Amhara Region President Office

Amhara Region President Office Amhara National Regional State president office is one of the Amhara region Governmental office that is established for public service delivery.

በእንስሳት እና ዓሣ ሃብት ልማት ለ173 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል።የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በመንግሥት በኩል ሰፊ ትኩረት ከተሰጣቸው ዘርፎች መካከል የእንስሳት እና ዓሣ ሃብት ዘር...
06/09/2026

በእንስሳት እና ዓሣ ሃብት ልማት ለ173 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል።

የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በመንግሥት በኩል ሰፊ ትኩረት ከተሰጣቸው ዘርፎች መካከል የእንስሳት እና ዓሣ ሃብት ዘርፍ አንዱ ነው።

በአማራ ክልልም የዘርፉን ጸጋ ወደ ኢኮኖሚ በመቀየር ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት አቅጣጫ ተይዞ እየተሠራበት ይገኛል።

የእመርታ ቀንን በማስመልከት የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሣ ሃብት ልማት ቢሮ እና የሌሎችም የሥራ ኀላፊዎች በባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር በዘርፉ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ልዩ አማካሪ ይትባረክ አወቀ በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት በክልሉ ውጤታማ የኾነ እና እመርታ የታየበት የእንስሳት እና ዓሣ ሃብት ልማት ሥራዎች እየተከናወኑ ነው።

የተሻለ ውጤት ለማምጣት ከመደበኛው አሠራር በተጨማሪ ዘርፉን በአሠራር፣ በሰው ኀይል፣ በምርምር እና በፋይናንስ ለመደገፍ የክልሉ መንግሥት ትኩረት ሠጥቶ እየሠራ ነው ብለዋል።

የእንስሳት ሃብት ልማቱን በኢንቨስትመንት በመደገፍ በጥራትም ኾነ በብዛት ተወዳዳሪ እንዲኾን መሥራት እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።

የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሣ ሃብት ልማት ቢሮ ኀላፊ ጋሻው ሙጨ (ዶ.ር) የእንስሳት ሃብትን በውጤታማነት በማልማት በሥርዓተ ምግብ ራስን ለመቻል ግብ ተደርጎ እየተሠራ ነው ብለዋል። በዚህም በከተማም በገጠርም ተጨባጭ ውጤቶች መገኘታቸውን አብራርተዋል።

ተኪ ምርቶችን በማምረት በኩልም እያንዳንዱ ከተማ እና ወረዳ የሚጠቀመውን የእንስሳት ሃብት በራሱ እንዲችል ለማድረግ ታቅዶ እየተሠራበት ስለመኾኑም ጠቁመዋል። ጥራትን በማሻሻል ለውጭ ገበያ ማቅረብ ላይ ትኩረት ስለመደረጉም አብራርተዋል።

ዘርፉ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል እየፈጠረ እንደሚገኝም አንስተዋል። በበጀት ዓመቱ በክልሉ ከ173 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉንም ገልጸዋል።

ከቢሮው የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በ2018 በጀት ዓመት ከ2ነጥብ 7ሚሊዮን ቶን በላይ የወተት ምርት፣ ከ895 ሺህ ቶን በላይ የሥጋ ምርት፣ ከ43 ሺህ ቶን በላይ የዓሣ ምርት እንዲሁም ከ36 ሺህ ቶን በላይ የማር ምርት ማምረት ተችሏል።

በ2019 በጀት ዓመት የታየውን እምርታ አጠናክሮ በማስቀጠል እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ በቅንጅት በመሥራት የተሻለ ውጤት ለማምጣት ጥረት እንደሚደረግም ቢሮ ኀላፊው ተናግረዋል።

"መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ልማዳዊና እንግልት የበዛበትን አሰራር ወደ ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥ የቀየረ ነው"ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
05/09/2026

"መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ልማዳዊና እንግልት የበዛበትን አሰራር ወደ ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥ የቀየረ ነው"

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

"መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዘልማዳዊ እና እንግልት የበዛበትን አሠራር የሚቀይር ነው" ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የጎንደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግ...
05/09/2026

"መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዘልማዳዊ እና እንግልት የበዛበትን አሠራር የሚቀይር ነው" ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የጎንደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመንግሥት የአገልግሎት አሠጣጥ ሪፎርም አካል መኾኑን ገልጸዋል። የመንግሥት ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት በአንድ ማዕከል በማሠባሠብ፣ በማደራጀት፣ ዲጂታል በማድረግ፣ ብልሹ አሠራርን በመቀነስ የተገልጋዮችን እርካታ ለማሻሻል ያለመ መኾኑን ገልጸዋል።

የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ቀደም ሲም የነበረውን ዘልማዳዊ እና እንግልት የበዛበት አሠራር የሚቀይር መኾኑን አንስተዋል። ተገልጋይን መሠረት ያደረገ መሠረታዊ ለውጥ አምጭ መኾኑን ገልጸዋል።

የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመንግሥት ተቋማትን በማቀናጀት፣ የእርስ በእርስ የመረጃ ልውውጣቸውን በማቀላጠፍ ለደንበኞች እርካታን የሚሰጥ መኾኑን ተናግረዋል። የተሻለ ተደራሽነትን፣ የላቀ ቅልጥፍናን፣ ግልጽነትን እና ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ መኾኑንም አንስተዋል።

በክልሉ ስድስት መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት አገልግሎት እየሰጡ ነው። በቅርቡ ደግሞ በኮምቦልቻ፣ በደብረ ማርቆስ እና ደብረ ብርሃን ከተሞች አገልግሎት እንደሚጀምር አንስተዋል። በሌሎች ሰባት መካከለኛ ከተሞችም አገልግሎት እንደሚጀምር አመላክተዋል።

እስከ መስከረም 30/2019 ዓ.ም 16 መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል ነው ያሉት። በ2019 በጀት ዓመት በሁሉም ወረዳዎች እና ከተሞች ለማስፋፋት እንደሚሠራም አመላክተዋል። መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እንደሚያስችልም ገልጸዋል።

የተቋማት መገፋፋት ሀገርን እና ሕዝብን ሲጎዳ ኖሯል፤ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ይሄን የሚያስቀር ነው ብለዋል።

ጎንደር እና የጎንደር ወዳጆች ይሄን የመሠለ ግንባታ በመገንባቱ እንኳን ደስ ያላችሁ ነው ያሉት። ያማረውን ሕንጻ ለገነቡ የከተማዋ መሪዎች ምሥጋና አቅርበዋል። ለጎንደር ከተማ መነቃቃት አስተዋጽኦ ላደረጉ ሁሉም ምሥጋና አቅርበውላቸዋል።

የጎንደር ሕዝብ ዛሬ በተሠራለት ሥራ ያመሠግነናል፤ ይህ ግን ለነገ አይኾንም፤ ነገስ ምን ይሠሩ ይኾን ብሎ ይጠብቀናል፤ ለሌላ ሥራ መዘጋጀት አለብን፤ ከዚህ የላቀ ሥራ ለመሥራት፣ ሕዝባችን እንደሚፈልገው ከፍ ያለ ሥራ ለመሥራት እንዘጋጅ ነው ያሉት። መሪዎችም ለላቀ ሥራ እንዲዘጋጁ አሳስበዋል።

05/09/2026
ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በመጠናቀቅ ላይ ያለውን የመገጭ ግድብ ጎበኙ።ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የመገጭ ግድብ ፕሮጄክትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።በጉብኝቱ ከርእሰ መሥተዳድሩ በተጨማሪ...
04/09/2026

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በመጠናቀቅ ላይ ያለውን የመገጭ ግድብ ጎበኙ።

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የመገጭ ግድብ ፕሮጄክትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በጉብኝቱ ከርእሰ መሥተዳድሩ በተጨማሪ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

የመገጭ ግድብ ፕሮጄክት ለአካባቢው አርሶ አደሮች ከፍተኛ የኾነ ለመስኖ ልማት አገልግሎት የሚሰጥ ነው። ከመስኖ ልማት ባለፈም የጎንደር ከተማ የንጹሕ መጠጥ ውኃ ችግርን በዘላቂነት እንደሚፈታ ተስፋ የተጣለበት ትልቅ ፕሮጄክት ነው።

ለዓመታት ሲጓተት የነበረው እና የሕዝብ ጥያቄ ኾኖ የኖረው መገጭ ግድብ አሁን ላይ በተሰጠው ልዩ ትኩረት በጥሩ አፈጻጸም ላይ ይገኛል።

ፕሮጄክቱ 94 በመቶ አፈጻጸም ላይ መድረሱም ተገልጿል። አሁን ላይ 33 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውኃ ይዟል።

"የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት አስተማማኝ እና ዘላቂነት ያለው የስነ ሕዝብ መረጃ የሚመነጭበት ነው" ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
04/09/2026

"የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት አስተማማኝ እና ዘላቂነት ያለው የስነ ሕዝብ መረጃ የሚመነጭበት ነው"

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

ሳፋሪኮም በአማራ ክልል እና የርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ መልእክት*******የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የሳፋሪ ኮም ከፍተኛ መሪዎችን በጽሕፈት ቤታቸው አወያይተዋል።ሳፋሪ ...
04/09/2026

ሳፋሪኮም በአማራ ክልል እና የርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ መልእክት
*******
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የሳፋሪ ኮም ከፍተኛ መሪዎችን በጽሕፈት ቤታቸው አወያይተዋል።

ሳፋሪ ኮም በአማራ ክልል እያከናወናቸው የሚገኙትን የኔትዎርክ ተደራሽነት ሥራዎች፤ ተቋሙ እያከናወናቸው ያለው የማኅበራዊ ኀላፊነት ድጋፎች እና እያጋጠሙ ባሉ ችግሮች ዙሪያ ነው ውይይት ያካሄዱት።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት ሳፋሪኮም በክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ መስፋፋት ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው ብለዋል።

በክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ መስፋፋት የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ገልጸዋል።

በቴክኖሎጂ ልማት ሥራዎችም አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።

በተጨማሪም በማኅበራዊ ኀላፊነት ላይ እያደረጉት ያለውን አስተዋጽኦ አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት እና ለመደገፍ የክልሉ መንግሥት በትኩረት እንደሚሠራም አንስተዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሳፋሪኮም በባሕር ዳር ከተማ ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ እና ለባሕር ዳር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሥልጠና ማሽኖችን ድጋፍ አድርጓል።

የሳፋሪኮም የውጭ ግንኙነት ኀላፊ አንዷለም አድማሴ በዚህ ወቅት እንደገለጹት ሳፋሪኮም በአማራ ክልል ሰፊ ኢንቨስትመንት እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።

የማኅበራዊ ኀላፊነቱንም በአግባቡ እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የክልሉ መንግሥት ለሳፋሪኮም እያደረገ ለሚገኘው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል።

በርክክቡ መልዕክት ያስተላለፋት የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ከተማ አሥተዳደሩ ከሳፋሪኮም ጋር በትብብር እንደሚሠራ ገልጸዋል።

ከተባበርን የተለወጠ ዜጋ እንፈጥራለን ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ሳፋሪኮም ማኅበራዊ ኀላፊነቱን ለመወጣት እያደረገ ላለው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል ሲል የዘገበው አሚኮ ነው።

በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተገነባው ሙዚየም የኢትዮጵያን የፍትሕ ሥርዓት በዲጅታልና በቁስ ሰንዶ የያዘ ነው።የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተገበራቸው ካሉ የተቋምና የሰው ኃይል ...
04/09/2026

በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተገነባው ሙዚየም የኢትዮጵያን የፍትሕ ሥርዓት በዲጅታልና በቁስ ሰንዶ የያዘ ነው።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተገበራቸው ካሉ የተቋምና የሰው ኃይል አቅም ግንባታ እና የዘመናዊ ዳኝነት አገልግሎት መስጫ መሰረተ ልማቶች ዝርጋታ በተጨማሪ የሀገሪቱን እና የክልሉን የዳኝነት እና የፍትሕ ሥርዓት ከጥንታዊ አሠራር እስከ ዘመናዊው ሥርዓት የሚዳስስ የፍትሕ ሙዚየም ግንባታ ይገኝበታል።

ለሙዚየሙ የሚሆን ዘመናዊ ሕንጻ ከመገንባት እስከ ማደራጀት እና ለጎብኝዎች ክፍት ማድረግ በርካታ ሂደቶችን አልፏል ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ።

ሙዚየሙ ርዕሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ፣ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ እና ሌሎችም መሪዎች በተገኙበት በይፋ ተመርቆ ለጎብኝዎች ክፍት ሆኗል።

በመረሀግብሩ ላይ የሙዚየሙን መገንባት እና መደራጀት አስፈላጊነት ለእንግዶቹ ያስረዱት የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዓለምአንተ አግደው፣ የዳኝነት እና የፍትሕ ሥርዓቱ የሀገሪቱ ታሪክ አንድ አካል መሆኑን ገልጸው ፣ ይህንን ታሪክ አደራጅቶ ለትውልድ ለማስተላለፍ፣ ትውልዱ የሀገሪቱን የዳኝነት እና የፍትሕ ሥርዓት ከጅማሮው እስከ አሁን ድረስ መረዳት እንዲኖረው ታስቦ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሙዚየሙን ለማደራጀት ዘመናዊ ሕንጻ ከመገንባት ጀምሮ፣ ለሙዚየሙ ግብዓት የሚሆኑ ታሪካዊ ሰነዶችን፣ መዛግብትን፣ የፎቶ፣ የድምጽ እና የቁሳቁስ ግብዓት ለመሰብሰብ እና ለማደራጀት ከክልሉ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ጨምሮ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሌሎች የሥራ ክፍል ኀላፊዎችን ያካተተ ቡድን ተቋቁሞ ዓመቱን ሙሉ ሲሠራ መቆየቱን አብራርተዋል።

ሙዚየሙ በሀገሪቱ የዳኝነት እና የፍትሕ ሥርዓት ላይ ምርምሮችን ለሚያካሂዱ ተመራማሪዎች፣ የሕግ ተማሪዎች፣ ዩኒቨርሲቲዎች እና ሌሎች ተቋማትና ግለሰቦች በማጣቀሻነት የሚያገለግሉ የሰነድና የምስል ክምችቶች አሉት።

ለፖሊሲ እና ሌሎች የዳኝነት እና የፍትሕ ስትራቴጂክ ሰነዶች ዝግጅት የሚያገለግሉ ግብዓቶች የሚገኙበት ማዕከልም ነው ብለዋል።

የፍትሕ ሙዚየሙ በከፊል ዲጂታል ሆኖ የተደራጀ ሲኾን፣ የሕግ ተማሪዎች እና እጩ ዳኞች የሚለማመዱበት ምስለ ችሎት ጨምሮ መደበኛ ችሎት መከታተል የሚችሉበትን የዲጂታል አገልግሎት የያዘ ነው። ሙዚየሙ ከነሐሴ 28/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት ተደርጓል ሲል የዘገበው አሚኮ ነው።

ከውኃ ሥር የሚበቅለው ነጭ ወርቅ******በዓለም ላይ ተወዳጅ፤ ተፈላጊ እና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ወሳኝነት አለው። ሕንድ፤ ቻይና እና መሰል ሀገራት በስፋት በማምረት ለምግብነት ይጠ...
04/09/2026

ከውኃ ሥር የሚበቅለው ነጭ ወርቅ
******
በዓለም ላይ ተወዳጅ፤ ተፈላጊ እና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ወሳኝነት አለው። ሕንድ፤ ቻይና እና መሰል ሀገራት በስፋት በማምረት ለምግብነት ይጠቀሙበታል።

በኢትዮጵያ ልዩ ትኩረት ባይሰጠውም በተለያዩ አካባቢዎች በስፋት የሩዝ ሰብል ይመረታል።

በአማራ ክልል የሩዝ ምርት በስፋት ከሚመረትባቸው አካባቢዎች የደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ አንዱ ነው።

በወረዳው በዘርፉ የተሰማሩ አርሶ አደሮች ከምርት ባሻገር የተደላደለ ሕይወት እንዲኖሩ ዕድል እየፈጠረላቸው ነው።

✅የቴክኖሎጂ እና የምርምር ድጋፍ!

የፎገራ ብሔራዊ የሩዝ ምርምር ሥልጠና ማዕከል ዳይሬክተር ፍስሃ ወረደ (ዶ.ር) ምቹ መሬትን በአግባቡ በመጠቀም፤ ምርታማነትን በማሳደግ በሩዝ ምርት የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ይቻላል ብለዋል።

በጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ድርጅት በሚደገፈው በኢትዮ ራይስ ፕሮጀክት አጋዥነት ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ ለማዕከሉ የላብራቶሪ አቅርቦትን በማሟላት፤ ከእርሻ ጀምሮ እስከ ማቀናበር የሚደርሱ ቴክኖሎጅዎችን በማቅረብ፤ አነስተኛ የማቀነባበሪያ ማሽኖችን በማሟላት እገዛ ማድረጉን አንስተዋል።

ከ40 በላይ የሩዝ ዝርያዎች መኖራቸውን የገለጹት ዳይሬክተሩ እንደየ አካባቢው የአየር ንብረት መሠረት ዘር እንደሚሠራጭም ተናግረዋል።

የሩዝ ምርት የምግብ ሉዓላዊነትን ከማረጋገጥ ባለፈ ተረፈ ምርቱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው አንስተዋል።

ገለባው ለእንስሳት መኖ፤ ለኀይል ምንጭ፤ ለምግብ ማብሰያ ማገዶ እና ለተለያዩ ተግባራት እንደሚያገለግልም ገልጸዋል።

የፎገራ ብሔራዊ የሩዝ ምርምር ማዕከል ተመራማሪ ሰገድ አይቸው ከደቡብ ጎንደር በተጨማሪ በተለያዩ ዞኖች የሩዝ ልማትን ማስፋት ተችሏል ብለዋል።

ከኢትዮ ራይስ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር 500 ተጠቃሚ አርሶ አደሮችን በመያዝ የተጀመረው የሩዝ ልማት አሁን ላይ 6 ሺህ 285 አርሶ አደሮችን በቴክኖሎጅ በማገዝ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ነው ያሉት።

አርሶ አደሮች በራሳቸው ዘር እንዲያባዙ እና በአቅራቢያቸው ለሚገኙ አርሶ አደሮች እና ለምርጥ ዘር ድርጅቶች እንዲያቀርቡ መደረጉንም አንስተዋል።

በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የኢትዮ ራይስ ፕሮጀክት አሥተባባሪ አለባቸው አሊጋዝ ወደ ልማት ያልገቡ አካባቢዎችን ወደ ልማት በማስገባት፤ አርሶ አደሮችን በማሠልጠን፤ የዘር ሥርዓቱን በማሻሻል የሩዝ ምርትን ለማሳደግ ተሠርቷል ብለዋል።

ከተለያዩ የምርምር ጣቢያዎች የሩዝ ዘርን በማምጣት ለአርሶ አደሮች በማቅረብ ውጤታማ እንዲኾኑ መሠራቱን ገልጸዋል።

አርሶ አደሮች የሩዝ ምርትን ጥቅም በመረዳታቸው ተጠቃሚ ከመኾናቸው ባሻገር የምርት ሽፋኑ እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል።

የሩዝ መፈልፈያ ማሽኖችን ለአርሶ አደሮች ይበልጥ ለማቅረብ እየተሠራ ነውም ብለዋል።

✅ የአርሶ አደሮች ምስክርነት

በሩዝ ምርት ልማት ላይ ከ10 ዓመት በላይ የተሳተፉ አርሶ አደሮች በዘርፉ ውጤታማ መኾናቸውን ተናግረዋል። ከራሳቸው አልፎ ለሌሎችም የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን ጠቁመዋል።

በባለሙያዎች የሚደረግ ድጋፍ እና የምርታማነት መጨመር በዘርፉ ይበልጥ ውጤታማ እንዲኾኑ ዕድል እየፈጠረላቸው መኾኑንም ገልጸዋል።

ከዘልማድ አሠራር በመውጣት በቴክኖሎጅ ታግዘው በማልማታቸው ለቤተሰብ የሚያስፈልገውን ግብዓት እንዲያሟሉ፤ የምግብ ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡ፤ ለገበያ በማቅረብ ሕይወታቸውን እንዲለውጡ እና በዘርፉ ስኬታማ እንዲኾኑ ማስቻሉንም ተናግረዋል ሲል የዘገበው አሚኮ ነው።

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Region President Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Amhara Region President Office:

Shortcuts

Share