የአብክመ ገቢዎች ቢሮ -ANRS Bureau's of Revenues

የአብክመ ገቢዎች ቢሮ -ANRS Bureau's of Revenues Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የአብክመ ገቢዎች ቢሮ -ANRS Bureau's of Revenues, Government Organization, Bahir Dar.

የህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በበጀት ዓመቱ 50 ቢሊዮን ብር እንደሚሰበስብ አስታወቀበአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ የህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የ2018...
28/08/2026

የህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በበጀት ዓመቱ 50 ቢሊዮን ብር እንደሚሰበስብ አስታወቀ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ የህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ አደረገ።

በመድረኩ የአብክመ ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ አቶ አታላይ ጥላሁንን ጨምሮ ሁሉም የም/ቢሮ ኃላፊዎች፣ የሚመለከታቸው ዳይሬክተሮች እና የዘርፉ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን አዲስ ተቋም ሲመሰረት ፈተና እና እድሎችም እንዳሉት የገለጹት ቢሮው ኃላፊው አቶ አታላይ ጥላሁን በሚፈለገው ደረጃ ተገቢ ስራ በመስራት ጠንካራ ተቋም መገንባት እድል እንደሚሆን በማስታወቅ የተቋቋመውን ተቋም በአግባቡ በማደራጀት ውጤታማ እንዲሆን ከወዲሁ አስቦ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

የአማራ ክልል የህብረተሰብ ተሳትፎ በ6 ዓለማዎች ላይ ተመስርቶ የሚሰራ እንደሆነ የጠቆሙት ቢሮ ኃላፊው አቶ አታላይ ጥላሁን ልማት በመንግስት ብቻ ስለማይመጣ ህብረተሰቡን በማሳተፍ እና የልማቱ ባለቤት በማድረግ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

በ2018 በጀት ዓመት በክልሉ በህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፈቃድ አገልግሎት እስከ 50 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅድ የተያዘ ሲሆን እቅዱ የታሰበውን ግብ ያሳካ ዘንድ ህብረተሰቡ የተሻለ የሚጠቅመውን የልማት ስራ መርጦ እንዲሰራ በማድረግ፣ ህበረተሰቡን በአግባቡ በማሳመንና በማሳተፍ መስራት እንደሚገባም አቶ አታላይ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

አቶ አታላይ አክለውም የእቅዱን ግቦች ለማሳካት የምንከተላቸውን የማስፈጸሚያ ስልቶች በአግበቡ በመያዝ ወደ ስራ መግባትና የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ስራን በአግባቡ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ለክልላችን ህዝብና ለሚመለከታቸው አጋር አካላት ተገቢ ግንዛቤ በመፍጠር ውጤታማ አፈጻጸም እንዲኖር ሁላችንም የድርሻችንን በመወጣት ለክልላችን ልማት መስራት ይገባል ሲሉ ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡

በሌላ በኩል የህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወርቁ ያየህ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመትን እቅድ ትውውቅ አቅረበው ያስገመገሙ ሲሆን በመድረኩ በተሰጠው ግብዓት መሰረት እቅዱን የበለጠ በማጠናከር ተዘጋጂቶ ለዞኖችና ወረዳዎች ጭምር በማውረድ እንደሚሰሩ አስታውቀዋል

፤ሁሉም የክልሉ ህዝብና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለዘርፉ ውጤታማነትና ስኬት የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል፡

የግብር ከፋዮች ስልጠናና የድጋፍ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ተገለጸነሐሴ 22/2018 ዓ.ም (አማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ)የክልል ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች በአዲሶቹ የገቢ ግብር አዋጆችና የ...
28/08/2026

የግብር ከፋዮች ስልጠናና የድጋፍ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ተገለጸ

ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም (አማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ)
የክልል ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች በአዲሶቹ የገቢ ግብር አዋጆችና የንግድ ገቢ ግምት ጥናት ዙሪያ በዞን መምሪያዎች፣ በሜትሮፖሊታን መምሪያዎች፣ በከተሞች እና ወረዳ ገቢ ጽህፈት ቤቶች ተሰማርተው የገቢ አሰባሰብ ሂደቱን አሳልጠዋል፣ የግብር ትምህርትና ቅስቀሳ ስራ ሰርተዋል።

በተፈጠሩ መድረኮች፤ ለደረጃ “ሀ” እና “ለ” ግብር ከፋዮች፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች እና ለነዋሪው ህዝብ ስለግብር አስፈላጊነት፣ ባለፈው በጀት ዓመት የተሰበሰበው ገቢ አገልግሎት እና የአዲሱ በጀት ዓመት የገቢ ዕቅድ ግንዛቤ ተሰጥቷል።

የዞን አስተዳዳሪዎች፣ ከንቲባዎች እና የፓርቲ ኃላፊዎች ማህበረሰቡን በማወያየት ግብር ከህዝብ ለህዝብ አገልግሎት የሚውል መሆኑን በማስገንዘብ ከፍተኛ ተሳትፎ አድርገዋል።

ግብር ከፋዮች የተሰጣቸውን ገለጻ አድንቀው ተከታታይ ግንዛቤ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

ያለደረሰኝ ከሚገዙ ነጋዴዎች ጋር አለመመጣጠን፣ የግብዓት ታክስ አወራረድ እና በሌሎች ስም ስለሚፈጸሙ ሽያጮች የተነሱ ጥያቄዎች ተለይተው በቂ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቷል።

ቢሮው ከተለመደው የሩቅ ክትትል ወጥቶ የክልል ልዩ ስልጠናና ክህሎት ያላቸው አመራሮችንና ባለሙያዎችን በቀጥታ እስከ መምሪያ እና ገቢ ጽ/ቤት ድረስ በማውረድ የቅርብ ድጋፍና ክትትል ማድረግ የክልሉን ገቢ ዓቅም በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሳድገው ታምኖበታል።

በመድረኮቹ ከተደረጉ ውይይቶች ባለፈ፣ ግብር ሰብሳቢው አካል እና ግብር ከፋዮች ለየዞኑና ለከተማው ልማት የሚውል ገቢ በትክክል እና በፍትሃዊነት እንዲሰበሰብ የጋራ መግባባትና ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ከተነሱት የግብዓት ታክስ አወራረር እና የገበያ ውድድር አለመመጣጠን ጋር የተያያዙ ክፍተቶችን ለመቅረፍ ቀጣይነት ያለው የባለድርሻ አካላት ውይይትና የህግ ማብራሪያ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

በደሴ ገላው

በአዊ ብሔሰብ ዞን በ2019 በጀት ዓመት ከ6.4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን አቶ ፈጠነ ጥላሁን ገለፁየአዊ ብሄ/አስ የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ20...
26/08/2026

በአዊ ብሔሰብ ዞን በ2019 በጀት ዓመት ከ6.4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን አቶ ፈጠነ ጥላሁን ገለፁ

የአዊ ብሄ/አስ የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ ከሚመለከታቸው ጋር አካሄዷል።

የአዊ ብሔረሰብ ዞን መምሪያ ሃለፊ ፈጠነ ጥላሁን በ2019 በጀት ዓመት የዞኑን ብሎም የክልሉን ሕዝብ የልማት ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ከ6.4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዷል ብለዋል።

የታቀደው ገቢ ከመደበኛ ገቢ 5,051,612,986 ብር እና ከከተማ አገልግሎት ገቢ 1,421,911,643 በድምሩ 6,473,524,629 ብር የሚሰበሰብ እንደሆነ ተናግረዋል።

በዚህም በ2019 በጀት ዓመት የብሄረሰብ አስተዳደሩን ህዝብ የልማት ተጠቃሚነት የሚያግዝ የገቢ እቅድ መታቀዱን ገልጸው 80 በመቶ የሚሆኑ የገቢ አሰባሰብ ስራዎች ከወረቀት ንክኪ ነፃ በሆነ ይሰራልም ብለዋል።

የደረሰኝ አጠቃቀም ሥርዓቱን ለማስተካከል እና ብልሹ አሠራሮችን ለማረም ሰፊ ሥራ እንደሚከናወንም ጠቁመዋል።

በመድረኩ የተገኙት የአዊ ብሄ/አስ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አለሙ ሰውነት የታቀደውን የገቢ እቅድ ለማሳካት ሁሉም አመራር ሰራተኛ እና ባለድርሻ አካላት የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል ፡፡

በተለይም የተቋሙ ሰራተኛ የሕዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ታሳቢ በማድረግ በኃላፊነት ስሜት መሥራት እንዳለባቸውም ተናግረዋል ።

ዕቅዱ እንዲሳካ የባለድርሻ አካላት ቅንጅትና በየደረጃው ያለው አመራር ገቢ የመሰብሰብ ሥራን የሥራዎች ሁሉ ቀዳሚ ተግባር አድርጎ ሊደግፉ እንደሚገባ አስገንዝበዋል
መረጃው የመምሪያው ግብር ትምህርትና ኮሙኒኬሽን ስራ ሀደት ነው

የጎንደር ከተማ ገቢዎች መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት 8.8 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰበ ማቀዱን ኣሳወቀበ17/12/2018 (የጎንደር ከተማ ገቢዎች መምሪያ) ከመምሪያ እና ከክፍለ ከተማ ማኔጅመንት...
24/08/2026

የጎንደር ከተማ ገቢዎች መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት 8.8 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰበ ማቀዱን ኣሳወቀ

በ17/12/2018 (የጎንደር ከተማ ገቢዎች መምሪያ) ከመምሪያ እና ከክፍለ ከተማ ማኔጅመንት አባላት ጋር የ2019 በጀት ዓመት አጠቃላይ የዕቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄዷል።

በመድረኩ ላይ የተቋሙ የማኔጅመንት አባላት፣ የክፍለ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የክፍለ ከተማ ማኔጅመንት አባላት እና የክልል ደጋፊ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ሰነድ በመምሪያው የእቅድ ዝግጅትና ክትትል ባለሙያ የሆኑት አቶ አየልኝ ዱቤ አቅርበዋል።

የመምሪያ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ጥሩየ አትክልት እንደገለጹት የጎንደር ከተማ ገቢዎች መምሪያ የእቅዱን ትኩረት በበጀት ዓመቱ በክልል ደረጃ የተሠጠውን የ8.8 ቢሊዮን ብር ከፍተኛ የገቢ መሰብሰብ ግብ ለማሳካት የሚያስችሉ የግብር ከፋይ መሰረትን ማስፋት፣ የአሰራር ማሻሻያዎችን የሰነድ አጠቃቀም በማዘመን የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ማጠናከር፣ እና የማኔጅመንት ቁርጠኝነት የመምሪያው እና የክፍለ ከተማ ማኔጅመንት አባላት የተጣለባቸውን ሀገራዊ ኃላፊነት በቁርጠኝነት ለመወጣትና የዕለት ተዕለት የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን አጠናክረው ማስቀጠል እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ተሳታፊ የሆኑት የገቢ ጽ/ቤት ኃላፊዎችም የ2019 የበጀት ዓመት እቅድ ከባለፈው ዓመት በእጥፍ እንደጨመረና በጣም ከፍተኛ እንደሆነ ለማሳካትም የሚያጋጥሙ ችግሮችን አንስተው እቅዱን መውሰዳቸውን ገልጸዋል።

በአጠቃላይ የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ከወረቀት ወደ መሬት ለማውረድና የተሳካ ውጤት ለማስመዝገብ ከባለድርሻ አካላትና ከሠራተኞች ጋር ያለው ቅንጅት በማጠናከር በቁርጠኝነትና በባለቤትነት ስሜት ወደ ስራ መግባት እንደሚገባ ገልጸው ውይይቱን አጠቃለዋል።

መረጃው፤ የመምሪያው ግብር ትምህርትና ኮሙኒኬሽን ስራ ሂደት ነው

የደሴ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት 8.2 ቢሊየን ገቢ ለመሰብሰብ ዕቅድ ይዞ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ። የደሴ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት...
22/08/2026

የደሴ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት 8.2 ቢሊየን ገቢ ለመሰብሰብ ዕቅድ ይዞ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።

የደሴ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ አካሂዷል።

የደሴ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሽመልስ ጌታቸው በመድረኩ እንደገለጹት የከተማዋን ገቢ በአግባቡ ለመሰብሰብ በተቀናጀና በተጠናከረ አሠራር መስራትና የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን ማሻሻል ይገባል ብለዋል።

በገቢ አሰባሰብ ሂደት የሚታዩ ችግሮችን በጋራ በመፍታትና የተጠናከረ ክትትል በማድረግ የከተማዋን የልማት እንቅስቃሴ ማሳካትና ከተማዋን ወደተሻለ የልማት ደረጃ ማሸጋገር እንደሚገባ አቶ ሽመልስ ጌታቸው አስገንዝበዋል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የደሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ስራ አስኪያጅ አቶ ቃሲም አበራም በሰጡት አስተያየት በ2018 በጀት ዓመት በተመዘገበው የገቢ አፈጻጸም የታዩ ችግሮችና የተገኙ ልምዶችን በጥልቀት በማየት በ2019 በጀት ዓመት የተቀመጠውን የገቢ ዕቅድ ለማሳካት በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የደሴ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ መንግስቱ አበበ በበኩላቸው ገቢ ለአገር ኢኮኖሚ ዋነኛ ምንጭ ከመሆኑም በላይ ለልማት ሥራዎች መሠረታዊ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

መምሪያው በ2018 በጀት ዓመት 5.1 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 3.4 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ገልጸው፤ በ2019 በጀት ዓመት 8.2 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ዕቅድ መያዙን አስታውቀዋል።

ይህንን ዕቅድ ለማሳካት በቅንጅት፣ በትኩረትና በተጠናከረ አሠራር መስራት እንደሚገባ አቶ መንግስቱ አስገንዝበዋል።

በቀጣይ የገቢ ክፍያዎች በዲጂታል ሥርዓት እንደሚፈጸሙ የገለጹት ኃላፊው፤ ይህም የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን ዘመናዊ፣ ግልጽና ቀልጣፋ በማድረግ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የሚያግዝ መሆኑን ጠቁመዋል።

በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት የገቢ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት የገቢ ዕቅድ ቀርቦ በዕቅዱ ላይ ውይይት ተካሂዷል።

ተሳታፊዎችም በ2018 የበጀት ዓመት አፈጻጸም ላይ ያሉ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል በ2019 በጀት ዓመት የተቀመጠውን የገቢ ዕቅድ ለማሳካት የተቀናጀ ሥራ፣ የተጠናከረ ክትትልና የተሻሻለ አሠራር በመከተል ውጤታማ ለማድረግ ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

ከአምስት ቢሊዮን 39 ሚሊዮን በላይ ገቢ ለመሰብሰብ እየሰራ መኾኑን የምዕራብ ጎጃም ዞን ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ። የ2018 በጀት ዓመት የአሻጋሪ እድገት እና ዘላቂ የልማት እቅድc አፈፃፀም...
21/08/2026

ከአምስት ቢሊዮን 39 ሚሊዮን በላይ ገቢ ለመሰብሰብ እየሰራ መኾኑን የምዕራብ ጎጃም ዞን ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ።

የ2018 በጀት ዓመት የአሻጋሪ እድገት እና ዘላቂ የልማት እቅድc አፈፃፀም ግምገማ እና የ2019 እቅድ ትውውቅ መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር አካሂዷል።

አቶ ግዛቶች ካሴ የዞኑ ገቢዎች መምሪያ ኀላፊ በ2019 በጀት ዓመት ከተለያዩ የገቢ አርዕስቶች ከአምስት ቢሊዮን 39 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ እየተሰራ መኾኑን ገልፀዋል።

በ2018 በጀት ዓመት ከታቀደው 3 ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር ገቢ ከ2 ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ቢሰበሰብም የፀጥታ ችግሩ የሚጠበቀውን ገቢ ለመሰብሰብ ተግዳሮት መፍጠሩን አስረድተዋል።

በተለይ በበጀት ዓመቱ የገቢ አሰባሰቡን ዲጂታላይዝድ ለማድረግ በሁለት ወረዳዎች እና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች ላይ ኢ _ ታስ የተሰኘ መተግበሪያ ተግባራዊ ማድረግ መቻሉን መምሪያ ሃላፊው አንስተዋል።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዕድሜዓለም አንተነህ ባለፉት የግጭት ዓመታት በገቢ ስራ ላይ ከፍተኛ ጫና መፈጠሩን አስታውሰዋል።

ሁለንተናዊ የልማት ስራዎችን ለማሳለጥ የገቢ ዓቅምን ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። ባለፉት ዓመታት ሳይሰበሰብ የቆየ ውዝፍ ገቢን በዚህ ዓመት ለመሰብሰብ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚጠይቅ ነው ያሳሰቡት።

አስተያየታቸውን የሰጡ የመድረኩ ተሳታፊዎች በችግር ውስጥም ቢኾን ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር የገቢ አቅምን ለማሳደግ መስራታቸውን ተናግረዋል።

እያደገ የመጣውን የልማት ፍላጎት ለማሟላት ዓቅምን አሟጦ በመጠቀም ገቢን ለመሰብሰብ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩም ነው የጠቆሙት።

በተለይ የተጀመረውን ዲጂታይዜሽን ተግባራዊ በማድረግ ገቢን ወጭን እና እንግልትን በቀነሰ መንገድ ለመሰብሰብ እንደሚተጉ አስረድተዋል።

ሕጋዊ የገቢ መሠብሠቢያ ኬላዎች የትኞቹ ናቸው?ድካማቸው እና ጥረታቸው በየመንገዱ በሚዘረጉ ሕገ ወጥ ኬላዎች ከንቱ የኾነባቸው አልሚ ባለሀብቶች እና ነጋዴዎች ሲማረሩ ይሰማል።በምዕራብ ጎንደር ...
21/08/2026

ሕጋዊ የገቢ መሠብሠቢያ ኬላዎች የትኞቹ ናቸው?
ድካማቸው እና ጥረታቸው በየመንገዱ በሚዘረጉ ሕገ ወጥ ኬላዎች ከንቱ የኾነባቸው አልሚ ባለሀብቶች እና ነጋዴዎች ሲማረሩ ይሰማል።
በምዕራብ ጎንደር ዞን በግብርና ልማት ላይ የተሰማሩት አቶ ማስተዋል ማዘንጊያ በብዙ ወጭ እና ድካም ያመረቱትን ምርት ወደ ገበያ ለማቅረብ በሚያደርጉት ጉዞ የሚያጋጥማቸው ፈተና የብዙዎችን እጣ ፈንታ የሚያንጸባርቅ ነው።
እንደ አቶ ማስተዋል ገለጻ በገንዳ ውኃ እና አብርሐጅራ ከተሞች የተዘረጉ ሕገ ወጥ ኬላዎች ዛሬም ድረስ አልተነሱም። የቁም እንስሳት፣ አኩሪ አተር፣ ሰሊጥ እና ሌሎች የግብርና ምርቶችን በሚጭኑበት እና በሚያራግፉበት ወቅት ምንም ዓይነት የታሪፍ ምጣኔን መሠረት ያላደረገ ያልተገባ ክፍያ እንዲከፍሉ ይገደዳሉ።
"በብዙ ወጭ እና ድካም ያመረትነውን ምርት በወቅቱ ወደ ገበያ አውጥተን በተሻለ ዋጋ እንዳንሸጥ ተደርገናል" ነው ያሉት።
በመኾኑም መንግሥት እነዚህን መሰናክሎች በአስቸኳይ በማስወገድ የአልሚዎችን እና የአርሶ አደሮችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንዲያረጋግጥ ይጠይቃሉ።
ለችግሩ ዕውቅና የሰጡት የአማራ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ኀላፊ ፈንታው ፈጠነ የገቢ ተቋማት ገቢ ለመሠብሠብ በሚል በየመጫኛ እና ማውረጃው ሕገ ወጥ ክፍያ ሲያስከፍሉ መቆየታቸውን ያረጋግጣሉ።
ይህ ድርጊት የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርት እንቅስቃሴን በማስተጓጎል፣ የምርት ዋጋ እንዲጨምር እና የኑሮ ውድነት በሕዝቡ ላይ እንዲባባስ ከፍተኛ ጫና ማሳደሩንም ጠቁመዋል።
ችግሩን ሥር ነቀል በኾነ መንገድ ለመፍታት የኮንትሮባንድ ንግድ ቁጥጥር ግብረ ኀይል ተቋቁሞ እንቅስቃሴ መጀመሩን የጠቆሙት አቶ ፈንታው እስከ አሁን ባለው እርምጃ 164 ሕገ ወጥ ኬላዎችን ማስነሳት መቻሉን እና በአሁኑ ወቅት የተሻለ የንግድ እንቅስቃሴ መፈጠሩን ገልጸዋል።
ኾኖም ግን አሁንም በምዕራብ ጎንደር እና በሌሎችም አንዳንድ አካባቢዎች "ለሥራ ዕድል ፈጠራ" እና ለሌሎች ምክንያቶች በሚል ሕገ ወጥ ኬላዎችን የመዘርጋት ሁኔታዎች እንደቀጠሉ የሚያሳይ ጥቆማ እየደረሳቸው መኾኑን አክለዋል።
"ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለሥልጣን ውጭ በክልሉ የሚገኝ የትኛውም የገቢ ተቋም ኬላ ዘርግቶ ገቢ የመሠብሠብ መብትም ኾነ ሕጋዊ ተልዕኮ የለውም፤ ከጉምሩክ ውጭ ኬላ መዘርጋት ሙሉ በሙሉ ወንጀል ነው!" ብለዋል።
መንግሥት በእነዚህ ሕገ ወጥ ድርጊቶች ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰዱን እንደሚቀጥል በመግለጽ ኅብረተሰቡም ከጉምሩክ ውጭ የሚዘረጉ ሕገ ወጥ ኬላዎችን በጋራ ሊያወግዝ እና ሊታገል እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

ዘጋቢ፦ ቴዎድሮስ ደሴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

ከቴምብር ቀረጥ ነጻ የሆኑ 👉 በመንግሥት በጀት የሚተዳደሩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፤ 👉 የአስመጪነት ፈቃድ ያላቸው ነጋዴዎች ለሽያጭ የሚያስመጡት ንብረት በአስመጪዎቹ ስም ሲመዘገብ፤ 👉 መንግ...
20/08/2026

ከቴምብር ቀረጥ ነጻ የሆኑ

👉 በመንግሥት በጀት የሚተዳደሩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፤
👉 የአስመጪነት ፈቃድ ያላቸው ነጋዴዎች ለሽያጭ የሚያስመጡት ንብረት በአስመጪዎቹ ስም ሲመዘገብ፤
👉 መንግሥት ባጸደቃቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እና ኮንቬንሽኖች መሠረት ሰነዶች ነጻ ሊደረጉ ይችላሉ፤

👉 ተመሳሳይ መብት የተሰጠ መሆኑ ሲረጋገጥ ገንዘብ ሚኒስቴር ኢምባሲዎችን፣ ቆንስላዎችን እና ዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖችን ከቴምብር ቀረጥ ነጻ ሊያደርጋቸው ይችላል፤
👉 የአክሲዮን ድርሻ የምስክር ወረቀት ሲመዘገብ፤

👉 ለኢንቨስትመንት በሚወሰድ ብድር የመያዣ ሰነድ፤
👉 አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አክሲዮን ማህበር ለጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞቹ በዱቤ ግዥ የሚያቀርባቸው የካፒታል ንብረቶች በስሙ ሲመዘገብ፤
👉 በኤክስፖርት ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች ለሥራ ማስከጃ ከሚወስዱት ብድር ጋር ተያይዞ የሚገኝ የመያዣ ሰነድ፤

👉 የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ሴቶች በገቢ ምንጭነት እንዲጠቀሙባቸው ከመንግሥት የተሰጡት ተሸከሪካሪዎች የባለቤትነት ስም ዝውውር ሰነድ፤
👉 የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅራቢ ድርጅት የማዳበሪያ አቅርቦት ለአርሶ አደር ለማደል ከሚወስደው ሜርቸንዳይዝድ ብደር ጋር በተገናኘ የመያዣ ሰነድ፤

👉 የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለኢንተርፕራይዞች ለሊዝ ፋይናንስንግ ሥርዓት የሚያቀርባቸው ተሽከሪካሪዎች በባንኩ ንብረት ባለቤትነት ስም ማስመዝገቢ

Address

Bahir Dar
746

Opening Hours

Monday 08:30 - 05:30
Tuesday 08:30 - 05:30
Wednesday 08:30 - 05:30
Thursday 08:30 - 05:30
Friday 08:30 - 05:30
Saturday 08:30 - 12:30

Telephone

+251582265774

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የአብክመ ገቢዎች ቢሮ -ANRS Bureau's of Revenues posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የአብክመ ገቢዎች ቢሮ -ANRS Bureau's of Revenues:

Shortcuts

Share