Amhara RoadTransport and Logistics Bureau

Amhara RoadTransport and Logistics Bureau Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Amhara RoadTransport and Logistics Bureau, Government Organization, Bahir Dar.

በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረብርሃን ዞናል  መናኸሪያ ውስጥ በሚገለገሉ ተጠቃሚዎች መካከል የሚፈጠረው የታሪፍ ልዩነት እንደ ተሽከርካሪዎች ደረጃና የተጠቃሚው ብዛት እንደሆነ ተገልጿል።የመነሀሪያዉ የ...
25/08/2026

በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረብርሃን ዞናል መናኸሪያ ውስጥ በሚገለገሉ ተጠቃሚዎች መካከል የሚፈጠረው የታሪፍ ልዩነት እንደ ተሽከርካሪዎች ደረጃና የተጠቃሚው ብዛት እንደሆነ ተገልጿል።

የመነሀሪያዉ የኢቲኬቲን ባለሙያዎች ሽፍት ማናጀር የሆኑት አቶ ያሬድ ወንድሙ እንደገለፁት በመነሀሪያ ዉስጥ ኢቲኬቲንግ ከተጀመረ ሁለት አመት እያስቆጠረ ነዉ።

የመነሀሪያዉ አገልግሎት አንዳንዴ ከፍተኛ የህዝብ እንቅስቃሴ ባለበት ወቅት እና አንደ ተሽከርካሪዉ ደረጃ የተወሰነ የመደበኛ ታሪፍ ክፍያ ልዩነት እንደሚኖር በመመሪያ የተፈቀደ አሰራር ስላለ ተጠቃሚ ሊረዳ ይገባል ብለዋል።

ነገር ግን አንዳንድ ተጠቃሚዎች ያለአግባብ ጭማሪ እንደተደረገባቸዉ ሲገልፁ ይታያሉ ፤ ይህን ለመረዳት ደግሞ ባግባቡ የሚጠይቁም መኖራቸዉን ገልፀዉ ኢቲኬቲንግ እያንዳንዱ ተሳፋሪ ባለሙያዎችን ጠይቆ በታሪፍ የተቀመጠውን ክፍያ ባግባቡ ከፍሎ ያለ ቅሬታ ወደ ሚፈለገው ቦታ እንዲንቀሳቀስ ከማድረጉ ባሻገር ለበርካታ ወጣቶችም የስራ እድል በመፍጠርም አስተዋፅዖ አድርጓል ሲሉ ገልፀዋል ።

🏗️ በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ዘርፍ  አዲስ የልማት ምዕራፍ በደብረ ብርሃን!****በ275 ሚሊዮን ብር በጀት በ1.6 ሄክታር መሬት ላይ የሚገነባውና እስከ 1,000 ከባድ ተሽከርካሪዎችን በ...
25/08/2026

🏗️ በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ዘርፍ አዲስ የልማት ምዕራፍ በደብረ ብርሃን!
****
በ275 ሚሊዮን ብር በጀት በ1.6 ሄክታር መሬት ላይ የሚገነባውና እስከ 1,000 ከባድ ተሽከርካሪዎችን በአንድ ጊዜ የማስተናገድ አቅም ያለው የደረቅ ጭነት ተርሚናል ግንባታ በይፋ ተጀምሯል።

ፕሮጀክቱ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ወደ አገልግሎት ይገባል። ይህም የደብረ ብርሃንን የንግድና የሎጂስቲክስ እንቅስቃሴ በማሳደግ፣ የከተማዋን የኢኮኖሚ እድገት በማጠናከር እና ለወጣቶች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ጉልህ ሚና ይኖረዋል።

በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ዘርፍ ደብረ ብርሃን ወደ አዲስ የልማት ምዕራፍ! 🚛🏗️

የኢ-ቲኬቲንግ አገልግሎት በሰሜን ሸዋ ዞናል መናኸሪያ  የተሻለ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠ ነው።*****በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኘው ዞናል መናኸሪያ ከተቋቋመ ሰባት ዓመታትን አስቆጥሯል። ...
25/08/2026

የኢ-ቲኬቲንግ አገልግሎት በሰሜን ሸዋ ዞናል መናኸሪያ የተሻለ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠ ነው።

*****
በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኘው ዞናል መናኸሪያ ከተቋቋመ ሰባት ዓመታትን አስቆጥሯል። በቀደሙት ዓመታት ተጠቃሚዎች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያገኙት በጣቢያው ውስጥም ሆነ ከጣቢያው ውጭ በሚከናወን አሰራር ነበር።

ይህ አሰራር ግን ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ወረፋና አላስፈላጊ ግርግር ይፈጥር እንደነበር አንዳንድ ተጠቃሚዎች ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት እነዚህን ችግሮች ለማቃለልና የተሻለ የትራንስፖርት አሰራር ለመፍጠር የኢ-ቲኬቲንግ አገልግሎት ተጀምሯል።

በዚህም ተጠቃሚዎች የሚፈልጉትን መዳረሻ እና የጉዞ ጊዜ በመምረጥ ተራቸውን አስይዘው አገልግሎቱን በቀላሉ ማግኘት ችለዋል።

ተጠቃሚዎች እንደገለጹት፣ ቀደም ሲል የነበረው የትራንስፖርት አሰራር ምቹ ባለመሆኑ በርካታ ግርግርና ወረፋዎች ይፈጠሩ ነበር። በዚህም ተጠቃሚዎች የግል ንብረቶቻቸውን የማጣት ችግር ያጋጥማቸው ነበር።

በተጨማሪም አብረው ለመጓዝ የወጡ ቤተሰቦች በግርግሩ ምክንያት የሚለያዩበትና ለተለያዩ ችግሮች የሚጋለጡበት ሁኔታ እንደነበርም አስታውሰዋል።

አሁን ግን በኢ-ቲኬቲንግ አገልግሎቱ አማካኝነት ያለአላስፈላጊ ግርግር ተራን በማስያዝ ወደሚፈለገው መዳረሻ በሰላምና በምቾት መጓዝ እንደቻሉ ተጠቃሚዎቹ ገልጸዋል።

አገልግሎቱ የጉዞ ሂደቱን ከማቀላጠፉ ባሻገር የተሻለና የተደራጀ የትራንስፖርት አሰራር እንዲኖር አስተዋጽዖ እያደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል።

መናኸሪያው (የመነሻ ጣቢያው) አስተዳደር ኃላፊ አቶ ገድሉ ካሳው እንደገለጹት፣ ቀደም ሲል መናኸሪያው በከተማ ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ ለተጠቃሚዎችም ሆነ ለአገልግሎት አሰጣጡ ምቹ አልነበረም። በአሁኑ ወቅት ግን ከከተማው ትንሽ ወጣ ብሎ በሰፊ ቦታ ተዘጋጅቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

አቶ ገድሉ አክለውም፣ የተሳፋሪዎችን አገልግሎት ይበልጥ ለማሻሻል የኢ-ቲኬቲንግ አሰራር መጀመሩን ገልጸዋል። በዚህም በጣቢያው ውስጥ ተሳፋሪዎችና የውስጥ ሠራተኞች ብቻ እንዲገቡ በማድረግ፣ ያለአላስፈላጊ ግርግር በርካታ ተገልጋዮች በቀላሉና በአጭር ጊዜ ወደሚፈልጉት መዳረሻ እንዲጓዙ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

የኢ-ቲኬቲንግ አገልግሎቱ ለተገልጋዮች የተሻለ ምቾትና ፍጥነት ከመስጠቱ ባሻገር፣ ለበርካታ ወጣቶችም የሥራ ዕድል መፍጠሩን አቶ ገድሉ ጠቁመዋል።

አገልግሎቱን ወደ ወረዳዎች እያስፋፉ መሆኑንና በቀጣይም አገልግሎቱን የበለጠ ለማሻሻል እቅድ እንዳላቸው አቶ ገድሉ ገልጸዋል። በመጨረሻም ተጠቃሚዎች የሚሰጣቸውን የኢ-ቲኬቲንግ አገልግሎት በአግባቡ በመጠቀም ከተሻለና ከተደራጀ የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑም መልዕክት አስተላልፈዋል።

እንኳን ለነቢዩ ሙሐመድ 1501ኛው የልደት በዓል (መውሊድ  በሰላም አደረሳችሁ !ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች፤ እንኳን ለነቢዩ ሙሐመድ 1501ኛው የልደት በዓል (መውሊድ ) በሰላም አ...
25/08/2026

እንኳን ለነቢዩ ሙሐመድ 1501ኛው የልደት በዓል (መውሊድ በሰላም አደረሳችሁ !

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች፤ እንኳን ለነቢዩ ሙሐመድ 1501ኛው የልደት በዓል (መውሊድ ) በሰላም አደረሳችሁ!

በዓሉ የእርስ በእርስ ፍቅር፣ የአብሮነት፣ የመተሳሰብ እና የሰላም እንዲሆንልን እመኛለሁ።
በዚህ ታላቅ በዓል አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል ለጉዞ እና ለቤተሰብ ጥየቃ የሚንቀሳቀስ በመሆኑ፣ ቢሯችን ከወትሮው በተለየ ዝግጅት ፈጣን፣ ቀልጣፋና ደህንነቱ የተጠበቀ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት እንዲኖር እየሰራ ይገኛል።

በበዓሉ ወቅት የትራፊክ እንቅስቃሴ የሚበዛ በመሆኑ፣ የፍጥነት ወሰንን በማክበር እና ደህንነትን በመጠበቅ አደጋን እንዲከላከሉ እያሳሰብን በጉዞ ላይ እርስ በእርስ በመረዳዳት እና የትራፊክ ህጎችን በማክበር የተረጋጋ የትራንስፖርት ፍሰት እንዲኖር የበኩላችሁን እንድትወጡ እንጠይቃለን።

መልካም፣ ሰላማዊ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የመውሊድ በዓል ይሁንልን!
ጋሻው አወቀ ዶ/ር
የአማራ መንገድ፣ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ቢሮ ኃላፊ

24/08/2026
በደብረ ብርሃን ከተማ በ275 ሚሊዮን ብር የደረቅ ጭነት ተርሚናል ግንባታ ተጀመረ*****​የአማራ ክልል ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ቢሮ በደብረ ብርሃን ከተማ በ275 ሚሊዮን ብር ለሚገነባው የ...
24/08/2026

በደብረ ብርሃን ከተማ በ275 ሚሊዮን ብር የደረቅ ጭነት ተርሚናል ግንባታ ተጀመረ
*****
​የአማራ ክልል ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ቢሮ በደብረ ብርሃን ከተማ በ275 ሚሊዮን ብር ለሚገነባው የደረቅ ጭነት ተርሚናል በከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።

​የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው፦ ፕሮጀክቱ የቆየ የሕዝብ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ እና በከተማዋ ያለውን ከፍተኛ የደረቅ ተሽከርካሪዎች ፍሰትና የትራንስፖርት መጨናነቅ የሚያሳልጥ መሆኑን በመጥቀስ፤ የክልሉ መንግሥት እና ቢሮው ችግሩን ለመቅረፍ ላደረጉት በሳል ውሳኔ አመስግነዋል።

​ከዚሁ ጋር በተያያዘ ደብረ ብርሃን የኢንዱስትሪ ከተማ በመሆኗ ፕሮጀክቱ የንግድ እንቅስቃሴውንና የኢኮኖሚ ፍሰቱን የሚያሳልጥ፣ ለአካባቢው ወጣቶች ሰፊ የሥራ ዕድል የሚፈጥርና የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ በመሆኑ ፋይዳው ከፍተኛ ነው ብለዋል።

​ቦታው በከተማው መዋቅራዊ ፕላን መሠረት የተመረጠ ሲሆን፣ ከአዋሽና ከጅቡቲ መስመር ጋር የሚያገናኝ በመሆኑ ከፍተኛ የተሽከርካሪ ፍሰት ያለበት እንደሆነ በመጠቆም፣ ግንባታው በፍጥነትና በታቀደለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ከተቋራጩና ከአማካሪ ድርጅቱ ጋር የከተማ አስተዳደሩ በቅንጅት እንደሚሠራ አረጋግጠዋል።

​የአማራ ክልል ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ቢሮ ኃላፊ ጋሻው አወቀ (ዶ.ር) በበኩላቸው፦ ደብረ ብርሃን የኢንዱስትሪና የኢንቨስትመንት ማዕከል በመሆኗ የከተማውን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ለማጠናከር፣ እንዲሁም የወጪና ገቢ ንግድ እንቅስቃሴን ለማቀላጠፍ የሚያስችል የደረቅ ጭነት ተርሚናል ግንባታ እንዲጀመር መደረጉን ገልጸዋል።

​እስከ 1 ሺህ ተሽከርካሪዎችን የማስተናገድ አቅም ያለው ይህ ፕሮጀክት፣ በ1 ነጥብ 6 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍና በ275 ሚሊዮን ብር የሚገነባ ነው ያሉት ዶክተር ጋሻው፣ በክልሉ በዓይነቱም ሆነ በኢኮኖሚያዊ ፋይዳው የመጀመሪያው ነው ብለዋል።

​የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ለፕሮጀክቱ መገንቢያ የሚሆን 1 ነጥብ 6 ሄክታር ቦታ ከሦስተኛ ወገን ነፃ በማድረግ ለሥራው ዝግጁ በማድረጉም አመስግነዋል።​ግንባታው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ዕቅድ መያዙን ጠቅሰው፣ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ማዕከል (ትራፊክ ኮምፕሌክስ) ተጠናቆ ተመረቁ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ*****በሰሜን ሸዋ ዞን መንገድ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መምሪ...
24/08/2026

የሰሜን ሸዋ ዞን የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ማዕከል (ትራፊክ ኮምፕሌክስ) ተጠናቆ ተመረቁ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
*****
በሰሜን ሸዋ ዞን መንገድ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መምሪያ አዘጋጅነት፣ ለአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት የሚውል ዘመናዊ ማዕከል (ትራፊክ ኮምፕሌክስ) በይፋ ተመርቆ ስራ ጀምሯል።

ማዕከሉ ለአካባቢው ነዋሪዎችና አሽከርካሪዎች የመንጃ ፈቃድ ብቃት ማረጋገጫ፣ የተሽከርካሪ ምርመራና ተያያዥ አገልግሎቶችን በተቀላጠፈና በዘመናዊ መንገድ ለመስጠት ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።

ይህም ቀደም ሲል በዞኑ ይስተዋል የነበረውን የአገልግሎት መጨናነቅና መጓተት እንደሚቀንስ፣ እንዲሁም በጎዳና ላይ የሚስተዋሉ አደጋዎችን ለመቀነስ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ይጠበቃል።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት፣ የክልሉ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጋሻው አወቀ፣ የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁ፣ የደብረ ብርሃን ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ጌታቸው እንዲሁም የክልል፣ የከተማውና የዞኑ ከፍተኛ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በባሕር ዳር ከተማ በሦስት ትምህርት ቤቶች ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ማስፋፊያ ግንባታ   የመሠረተ ድንጋይ ተቀመጠ*******በባሕር ዳር ከተማ በሦስት ትምህርት ቤቶች የቅድመ አንደኛ ደረጃ...
22/08/2026

በባሕር ዳር ከተማ በሦስት ትምህርት ቤቶች ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ማስፋፊያ ግንባታ የመሠረተ ድንጋይ ተቀመጠ
*******
በባሕር ዳር ከተማ በሦስት ትምህርት ቤቶች የቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ማስፋፊያ ግንባታ መሠረተ በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ማሪታይም የበጀት ደጋፍ የመሠረተ ድንጋይ ተቀመጠ።

በዕለቱ ክቡር አቶ ደንጌ ቦሩ እንደገለጹት፣ ትምህርትና የትውልድ ግንባታ የማይነጣጠሉና የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። ትምህርት መረጃና እውቀትን ጨብጦ ለማለፍ ብቻ ሳይሆን፣ የተስተካከለ ስብዕና፣ በጎ ግብረ ገብነትና አገራዊ ፋይዳ ያለው አዲስ ትውልድ ለመቅረጽ የሚያገለግል ዋነኛ መሣሪያ ነው፤ ብለዋል።

ክቡር ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው ባስተላለፉት መልዕክት፣ ትምህርት አገር ተረካቢና ተወዳዳሪ ትውልድ በመገንባት መብቱን የሚያውቅና ግዴታውን በአግባቡ የሚወጣ፣ አገር ወዳድና ለአካባቢው ተቆርቋሪ ዜጋ ለመፍጠር ወሳኝ ሚና አለው።

በተጨማሪም ትውልዱ ነገሮችን በጥልቀት እንዲመረምር፣ እውነትና ሐሰትን እንዲለይና ችግሮችን በምክንያታዊነት እንዲፈታ ያግዛል፤ ብለዋል ክቡር ከንቲባ።

በባሕር ዳር ከተማ የትምህርት ቤቶችን ገጽታ የመቀየር ተግባር በትኩረት እየተሠራበት ይገኛል። በዚህም ተግባር መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት በመተባበር በርካታ ትምህርት ቤቶችን ለተማሪዎችና ለመምህራን ምቹ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል።

ለአብነትም፣ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር የአየር ጤና እና የድልችቦ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶችን የሚገነባ ሲሆን የኢትዮጵያ ማሪታይም አካዳሚ የወተር በር ት/ቤት ማስፋፊያ ይገነባል ። በሦስቱ ትምህርት ቤቶች የማስፋፊያ ሥራ ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል ።

በዕለቱ የፌዴራል፣ የክልልና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በባሕር ዳር ከተማ የኮሪደርና የጣና ዳር የመሠረተ ልማት ጉብኝት አድርገዋል። እንዲሁም በከተማዋ አረንጓዴ አሻራቸውን አስቀምጠዋል።

የአብክመ መንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ቢሮ ባዘጋጃቸው ደንቦችና መመሪያዎች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር መከረ‎****‎አዲስ የሕግ ማዕቀፎች የአሠራር ክፍተቶችን በመዝጋት የተሻለና ፍት...
20/08/2026

የአብክመ መንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ቢሮ ባዘጋጃቸው ደንቦችና መመሪያዎች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር መከረ
‎****
‎አዲስ የሕግ ማዕቀፎች የአሠራር ክፍተቶችን በመዝጋት የተሻለና ፍትሐዊ አገልግሎት ለመፍጠር ያግዛሉ የተባለ
‎የአብክመ መንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ቢሮ በዘርፉ የተሻለ አሠራርን ለመፍጠርና የተግባራትን አፈጻጸም ለማዘመን ባዘጋጃቸው ደንቦችና መመሪያዎች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።

‎መድረኩን የከፈቱት የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ጋሻው አወቀ፣ ቢሮው በመንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የሚከናወኑ ሥራዎችን በሕግና በተደራጀ አሠራር ለመምራት የተለያዩ ደንቦችና መመሪያዎችን ማዘጋጀቱን ገልጸዋል።

‎ዘርፉ ለሕብረተሰቡ የተለያዩ አገልግሎቶችን ከመስጠቱ ባሻገር የቁጥጥርና የክትትል ሥራዎችንም የሚያከናውን በመሆኑ፣ እነዚህን ተግባራት ውጤታማና ቀልጣፋ ለማድረግ ቢሮው ከፍትህ ቢሮ፣ ከፖሊስና ከሌሎች ተቋማት ጋር በመናበብና በመቀናጀት እየሠራ መሆኑን ዶ/ር ጋሻው አስረድተዋል።

‎በተለይም ከመንገድ ደህንነት ጋር በተያያዘ በክልል ደረጃ ጠንካራ የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት አስፈላጊ በመሆኑ፣ በዚህ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ለመወያየት የምክክር መድረኩ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።

‎እንዲሁም ከትራንስፖርት ስምሪት፣ ቁጥጥርና ክትትል ጋር በተያያዘ ራሱን የቻለ ደንብና መመሪያ በማውጣት የተግባራትን አፈጻጸም ማዘመን እንደሚገባ ኃላፊው አስገንዝበዋል።

‎“በመንገድ ግንባታ፣ ጥገናና ሌሎች ተያያዥ ተግባራት የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ሁሉም ባለድርሻ አካላትና ተቋማት በመናበብና በመቀናጀት መሥራት ይጠበቅባቸዋል” ሲሉም ገልጸዋል።

‎ደንቦችና መመሪያዎቹ የአሠራር ክፍተቶችን ለመዝጋት ያለሙ ናቸውደንቦችና መመሪያዎቹን ያቀረቡት ከፍትህ ቢሮ የተውጣጡ የሕግ ባለሙያዎች ሲሆኑ፣ ሰነዶቹ የተዘጋጁበትን ምክንያት፣ የክልላዊ የመንገድ ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ የማውጣት ሥልጣንና የሕግ መሠረት፣ የመመሪያዎቹን አስፈላጊነት፣ ዳራ፣ ዓላማና የሚጠበቀውን ውጤት በዝርዝር አብራርተዋል።

‎አዲሶቹ ደንቦችና መመሪያዎች በዘርፉ የሚስተዋሉ የአሠራር ክፍተቶችን ለመዝጋት፣ የተቋማትን ሚናና ኃላፊነት በግልጽ ለመለየት፣ የቁጥጥር ሥርዓቱን ለማጠናከርና ለተገልጋዮች ፍትሐዊ፣ ግልጽና ተገማች አገልግሎት ለማስፈን የሚያግዙ መሆናቸውም ተገልጿል።


‎በመድረኩ ተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳቦችና ጥያቄዎችን አንስተዋል። በተለይም ደንብና መመሪያዎቹ ሥራዎችን በተገቢው ለማስፈጸም የተዘጋጁ ቢሆኑም፣ በተለያዩ ተቋማት የሚከናወኑ ተግባራት እንዳይደጋገሙና የሥራ መደራረብ እንዳይፈጠር የተቋማት ሚናና ኃላፊነት በግልጽ መለየት እንዳለበት ጠይቀዋል።

‎ከተሽከርካሪዎች ጥፋት ጋር በተያያዘ የተቀመጡ ቅጣቶችም ከወቅታዊ ሁኔታዎችና ከጥፋቶቹ ክብደት ጋር የሚመጣጠኑ መሆናቸው እንዲገመገም ሀሳብ ቀርቧል።

‎ተሳታፊዎቹ ቅጣቱ ከሕገወጥ ተግባር የሚገኘውን ጥቅም ሊያስቀር የሚችል መሆን እንዳለበት፣ የሕግ ተገዢነትን ለማሳደግም ቅጣት ብቻ ሳይሆን ትምህርትና ግንዛቤ በመፍጠር ላይም ትኩረት መሰጠት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

‎“ደንብና መመሪያ ዋጋ የሚኖረው በተግባር ሲተረጎም ነው”የፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ጎሹ በበኩላቸው፣ የምክክር መድረኩ ዋና ዓላማ የወጡት ደንቦችና መመሪያዎች በወረቀት ላይ ብቻ እንዳይቀሩ በተግባር እንዲተረጎሙና ግልጽ፣ ፍትሐዊ፣ ተገማችና አሳታፊ አሠራር እንዲፈጠር ሁሉም ባለድርሻ አካል የበኩሉን ሚና መወጣት እንዳለበት ገልጸዋል።

‎“ደንብና መመሪያ የሚያሳካው ዓላማ የሚለካው በወጣበት ወቅት ሳይሆን በተግባር ሲተረጎም በሚፈጥረው ለውጥ ነው” በሚል መርህ፣ ተቋማት በቅንጅት መሥራት፣ የአፈጻጸሙን ሂደት በየጊዜው መገምገምና በተግባር የሚታዩ ክፍተቶችን በወቅቱ ማረም እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

‎በመጨረሻም፣ በመድረኩ የየርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ ልዩ አማካሪዎች፣ የቢሮዎች ኃላፊዎች፣ የሥራ አመራር ኮሚቴ አባላት፣ የተለያዩ ባለድርሻ ተቋማት ኃላፊዎችና ሌሎች አካላት ተሳትፈዋል

የደቡብ ወሎዞን  መንገድ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መምሪያ ከ839 ሺህ ብር በላይ የሚገመቱ የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደረገ፤******የደቡብ ወሎ ዞን መንገድ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መም...
19/08/2026

የደቡብ ወሎዞን መንገድ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መምሪያ ከ839 ሺህ ብር በላይ የሚገመቱ የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደረገ፤
******
የደቡብ ወሎ ዞን መንገድ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መምሪያ ባቀረበው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ጥሪ መሠረት፣ የአሽከርካሪ ማህበራትና የተሽከርካሪ ተቋማት ከ839 ሺህ ብር በላይ የሚገመቱ የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርገዋል።

በዞኑ የሚገኙ ሰባት የትራንስፖርት ማህበራት ድጋፉን ማበራከታቸውን የገለጹት የለጎ ሐይቅ ከፍተኛ፣ መካከለኛና አነስተኛ ሕዝብ ማመላለሻ ባለሃብቶች ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ አስመሮው ባይህ፤ ለወላጅ አልባዎችና አቅም ለሌላቸው ወገኖች ድጋፍ ማድረግ በመቻላቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ተናግረዋል።

አክለውም ማህበራቸው ከ600 ደርዘን በላይ ደብተርና እስክሪብቶ ማበርከቱን ገልጸው፣ ይህ ዓይነቱ የበጎ አድራጎት ተግባር በሁሉም ዘንድ ሊቀጥል እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

በተመሳሳይ የደሴ ከተማ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋም ሰብሳቢ አቶ በዙነህ ሀይሌባህሩ በበኩላቸው፤ በማህበሩ ሥር የሚገኙ 10 ባለሃብቶች 100 ደርዘን ደብተርና 100 ደርዘን እስክሪብቶ ማበርከታቸውን ገልጸዋል።

የዘንድሮው ድጋፍ ከቀደሙት ዓመታት በይዘቱና በመጠኑ የተሻለ መሆኑን ጠቁመው፣ የትምህርት ቁሳቁስ መግዛት ለማይችሉ ወገኖች እጅ መዘርጋት የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የደቡብ ወሎ ዞን መንገድ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መምሪያ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም አሰን፤ በተደረገው እንቅስቃሴ ከ600 ደርዘን በላይ ደብተርና ከ245 ባኮ በላይ እስክሪብቶ መሰብሰቡን አብራርተዋል።

የተሰበሰበው ቁሳቁስ በዞኑ አብይ ኮሚቴ አማካኝነት እስከ ወረዳ ድረስ ላሉ አቅመ-ደካሞችና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ወገኖች ልጆች እንደሚሰራጭ ተናግረዋል።

ኃላፊው አክለውም፣ አሽከርካሪዎችና ተቋማት ባሉባቸው ችግሮችና ውጣ ውረዶች ውስጥ ሆነው ላደረጉት ወገናዊ ደጋፍና ለላቁት በጎ አድራጎት በመምሪያው ስም ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

መረጃው የደቡብ ወሎዞን መንገድ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መምሪያ ነው።

Address

Bahir Dar

Opening Hours

Monday 02:30 - 23:30

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara RoadTransport and Logistics Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share