ANRS Public Enterprise Administration

ANRS Public Enterprise Administration Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ANRS Public Enterprise Administration, Government Organization, bahir dar, Bahir Dar.

የኢንቨስትመንት ሆልዲንግ መቋቋም ድርጅቶቹ ተወዳዳሪና ውጤታማ በመኾን አማራ ክልል እያጋጠሙት ያሉትን የምጣኔ ሃብት ችግሮች ለመቅረፍ ያስችላል፤ የልማት ድርጅቶቹ በነፃ ገበያው ላይ ተወዳድረው...
21/03/2025

የኢንቨስትመንት ሆልዲንግ መቋቋም ድርጅቶቹ ተወዳዳሪና ውጤታማ በመኾን አማራ ክልል እያጋጠሙት ያሉትን የምጣኔ ሃብት ችግሮች ለመቅረፍ ያስችላል፤

የልማት ድርጅቶቹ በነፃ ገበያው ላይ ተወዳድረው አሸናፊ መሆን እንዲችሉ በንግድ የስራ አመራር ጥበብ የሚመራ ሥርዓትን የሚመጥኑ ሁነው ሊደራጁ ይገባል፤

ድርጅቶች ለሕዝብ የሚያደርጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንዲሆን ዋናው ተልዕኳቸው ሃብት ፈጠራ ሊሆን ይገባል፤
(ክቡር ርዕሰ መስተዳደር አረጋ ከበደ)

የአማራ ክልል በመንግሥት የልማት ድርጅቶች የልህቀት ማዕከል ይኾን ዘንድ በኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ደረጃ ተቋቁሞ አዳዲስ ኢንቨስትመንት ላይ መሠማራት ይጠበቅበታል፤

የኢንቨስትመንት ሆልዲንግ "ድርጅቶች ለትውልድ ሀብት መፍጠርን ታሳቢ ያደረጉ እንዲሆኑና ከተደጋፊነት ወጥተው ራሳቸውን ችለው ትርፋማ እንዲኾኑ ያስችላቸዋል፤

የሚቋቋመው ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ አመራር መለኪያው ውጤታማነት በመሆኑ ትርፋማነት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል፤ ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)

"ልማት ድርጅቶቹ ተገቢ ካልሆነ ጣልቃ ገብነት ነጻ ሁነው በቢዝነስ አስተሳሰብ እንዲመሩ ማድረግ ያስችላል፤"

የአመራር ክህሎትን ከፍ በማድረግና ትብብርን በመፍጠር ስኬታማ እንዲኾኑ ከማስቻሉም ባሻገር የሕዝቡን የመልማት ጥያቄዎች የሚፈቱ ያደርጋቸዋል፤ /የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ዋና ሥራ አሥኪያጅና የኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ምሥረታ የጥናት ኮሚቴ ሠብሣቢ ወንዶሰን ጌታነህ/

"የልማት ድርጅቶች  ቀጣይነት ያለው ትርፍ ማስመዝገብና ሕዝብን የበለጠ ማገልገል እንዲችሉ የውስጥ አሠራራቸውን ማዘመን፤ ቴክኖሎጂን መታጠቅና ከተለምዷዊ የኮርፖሬት አሥተዳደር ስርዓት ወጥተው ...
12/03/2025

"የልማት ድርጅቶች ቀጣይነት ያለው ትርፍ ማስመዝገብና ሕዝብን የበለጠ ማገልገል እንዲችሉ የውስጥ አሠራራቸውን ማዘመን፤ ቴክኖሎጂን መታጠቅና ከተለምዷዊ የኮርፖሬት አሥተዳደር ስርዓት ወጥተው ቀልጣፋና ውጤታማ አሠራሮችን በመተግበር ተሞክሮ ሊወሰድባቸው የሚገቡ መሆን አለባቸው" ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)

"ትልቁ ችግር መውደቅ ሳይሆን ወድቆ መቅረት ነው"  የካቲት 24/2017 ዓ.ም (ኮምቦልቻ)ዘርፈ ብዙ ኪሳራዎችን ያደረሰውና የብዙዎችን ልብ የሰበረው የሰሜኑ ጦርነት በከፍተኛ ደረጃ ዳፋውን ካ...
04/03/2025

"ትልቁ ችግር መውደቅ ሳይሆን ወድቆ መቅረት ነው"

የካቲት 24/2017 ዓ.ም (ኮምቦልቻ)

ዘርፈ ብዙ ኪሳራዎችን ያደረሰውና የብዙዎችን ልብ የሰበረው የሰሜኑ ጦርነት በከፍተኛ ደረጃ ዳፋውን ካሳረፈባቸው የልማት ድርጅቶች መካከል ጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት ዋነኛው ነው።

ድርጅቱ "ትልቁ ችግር መውደቅ ሳይሆን ወድቆ መቅረት ነው" የሚለውን ሀሳብ ዕውን በማድረግ አፈር ልሶ /ወድቆ/ መነሳትን ያስተማረ ድርጅት መሆኑን የድጋፍ ቡድኑ መመልከት ችሏል።

ድርጅቱ በከፍተኛ ደረጃ የተዘረፈና ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የወደመ ቢሆንም ተስፋ ከመቁረጥ ወጥቶ የሚቻለውን ሁሉ በመሞከር የድርጅቱን ህልውና ከማስቀጠል ባለፈ በአጭር ጊዜ ውስጥ ትርፋማ መሆን የቻለ ድርጅት ሁኗል።

የቀጣይ ተወዳዳሪነቱንና ተመራጭነቱን ለማሳደግም የሰው ሀይል ስምሪቱን እንደገና የመፈተሽና የማስተካከል፣ ማሽኖችን በውስጥ አቅም እየጠገኑ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ እንዲገቡ የማድረግ፣ ተጨማሪ አዳዲስ ማሽኖችን የመግዛት እንቅስቃሴዎች፣ ከክልሉ በመውጣት በሌሎች ክልሎች ገብቶ ገበያ የማምጣትና መሠል እንቅስቃሴዎችና የተገኙ ውጤቶች እጅግ የሚበረታቱ ናቸው።

ሆኖም ግን ድርጅቱ የአደረጃጀት፣ የገንዘብ ዕጥረት፣ የዋጋ ንረት፣ የብድር አገልግሎት እጦት፣ ከጸጥታው መደፍረስ ጋር በተገናኘ እንደልብ ተንቀሳቅሶ ምርቱን ለተጠቃሚዎች ማድረስ አለመቻል፣ የራሱ የሆነ የመስሪያ ቦታ /መሬት/ አለመኖርና መሠል ጉዳዮች እንቅፋት የሆኑበት በመሆኑ የሚመለከተው አካል ሁሉ እገዛ ሊያደርግለት ይገባል እንላለን።

መልካም ጊዜ!

"ያለፈው ትውልድ በተቸገረበት ችግር፤ መጪው ትውልድ እንዳይቸገር፤ ተረኛው ትውልድ የለውጥ መሸጋገሪያ ድልድይ ሊሆን ይገባል!"  የካቲት 24/2017 ዓ.ም (ኮምቦልቻ) የዘመን ኮንስትራክሽን ...
03/03/2025

"ያለፈው ትውልድ በተቸገረበት ችግር፤ መጪው ትውልድ እንዳይቸገር፤ ተረኛው ትውልድ የለውጥ መሸጋገሪያ ድልድይ ሊሆን ይገባል!"

የካቲት 24/2017 ዓ.ም (ኮምቦልቻ)

የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ምስራቅ አማራ ቅ/ጽቤት "ያለፈው ትውልድ በተቸገረበት ችግር፤ መጪው ትውልድ እንዳይቸገር፤ ተረኛው ትውልድ የለውጥ መሸጋገሪያ ድልድይ ሊሆን ይገባል!" የሚል ሃሳብን አንግቦ ለትውልድ የሚተላለፉ ጥሪቶችን በጥራት እየገነባ ዘመን አይሽሬ አሻራውን እያሳረፈ ይገኛል።

ቅ/ጽቤቱ በአሁኑ ስዓት ከ22 በላይ ፕሮጀክቶችን ይዞ በጥራት እየገነባ የሚገኝ ከመሆኑም ባሻገር በላፋት ሰባት ወራት ውስጥ ብቻ ገበያ ማፈላለግ ላይ በትኩረት በመስራት አምስት አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ውል በመያዝ ለሌሎች የልማት ድርጅቶችም ተሞክሮ መሆን የሚችል ተግባር አከናውኗል።

የድጋፍ ቡድኑ በመስክ ምልከታው የጎበኛቸው የደሴ ዲያግኖስቲክ ሆስፒታል ግንባታ፣ የአባይ ባንክ ደሴ ዲስትሪክት ቢሮ ግንባታ፣ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን/አሚኮ/ ደሴ ቅርንጫፍ ቢሮ ግንባታ፣ የኮርፖሬሽኑ ምስራቅ አማራ ቅ/ፅ/ቤት ቢሮ ግንባታና የኮርፖሬሽኑ የደሴ የግንባታ ግብዓት ማምረቻ ድርጅት ውጤታማ አፈፃፀም እንዳላቸው መመልከት ተችሏል።

በተለይም ደግሞ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን/አሚኮ/ ደሴ ቅርንጫፍ ቢሮ ግንባታ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ከተያዘለት የውለታ ጊዜ ቀድሞ በመጨረስ ለማስረከብ እየተደረገ ያለው ርብርብ ለሌሎች ፕሮጀክቶችም ለአርአያነት መቅረብ የሚችል ነው።

በተመሳሳይም የደሴ ግንባታ ግብዓት ማምረቻ ድርጅት ግብዓቶችን በጥራት በማምረት "ያገሩን ሰርዶ በአገሩ በሬ" እንዲሉ የኮርፖሬሽኑ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ መጠናቀቅ እንዲችሉ ጉልህ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል።

በአጠቃላይ ኮርፖሬሽኑ በ2030 በኮንስትራክሽን ዘርፉ በምስራቅ አፍሪካ ደረጃ ተወዳዳሪና ተመራጭ ለመሆን የሚያስችሉ በርካታ የሪፎርም ስራዎችን በመስራት አመርቂ ውጤቶችን እያስመዘገበ ይገኛል።

መልካም የስራ ጊዜ!

የመስክ ምልከታና የአካል ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል።              **********     (የካቲት /2017 ዓ.ም ኮምቦልቻ)በምስራቅ አማራ የሚገኙ የመንግሥት ልማት ድርጅቶችን፣ ቅ/ፅቤ...
02/03/2025

የመስክ ምልከታና የአካል ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
**********
(የካቲት /2017 ዓ.ም ኮምቦልቻ)

በምስራቅ አማራ የሚገኙ የመንግሥት ልማት ድርጅቶችን፣ ቅ/ፅቤቶችንና ፕሮጀክቶችን በመደገፍና በመከታተል ላይ የሚገኘው የድጋፍ ቡድን ባለፋት ተከታይ ቀናት የውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ምስራቅ አማራ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፣ የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ኮምቦልቻ ዘር ማበጠሪያ ማዕከልና የአብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት ምስራቅ አማራ ቅ/ጽ/ቤትን ተመልክቷል።

ድርጅቶቹ ወቅታዊ ሁኔታውን ተቋቋመው ትርፋማ ለመሆን እያደረጉት ያለው እንቅስቃሴ እጅግ የሚበረታታ ቢሆንም ከፀጥታው መደፍረስ ጋር በተያያዘ እንደልብ ተንቀሳቅሶ መሥራት አለመቻ'ሉ ከፈጠረው የስራ መቀዝቀዝ ባለፈ ስርዓት አልበኝነት፣ የፍርድ ቤቶች ውሳኔ አሰጣጥ ችግር፣ የግብዓት አቅርቦት ዕጦት፣ አሰሪዎች የቅድመና ዙር ክፍያዎችን በወቅቱ መክፈል አለመቻል፣ የክልል ፕሮጀክቶች ዋጋ ማሻሻያ አለመደረግ፣ የመለዋወጫ ችግር፣ የነዳጅ እጥረት፣ ድርጅቶችን በቢዝነስ አስተሳሠብ ቃኝቶ መምራት አለመቻል፣ ፕሮጀክቶችን በጊዜ ማጠናቀቅ አለመቻል፣ ከዋና ቢሮዎች ጋር በሚገባ ተቀናጅቶና ተናቦ የመስራት ውስንነት፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክፍተት፣ የህዝብ ግንኙነትና የገጽታ ግንባታ ስራዎችን ትኩረት ሰጥቶ አለማከናወንና መሠል ጉዳዮች የሚፈለገውን ያህል ውጤት እንዳይገኝ ያደረጉ ማነቆዎች እንደሆኑ መታዘብ ተችሏል።
በአጠቃላይ የድጋፍ ሂደቱ በኮምቦልቻና ደሴ ከተሞች እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶች ያሉበትን ደረጃ ተዘዋውሮ ከመመልከት ባለፈ በየስራ ዘርፉ ያለው የስራ እንቅስቃሴ ምን እንደሚመስል በዝርዝር የተገመገመ ሲሆን መልካም አፈጻጸሞች የበለጠ እንዲጠናከሩ መስተካከል ያለባቸው ደግሞ እንዲስተካከሉ አቅጣጫዎችን የማሳየት ስራዎች ተሰርተዋል።

መልካም ጊዜ!!

ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የልማት ድርጅቶችን ለይቶ ልዩ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ!(የካቲት 2017 ዓ.ም ኮምቦልቻ)በምስራቅ አማራ በሚገኙ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች፣ ቅ/ፅቤቶችና ፕ...
01/03/2025

ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የልማት ድርጅቶችን ለይቶ ልዩ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ!

(የካቲት 2017 ዓ.ም ኮምቦልቻ)

በምስራቅ አማራ በሚገኙ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች፣ ቅ/ፅቤቶችና ፕሮጀክቶች ላይ የመስክ ምልከታ በማድረግ ላይ የሚገኘው የድጋፍ ቡድን የልማት ድርጅቶችን እንደየስራ ባህሪያቸው ለይቶ ልዩ ድጋፍ ማድረግ የሚገባ መሆኑን መገንዘብ ችሏል።

በ2012 ዓ.ም ከተከሰተው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በቀጠለው ክልላዊ፣ አገራዊና ዓለምአቀፍዊ ቀውስ ምክንያት ዳፋው ካረፈባቸው የልማት ድርጅቶች መካከል ኮምቦልቻ ዶሮ ሀብት ልማት ኢንተርፕራይዝ ዋነኛው ነው።

ከፀጥታዉ መደፍረስ ጋር በተገናኘ እንቁላል፣ የርቢና የምግብ ዶሮዎችን፣ በተለይም ደግሞ የአንድ ቀን ጫጩቶችን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እንደልብ ተንቀሳቅሶ ማድረስ እጅግ ፈታኝ ሁኖበታል።

ኢንተርፕራይዙ በአሁኑ ስዓት በዋጋ፣ በጥራት፣ በዝርያ፣ በቴክኖሎጂ አጠቃቀምና መሠል ጉዳዮች ተወዳዳሪ መሆን እየቻለ አይደለም።
ለዚህ ደግሞ የአደረጃጀት/የመዋቅር/ ችግር፣ የጥሬ ገንዘብ ዕጥረት፣ የመኖ አቅርቦት ዋጋ መናርና በቅርብ ማግኘት አለመቻል፣ የዋጋ ንረት፣ የብድር አገልግሎት እጦት፣ ከጸጥታ መደፍረስ በዘለለ እንቁላልና የአንድ ቀን ጫጩቶችን እንደልብ ተንቀሳቅሶ ለተጠቃሚዎች ማድረስ አለመቻልና መሠል ጉዳዮች "በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ" የሚለው ብሂል እውን እንዲሆን ገፊ ምክንያቶች ናቸው።

ሆኖም ግን ቀውሱን ተቋቁሞ ወደ ትርፋማነት ለመምጣት እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ "ይበል" የሚያሰኝ ስለሆነ የከተማ አስተዳደሩ፣ የግብርና እና እንስሳት ሀብት ልማት ዘርፍ ተቋማት፣ የፀጥታ አካላት፣ የስራ አመራር ቦርድ አባላት፣ የልማት ድርጅቶች አስተዳደርም ሆነ ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ልዩ ድጋፍ በማድረግ ቢያጠናክሩት ከክልል አልፎ ለአገር መትረፍ የሚችልና እምቅ ሀብቶች ያሉት ተስፈኛ ድርጅት መሆኑን የድጋፍ ቡድኑ ማረጋገጥ ችሏል።

በአጠቃላይም ህይወት ያለው የሚታመምና የሚሞት ነገርን ማስተዳደርና ህይወት የሌለው የማይታመምና የማይሞት ነገርን ማስተዳደር ሰፊ ልዩነት ያላቸው በመሆኑ ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የልማት ድርጅቶችን ለይቶ ልዩ ድጋፍ ማድረግ የሚገባ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል ሲል የድጋፍ ቡድኑ ለመጠቆም ይወዳል።

መልካም ጊዜ!

የመንግስት ልማት ድርጅቶች የእርስ በዕርስ ትስስራቸውን የበለጠ ሊያጠናክሩ እንደሚገባ ተጠቆመ።     (የካቲት 19/2017 ዓ.ም ኮምቦልቻ)በምስራቅ አማራ በሚገኙ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች፣...
26/02/2025

የመንግስት ልማት ድርጅቶች የእርስ በዕርስ ትስስራቸውን የበለጠ ሊያጠናክሩ እንደሚገባ ተጠቆመ።

(የካቲት 19/2017 ዓ.ም ኮምቦልቻ)

በምስራቅ አማራ በሚገኙ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች፣ ቅ/ፅቤቶችና ፕሮጀክቶች ላይ የመስክ ምልከታ በማድረግ ላይ የሚገኘው የድጋፍ ቡድን እስካሁን ባለው ሂደት የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ፣ የኮምቦልቻ ዶሮ ሀብት ልማት ኢንተርፕራይዝና የአማራ ብረታብረት ኮምቦልቻ የእርሻ መሳሪያዎችና ማሽን ማምረቻ ፋብሪካን የተመለከተ ሲሆን ካለፈው በጀት ዓመት አፈጻጸም አንፃር ሲታይ ባለፉት ወራት መልካም የሚባሉ ውጤቶች የተመዘገቡ መሆኑን መገንዘብ ተችሏል።

ሆኖም ግን የገንዘብ ዕጥረት፣ የግብአት አቅርቦት፣ የዋጋ ንረት፣ ከጸጥታ መደፍረስ ጋር በተያያዘ እንደልብ ተንቀሳቅሶ መስራት አለመቻል /የትራንስፖርት ችግር/ እና መሠል ችግሮች የሚፈለገውን ያህል ውጤት እንዳይገኝ ያደረጉ ምክንያቶች መሆናቸውን መረዳት ተችሏል።

ድርጅቶቹ በተለይም ደግሞ የገበያ ትስስር በመፍጠር፣ የገንዘብና የማሽነሪ ውሰት በማድረግ ተባብሮ በመስራት አብሮ ለማደግ እያደረጉት ያለው እንቅስቃሴ አበረታች በመሆኑ ካልተገባ ፉክክርና ክርክር በመውጣት የመነቃቀፍን ሳይሆን የመደጋገፍ ባህልን ለማዳበር እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ መልካም በመሆኑ የበለጠ ሊዳብር ይገባዋል ሲል የድጋፍ ቡድኑ ለመጠቆም ይወዳል።

መልካም ጊዜ!!

በምስራቅ አማራ በሚገኙ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች፣ ቅ/ፅቤቶችና ፕሮጀክቶች የመስክ ምልከታና ድጋፍ መካሄድ ጀመረ። የካቲት 18/2017 ዓ.ም (ኮምቦልቻ)ከአብክመ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ...
25/02/2025

በምስራቅ አማራ በሚገኙ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች፣ ቅ/ፅቤቶችና ፕሮጀክቶች የመስክ ምልከታና ድጋፍ መካሄድ ጀመረ።

የካቲት 18/2017 ዓ.ም (ኮምቦልቻ)

ከአብክመ የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር የተወጣጣ የድጋፍ ቡድን በምስራቅ አማራ የሚገኙ የልማት ድርጅቶች በ2017 በጀት ዓመት ባለፉት ሰባት ወራት የተከናወኑ ተግባራትን መሠረት ያደረገ የአካል ድጋፍና የመስክ ምልከታ ማካሄድ ጀምሯል።

የመስክ ምልከታውና የአካል ድጋፉ አላማ ባለፉት ወራት የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት መስተካከል ያለባቸው እንዲስተካከሉና በየድርጅቶች ያሉ የተሻሉ ልምዶችንና ተሞክሮዎችን ማለዋወጥን ታሳቢ ያደረገ ነው።

በመጀመሪያው ቀን በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ በመገኘት አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴው ምን እንደሚመስል በዝርዝር በመፈተሽና በመወያየት ጠቃሚ ግብዓቶችን መውሰድ ተችሏል።

በቀጣይ ቀናትም የቀሪ ድርጅቶች ዋና ቢሮዎች፣ ቅርንጫፎችና የተመረጡ ፕሮጀክቶች የሚታዩ ይሆናል።

መልካም ጊዜ!!

ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን /"DELIVERING EXCELLENCE"/ የካቲት 15/2017 ዓ.ም  (ባሕርዳር)የቀድሞው የአማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት የአሁኑ ዘመን ኮንስትራክ...
23/02/2025

ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን /"DELIVERING EXCELLENCE"/

የካቲት 15/2017 ዓ.ም (ባሕርዳር)

የቀድሞው የአማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት የአሁኑ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የስያሜ ለውጥና የንግድ መለያ ምልክት ትውውቅ መርሐግብር አካሂዷል።

በመርሐግብሩ መክፈቻ ኮንስትራክሽን ዘርፉ በርካታ ሳንካዎች ያሉበት ቢሆንም ወቅታዊ ሁኔታውን ታሳቢ ያደረገ የቀውስ ጊዜ ዕቅድ አቅዶ ወደተግባር በመግባት ትርፋማ እየሆነ የመጣና በርካታ የሪፎርም ስራዎችን በመስራት በ2030 በኮንስትራክሽን ዘርፉ በአፍሪካ ደረጃ ተወዳዳሪና ተመራጭ ለመሆን የሚያስችሉ በርካታ ስራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታደሰ ግርማ ገልጸዋል።

የኮርፖሬሽኑ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማእረግ የከተማ ልማት ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አህመዲን መሀመድ (ዶ.ር) በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑን እንደ ስሙ የዘመነ ለማድረግ የአሰራርና መመሪያ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ፣ ብቁና የሰለጠነ የሠው ሀይል እንዲፈጠር፣ ቴክኖሎጂን የማፍለቅ አልያም የማምጣት፣ ሁለንተናዊ ትብብርን የሚያጠናክሩ ስራዎችን የመስራትና የቅርብ ድጋፍና ክትትል በማድረግ "Delivering Excellence" የሚለው የኮርፖሬሽኑ መሪ ቃል ወደተግባር እንዲቀየር የስራ አመራር ቦረድ አባላት በትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የዕለቱ የክብር እንግዳ የአማራ ክልል ምክርቤት ዋና አፈጉባዔ ክብርት ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬ በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ ልዩ ልዩ የመሠረተ ልማት አውታሮችን በጥራት ገንብቶ በማስረከብ የገበያ ክፍተትን ከመሙላቱም ባሻገር ማህበራዊ ሃላፊነትን በመወጣት በኩል በሚፈለገው ጊዜና ቦታ ሁሉ ፈጥኖ ደራሽ በመሆን ያበረከተው አስተዋጽኦ እጅግ የሚያስመሰግነው መሆኑን በመግለጽ ወደፊትም ተወዳዳሪነትንና ተመራጭነትን ተሳቢ ባደረገ መልኩ አጠናክሮ ሊቀጥልበት ይገበዋል ሲሉ ገልጸዋል።
አያይዘውም የማንኛውም ተቋምም ይሁን ድርጅት ትልቁ ሀብቱ ሰው ስለሆነ ኮርፖሬሽኑ ሰው ለይ /ሰው ተኮር/ ስራዎችን በትኩረት መስራት ይገባዋል ሲሉ ጠቁመዋል።

እኛም በበኩላችን "ዘመን ተሻጋሪ ግንባታ መለያችን ነው!" የሚለውን መሪ ሀሳብ ወደተግባር ለመቀየርና ስሙን የሚመጥኑ ተግባራትን በማከናወን ዘመን የማይሽረው አሻራውን እንዲያሳርፍ የሁሉም አካላት ቅንጅትና ትብብር ያስፈልጋል የሚል መልዕክት እያስተላለፍን መልካም የስኬት ጉዞ ማለትን እንወዳለን።

መልካም ጊዜ!!

የልማት ድርጅቶች የአደረጃጀት፣ የስያሜና የሎጎ ለውጥ ከማድረግ በዘለለ ሁለንተናዊ ለውጥ ሊያደረጉ ይገባል!የካቲት 13/2017 ዓ.ም  (ባሕርዳር)የቀድሞው የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት የአ...
20/02/2025

የልማት ድርጅቶች የአደረጃጀት፣ የስያሜና የሎጎ ለውጥ ከማድረግ በዘለለ ሁለንተናዊ ለውጥ ሊያደረጉ ይገባል!

የካቲት 13/2017 ዓ.ም (ባሕርዳር)

የቀድሞው የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት የአሁኑ ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የአደረጃጀት፣ የስያሜና የሎጎ ለውጥ ይፋዊ የማስተዋወቂያና የሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር አካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው የስራ አቅጣጫ ያስቀመጡት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ ኮርፖሬሽኑ የመንግሥትን ችሮታ ከመጠበቅ ወጥቶ ተወዳድሮ ማሸነፍን ታሳቢ ያደረገ ስራ ሊሠራ ይገባዋል ሲሉ ገልጸዋል።

ለዚህም ፈጠራ፣ ተወዳዳሪነት፣ የደንበኞች እርካታ፣ የአመለካከት ግንባታ፣ ምቹ የስራ ባህል ፈጠራና በውጤታማነት የመፈጸም አቅምን ማሳደግ ላይ ማተኮር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በርካታ ፈተናዎችን አልፎ እዚህ የደረሰው ኮርፖሬሽኑ "ነገን እንገነባለን" የሚለውን ምናባዊ ሀሳብ/መሪ ቃል/ ወደ ዕውናዊነት ሊቀይረው ይገባል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው አስረድተዋል።

በአጠቃላይ የልማት ድርጅቶች የአደረጃጀት፣ የስያሜና የሎጎ ለውጥ ከማድረግ ባለፈ የአመራር፣ የስራ በህል፣ የቴክኖሎጂ፣ ተወዳዳሪነትንና መሰል ጉዳዮችን ታሳቢ ያደረገ ሁለንተናዊ ለውጥ ሊያደረጉ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።

መልካም የስኬት ጉዞ!!

በአማራ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪና ማሽን ቴክኖሎጅ ልማት ኢንተርፕራይዝ በባህር ዳር ከተማ የተመረቱ ስማርት ፖሎች፣ የዲች ከቨሮች እና ሌሎች ምርቶች በክልሉ እየተሰሩ ላሉ የኮሪደር ልማቶች  ጥ...
20/02/2025

በአማራ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪና ማሽን ቴክኖሎጅ ልማት ኢንተርፕራይዝ በባህር ዳር ከተማ የተመረቱ ስማርት ፖሎች፣ የዲች ከቨሮች እና ሌሎች ምርቶች በክልሉ እየተሰሩ ላሉ የኮሪደር ልማቶች ጥቅም ላይ መዋል ጀምረዋል።
(ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ)

በጥናትና ዲዛይን፣ በማማከርና ቁጥጥር ዘርፍ ተወዳዳሪና ተመራጭ ለመሆን እየተጋ የሚገኘው "ልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን"  የካቲት 03/2017 ዓ.ም (ባህርዳር)ኮርፖሬሽኑ በውሃ፣ መ...
11/02/2025

በጥናትና ዲዛይን፣ በማማከርና ቁጥጥር ዘርፍ ተወዳዳሪና ተመራጭ ለመሆን እየተጋ የሚገኘው "ልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን"

የካቲት 03/2017 ዓ.ም (ባህርዳር)

ኮርፖሬሽኑ በውሃ፣ መስኖና ኢነርጅ ዘርፍ የመስኖ፣ የመጠጥ ውኃና የመሬት አጠቃቀምና አካባቢ ጥናት ሥራዎችን፤ በትራንስፖርት መሰረተ ልማትና ህንፃ ዘርፍ ደግሞ የህንፃ፣ የመንገድና የድልድይ ፕሮጀክቶችን ከማከናወን በተጨማሪ የውኃ ሀብት መገኛ ጥናት፣ የላብራቶሪ አገልግሎትና የቅየሳ ተግባራትን በማከናወን አይተኬ ሚናውን እየተወጣ ይገኛል።

የቀድሞዎቹ የአማራ ዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች ድርጅትና የመንገድና ህንጻ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ሥራዎች ድርጅት መዋሀድ የስራ ድግግሞሽን በማስቀረት፣ የስራ ኃላፊዎችን በ50% በመቀነስ፣ የተበታተነውን ሀብት ወደአንድ በማሰባሰብ፣ በርካታ የአሰራር ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር በኩል ያበረከተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን መረዳት ተችሏል።

ኮርፖሬሽኑ እየሰራቸው ያሉ የግቢ ማስዋብ፣ የቢሮ ዕድሳትና ማስፋፊያ ስራዎች፣ የERP ሶፍትዌር ልማት ስራዎች፣
ሁሉም ተግባራት በስታንዳርድ እንዲመሩ ለማድረግ የተሠራው ስራ፣ ከሌሎች የልማት ድርጅቶችና ተቋማት ጋር ያለው መልካም ግንኙነትና መሠል ተግባራት ለተሞክሮነት የሚቀርቡ መሆናቸውን የድጋፍ ቡድኑ መመልከት ችሏል።

በተለይም ደግሞ ገበያን ከማስፋት አንጻር ከክልሉ ባለፈ ቤንሻንጉል፣ ሲዳማና አፋር ክልሎች መግባት መቻሉ የሚበረታታና ወደምስራቅ አፍሪካ ለመግባት የሚደረገውን ጉዞ የሚያፋጥን መልካም ጅማሮ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባዋል።

መልካም ጊዜ!!

Address

Bahir Dar
Bahir Dar

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 11:30
Wednesday 09:00 - 11:30
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+2510583203556

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ANRS Public Enterprise Administration posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ANRS Public Enterprise Administration:

Share