Bahir Dar International Stadium Center

Bahir Dar International Stadium Center This is the official page of Bahir dar international stadium center LETS DO !!!

ግዙፉን ስታዲየም ወደ ቀደመ ግርማው!🏟️የወልድያ ሼህ መሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን ስታዲየምን ከደረሰበት ጉዳት ጠግኖ ወደ አገልግሎት ለመመለስ የሚያስችል ዝግጅቶች ሲደረጉ ቆይተዋል።የወልድያ ...
24/08/2026

ግዙፉን ስታዲየም ወደ ቀደመ ግርማው!🏟️

የወልድያ ሼህ መሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን ስታዲየምን ከደረሰበት ጉዳት ጠግኖ ወደ አገልግሎት ለመመለስ የሚያስችል ዝግጅቶች ሲደረጉ ቆይተዋል።

የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ስታዲየሙን ነጻ በማድረግ ጥገና እንዲደረግለት ለክልሉ መንግሥት ርክክብ ማድረጉን አሚኮ ከወራት በፊት መዘገቡ የሚታወስ ነው።

የአማራ ክልል ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ኀላፊ መልካሙ ጸጋዬ ለአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ እንደተናገሩት የክልሉ መንግሥት ለስፖርት ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቷል ብለዋል። በዚህም የስፖርት መሠረተ ልማቶች በተሻለ መንገድ ወደ ሥራ እንዲገቡ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየተሠራ ስለመኾኑ አብራርተዋል።

በወልድያ ሼህ መሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን ስታዲየም ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመጠገን የሚያስችሉ ልዩ ልዩ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን ጠቁመዋል።

ለዚህም የክልሉ መንግሥት ቁርጠኝነቱን ወስዶ ለስታዲየሙ ጥገና የሚውል አስፈላጊውን በጀት መመደቡን አስታውቀዋል። ከቀጣይ መስከረም 2019 ዓ.ም ጀምሮ ጨረታ በማውጣት የጥገና ሥራው እንደሚጀመርም ገልጸዋል።

ከጥገና ሥራው ጎን ለጎን በከተማዋ ተጨዋቾችን እና የስፖርት ቤተሰቡን ማስተናገድ የሚችሉ የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት እንዲሟሉ ጥረት እየተደረገ ስለመኾኑም ተናግረዋል።

ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የእንግዳ ማረፊያዎች እና ሌሎችም የአገልግሎት መስጫ መሠረተ ልማቶች እንዲሟሉ ከከተማ አሥተዳደሩ እና ከባለሃብቶች ጋር በመቀናጀት እየተሠራ መኾኑን አብራርተዋል።

ይህንን መሠረት አድርገው ወደ ሥራ የገቡ ባለሃብቶች መኖራቸውንም ቢሮ ኀላፊው ጠቁመዋል። ሌሎች ባለሃብቶችም በሆቴል እና ቱሪዝም ዘርፍ እንዲያለሙ ጥሪ የማድረግ እና ምቹ ሁኔታዎችን የመፍጠር ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙም አመላክተዋል።

ስታዲየሙ እውቅና ያገኘው በካፍ እንዲስተካከሉ የተሰጡትን አስተያየቶች በማስተካከላችን ነው፡፡ (አቶ ጋሻው ተቀባ-የአብክመ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ)የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ...
18/08/2026

ስታዲየሙ እውቅና ያገኘው በካፍ እንዲስተካከሉ የተሰጡትን አስተያየቶች በማስተካከላችን ነው፡፡ (አቶ ጋሻው ተቀባ-የአብክመ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ)

የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም አፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን እውቅና ተሰጥቶታል፡፡ የስታዲየሙን አጠቃላይ ሂደትና አሁን ያለበትን ደረጃ አስመልክቶ የአብክመ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ማብራሪያ ስታዲየሙ እውቅና ያገኘው ከዚህ ቀደም በካፍ እንዲስተካከሉ የተሰጡትን አስተያየቶች በማስተካከላችን ነው ብለዋል፡፡ አቶ ጋሻው ስታዲየሙ በቀጣይ መሰከረም 2019 ዓ.ም የሚካሄዱ ዓለም አቀፍ ጨዋታዎችን እንደሚያስተናግድ ገልጸው የሚሰሩ ስራዎች ከካፍ መስፈርት በላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

የካፍን መስፈርቶች በመከተል ስታዲየሙ ለዓለም አቀፍ ውድድሮች ብቁ እንዲሆን በርካታ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን የገለጹት ኃላፊው በዚህም የተጫዋቾች ማረፊያ ክፍል ደህንነት፣ የልዩ እንግዳ ቦታዎች (ቪ አይ ፒ) ደህንነትና የሜዳ ጥራት በከፍተኛ ትኩረት የተከናወኑ ተግባራት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በስታዲየሙ የተሰሩት ስራዎች ውጤታማ በመሆናቸውና በካፍ እውቅና በማግኝቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጪው መስከረም ወር የሚያደርገውን የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ መርሃ ግብር በዚሁ ስታዲየም እንደሚያካሄ,ሂድም ጠቁመዋል፡፡

አቶ ጋሻው ስታዲየሙ የካፍን መመዘኛ በማሟላት ፈቃድ እንዲያገኝ ስራዎችን በንቃትና በትኩረት ለሰሩና ለተሳተፉ አካላት ሁሉ ምስጋናቸውንም ገልጸዋል፡፡

የባህር ዳር ስታዲየም ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ፈቃድ አገኘ። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በቅርቡ በባህር ዳር ስታዲየም ላይ ያደረገውን ፍተሻ እና ግምገማ  ተከተሎ ብሄራዊ ...
15/08/2026

የባህር ዳር ስታዲየም ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ፈቃድ አገኘ።

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በቅርቡ በባህር ዳር ስታዲየም ላይ ያደረገውን ፍተሻ እና ግምገማ ተከተሎ ብሄራዊ ቡድናችን በመስከረም ወር 2019 በሜዳው ለሚያደርገው ጨዋታ የሚያገለግል ጊዜያዊ የካቴጎሪ 3 (CAT 3) ፈቃድ መስጠቱን ዛሬ ለኢ/እ/ፌ በላከው ደብዳቤ አስታውቋል። ይህ ጊዜያዊ ፈቃድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሚጠብቀውን የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የሜዳው ጨዋታን በሀገሩ እንዲያደርግ ያስችለዋል።

ካፍ በስታዲየሙ የተመዘገቡ መሻሻሎችን በማድነቅ በላከው ደብዳቤ አሁንም ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ያልተጠናቀቁ ጉዳዮች እንዳሉ ገልጿል። የተቆጣጣሪ ቡድኑን ግኝቶችና የሚቀሩ የማስተካከያ እርምጃዎችን የያዘ ሙሉ ቴክኒካዊ ሪፖርት በቅርቡ ለፌዴሬሽኑ እንደሚላክ ገልፆ ጨዋታው በሚደረግበት ቀን የስታዲየሙን ዝግጁነት እና የደንቦች አተገባበር ለመከታተል የስታዲየም ተቆጣጣሪ ሊመድብ እንደሚችልም አስታውቋል።

ካፍ አያይዞም ለኢትዮጵያ መንግሥት፣ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ ለስታዲየሙ አስተዳደር እና ለሚመለከታቸው አካላት በሂደቱ ላደረጉት ትብብር ምስጋናውን አቅርቧል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

የምስራች ለኢትዮጵያ ስፖርትየአብክመ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ መልካሙ ፀጋየ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፋት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታ...
15/08/2026

የምስራች ለኢትዮጵያ ስፖርት

የአብክመ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ መልካሙ ፀጋየ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፋት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የካፍ (CAF) መስፈርቶችን ማሟላቱን ገልፀዋል።

ቢሮ ኃላፊው አክለውም ለበርካታ ዓመታት የኢንተርናሽናል ውድድሮች እገዳ ተጥሎበት የቆየው የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም፣ በተደረገለት ሰፊና ዘመናዊ የሁለተኛ ምዕራፍ የማሻሻያና የግንባታ ሥራ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) መስፈርቶችን በማሟላት ለዓለም አቀፍ ውድድሮች ዝግጁ መሆኑ ተረጋገጧል ብለዋል።

ይህ ትልቅ የስፖርት ስኬት የሀገራችን ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) እና ክለቦቻችን በሜዳቸውና በደጋፊያቸው ፊት የመጫወት ዕድላቸውን በጥንካሬ የሚመልስ ከመሆኑም በላይ፣ ኢትዮጵያ ወደፊት አበይት የአህጉር አቀፍ ውድድሮችን ለማስተናገድ የምታደርገውን ጉዞ ያፋጥነዋል በማለት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ህልም ያላቸው ሀገርን የሚወክሉ ታዳጊወችን ማፍራት የሚቻለው ደረጃውን የጠበቀ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ ሲኖር ነው።አቶ ጋሻው ተቀባ የአብክመ ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ ሐምሌ ...
22/07/2026

ህልም ያላቸው ሀገርን የሚወክሉ ታዳጊወችን ማፍራት የሚቻለው ደረጃውን የጠበቀ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ ሲኖር ነው።
አቶ ጋሻው ተቀባ የአብክመ ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ
ሐምሌ 15/2018 ዓ.ም

ባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ማዕከል BKG የመለማመጃ ሜዳወች (የፋትሳል ሜዳ) አገልግሎት ማስጀመሪያ ዝግጅት ዛሬ ተካሂዷል።

ባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ማዕከል ከBKG ግሩፕ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በሰው ሰራሽ ሳር የተሰሩ 3 መለስተኛ የመለማመጃ ሜዳወች (የፋትሳል ሜዳ) በታዳጊወች ስልጠና በይፋ ስራ እንዲጀምር ተደርጓል።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የተገኙት አቶ ጋሻው ተቀባ እንደ ገለፁት ሀገርን የሚወክል ህልም ያለው ስፖርተኛ ማፍራት የሚቻለው እንደዚህ አይነት ደረጃውን የጠበቀ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ በየአካባቢው ሲስፋፋ ነው ብለዋል።

ም/ቢሮ ኃላፊው አክለውም ወጣቱን ትውልድ በስፖርት የማነፅና ከአልባሌ ቦታወች እንዳይውል የስፖርት ማዘውተሪያወችን ማስፋፋት የመንግስት ድርሻ ብቻ ሳይሆን የሁሉም አካላት ርብርብ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

የማዕከሉ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ምስክር ሰውነት በበኩላቸው ባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ማዕከል አይነተ ብዙ አገልግሎቶችን ለመስጠት በአደረጃጀት ራሱን አጠናክሮ ወደ ስራ የገባ መሆኑን ገልፀዋል።

እነዚህ ሜዳወችም ሆነ ሌሎች የማዕከሉ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳዎች አሰራር ተዘጋጅቶላቸው ለስልጠና እና ውድድር እንዲሁም ለጤናና አካል ብቃት እንቅስቃሴ አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል ብለዋል።

ዘወትር ስፖርቱን ከመደገፍ ወደ ኋላ የማይሉት አቶ በላይነህ ክንዴ (BKG) ይህን የመሰለ የስፖርት ሜዳ አሰገንብተው ለማዕከሉ በማስረከባቸው ከፍተኛ ምስጋና እንደሚያቀርቡም ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጿል።

ሜዳወቹ ዘወትር ከማክሰኞ እስከ እሁድ ማዕከሉ በሚያወጣው ፕሮግራም መሰረት ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆኑም በዝግጅቱ ላይ ተገልጿል።

በመጨረሻም ከማዕከሉ ጋር ሜዳውን ለመጠቀም ስምምነት ያደረጉት የኮች ምትኬ ሴቶች ቡድንና አሃዱ የታዳጊወች ማሰልጠኛ ይፋዊ የስራ ማስጀመሪያ የክብር እንግዶች በተገኙበት ተካሂዷል።

!!

የፈተና ቀን ስለማሳወቅ
23/06/2026

የፈተና ቀን ስለማሳወቅ

የቃል ፈተና ጥሪዛሬ ሰኔ 15/2018 ዓ.ም በተሰጠው የአረንጓዴ ቦታወች እንክብካቤና ክትትል ባለሙያ፣ የግቢ ፅዳት ደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ክትትል ባለሙያ እና የእግር ኳስ ሜ...
22/06/2026

የቃል ፈተና ጥሪ
ዛሬ ሰኔ 15/2018 ዓ.ም በተሰጠው የአረንጓዴ ቦታወች እንክብካቤና ክትትል ባለሙያ፣ የግቢ ፅዳት ደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ክትትል ባለሙያ እና የእግር ኳስ ሜዳዎች እንክብካቤ አስተባባሪ የስራ መደብ ተፈተናችሁ ለቃል ፈተና ያለፋችሁ የቃል ፈተና ነገ ሰኔ 16/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ የሚሰጥ በመሆኑ ባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ማከል እንድትገኙ እናሳስባለን።

ለፈተና እንድትገኙ ጥሪ ስለማስተላለፍ
19/06/2026

ለፈተና እንድትገኙ ጥሪ ስለማስተላለፍ

የቅጥር ማስታወቂያ
16/06/2026

የቅጥር ማስታወቂያ

የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ
05/06/2026

የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ

Address

Bahirdar
Bahir Dar

Telephone

+251582202202

Website

and sport face book.

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bahir Dar International Stadium Center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share