South Gondar zone Education Department /ደቡብ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ

  • Home
  • Ethiopia
  • Bahir Dar
  • South Gondar zone Education Department /ደቡብ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ

South Gondar  zone Education Department /ደቡብ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ Quality Education for All !!

‎በመካነ ኢየሱስ ከተማ አሥተዳደር ከ900 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።‎‎በደቡብ ጎንደር ዞን በመካነ ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር "በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ምክን...
30/08/2026

‎በመካነ ኢየሱስ ከተማ አሥተዳደር ከ900 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።

‎በደቡብ ጎንደር ዞን በመካነ ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር "በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት አንድም ተማሪ ከትምህርት ገበታ መቅረት የለበትም" በሚል መሪ ቃል በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተሰበሰበ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች ተሰራጭቷል።

‎በበጎ ፈቃድ የተሰበሰበው የትምህርት ቁሳቁሱ ከከተማዋ ነዋሪዎች ከተለያዩ ተቋማት ድርጅቶችና ባለሀብቶች የተገኘ መሆኑ ተገልጿል።

‎ድጋፉ በገንዘብ ሲተመን ከ600 ሺህ በላይ ብር የሚያወጣ ሲሆን ከ800 ደርዘን በላይ ደብተር እና ከ130 ባኮ በላይ እስክሪብቶ ነው።

‎የተሰበሰበው የትምህርት ቁሳቁስም ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ከ900 በላይ ለሚሆኑ የነገ ሀገር ተረካቢ ተማሪዎች ስርጭት ተደርጓል።

‎በትምህርት ቁሳቁስ ስርጭቱ ላይ ተገኝተው ለተማሪዎች ድጋፉን ያሰራጩት የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና የንግድ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ሙሉአለም እንደገለጹት ድጋፉ የልጆችን የትምህርት ቁሳቁስ ችግር ከመቅረፉ ባሻገር ዛሬ ከሚያዩት ማህበራዊ ተግባር መረዳዳትንና መተጋገዝን ተምረው እንዲያድጉ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።

‎የከተማ አስተዳደሩ የብልፅግና ፓርቲ የአቅም ግንባታና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መኳንንት ታደሰ በበኩላቸው በዚህ ክረምት የቤት እድሳት የእህል ድጋፍና የማዕድ ማጋራትን ጨምሮ በርካታ አቅመ ደካሞችን የደገፉ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

‎በስርጭት መርሃ ግብሩ የከተማና የቀበሌ አመራሮች፣ ተማሪዎች እንዲሁም የተማሪ ወላጆች በቦታው ተገኝተዋል።

‎"የመረዳዳት እና የበጎ ፈቃድ ባህላችን ይለምልም!"

🇪🇹🇪🇹🇪🇹ነሐሴ 24/2018 ዓ.ም🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹👉 #እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናት ተማሪዎችን  በማስመዝገብ  የዜግነት ግዴታችን እንወጣ።🇪🇹📢📢  🇪🇹🇪🇹🇪🇹  🇪🇹🇪🇹
30/08/2026

🇪🇹🇪🇹🇪🇹ነሐሴ 24/2018 ዓ.ም🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉 #እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናት ተማሪዎችን በማስመዝገብ የዜግነት ግዴታችን እንወጣ።🇪🇹📢📢
🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹

በእስቴ ወረዳ ድጋፍ ለሚሹ 630 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ፤​በደቡብ ጎንደር ዞን በእስቴ ወረዳ ከየቀበሌው ለተወጣጡ እና ድጋፍ ለሚሹ 630 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ...
30/08/2026

በእስቴ ወረዳ ድጋፍ ለሚሹ 630 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ፤

​በደቡብ ጎንደር ዞን በእስቴ ወረዳ ከየቀበሌው ለተወጣጡ እና ድጋፍ ለሚሹ 630 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።

​በበጎ ፈቃደኞች የተቀናጀ እንቅስቃሴ ከተሰበሰቡት የትምህርት ቁሳቁሶች መካከል ደብተር፣ እስክሪብቶ እና ቦርሳ የሚገኙበት ሲሆን የቁሳቁሱ አጠቃላይ ዋጋም ከ341 ሺህ ብር በላይ እንደሚገመት ተገልጿል።

​የእስቴ ወረዳ ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ተስፋየ ላዋይ በሰጡት አስተያየት ድጋፉ አቅም የሌላቸውን ወላጆች ለማገዝ እና ልጆች ከትምህርታቸው እንዳይበተኑ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸው በበጎ ፈቃድ ሥራው ለተሳተፉ አካላት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

​የእስቴ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዱኛው ጎቤ በበኩላቸው የተደረገው ድጋፍ ለተማሪዎቹ ከፍተኛ እገዛ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

​ተማሪዎቹም በተደረገላቸው ድጋፍ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

​የቁሳቁስ ድጋፍ ርክክቡ የእስቴ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሞላ አበበ፣ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ኮማንደር እህትሁን ተማች እንዲሁም የኮሚቴው አባላት በተገኙበት ተካሂዷል።



ነሐሴ 24/2018 ዓ.ም

ማስታወቂያበፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመማር ለተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ።ትምህርት ሚኒስቴር ለ2019 የትምህርት ዘመን ትምህርት በሚሰጥባቸው ነባርና አዲስ የፌዴራል ል...
30/08/2026

ማስታወቂያ
በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመማር ለተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ።

ትምህርት ሚኒስቴር ለ2019 የትምህርት ዘመን ትምህርት በሚሰጥባቸው ነባርና አዲስ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎችን አወዳድሮ ለመቀበል ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት ተመዝግባችሁ በመጠባበቅ ላይ ያላችሁና ለፈተና የተመረጣችሁ ተማሪዎች በተመዘገባችሁበት ሊንክ መለያ ኮዳችሁን ( Reference Number) በማስገባት ማየት የምትችሉ መሆኑ እንገልጻለን።

በተጨማሪም ለፈተና የተመረጣችሁ ተማሪዎች ፈተና የሚሰጠው በበየነ መረብ (online) ስለሆነ የሚቀርባችሁን የፈተና መስጫ ማዕከል በዛው ሊንክ በመግባት መምረጥ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የሙከራ ፈተና እሮብ ነሃሴ 27/2018 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን ዋና ፈተናው ነሃሴ 28/2018 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑ አውቃችሁ ዝግጅት እንድታደርጉ ለማሳሰብ እንወዳለን።

በደቡብ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ በ2018 የትምህርት   ዘመን በ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና በትምህርት ዘመኑ  ከፍተኛ ነጥብ ከ500 እና በላይ ያመጡ ተማሪዎች
29/08/2026

በደቡብ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ በ2018 የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና በትምህርት ዘመኑ
ከፍተኛ ነጥብ ከ500 እና በላይ ያመጡ ተማሪዎች

የፎገራ ወረዳ ትምህርት ፅህፈት ቤት የ2019 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባን ለመገምገም ያለመ ውይይት አካሄደ።በደቡብ ጎንደር ዞን የፎገራ ወረዳ ትምህርት ፅህፈት ቤት የ2019 የትምህ...
29/08/2026

የፎገራ ወረዳ ትምህርት ፅህፈት ቤት የ2019 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባን ለመገምገም ያለመ ውይይት አካሄደ።

በደቡብ ጎንደር ዞን የፎገራ ወረዳ ትምህርት ፅህፈት ቤት የ2019 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ለመገምገም ያለመ ውይይት የትምህርት ቤተሰቦች የወረዳ የስራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው አካላት በተሳተፉበት ውይይት አካሂዷል ።

በዚሁ ውይይት የ2019 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ያለበትን ደረጃ የሚገልፅ ሰነድ የቀረበ ሲሆን በቅድመ 1ኛ ደረጃ 13ሺ 284 ተማሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ 3ሺ 313 ተማሪዎች በመመዝገብ የእቅዱን 25 በመቶ ፤ ከ1ኛ -8ኛ ክፍል 69ሺ 119 ተማሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ 18ሺ 656 ተማሪዎች በመመዝገብ የእቅዱን 27 በመቶ እንዲሁም ከ9-12ኛ ክፍል 4ሺ 29 ተማሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ 429 ተማሪዎችን በመመዝገብ የእቅዱን 25 በመቶ በ5 ቀናት ውስጥ የተመዝገበ ሲሆን ይህ አፈፃፀምም ዝቅተኛ መሆኑን በሰነዱ ተመላክቷል።
ተሳታፊዎችም በምዝገባ ሂደት የገጠሙ ችግሮችና ጥንካሪዎችን በማንሳት ውይይት ያደረጉ ሲሆን በቀጣይ እስከ ጳጉሜ 05/2018 ዓ.ም ከችግሮች በመማርና በቅንጅት በመስራት እቅዱን ሙሉ በሙሉ መከዎን እንደሚገባ ተሳታፊዎች አመላክተዋል።

የፎገራ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊ ሙላት ፀጋየ
ትምህርት የአንድ አገር የጀርባ አጥንት የቀጣይ ትውልድም ጉዳይ ነው። የተማሪዎች ምዝገባ ዝቅተኛ አፈፃፀም የታየበት ለውጤቱም ማሽቆልቆል የትምህርት አመራሩ ቸለልተኝነትና ሁሉም መምህራን በትምህርት ገበታ በመገኘት የምዝገባ ስራውን ያለመከወን ችግር መሆኑን ያመላከቱት አቶ ሙላት በቀጣይ ከችግራችን በመማር በቅንጅትና በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የፎገራ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ማሪቱ መርአዊ ዶ/ር በትምህርት ዘርፉ የ3 ዓመታት እዳ ያለብን በመሆኑ በቀጣይ በቁጭት ልንሰራ ይገባል። ከወደቅንበት ለመነሳት የሃይማኖት አባቶችን፣የአገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ሰዎች ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ያመላከቱት ዶ/ር ማሪቱ ለአመቱ የትምህርት ስኬት አሁን የምንሰራው የተማሪ ምዘገባ መሆኑንም ተናግረዋል።

በመጨረሻም የፎገራ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የአቅም ግንባታና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ይበልጣል ጓዴ በበኩላቸው ትምህርት ወደ ስልጣኔ ማማ የምንወጣበት መሳሪያ ነው።የቀጣይ ዘመን ትውልድ በእኛ እጅ ላይ ነው እኛ ጠንክረን ከሰራን የቀጣይ ትውልድ ህይዎት ብሩህና የተስተካከለ ይሆናል ያሉት አቶ ይበልጣል ወድቆ መነሳት የጥንካሬ መገለጫ በመሆኑ ከወደቅንበት ለመነሳት ያልተጠቀምንባቸውን ጉልበቶችና እምቅ ሃብቶች መጠቀም እንደሚገባ አመላክተዋል።

#የፎገራ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን
ነሀሴ23/2018 ዓ.ም

27/08/2026
አልማ በትምህርት መሠረተ ልማት ማስፋፋት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ ነው።የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) በትምህርት ጥራትና መሰረተ ልማት ማስፋፋት ላይ እያደረገ ያለውን አስተዋጽኦ አጠናክሮ...
27/08/2026

አልማ በትምህርት መሠረተ ልማት ማስፋፋት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ ነው።

የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) በትምህርት ጥራትና መሰረተ ልማት ማስፋፋት ላይ እያደረገ ያለውን አስተዋጽኦ አጠናክሮ መቀጠሉን አስታወቀ።

ማህበሩ ከአባላቱ ባሰባሰበው ሀብት በግንባታ ሂደት ላይ ከነበሩ 2 ሺህ 797 የመማሪያ ክፍሎች መካከል 1 ሺህ 136 ያህሉን ግንባታ አጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረጉንም ገልጿል።

የማህበሩ የስትራቴጂና ኢኖቬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አበረ መኩሪያ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ማህበሩ በትምህርት ጥራትና መሰረተ ልማት ማስፋፋት ረገድ እያደረገ ያለውን አስተዋጽኦ አጠናክሮ ቀጥሏል።

ማህበሩ የልማት ክፍተቶችን በመለየት ከቅድመ መደበኛ እስከ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎችን በመገንባት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ እንዳይሆኑ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።

በቀጣይም በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኙ ያልተጠናቀቁ ቀሪ የመማሪያ ክፍሎችን በፍጥነት አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጸው፤ ለግንባታዎቹም ከ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገም ተናግረዋል።

ማህበሩ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎችን ከመገንባት ጎን ለጎን በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጪ እንዳይሆኑ ቁሳቁስ የማሟላትና የማስረከብ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

የደቡብ ጎንደር ዞን ምክትል አሰተዳዳሪ እና ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ደስታ አስራቴ በበኩላቸው፤ አልማ የትምህርት ቤቶችን ገጽታ በመቀየር እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎችን ከመገንባት ባለፈም የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶችን በማስፋፋትና የውስጥ ቁሳቁስ በማሟላት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ የድርሻውን እየተወጣ እንደሚገኝም አብራርተዋል።

በአሁኑ ወቅት የማህበሩ የአባላት ቁጥርን ከ4 ነጥብ 9 ሚሊዮን በላይ ማድረስ መቻሉንም ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ዓባይ ባንክ በትምህርት ቁሳቁስ ችግር ምክንያት መማር ለሚቸገሩ ተማሪዎች 50 ሺህ የመማሪያ ደብተሮችን ድጋፍ አደረገ።ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም /ትምህርት ቢሮ/ ዓባይ ባንክ ማኅበራዊ ኃላ...
27/08/2026

ዓባይ ባንክ በትምህርት ቁሳቁስ ችግር ምክንያት መማር ለሚቸገሩ ተማሪዎች 50 ሺህ የመማሪያ ደብተሮችን ድጋፍ አደረገ።

ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም /ትምህርት ቢሮ/ ዓባይ ባንክ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እና የትምህርት ዘርፉን ከማሳደግ አኳያ በኢኮኖሚ ጫና ምክንያት ለልጆቻቸው የትምህርት ቁሳቁስ ማሟላት ለማይችሉ ወላጆች እና ልጆች ከትምሕርት ገበታቸው እንዳይቀሩ የሚያግዝ የ50,000 ባለ50 ገጽ ደብተሮችን ለአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስረክቧል፡፡

ድጋፉ በክልሉ በተለያየ ምክንያት ትምህርታቸውን መከታተል እየፈለጉ በቁሳቁስ ዕጥረት ለተቸገሩ ተማሪዎች በፍትሐዊነት ለሁሉም ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የሚሰራጭ ነው።

የትምሕርት ቁሳቁስ ድጋፉ በአማራ ክልል መማር እየፈለጉ በአቅም ማነስ እና በሌሎች ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ችግሮች ምክንያት እገዛ ማግኘት ላልቻሉ ተማሪዋች በባንኩ መለያ በልዩ ህትመት የተዘጋጁ ደብተሮች ናቸው።

ርክክቡ ዛሬ ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በባሕርዳር ከተማ ሲካሄድ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መኳንንት አደመ ባደረጉት ንግግር፣ “የክልሉን የትምሕርት ስትራቴጂ ከማሳካት አኳያ እንደ ዓባይ ባንክ ያሉ አጋሮች የተቀናጀ ኢንቨስትመንት ከማካሄድ ባሻገር የማኅበራዊ ልማት ላይ በንቃት መሳተፍ ድርሻው ከፍ ያለ ነው” ብለዋል።

ሀገራዊ የትምህርት ዘርፋን ለማሳደግ እና የተማሪዎችን ውጤታማነት ከፍ ለማድረግ ከሚደረገው እንቅስቃሴ ጎን ለጎን እንደ ዓባይ ባንክ ያሉ ቀዳሚ የልማት እና የፋይናንስ አጋሮች የሚያደርጉት ድጋፍ ለሌሎችም ምሣሌ የሚሆን ነው ተብሏል።

ኃላፊው በክልሉ የትምህርት ዘርፍ የመሠረተ-ልማት እና የግብዓት እጥረቶችን ለመፍታት በሚያደርገው ጥረት የፋይናንስ ተቋማት እገዛ ወሳኝ መሆኑን ገልፀው፣ የዓባይ ባንክ የመማሪያ ደብተር ድጋፍም በከልሉ የተማሪዎችን የማቋረጥ ምጣኔን ለመቀነስ ለሚደረገው ጥረት ትልቅ ዐቅም ይኖረዋል ብለዋል። ድጋፋ በትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ እጥረት ወደ ትምህርት ገበታ መሄድ ያልቻሉ የክልሉ ተማሪዋችን ችግር ለመቅረፍ እና “በዚህ ችግር ወደ ትምህርት ገበታቸው ያልመጡ ተማሪዋችን ተስፋ የሚያለመልም ነው” በማለት ምስጋናቸውን ለባንኩ አቅርበዋል፡፡

የዓባይ ባንክ ስትራቴጂ ዋና መኮንን አቶ ወንድይፍራው ታደሰ ባንኩ የማኅበራዊ ልማት ዘርፉን ከማሳደግ አኳያ እያከናወነ ያለውን ድጋፍ አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል። ዓባይ ባንክ “በእያንዳንዱ የማኅበረሰብ ጎጆ ገብቶ ቀዳሚ የፋይናንስ አጋር የመሆን ፍኖት እና በቀጣዩ ትውልድ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ ዕውቀት-መር የኢንቨስትመንት አስተሳሰብ መገንባት” እየተተገበረ ያለ አቅጣጫ መሆኑን አሳውቀዋል። ባንኩ በተለያዩ ዘርፍች ማኅበረሰቡን የሚጠቅሙ እና የማህበራዊ ኃለፊነት የመወጣት ዕቅዱ አካል የሆኑ ድጋፎችን በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ለሚገኙ ተቋማት እና ዜጎች ሲያደርግ መቆየቱንም አውስተዋል።

ዓባይ ባንክ በፋይናንሱ ዘርፍ ለብዙዎች የታላቅነት ምንጭ ከመሆን ባሻገር የኮርፖሬት ማኅበራዊ ኃላፊነትን እንደ ቁልፍ ስትራቴጂያዊ የማኅበረሰብ አጋርነት እና ተቋማዊ ትሥሥር ዓላማ የሚያውል መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ዓባይ ባንክ አሁን ላይ ካደረገው የትምህርት ግብዓት ድጋፍ ባሻገር በጥቅል የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ከ4.8 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ደንበኞቹ ሰፊ የዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች በማቅረብ ግንባር ቀደም የፋይናንስ አጋር በመሆን እየሠራ መሆኑ ተጠቅሷል።

በደቡብ ጎንደር ዞን የወረታ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የትምህርት ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን ገለጸ።በደቡብ ጎንደር ዞን በወረታ ከተማ አስተዳደር  በክረምት በጎፈቃድ አ...
26/08/2026

በደቡብ ጎንደር ዞን የወረታ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የትምህርት ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን ገለጸ።

በደቡብ ጎንደር ዞን በወረታ ከተማ አስተዳደር በክረምት በጎፈቃድ አገልግሎት "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ!" በሚል መሪ ቃል ድጋፍ ለማድረግ የወረታ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ከአመራሮች የተቋማት ባለሙያዎች ገንዘብ በማሰባሰብ የትምህርት ቁሳቁስ ማለትም 100 ደርዘን ደብተርና 6 ፖኮ እስክብሪቶ ድጋፍ በማድረግ በዛሬው ዕለት ለወረታ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናት ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ማስረከቡን የወረታ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ምስጋናው ገልጸዋል።

የወረታ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናት ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ያምላክእርቅ አስፋው እንደገለፁት የከተማ አስተዳደሩ ተቋማትና ቀበሌዎች በክረምት በጎፈቃድ አገልግሎት የትምህርት ቁሳቁስ የአልባሳትና የምግብ ፍጆታ ጥሬ እቃዎችን በማሰባሰብ ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውንና በዛሬው ዕለትም የወረታ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኪኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ላደረገው የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ምስጋና አቅርበው በቀጣይ ሁሉም ቀበሌ አስተዳደሮች ና ተቋማት በክረምት በጎፈቃድ አገልግሎት የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ድጋፋቸውን አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተናግረዋል።

በርክክብ መርሃግብሩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የወረታ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ዘመነ ማንደፍሮ ና የወረታ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ደጉ በየበኩላቸው እንደተናገሩት የከተማ አስተዳደሩ ተቋማትና ቀበሌዎች የተቋማቸውን ሰራተኞችና ባለሙያዎች በማስተባበር የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ትልቅ ምስጋና ይገባቸዋል ብለው በቀጣይም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የወረታ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ቀደም ሲል ከ48 ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ የአንዲት የአቅመ ደካማ አረጋውያን ቤትን እድሳትና ጥገና አድርጎ ለአረጋውያኗ ማስረከቡ የሚታወስ ነው።

መረጃው የወረታ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን

Address

Debre Tabor
Bahir Dar

Telephone

+251584412987

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South Gondar zone Education Department /ደቡብ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to South Gondar zone Education Department /ደቡብ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ:

Shortcuts

Share