Amhara Industry and Investment Bureau

Amhara Industry and Investment Bureau The Amhara industry & Investment is found at Bahir Dar town which is the capital of Amhara Region

🌱 እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!የጷጉሜ -1 የእመርታ ቀን በወልድያ ከተማ ተከበረ!የጷጉሜ -1 የእመርታ ቀን በወልድያ ከተማ አስተዳደር ግብርና መምሪያ አስተባባሪነት በተለያዩ የግብርና፣ የእንስሳት...
06/09/2026

🌱 እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!

የጷጉሜ -1 የእመርታ ቀን በወልድያ ከተማ ተከበረ!

የጷጉሜ -1 የእመርታ ቀን በወልድያ ከተማ አስተዳደር ግብርና መምሪያ አስተባባሪነት በተለያዩ የግብርና፣ የእንስሳትና የአሳ ሀብት ልማት እንዲሁም የኢንዱስትሪ ስራዎችን በማሳየት ተከብሯል!

በዕለቱ የግብርና መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ደስታ ሞላ እንደገለጹት፣ ግብርና የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ለኢንዱስትሪ ዘርፍ ግብዓት የሚያቀርብ የኢኮኖሚ መሠረት ነው።

በዘርፉ የምርታማነት ማሳደግ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርትን ማስፋፋት፣ እሴት ጨምሮ ማቀነባበርና ለኢንዱስትሪ የሚሆን ጥሬ ዕቃ ማቅረብ ላይ ትኩረት ተደርጎ ይሰራልም ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ አስናቀች ኃይሌ በበኩላቸው፣ የእመርታ ቀን ያለፈውን የምንገመግምበት፣ የተሳካውን የምናጠናክርበት፣ ያልተሳካውን የምንለይበትና ለቀጣይ የተሻለ የልማት ጉዞ የምንዘጋጅበት ቀን መሆኑን ገልጸዋል።

በዕለቱ ከተጎበኙ የልማት ቦታዎች መካከል የደሳለኝ ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ አንዱ ሲሆን፣ የድርጅቱ ባለቤት አቶ ደሳለኝ ፈንታው በፋብሪካቸው የኮሪደር ልማት አካል የሆኑ ስማርት ፖሎችን፣ተንጠልጣይ ድልድዮችን እያመረቱ ለተለያዩ ዘኖች እና ወረዳዎች ተደራሽ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።

በቀጣይ የብድርና የፋይናንስ ድጋፍ ከተመቻቸላቸው የማምረት አቅማቸውን በማስፋፋት ከዚህ በበለጠ ስፋት ለከተማው የልማት ስራዎች ግብዓት ለማቅረብ ዝግጁ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በተመሳሳይ የከተማ አስተዳደሩ እንስሳትና አሳ ሀብት ልማት መምሪያ በእንስሳት ልማት እና በአሳ እርባታ ዘርፍ የተጀመሩ ስራዎችን አስተዋውቋል።

የመምሪያዉ ኃላፊ አቶ በላይ ገሰሰ በበኩላቸዉ በዘርፉ የተጀማመሩት ስራዎች አይን ገላጭ ሲሆኑ በዚህ በጀት አመት በስፋት ወደ ስራ የሚገባበት ዘርፍ እንደሆነ ገልጸዋል።

በአትክልትና ፍራፍሬ፣ በአሳ እርባታ እና በፍየል ማድለብ ስራዎች የተሰማሩት አቶ አበበ ግርማይ በበኩላቸው፣በዚህ ስራ በመሰማራታቸዉ የራሳቸዉን ፍላጎት ከማሟላት ባሻገር የገቢ ምንጫቸውን ማስፋፋት እንደቻሉ ገልጸው፣ የግብርናዉ ዘርፍ በተገቢ መንገድ ድጋፍ ካገኘ እና በተደራጀ አሰራር ከተመራ ለስራ ዕድል ፈጠራና ለገቢ ማስገኛ ሰፊ አቅም እንዳለው አስረድተዋል።

እመርታ የስራ ውጤት ብቻ ሳይሆን፣ የቀጣይ ዕድገት መነሻ ነው

የእምርታ ቀን (ጳጉሜ 1) ስናከብር የማህበረሰባችንን የላቀ ተጠቃሚነትና ስኬት የምናረጋግጥበት ዘመን እንዲሆን ለማድረግ ነውበደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የእመርታ ቀን (ጳጉሜን-1) "የኢ...
06/09/2026

የእምርታ ቀን (ጳጉሜ 1) ስናከብር የማህበረሰባችንን የላቀ ተጠቃሚነትና ስኬት የምናረጋግጥበት ዘመን እንዲሆን ለማድረግ ነው
በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የእመርታ ቀን (ጳጉሜን-1) "የኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል በማምረት ላይ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን እና በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን በመጎብኘት ተካሂዷል።

በጉብኝቱም የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ስለሽ ተመስገንን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ የስራ ሃላፊዎች፣ የከተማዋ የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ተሳትፈዋል።

የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲ ስለሽ ተመስገን "ጳጉሜ 1 "የእምርታ ቀንን" ስናከብር የማህበረሰባችንን የላቀ ተጠቃሚነትና ስኬት የምናረጋግጥበት ዘመን እንዲሆን ለማስቻል ነው ብለዋል።

የማንሰራራት ቀንን ስናስብ የባህልና ሀሳብ ሽግግር ማድረግ፣ሁሉን አቀፍ ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት ማምጣት አስፈላጊ ስለመሆኑ ምክትል ከንቲባው አስገንዝበዋል።

"የኢትዮጵያ መንሰራራት" በሚል መሪ ቃል እየተከበረሩ የሚገኙ የጳጉሜ ቀናቶችን ስናስብ ብዝሃነትን እንደ ፀጋ መጠቀም ያስፈልጋል ያሉት ምክትል ከንቲባ ስለሽ ተመስገን የኢኮኖሚ ዘርፉን በፊት ከነበረው መዋቅራዊ ሽግግር የሚያመጣ ስራ በትኩረት ለመፈፀም በከተማ አስተዳደሩ የተሰሩ ኢንዱስትሪና የግብርና ዘርፎች ጉብኝት ተካሂዷል ብለዋል።

​ሀገራዊውን የኢትዮጵያ ታመርት ንቅናቄ መሠረት በማድረግ በእምርታ ቀን በማምረት ላይ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ጉብኝት መካሄዱን የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ተመስገን ተድላ ገልፀዋል።

​በእምርታ ቀን በከተማዋ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎችና ኢንቨስተሮች በሙሉ አቅማቸው እንዳያመርቱ ያገዷቸውን የቴክኒክ፣ የፋይናንስና የመሠረተ ልማት ማነቆዎችን ለመፍታት ጉብኝት መካሄዱንና ማህበረሰቡም ልማቱን በማየት ደጋፊ እንዲሆን ነው ብለዋል።

ኃላፊው አምራቾችና ኢንቨስተሮች የቴክኖሎጂ ሽግግር በማድረግ የምርቶቻቸውን ጥራትና ብዛት እንዲያሳድጉ ጥሪ አቅርበው፣ መምሪያው ዘርፉ የሚጠይቀውን የሙያና የቴክኒክ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በከተማዋ በአምራች ኢንዱስትሪዎችና በግብርና ዘርፉ የተመለከቷቸው ስራዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን የገለፁት የጉብኝቱ ተሳታፊ የሀገር ሽማግሌ አቶ በቀለ መንግስት ሰላማችንን ጋረጋገጥን በርካታ ፕሮጀክቶችን መስራት ስለሚቻል ለሠላም ቅድሚያ ሰጠን ልንሰራ ይገባል ብለዋል።

ሌላኛዋ የጉብኝቱ ተሳታፊ ወጣት ድንቅነሽ መንግስት በጉብኝቷ መደሰቷን ገልፃ፤ የፍብሪካዎች ወደ ስራ መግባት ለወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ላይ የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ ስለሆነ ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል።

''እመርታ ፣ለዘላቂ ከፍታ!"‎‎በሰሜን ጎጃም ዞን በሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ጳጉሜ 1 "የእምርታ ቀን"በአንድነትና በትብብር ሃገርን እናሻግራለን" እመርታ ፣ለዘላቂ ከፍታ!በሚል መሪ ...
06/09/2026

''እመርታ ፣ለዘላቂ ከፍታ!"

‎በሰሜን ጎጃም ዞን በሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ጳጉሜ 1 "የእምርታ ቀን"በአንድነትና በትብብር ሃገርን እናሻግራለን" እመርታ ፣ለዘላቂ ከፍታ!በሚል መሪ ቃል በደመቀ ሁኔታ በተለያዩ ኩነቶች ተከብሯል

06/09/2026

የቀን 7 ሰዓት አማርኛ ዜና … ጳጉሜን 01/2018 ዓ.ም ...

06/09/2026
06/09/2026

ኢትዮጵያ ከጥንታዊ ሥልጣኔዋ ጀምሮ በወርቅ፣ በመዳብ፣ በሊቲየም፣ በፖታሽ እና በሌሎች የከበሩ ማዕድናት የበ...

06/09/2026

የኢትዮጵያ የልማት ጉዞ በአንድ ዘርፍ ብቻ የሚለካ አይደለም። ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝም፣ ኃይ...

06/09/2026

አንዲት ሀገር ምግቧን፣ ትምህርቷን እና የመሠረተ ልማት ወጪዋን ከሌሎች እጅ እየጠበቀች እንዴት 'ሉዓላዊ ነ...

Address

Ethiopia, Amhara Provision
Bahir Dar

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251582201454

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Industry and Investment Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share