Amhara marketing enterprise

Amhara marketing enterprise The Amhara marketing center for agricultural and industrial products.

we provide fair marketing integration between the agricultural producers like Farmers and consumers like city residents directly.

18/07/2023

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 75.8 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ
*********************************

ኢትዮ ቴሌኮም የ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀሙን በተመለከተ ለሚዲያዎች መግለጫ እየሰጠ ነው።

ተቋሙ በ2015 በጀት ዓመት 75.8 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገልፀዋል።

ተቋሙ 18.7 ቢሊየን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱም ተነስቷል።

የበጀት ዓመቱ አፈፃፀም 101 ከመቶ ስኬት የተገኘበት ሲሆን፣ ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የ23 በመቶ ብልጫ የታየበት መሆኑ ተነስቷል።

164 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ የተገኘበት ዓመት መሆኑንም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ገልፀዋል።

ተቋሙ በበጀት ዓመቱ 203 የተለያዩ ምርትና አገልግሎቶችን ለደንበኞች ያቀረበ ሲሆን፤ 116ቱ አዳዲስ አገልግሎቶች ናቸው ተብሏል።

ግዙፉ የቴሌኮም ተቋም ዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎቱን ለደንበኞቹ ተደራሽ ለማድረግ ‘ሊድ ግሮውዝ ስትራቴጂ’ አሰራሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ጠቁመዋል።

በአሚር ጌቱ

09/03/2023

ሩሲያ በዩክሬን ከተሞች የሚሳኤል ጥቃት መፈጸሟን የዩክሬን ባለስልጣናት ገለጹ

ሩሲያ በዩክሬን የተለያዩ ከተሞች ላይ የሚሳኤል ጥቃት መፈጸሟን የዩክሬን ባለስልጣናት ገለጹ፡፡

አሁን ላይ የዩክሬንን ዋና ከተማ ኪየቭን ጨምሮ ጥቁር ባሕር ፣ የኦዴሳ ወደብ እና የሰሜን ምሥራቅ ካርኪቭ ከተማ በሚሳኤል መመታታቸውን የአካባቢዎቹ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡

የሚሳኤል ጥቃቱ በኦዴሳ የሚገኘውን የኃይል ተቋም ማውደሙንም አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በካርኪቭ ወሳኝ የመሠረተ ልማት አውታሮች መመታታቸውን የጠቆሙት የከተማዋ ከንቲባ ኢሆር ቴሬኮቭ ናቸው፡፡

በከተማዋ አንዳንድ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቋረጡንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡ (ኤፍ ቢ ሲ)

09/03/2023
እንኳን ለ127ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
02/03/2023

እንኳን ለ127ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

29/01/2023

አራት የስኳር ፋብሪካዎች ወደ ምርት መመለሳቸው ተገለጸ።

ባሕር ዳር :ጥር 21/2015 ዓ.ም (አሚኮ) አራት የስኳር ፋብሪካዎች ከታኅሣሥ እና ጥር ወር ጀምሮ ወደ ምርት መመለሳቸውን የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አስታወቀ፡፡

እስካሁን ፊንጫ፣ ወንጂ ሸዋ፣ ኦሞ ኩራዝ 2 እና ኦሞ ኩራዝ 3 የስኳር ፋብሪካዎች የክረምት ወቅት አጠቃላይ ጥገና ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ወደ ምርት መግባታቸውን በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሕዝብ ግንኙነትና ተሳትፎ ዋና ክፍል ኃላፊ ረታ ደመቀ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም ጣና በለስ፣ ከሰም፣ አርጆ ዴዴሳ እና መተሐራ የስኳር ፋብሪካዎች ከጥር መጨረሻ እስከ መጋቢት ድረስ ወደ ምርት እንደሚገቡ አመላክተዋል፡፡

ያለውን የስኳር አቅርቦት እጥረት መሰረት በማድረግ ላለፉት ጥቂት ወራት ለሸማቾች የኮታቸውን 25 በመቶ ብቻ ይሰጣቸው እንደነበር አስታውሰው÷ ከጥር ወር ጀምሮ ግን የኮታቸውን 50 በመቶ ያገኛሉ ነው ያሉት።

ሁሉም ፋብሪካዎች ወደ ምርት ሲገቡ እና ከውጭ የሚገባውን ስኳር ጨምሮ የኮታቸውን መቶ በመቶ እንደሚያገኙም ጠቁመዋል፡፡

የስኳር ምርት አቅርቦቱን ለማሳደግ ከውጭ በግዥ ከሚገባው በተጨማሪ በሀገር ውስጥ የሚገኙ የስኳር አምራች ፋብሪካዎችን ወደ ምርት ማስገባት ትኩረት የተሰጠው ተግባር መሆኑንም አስረድተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ እውነታ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck

20/01/2023

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ

10/01/2023

ዳሸን ባንክ ‘ዱቤ አለ’ የተሰኘ በቴክኖሎጂ የታገዘ የዱቤ ግብይት አስተዋወቀ
*******************

ዳሸን ባንክ "ዱቤ አለ" የተሰኘ በቴክኖሎጂ የታገዘ የዱቤ ግብይት አገልግሎት አስተዋውቋል።

ባንኩ በቴክኖሎጂ የታገዙ አገልግሎቶችን በማስተዋወቅ በሚሊየን የሚቆጠሩ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የባንክ አገልግሎቶችን በቀላሉ እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ይገኛል።

ባንኩ አዳዲስ አገልግሎቶችን የማስተዋወቅ ጥረቱን በመቀጠል አሁንም ከኤግል ላየን ቴክኖሎጂስ ጋር በመተባበር የቆየውን የማኅበረሰባችንን የዱቤ ግብይት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና አስተማማኝ የባንክ አሠራር በማገዝ “ዱቤ አለ” የተሰኘ እና ሸማቾች በዱቤ በፈለጉት ጊዜ ያሻቸውን ገዝተው ቆይተው መክፈል የሚችሉበትን አሠራር እና መተግበሪያ ጥር 02 ቀን 2015 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል አስመርቋል።

አገልግሎቱን የማስተዋወቅ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የዳሸን ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙን ጨምሮ በርካታ የንግድ ማኅበረሰቡ ተገኝተዋል።

ይህ አገልግሎት ዳሸን ባንክ ከተለያዩ የንግድ ተቋማት ጋር በመተባበር ኅብረተሰቡ ቋሚ እና አላቂ ዕቃዎችን እና በርካታ አገልግሎቶችን በ3 ወር፣ በ6 ወር እና በ12 ወር በሚመለስ ዱቤ በወለድ እና ያለወለድ መግዛት የሚያስችል አማራጭ መሆኑ ተገልጿል።

ይህም የማኅበረሰቡን የኑሮ ጫና እንደሚቀንስ፣ በገበያው ውስጥ ምርት እንዲገላበጥ እንደሚያደርግ፣ አገልግሎቶችም ይበልጥ ጥቅም ላይ እንዲውሉ እና የንግዱ ማኅበረሰብ ሽያጭ እንዲያድግ ብሎም ኢኮኖሚው እንዲነቃቃ ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል ተብሏል።

“ዱቤ አለ” የምርት እና አገልግሎት አቅራቢዎች ለደንበኞቻቸው እጅግ አመቺ የሆነ የዱቤ አገልግሎት በማቅረብ ተመራጭነታቸውን እንዲያሳድጉም እንደሚረዳ ነው የተገለጸው።

ደንበኞች መተግበሪያውን ከፕሌይ ስቶር ወይም ከአፕል ስቶር በማውረድ ለአገልግሎቱ መመዝብ እንደሚችሉ እና ከተመዘገቡ በኋላም ወደ ዳሸን ባንክ ቅርንጫፍ በማምራት የዱቤ ገደብ ማስፈቀድ እና የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ተገልጿል።

በዓለም ይልፉ

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ
https://www.tiktok.com/

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን በሙሉእንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።ለአምራቾች፣ ለነጋዴዎችና ለሸማቾች ጥቅም በትጋት እን...
07/01/2023

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን በሙሉ
እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ለአምራቾች፣ ለነጋዴዎችና ለሸማቾች ጥቅም በትጋት እንሰራለን።

ከ30 ሚሊዮን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ለማህበረሰቡ እየተሰራጨ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ
30/12/2022

ከ30 ሚሊዮን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ለማህበረሰቡ እየተሰራጨ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ

ከ30 ሚሊዮን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ለማህበረሰቡ እየተሰራጨ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ
****************************

በመንግስት የውጪ ምንዛሪ ድጋፍ የቀረበ 30.3 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ለማህበረሰቡ በመሰራጨት ላይ እንደሚገኝ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

ሚኒስቴሩ መጪውን የገና እና የጥምቀት በዓላት አስመልክቶ ከሚፈጠር ሰው ሰራሽ የአቅርቦት እጥረትና የዋጋ ጭማሪ ሕብረተሰቡን ለመታደግ የቅድመ ዝግጅት እቅድ አውጥቶ በተዋረድ ካለው መዋቅርና ከባለድርሻዎች ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ ነው የገለጸው፡፡

የቅድመ ዝግጅት እቅድ አፈፃጸሙንም በዛሬው እለት ከአምራቾች፣ ከአቅራቢዎችና ከሌሎች ባለድርሻዎች ጋር የገመገመ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት 30 ሚሊዮን 340 ሺ 667 ሊትር የምግብ ዘይት የትግራይ ክልልን ጨምሮ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል እየተሰራጨ እንደሚገኝ በግምገማ መድረኩ ተገልጿል፡፡

በቅድመ ዝግጀት እቅዱ በተሰራ የንቅናቄ ስራ በሀገር ውስጥ በቂ ምርት የቀረበ በመሆኑ ለመጪዎቹ በዓላት ምንም አይነት የምግብ ዘይት እጥረት እንደማያጋጥም ተረጋግጧል፡፡

27/12/2022

ከበዓላት ጋር በተያያዘ አላስፈላጊ የዋጋ ንረት እንዳይፈጠር እየሠራ መኾኑን የጎንደር ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ)

👉 ከበዓላት ጋር በተያያዘ አላስፈላጊ የዋጋ ንረት እንዳይፈጠር እየሠራ መኾኑን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታውቋል።

👉 ከተማ አስተዳደሩ በልደት እና በጥምቀት በዓላት ሳቢያ ሊከሰቱ የሚችሉ አላስፈላጊ የዋጋ ንረቶችን እየተቆጣጠርኩ ነው ብሏል።

👉 የከተማ አስተዳደሩ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኀላፊ ቴዎድሮስ ፀጋዬ የጎንደር የንግድ እንቅስቃሴ በመነቃቃት ላይ መኾኑን ገልጸዋል።

👉 ከተማ አስተዳደሩ በዓልን ምክንያት በማድረግ በከተማዋ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች አቅርቦቶችን በተመጣጠነ ዋጋ ለማስገባት እየሠራ ነውም ብለዋል። ከበዓላት ጋር በተያያዘ የምርት እጥረት እንደማይገጥማቸውም ተናግረዋል።

👉 የገበያ ማረጋጋት እና ሕገወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን የመከላከል ሥራ እየተሠራ ነውም ተብሏል። የመንገድ ላይ ንግዶችን ሥርዓት የማስያዝ ሥራ እየሠሩ መኾናቸውንም አስታውቀዋል።

👉 የተቋቋመው ግብረ ኀይል በመቀናጀት ውጤታማ የኾነ ሥራ እየሠራ ነው።በክልሉ የማይገኙ የኢንዱስትሪ ምርቶችን ከክልሉ ውጭ ለማስመጣት እየተሠራ መኾኑንም ገልጸዋል። ለጥምቀት በዓል የሚመጣውን የሕዝብ ቁጥር ታሳቢ ያደረገ ዝግጅት እያደረጉም ነው።

👉 በበዓል ወቅት ጎብኚዎች የቆይታ ጊዜያቸው እንዲራዘም የዋጋ ቅናሽ ማድረግ፣ ካልኾነ በነበረበት ዋጋ እንዲቆይ እየተሠራ መኾኑንም ገልጸዋል።

👉 ወደ ጎንደር የሚመጣ እንግዳ ላይ በዓል ስለኾነ ብቻ ዋጋ የሚጨምርበት ምንም ምክንያት አይኖርምም ብለዋል። ምርቶች በሕገወጥ መንገድ እንዳይከዘኑ እየተቆጣጠሩ ስለመኾኑም ነው ያስገነዘቡት።

👉 በዓላትን ምክንያት በማደደረግ አላግባብ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ የእርምት እርምጃ ይወሳዳልም ነው ያሉት። የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ የንግድ ተቋማትን እናሽጋለን ያሉት ኀላፊው ይህ ከመኾኑ በፊት ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ እንግዶች የአካባቢው መገለጫ በኾነው የእንግዳ ተቀባይነት ባሕል ሊስተናገዱ ይገባቸዋልም ብለዋል።

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ እውነታ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck

Address

Amhara
Bahir Dar

Telephone

+251975090403

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara marketing enterprise posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Amhara marketing enterprise:

Share