ANRS Disaster Risk Management Commission

ANRS Disaster Risk Management Commission ለአደጋ የማይበገርና የምግብ ዋስትናው የተረጋገጠ ማህበረሰብ ለመፍጠር ተግተን እንሰራለን!

06/09/2026
ጳጉሜን 1 — የእመርታ ቀን፤ ከተረጅነት ወደ አምራችነት!በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ያለመው የስንዴ ልማት በመስክ ምልከታ ተካሄደ።"የኢትዮጵያ መንሰራራት" በሚል ...
06/09/2026

ጳጉሜን 1 — የእመርታ ቀን፤ ከተረጅነት ወደ አምራችነት!

በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ያለመው የስንዴ ልማት በመስክ ምልከታ ተካሄደ።

"የኢትዮጵያ መንሰራራት" በሚል መሪ ቃል እንደ ሀገር እየተከበረ የሚገኘውን የጳጉሜን ቀናቶች የጳጉሜን 1 «የእመርታ ቀን» ምክንያት በማድረግ በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ሀገራችን ከተረጂነት ወደ አምራችነት እያደረገች ያለችውን ታሪካዊ ሽግግር የሚያበስር የመስክ ጎበኝት ተደርጓል።

በምልከታው ለአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ የሚውልና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየለማ የሚገኘው ከ28 ሄክታር በላይ የሚሸፍን የምርጥ ዘር ስንዴ ሰብል በቦታው በመገኘት የወረዳው አመራሮችና የማኔጅመንት አባላት ጎብኝተዋል።

በአረንጓዴው አሸብርቆ የሚታየው ይህ ሰብል የወረዳችንን አምራችነትና የምግብ ዋስትና የማረጋገጥ ራዕይ በተግባር የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ የያዘውን ልማትና የህዝባችንን የጽናት ጉዞ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው።

#ሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ኮሙኒኬሽን

"እመርታ ለዘላቂ ከፍታ"“ከተረጅነት ወደ ምርታማነት  ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነት"ሀገራችን ከተረጂነት አስተሳሰብ ለመውጣት የያዘችው ትልቁ ስትራቴጂ ግብርናን ማዘመንና ምርታማነትን ማሳደግ ነው...
06/09/2026

"እመርታ ለዘላቂ ከፍታ"

“ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነት"

ሀገራችን ከተረጂነት አስተሳሰብ ለመውጣት የያዘችው ትልቁ ስትራቴጂ ግብርናን ማዘመንና ምርታማነትን ማሳደግ ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ በሌማት ትሩፋት በየጓሮው የሚከናወኑ የእንስሳት፣ የዶሮ፣ የንብና የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ስራዎች የዜጎችን አመጋገብ ከመቀየር ባለፈ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ድርሻው የጎላ በመሆኑ በትኩረት እየተሰራበት ይገኛል።

የሌማት ትሩፋት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር የኢኮኖሚ ሉዓላዊነቷን ያስከበረች ነጻ ሀገር እውን ለማድረግ ያለመ ነው።

በምግብ ራስን ከመቻል በላይ የኢትዮጵያን የአምራችነት ታሪክ የመቀየር ግብ ለሰነቀው የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር ስኬታማነት ከመቼውም ጊዜ በላይ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

በስማዳ ወረዳ እና በወገዳ ከተማ አስተዳደር የኢትዮጵያ ማንሰራራት በሚል መሪ መልዕክት ጳጉሜ 1 "የእመርታ ቀንን" ምክንያት በማድረግ በስማዳ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አስተባባሪነት በግብርናው ዘርፍ በሰብል ልማት እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች ላይ የመስክ ጉብኝት በማድረግ እና በፓናል ውይይት ተከብሯል።

#የስማዳ ወረዳ ኮሙኒኬሽን

የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ግንዛቤና ንቃተ ህሌናን በማጎልበት ለአደጋ ስጋት የማይበገር ህብረተሰብ መገንባት ተገቢ መሆኑ ተገለጸየፌደራል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በአደጋ ስጋት ሥራ አ...
05/09/2026

የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ግንዛቤና ንቃተ ህሌናን በማጎልበት ለአደጋ ስጋት የማይበገር ህብረተሰብ መገንባት ተገቢ መሆኑ ተገለጸ

የፌደራል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በአደጋ ስጋት ሥራ አመራርና በምግብ ራስን መቻል ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ። በመድረኩ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ተግባራትን ማከናወን ማለት ውጤታማ የአደጋ ስጋት መከላከልን፣ ማቅለልን፣ ዝግጁነትን፣ ምላሸን፣ መልሶ ማቋቋምን እና የማህበረሰብ የመቋቋም ብቃት መገንባትን የሚጨምር ሁለንተናዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ሥርዓትን መዘርጋትን ያካተተ ሰፊ ጉዳይ መሆኑ ተገልጿል። በገለጻው እንደተብራራው አደጋ ከህብረተሰብ ጋር አብሮ የሚኖር ጉዳይ ነው። ነገር ግን በሚኖረን የቅድመማስጠንቀቂያ መረጃ መሠረት የምላሽ አቅምን ማጠናከር ያስፈልጋል። ስለሆነም የቅድመማስጠንቀቂያ ሥርዓቱን ማዘመን ድጋፍ የሚፈልጉ የህብረተሰብ ክፍሎችን መሠረት አድርጎ
ለችግሩ ፈጣን የሆነ የሰብዓዊ ድጋፍ ምላሽ ከመስጠት ባሻገር፣ የህብረተሰቡን የመቋቋም አቅም በመፍጠር ሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም ማጠናከርን የሚጠይቅ ነው ተብሏልል።

እንደሀገር ከተረጂነት ለመውጣት በምግብ ራስን የመቻል ስትራቴጂ ተቀርጾ ለእለት ደራሽ እርዳታ ፈላጊዎች፣ ለተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ለገጠር እና ለከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች፣ በከተማ ውስጥ ላሉ ተጋላጭ ወገኖች፣ ለጎዳና ተዳዳሪዎችና የኑሮ መሠረት ለሌላቸው የስደት ተመላሾች አዲስ ሕይወት እንዲጀምሩ የኢኮኖሚና ማህበራዊ መሰረት ለመጣል ሥራዎች እየተሠሩ የሚገኝ መሆኑ ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪ የምላሽ አቅምን ለማጎልበት የመጠባበቂያ ክምችትን ማሳደግ፣ ምርት በማምረት መዘጋጀትና ደረጃቸውን የጠበቁ መጋዘኖችን መገንባትና የመረዳዳት ባህላችንን መጠቀም ይገባል ተብሏል።

04/09/2026
"የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ"  የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለ...
03/09/2026

"የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ"

የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ሚቴዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው የሆኑ የደቡብና ደቡብ ምሥራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ተገልጻል።

ኢንስቲትዩቱ ለጋዜጣ ፕላስ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በሚቀጥሉት አሥር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ።

በመጪዎቹ አሥር ቀናት ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የጠቆመው ኢንስቲትዩቱ፤ በሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ መካከለኛውና ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር አመላክቷል።

በወሩ የመጨረሻ ሳምንት ዝናብ ሰጪ ክስተቶች እየተዳከሙ እንደሚመጡ በመግለጽ፤ አብዛኞቹ የሰሜን ምሥራቅ፣ መካከለኛውና ምሥራቅ አካባቢዎች በበጋው ደረቅ የአየር ጠባይ ተፅዕኖ ሥር መሆን እንደሚጀምሩ ተጠቅሷል።

በምዕራብ አማራ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና የኦሮሚያ ምዕራባዊ አጋማሽ ላይ የክረምቱ ዝናብ እስከ ወሩ መጨረሻ ድረስ እንደሚቀጥልም መግለጫው ያመላክታል።

የምሥራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች፣ የሶማሌ ማዕከላዊ እና ደቡባዊ ክፍል፣ ከኦሮሚያ ምዕራብና ምሥራቅ ሐረርጌ፣ አርሲ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምሥራቅ ባሌ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ የሲዳማና የአፋር ደቡባዊ ክፍል ቀላል መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል የደቡብ ኢትዮጵያ፣ ከደቡብ ኦሮሚያ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምሥራቅ ቦረና ዞኖች፣ እንዲሁም የደቡብ ሶማሌ አካባቢዎች ከወሩ አጋማሽ ጀምሮ ዝናብ እንደሚያገኙ ተመላክቷል።

እየተጠናከረ የመጣው ኤል ኒኖ ከባድ የአየር ሁኔታ ስጋት እያሳደረ እንደሆነ ተገለጸ የዓለም ሜትሮሎጂ ድርጅት እንደገለጸው አሁን ላይ እየተስተዋለ የሚገኘው  የኤል ኒኖ ክስተት በ70 ዓመታት ...
03/09/2026

እየተጠናከረ የመጣው ኤል ኒኖ ከባድ የአየር ሁኔታ ስጋት እያሳደረ እንደሆነ ተገለጸ

የዓለም ሜትሮሎጂ ድርጅት እንደገለጸው አሁን ላይ እየተስተዋለ የሚገኘው የኤል ኒኖ ክስተት በ70 ዓመታት ውስጥ ከታዩት በጣም ኃይለኛ ክስተቶች አንዱ ሊሆን እንደሚችል ያስታወቀ ሲሆን፥ክስተቱም ቢያንስ እስከ የካቲት 2027 ሊቀጥል እንደሚችል ተገልጿል።

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ዓለም ከፍተኛ የአየር ሁኔታ አደጋ ወደሚበዛበት ደረጃ እየገባች መሆኑን አንስተው፥ኤል ኒኖ እየጠነከረ በመምጣቱ የድርቅ፣ የጎርፍ፣ የመሬት ናዳ እና የከፍተኛ ሙቀት አደጋዎች ሊባባሱ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

በፓሲፊክ ውቅያኖስ ማዕከላዊና ምሥራቃዊ ክፍል የባሕር ሙቀት በቅርብ ወራት በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ ሲሆን፥በተለይም የባሕር ወለል ሙቀት ከመደበኛው በ2 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል ።

የኤል ኒኖ ተጽዕኖ በሰው ልጅ ከሚመነጨው የረጅም ጊዜ የአየር ንብረት ሙቀት መጨመር ላይ ተደምሮ የከፋ የአየር ሁኔታ ሊያስከትል እንደሚችል ሳይንቲስቶች ገልጸዋል።

ባለሙያዎች በበኩላቸው የኤል ኒኖ ተጽዕኖ በሰዎች ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ ቅድመ ማስጠንቀቂያ፣ የሕክምና ድጋፍና የአደጋ ዝግጅት ሥርዓቶችን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

"የመረጃ ጥራትን ማረጋገጥና ተጋላጭ ማህበረሰቦችን በዘላቂነት ማቋቋም ይገባል" — ኮሚሽኑየአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አመራሮች ከዞን ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ...
03/09/2026

"የመረጃ ጥራትን ማረጋገጥና ተጋላጭ ማህበረሰቦችን በዘላቂነት ማቋቋም ይገባል" — ኮሚሽኑ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አመራሮች ከዞን ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ሀላፊዎች ጋር በሰብዓዊ ድጋፍ፣ በራስ አቅም ኢኒሼቲቭ፣ በሪፖርት አቀራረብና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ የምክክር መርሃ-ግብር አካሂደዋል።

በኮሚሽኑ የሀብት ማሰባሰብና አቅም ማጎልበት ተወካይ ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ጌቴ ምህረቴ የቀረበው የመወያያ ሰነድ የሰብዓዊ ድጋፍና የበራስ አቅም ስራዎችን ከክልላዊ የሪፖርት ፎርማቶች ጋር ማቀናጀት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ ከውይይቱ ተሳታፊ አመራሮች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የኮሚሽኑ አመራሮች ምላሽና ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ ሠርክአዲስ አታሌ በሰጡት ማብራሪያ፣ ድጋፍ በሚደረግበት ወቅት እውነተኛ ችግረኞችን በመለየት አላግባብ ተጠቃሚ የሚሆኑትን ማስወገድ እንደሚገባ አሳስበዋል። አክለውም የጎዳና ተዳዳሪዎችን በስነ-ልቦናና ማህበራዊ ህክምና ድጋፍ ወደ ማህበረሰቡ ማቀላቀል፣ እንዲሁም የሴፍቲኔትና የመልሶ ማቋቋም ፕሮግራሞችን ከአካባቢ ጥበቃ ጋር በማስተሳሰር ማህበረሰቡን ከተጠባባቂነት ወደ ራሱ አቅም ማሸጋገር እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዲያቆን ተስፋው ባታብል በበኩላቸው፣ ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም የመሬት በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል። የሪፖርት ጥራትን መጠበቅ፣ በዕርዳታ ማከፋፈል ወቅት የሚታዩ ህገ-ወጥ አሰራሮችን በመቆጣጠር ሀብትን ለታለመለት አላማ ማዋል እና የስራ ጊዜ ሰሌዳን ጠብቆ መፈጸም እንደሚገባም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

በመጨረሻም መርሃ-ግብሩ በክልሉ የሚከናወኑ የሰብዓዊ ድጋፍና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ግልጽነት ባለው መልኩ የማህበረሰቡን ዘላቂ በራስ አቅም መቆም በሚያረጋግጥ መንገድ እንዲከናወኑ በጋራ ስምምነት ተጠናቋል።

03/09/2026

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ANRS Disaster Risk Management Commission posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ANRS Disaster Risk Management Commission:

Shortcuts

Share