Visit Bahir Dar

Visit Bahir Dar ይህ ገፅ ውቢቷ ባህር ዳር ያሏትን ሊጎበኙ የሚችሉ ገፀ በረከቶች የሚተዋወቁበት ገፅ ነው። ይወዳጁን በሀላፊነት እንሰራለን።

የምረቃዋ ዕለት ቤተሰብ ያልመጣላትን ተመራቂ በደስታ እንባ ያራጩት የባህርዳር ልጆች🔥ባህርዳር ዩኒቨርስቲ ከትናንት ወዲያ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን ተማሪዎች በይፋ አስመርቋል።...
29/06/2026

የምረቃዋ ዕለት ቤተሰብ ያልመጣላትን ተመራቂ በደስታ እንባ ያራጩት የባህርዳር ልጆች🔥

ባህርዳር ዩኒቨርስቲ ከትናንት ወዲያ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን ተማሪዎች በይፋ አስመርቋል። ከነዚህ አንዷ ይህቺ የህግ ትምህርት ቤት ምሩቅ ነች።

ምሩቋ የተመራቂዎች ቤተሰቦች ተሰባስበው በሚመጡበት ዕለት ቤተሰቦቿ አልመጡም (የአቅም ጉዳይም ሊሆን ይችላል)። በዚህም በጣም የተከፋችው ተመራቂ በዶርም ስታለቅስ ቆይታ ተጣጥባ ወደ ከተማ ታመራለች። ከአንድ ካፌም ትቀመጣለች።

በካፌ ተቀምጣ ምግብ በልታና ጠጥታ በዚያ ተክዛ ሳለች፣ ድንገት በቤቱ ያለ ሙዚቃ ወደ ሌላ ይቀየራል። "እንኳን ደስ አላችሁ" ሲል በካፌው ምን መጣ አልኩ ትላለች።

በድንገት ዞር ስትልም ታስቦ እንደተዘጋጀ 4 የባህርዳር ልጆች 'እንኳን ደስ አለሽ" የሚል ፅሁፍ ያረፈበትን ኬክ ከሻማው ጋር እንድትቆርሰው ጋብዘው በእንባ አራጭተዋታል።

ይህንን ያልጠበቀችው ተማሪ በብዙ እንባ ደስታዋን የገለፀች ሲሆን 'እስከ ዛሬ ብቻዬን ነበርኩ። የቅርብ ጓደኛ እንኳን የለኝም። የሚከፋኝም አይመስለኝም ነበር። ነገርግን በእለቱ ከፋኝ። አለቀስኩ። ስወጣም ይህ ሆነ ስትል" ደስታዋን ገልጻለች።

Visit Bahir Dar

 #ጢስ  #አባይ  #ፏፏቴ ከአይሮፕላን ከ1959-1965 ዓ.ም ድረስ ባለ ጊዜ የተነሳ ፎቶግራፍThe Blue   Falls,  , from the air sometime between 1967 & 19...
23/06/2026

#ጢስ #አባይ #ፏፏቴ ከአይሮፕላን ከ1959-1965 ዓ.ም ድረስ ባለ ጊዜ የተነሳ ፎቶግራፍ

The Blue Falls, , from the air sometime between 1967 & 1973

Paul Molyneux – Berry Flickr Archive/Transport in East Africa/Source link on the comment section:

Source:-Ethiopian History

የጎጃም ስያሜ አመጣጥ‼️የጎጃምን ስያሜ አመጣጥ ስናይ፦ግብፃውያን ግዮን ፊልቆ የግብፅን ምድር የሚያረሰርሰው ከአምላክ ዙፋን ስር ነው ብለው ያምኑ ስለነበር ጎጃም ተባለ የሚሉ ጥንታዊ ሠነደች ...
21/06/2026

የጎጃም ስያሜ አመጣጥ‼️

የጎጃምን ስያሜ አመጣጥ ስናይ፦
ግብፃውያን ግዮን ፊልቆ የግብፅን ምድር የሚያረሰርሰው ከአምላክ ዙፋን ስር ነው ብለው ያምኑ ስለነበር ጎጃም ተባለ የሚሉ ጥንታዊ ሠነደች አሉ።

"ጎጃም" ማለት ነው። የአምላክ ምድር የአምላክ መጣሪያ ማለት ነው። ከክርስቶስ ልደት በፊት ወደ ግዮን ምድር የመጣው ግሪካዊው ሄሮዱቱ " ጎጃም ማለት የአምላክ ምድር" የደጋጎች" የበቁ ቅዱሳን መኖሪያ ናት ብሎ ጽፏል።

አለቃ ተክለ እየሱስ በጎጃም ትውልድ መፅሃፋቸው ውስጥ ገጽ 7 ላይ የጎጃም ህዝብ አባት በሆነው ጎዜ" ጎዜ/በጎዜ/ላይ በጎጄ" ስም ("ጎጃም) እንደተባለ፦ "የጎዜ ወንድሞች ሁሉ አገራቸውን በየስማቸው ጠሩት" ሲሉ አለቃ ተክሌ ፅፈዋል:: ይህ ከሆነ ደግሞ የጎጃም ስም ከዛሬ 3871 ዓመታት ላይ በጎዜ መጠራት ጀምሮ በጎጃም የፀና ነው‼️
ጎጃም ደብረ ማርቆስ የመንበረ መንግስት ግምጃ ቤት ኪዳነምህረት አገልጋይ የሆኑት መርጌታ ዘውዴ የተባሉት የ85 ዓመት የዕድሜ ባለፀና የጎጃምን ትውልድ በቃላቸው ከወጀመሪያው ጀምረው መናገር የሚችሉ የታሪክ አዋቂ እንደተናገሩት "ጎጃም የሚለው፣ ስም የመጣው የጎጃም ህዝብ ከሌሎች ተለይቶ ቤት እየሰራ መኖር ሲጀምር "ጎጇም" እነዚህ ጎጇሞች እያሉ እንደስም አድርገው ሕዝቡን ስለተናገሩትና በየቦታው ጎጆ ቤቶች ስለነበሩ ጎጇም እያሉ ሲጠሩን በዚያው "ጎጃም" ተባለ ሲሉ ተናግረዋል::

ይህም ጎጃም ማለት የመጀመሪያው ቤተ ሰሪ, የመጀመሪያ ከተማ መስራች እና የመጀመሪያ የስልጣኔ ምንጭ ማለት ነው:: በተጨማሪም ጎጃም የሚለው ስያሜ የመጣው እርሻን የጀመረ ስለሆነ አራሽ አምራች ለማለት "ጉዛም" ከሚለው ወደ ጎዣም ከዛም "ጎጃም" ወደሚለው ስያሜ እንደተቀየረም ይነገራል::

የጎጃም ሰው ትጉህ ገበሬን ሲጠራ "እንዴት ያለ ጉዛም ነው መሰለህ, እሱ ጉዛም ነው " በማለት ነው የሚገልፀው ::

ጎጃም የጤፍ መገኛም ሲሆን የእርሻ መሳርያ ሰርቶ እርሻ እንዴት እንደሆነ ያስተማረ, ጤፍንም በብቸኝነት ሲያመርት የኖረ ህዝብ ነው:: እስካሁንም ድረስ የታወቀ አንደፋርሾ አራሽ እና አምራች ህዝብ ነው::
ጤፍን የምታህል ረቂቅ ነገር ከሳር ለይቶ ለምግብብነት ከማዋልም አልፎ፤ ለጤፍ ዘር ሲሆን መሬቱ እንዴት መታረስና መለስለስ እንዳለበት ያወቀ; መሬቱ ለስልሶ ከታረሰ በኅላ ተመልሶ በሰው ወይንም በእንስሳት ተደምድሞ ከተደመደመው/ከተተመተመው ላይ ጤፍ ተቀምጦ ጎርፍ ሳይወስደው፡ ስር ሰዶ ይበቅላል ብሎ ሰርቶ አሳይቷል።

በመቀጠልም ተፈጭቶ የሚበላ መሆኑን ለማሳየት እንጀራ ሆኖ እስከሚወጣ ድረስ ያለውን ሂደት ማወቅ ራሱን የቻለ አንድ የምርምር ውጤት ነው‼️

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ከግሽ ዓባይ ኪነት ቡድን ጀምሮ ዘመን ተሻጋሪ ባህላዊ ሙዚቃዎችን እና የትወና ሥራዎችን በማበርከት ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈ አርቲስት ነበር፡፡ለሰማኸኝ በለው ቤተሰቦች...
20/06/2026

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ከግሽ ዓባይ ኪነት ቡድን ጀምሮ ዘመን ተሻጋሪ ባህላዊ ሙዚቃዎችን እና የትወና ሥራዎችን በማበርከት ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈ አርቲስት ነበር፡፡

ለሰማኸኝ በለው ቤተሰቦች እና ለመላው አድናቂዎች መጽናናትን እንመኛለን።

07/05/2026
28/04/2026
Visit Bahir Dar | ባህ ዳርን ይጎብኙ🌴ⒸShalomBshalom
26/02/2026

Visit Bahir Dar | ባህ ዳርን ይጎብኙ🌴

ⒸShalomBshalom

ገዳመ ዘጌ   ባህር ዳር።
23/02/2026

ገዳመ ዘጌ ባህር ዳር።

Happy   🦩 🦢🦢     Visit Bahir Dar
15/02/2026

Happy 🦩 🦢🦢
Visit Bahir Dar

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Visit Bahir Dar posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Visit Bahir Dar:

Shortcuts

Share

Category