18/02/2022
✅ ሰው አፈር ነው አሉ - ታጥቦ የማይጠራ
እድፍ የሞላበት - ከጭቃ የተሰራ
✅ ሰው ሸክላ ነው አሉ - ድንገት ተሰባሪ
ወድቆ ለመነሳት - ምን ይሉኝን ፈሪ
✅ ሰው ህልም ነው አሉ - ታይቶ ማይጨበጥ
ኪዳኑን አፍርሶ - በሌላ ሚለውጥ
✅ ሰው ቅጠል ነው አሉ - ጠውላጊ ደራቂ
የሱን እልፍኝ ዘግቶ - የሰውን አድማቂ
✅ ሰው ዝንብ ነው አሉ - ከክፉም ከደጉ ከሁሉ አራፊ
መዘዝን ሰብሳቢ - በሽታን ጠላፊ
🌀 ሰው እሳት ነው አሉ -ለብልቦ ሚያቃጥል
በ አይን ተጋርፎ - በግልምጫ ሚጥል
🌀 ሰው ጊንጥ ነው አሉ - መርዛም ተናዳፊ
በምላሱ ልሶ - የሰውን ስም አጥፊ
🌀 ሰው ጅብ ነው አሉ - ሆዳም እራስ ወዳድ
አንዴ ካስቀመጡ - አላየንም ሲወርድ
🌀 ግና ሰው ብርቱ ነው አሉ - ስለ ሁሉ ታጋሽ
ተቀማጩ አይሰማው - ለ አምላኩ አልቃሽ
ሼርርርር