ርዕይ የሚታትር፣ በዓላማ የተግባባ እና የጋራ ግብ ያለው አመራር ማረጋገጥ ተችሏል"

ርእሰ መሥተዳድር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ
Arega Kebede Legas/አረጋ ከበደ ለጋስ

26/08/2026
“በ2018 በጀት ዓመት ሁለንተናዊ የማስፈጸም አቅምን በማሳደግ የሕዝብን አደራ በላቀ ኃላፊነት የሚወጣ አመራር በማረጋገጥ ስኬታማ ሥራዎች ተከናውነዋል”አቶ ይርጋ ሲሳይ ቅጣውበብልፅግና ፓርቲ ...
26/08/2026

“በ2018 በጀት ዓመት ሁለንተናዊ የማስፈጸም አቅምን በማሳደግ የሕዝብን አደራ በላቀ ኃላፊነት የሚወጣ አመራር በማረጋገጥ ስኬታማ ሥራዎች ተከናውነዋል”

አቶ ይርጋ ሲሳይ ቅጣው
በብልፅግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ
Yirga Sisay Kitaw / ይርጋ ሲሳይ ቅጣው

25/08/2026

ህገ-ወጥ ግንባታ የመሬት ወረራ የከተሞች እድገት ፀር ነው!!❗️❗️

22/08/2026

እንኳን ለሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በክልላችን ከነሐሴ ወር መጀመሪያ አንስቶ በዋግኽምራ፣ በሰሜን ውሎና አካባቢው በድምቀት የሚከበሩት ሻደይ፣ አሸንድየና ሶለል ረጅም ዘመናትን የተሻገሩ የሕዝባችን መገለጫ በዓላት ናቸው፡፡

የሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል በዓል በልጃገረዶችና በወጣቶች ባሕላዊ ጨዋታ ደምቀው በአደባባይ ይከበራሉ።

ልዳገረድችና ወጣቶች በክረምቱ የለመለሙ ዕፅዋትን በመጠቀም ባሕልና እሴታቸውን የሚገልጹበት እንዲሁም ወደ ብርሃኑ የመስከረም ወር እና አዲስ ዓመት ለመሸጋገር የተስፋና የደስታ ማብሰሪያቸው ነው፡፡

ሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጎብኚዎችን የሚስቡ የሕዝባችን ማህበራዊ ቁርኝትና አብሮነት የሚያጠናክሩ የማይዳሰሱ ባሕላዊ ቅርሶቻችን ናቸው።

በዓላቱን ስናከብር ሕዝባችን ለዘመናት ጠብቆ ያቆያቸውን ባህላዊ እሴቶች በማክበርና በማሳደግ፣ ለተከታዩ ትውልድ ትውፊታዊ ይዘታቸውን ጠብቀን ለማስተላለፍ በጋራ በመሥራት ሊሆን ይገባል፡፡

መልካም የሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል በዓል!

የገጠር ልማት መለካት ያለበት በሚገነቡት መሠረተ ልማቶች ብቻ ሳይሆን፣ ተከትሎ በሚመጣው የሰዎች ሕይወት ለውጥ መሆን አለበት። ‎‎በመሆኑም የገጠር ኮሪደር ልማት ውጥን ተግባራዊና ሰውን ማዕከ...
22/08/2026

የገጠር ልማት መለካት ያለበት በሚገነቡት መሠረተ ልማቶች ብቻ ሳይሆን፣ ተከትሎ በሚመጣው የሰዎች ሕይወት ለውጥ መሆን አለበት።

‎በመሆኑም የገጠር ኮሪደር ልማት ውጥን ተግባራዊና ሰውን ማዕከል ያደረገ አካሄድን በመከተል ላይ ይገኛል። ይህም ትስስርን ማሻሻል፣ ምቹ የኑሮ ሁኔታዎችን መፍጠር እና በገጠር ማሕበረሰብ ውስጥ የኢኮኖሚ ዕድሎችን ማስፋፋት ነው።

‎የዚህ ዐበይት ግብ የተበታተነና የተቆራረጠ ሐብትን በማስተካከል አምራች፣ እርስ በርስ የተሳሰሩ፣ ዘላቂ ልማት ያላቸው እንዲሁም ለመኖርና ለመሥራት ማራኪ የሆኑ የገጠር አካባቢዎችን መገንባት ነው።

Rural development must be measured not only by what is built, but by how people’s lives change as a result.

The rural corridors initiative is therefore taking a practical, people-centered approach: improving connectivity, creating better living conditions, and unlocking economic opportunities within rural communities.

The goal is to move beyond fragmented interventions and build rural areas that are productive, connected, resilient, and attractive places to live and work.


Abiy Ahmed Ali

የተከበሩ ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬ ለሻደይ፣ አሸንድየና ሶለል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉየአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬ ለ...
22/08/2026

የተከበሩ ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬ ለሻደይ፣ አሸንድየና ሶለል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬ ለሻደይ፣ አሸንድየና ሶለል በዓል የሚከተለውን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላፍተዋል፦

ከጥንት ጀምሮ በክልላችን የሚከበረው የሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል በዓል ታሪካዊና መንፈሳዊ ትስስር ያለው ነው። የሻደይ ቅጠል የሕይወት፣ የተስፋና የበረከት ምልክት ሆኖ በልጃገረዶች ዝማሬና እልልታ የሚደምቅ የማንነታችን ውብ ቅርስ ነው፤ በዓሉም የታሪክ፣ የእምነት፣ የማንነትና የትውልድ ትስስር የሚገለጥበት ታላቅ እሴታችን ነው።

ልጃገረዶች በነጭ ባህላዊ አልባሳት ተውበው፣ የሻደይ ቅጠል በወገባቸው አስረው በዝማሬ፣ በእልልታና በጭፈራ በሕብረት የሚያከብሩበት መንገድ በእጅጉ ይማርካል። ይህ በዓል የሴቶች የነፃነት ቀን ተደርጎም የሚወሰድ በመሆኑ፣ ሴቶች በዓሉን ሲያከብሩ ለአብሮነትና ለሰላም ግንባታ የሚኖረውን ሚና ማጠናከር ያስፈልጋል።

በዓሉ ባህላዊ ቱፊቱን ጠብቆ ለቀጣይ ትውልድ እንዲተላለፍ እየተከናወነ ያለው ሥራም የሚደነቅ ሲሆን፣ ይህ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል።

አፈ ጉባኤዋ በመጨረሻም በድጋሜ እንኳን ለሻደይ፣ አሸንድየና ሶለል በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን! በማለት መልካም የመልካም በዓል ምኞታቸውን ገልጸዋል።

"የውኃ ማማነታችን የሚረጋገጠው የታዳሽ ኃይል ማማ ስንሆን ነው።"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
22/08/2026

"የውኃ ማማነታችን የሚረጋገጠው የታዳሽ ኃይል ማማ ስንሆን ነው።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)





22/08/2026

Address

Bahir Dar

Telephone

+251918768463

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share