Bahirdar City Communications

Bahirdar City Communications This is Home Page for Bahir Dar City Communication Affairs Office. which is used as a Bridge between Peoples of Bahir dar city and Government.

በደባርቅ ወረዳ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች የሰላምን አማራጭ ተቀበሉ።በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን መቀበል ቀጥለዋል።በወረዳው ከሰሞኑ በርካ...
06/09/2026

በደባርቅ ወረዳ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች የሰላምን አማራጭ ተቀበሉ።

በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን መቀበል ቀጥለዋል።

በወረዳው ከሰሞኑ በርካታ ታጣቂዎች የሰላም እጦት በኅብረተሰቡ ላይ እያሳደረ የሚገኘውን ዘርፈ ብዙ ጫና በመገንዘብ የሰላም አማራጭን እየተቀበሉ ነው።

ጷግሜ 01/2018 ዓ.ም በወረዳው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 32 ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን መቀበላቸውን የደባርቅ ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ገልጿል።

አማራ ኮሙኒኬሽን

በባሕርዳር ከተማ አጼ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለዝቅተኛ ነዋሪዎች የማዕድ ማጋራት ተካሄደ።            በባሕርዳር ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የክረምት የበ...
06/09/2026

በባሕርዳር ከተማ አጼ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለዝቅተኛ ነዋሪዎች የማዕድ ማጋራት ተካሄደ።

በባሕርዳር ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የኅብረ-ብሔራዊ አንድነት ማጠናከሪያ ከመሆኑ ባሻገር በርካታ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደረጉ ሰው ተኮር ተግባራት እየተከናወነ ይገኛል።

የአጼ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ፈንቴ እንዳለው እንደገለፁት የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ህብረተሰቡን በንቃት በማሳተፍ በተለይም ወጣቶችና ሴቶች ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እያስቻለ መሆኑን ተናግረዋል።

የበጎ ፈቃድ ስራ በትርፍ ጊዜ የሚሰራ ሳይሆን ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የዜጎችን ኑሮና ሀገራዊ ኢኮኖሚን የሚያጎለብት ትልቅ የመንግስት ኢኒሼቲቭ መሆኑንም አብራርተዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-የባሕርዳር ከተማ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ገጽ ይወዳጁ:-
Facebook
https://www.facebook.com/BahirdarcityGovenmentalCommunicationAffairsoffice
YouTube
https://www.youtube.com/channel/UCNoAcvzPiExah4lyaAb6_BQ
Telegram
https://t.me/Bahirdarcitycommunication
Twitter
https://x.com/BahirdarO8493?s=35
Tiktok
https://www.tiktok.com/

በዓላት ትናንትን ከዛሬ፤ ዛሬን ከነገ የሚያገናኙ ድልድዮች ናቸው!የአማራ ክልል ባሕል ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ የክረምት የአደባባይ በዓላት የማጠቃለያ መርኀ ግብር በባሕር ዳር ከተማ እያካሄደ...
06/09/2026

በዓላት ትናንትን ከዛሬ፤ ዛሬን ከነገ የሚያገናኙ ድልድዮች ናቸው!

የአማራ ክልል ባሕል ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ የክረምት የአደባባይ በዓላት የማጠቃለያ መርኀ ግብር በባሕር ዳር ከተማ እያካሄደ ነው።

በመርሐ ግብሩ የተገኙት የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ በዓላትን ማክበር የመዝናኛ እና የመደሰቻ ብቻ ሳይኾን የማንነት፤ የታሪክ እሴቶችን፤ የትውልድ ቅብብሎሽን የሚያሳዩ መንገዶች ናቸው ብለዋል።

ክብረ በዓላት ትናንትን ከዛሬ፤ ዛሬን ከነገ የሚያገናኙ ድልድዮች መኾናቸውን ተናግረዋል። የበዓላት መከበር የባሕል ልምድን ለመጠበቅ፤ ለማጎልበት፤ የልጃገረዶችን ተሳትፎ ለማጠናከር፤ የሴቶችን ባሕላዊ ሚና ለማክበር እና የቱሪዝም ሃብት የኾኑት በዓላት ትውፊታቸው ተጠብቆ እንዲዘልቅ ጠቀሜታው የጎላ መኾኑን አንስተዋል።

በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) በኢትዮጵያ የክረምት ወቅት የልጃገረዶች የነጻነት፣ የአብሮነት እና የባሕል ማሳያ የኾኑ በዓላት በድምቀት የሚከበሩበት ልዩ ጊዜ ነው ብለዋል።

ክብረ በዓላት የቱሪዝም መስህቦች መኾናቸውን ተናግረዋል። ባሕልን እንደ ታላቅ ሃብት ማየት እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ቱሪዝም የሥራ ዕድል መፍጠሪያ፤ የኢኮኖሚ ማነቃቂያ እና የገቢ ምንጭ መኾኑንም አንስተዋል።

ወጣቶች የሕዝብ መገለጫ በጎ ባሕሎችን ወደ ዲጂታል ዓለም ልታመጡት ይገባል ነው ያሉት። የማይዳሰሱ የባሕል ቅርሶችን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

የተከበሩ የባሕል እሴቶችን ከዘመናዊው የዴሞክራሲ ባሕል ጋር ማስተሳስር ይገባል ነው ያሉት። በዓላት እና ባሕላዊ ሥርዓቶች የጋራ ማንነትን ያጠናክራሉ፤ ትውልድን ከትውልድ ያስተሳስራሉ፤ የፍቅር እና የመከባበር እሴቶችን ያስተላልፋሉ፤ የጋራ ታሪካችንንም በሕያው መልኩ ያስቀጥላሉ ነው ያሉት። በዓላትን በአንድነት እናክብር፣ በጋራ እንድመቅ፣ በመከባበር አንድነታችንን እናጠናክር ብለዋል።

#ኢትዮጵያ

በባሕርዳር ከተማ አጼ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ ማራኪ ቀበሌ የማህበረሰብ ፓርክ ለመገንባት ለነዋሪዎች ርክክብ ተካሄደ። ጳጉሜ 1/2018ዓ.ም( ባሕርዳር ከቸማ ኮሙዩኒኬሽን )የማህበረሰብ ፓርክ (...
06/09/2026

በባሕርዳር ከተማ አጼ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ ማራኪ ቀበሌ የማህበረሰብ ፓርክ ለመገንባት ለነዋሪዎች ርክክብ ተካሄደ።

ጳጉሜ 1/2018ዓ.ም( ባሕርዳር ከቸማ ኮሙዩኒኬሽን )
የማህበረሰብ ፓርክ (Community Park) በአንድ አካባቢ በሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የጋራ ጥረትና ተሳትፎ የሚገነባ ሲሆን የአካባቢው ነዋሪዎች ፓርኩን ለመገንባት ስለሚኖራቸው ድርሻ ምክክር ተካሂዷል።

ፓርኩ የተለያዩ ጠቀሜታዎች ያሉት ሲሆን የአካባቢው ነዋሪዎች የሚገናኙበት፣ የሚወያዩበትና ህፃናት አብረው የሚጫወቱበት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል።

ከዚህ በተጨማሪም የእግር መንገድ፣ የስፖርት መስሪያ ቦታዎች እና የህፃናት መጫወቻዎች ስለሚኖሩት የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ያበረታታል። አረንጓዴ ሽፋን ይጨምራል፣ እንዲሁም የአካባቢውን ውበት ያጎላል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-የባሕርዳር ከተማ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ገጽ ይወዳጁ:-
Facebook
https://www.facebook.com/BahirdarcityGovenmentalCommunicationAffairsoffice
YouTube
https://www.youtube.com/channel/UCNoAcvzPiExah4lyaAb6_BQ
Telegram
https://t.me/Bahirdarcitycommunication
Twitter
https://x.com/BahirdarO8493?s=35
Tiktok
https://www.tiktok.com/

ውጫዊ የወረራ ስጋትንና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀነስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን። ጳጉሜ 1/2018 ዓ/ም (ባሕርዳር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን) ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የ...
06/09/2026

ውጫዊ የወረራ ስጋትንና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀነስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን።

ጳጉሜ 1/2018 ዓ/ም (ባሕርዳር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን) ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀነስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን!” በሚል መሪ ሐሳብ በባሕርዳር ከተማ ዳግማዊ ሚኒሊክ ክፍለ ከተማ ይነሳ ቀበሌ ነዋሪዎች ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ።

በውይይቱ ዘላቂ ሰላም በማጽናት የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እንዲሁም የቀበሌው ነዋሪዎች በአስተሳሰብ እና በተግባር ራሳቸውን ዝግጁ በማድረግ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራትን ማከናወን እንዳለባቸው ተገልጿል።

አሁን የምንገኝበት ነባራዊና ህሊናዊ ሁኔታን በትክክል በመረዳት በውስጥ እና በውጭ የሚገኙ የጥፋት ሀይሎች ኢትዮጵያን ለማዳከም የጥፋት ተልዕኮ በመያዝ የአገሪቱን አንድነትና የሕዝቦችን አብሮ የመኖር እሴት ሲጎዱ ቆይተዋል ስለሆነም የቀበሌው ነዋሪዎች አገራዊ ሁኔታውን በመገንዘብ የፅንፈኝነት አስተሳሰቦችን መታገልና ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ አገርን የማዳን ድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-የባሕርዳር ከተማ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ገጽ ይወዳጁ:-
Facebook
https://www.facebook.com/BahirdarcityGovenmentalCommunicationAffairsoffice
YouTube
https://www.youtube.com/channel/UCNoAcvzPiExah4lyaAb6_BQ
Telegram
https://t.me/Bahirdarcitycommunication
Twitter
https://x.com/BahirdarO8493?s=35
Tiktok
https://www.tiktok.com/

06/09/2026
🌱 ጳጉሜ 1  "የእምርታ ቀን" በባሕርዳር ከተማ "የእምርታ ቀን" እየለማ የሚገኘውን የበቆሎ ሰብል በመስክ ምልከታና በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል። ጳጉሜ 1/2018ዓ....
06/09/2026

🌱 ጳጉሜ 1 "የእምርታ ቀን"

በባሕርዳር ከተማ "የእምርታ ቀን" እየለማ የሚገኘውን የበቆሎ ሰብል በመስክ ምልከታና በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል።

ጳጉሜ 1/2018ዓ.ም( ባሕርዳር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ) የግብርና ልማት የአንድን ሀገር ኢኮኖሚ ለማሳደግ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል ወሳኝ ዘርፍ ነው።

በባሕርዳር ከተማ "የእምርታ ቀን" በማስመልከት በግብርና መምሪያ እና በእንስሳት ሀብት ልማት መምሪያ በትብብር የተዘጋጀ የክላስተር የበቆሎ ሰብለ ልማትና የዘመናዊ ደሮ እርባታ ጉብኝት ተካሂዷል።

በዕለቱ መልዕክት ያስተላለፉት የባሕርዳር ከተማ ገቢዎች መምሪያ ሀላፊ አቶ ሀይለማርያም እሸቴ እንደገለጹት ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገርና የምግብ ሉዓላዊነታችን ለማረጋገጥ የግብርናው ዘርፍ ማዘመን፣ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ምርትና ምርታማነት ማሳደግ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የባሕርዳር ከተማ ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ የሰውዘር ደመላሽ እንደተናገሩት በግብርና መምሪያ እና በአጋር አካላት ትብብር በክላስተር የለማው የበቆሎ ሰብል የተሞክሮ ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

በጉብኝቱ የባሕርዳር ከተማ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት የከተማ አስተዳድሩ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-የባሕርዳር ከተማ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ገጽ ይወዳጁ:-
Facebook
https://www.facebook.com/BahirdarcityGovenmentalCommunicationAffairsoffice
YouTube
https://www.youtube.com/channel/UCNoAcvzPiExah4lyaAb6_BQ
Telegram
https://t.me/Bahirdarcitycommunication
Twitter
https://x.com/BahirdarO8493?s=35
Tiktok
https://www.tiktok.com/

የክረምት በዓላት የአዲስ ዓመት የብሥራት ምልክት ናቸው።የአማራ ክልል ባሕል ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ የክረምት የአደባባይ በዓላት የማጠቃለያ መርኀ ግብር እየተካሄደ ነው።በመርሐ ግብሩ መልእክ...
06/09/2026

የክረምት በዓላት የአዲስ ዓመት የብሥራት ምልክት ናቸው።

የአማራ ክልል ባሕል ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ የክረምት የአደባባይ በዓላት የማጠቃለያ መርኀ ግብር እየተካሄደ ነው።
በመርሐ ግብሩ መልእክት ያስተላለፉት የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ባሕላችን የአማራነት እና የኢትዮጵያዊነት መገለጫ መልክ ነው ብለዋል።

ባሕላችን ሳይበረዝ ለቀጣዩ ትውልድ እንዲተላለፍ በጋራ መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል። በአንድነት ስናከብር ልዩነታችንን በማራቅ የጋራ እሴታችንን የምናጠነክርበት ነው ብለዋል። በአንድነት ማክበራችን አንድነታችን የጠነከረ መኾኑን ያሳያል ነው ያሉት።

በክልሉ ልዩነትን የሚፈጥር አንድም ነገር ሊኖር አይገባም ብለዋል። ባሕርዳር ከተማ የሁላችንም ቤት ናት በቆይታችሁ ደስተኛ እንደኾናችሁ ተስፋ አደርጋለሁም ነው ያሉት።

የአማራ ክልል ባሕል ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ኀላፊ መልካሙ ጸጋዬ የአማራ ክልል የቀደምት ሥልጣኔ አሻራዎችን የያዘ፤ የርካታ ቅርሶች እና የመስህብ ቦታዎች መገኛ፣ የልዩ ልዩ ባሕላዊ ክዋኔዎች መገኛ እና ለኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ክልል ነው ብለዋል፡፡

አሮጌው ዓመት ሲገባደድ በአዲሱ ዓመት ዋዜማ ደብረ ታቦር (ቡሄ)፣ ሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል፣ እንግጫ ነቀላ፤ከሴ አጨዳ እና አሱሪቴ የነሐሴ ወር ጸጋዎች፤ የማኅበረሰቡ የተስፋ ማሳያዎች እና ስጦታዎች መኾናቸውን ተናግረዋል።

የክረምት በዓላት የአዲስ ዓመት የብሥራት ምልክት ናቸው ብለዋል።

በበዓላቱ ልጃገረዶች እና ወጣቶች በባሕላዊ አልባሳት አምረው፣ በእልልታ ታጅበው ሕያው ዜማዎችን የሚያዜሙበት፤ ጎዳናዎችን የሚያደምቁበት፤ የሴቶች ነጻነት እና ማኅበራዊ ክብራቸው በጎላ ሁኔታ የሚታይበት መኾኑን ተናግረዋል።

በክልሉ የአደባባይ በዓላት የመደጋገፍ፤ የመተባበር፤ የጋራ ሕልውና፣ የጽናት እና የዘላቂ ስላም ዋነኛ ምሰሶዎች ኾነው ቆይተዋል ነው ያሉት።

በዓላት በጎ ተግባራት የሚያከናውነባቸው፤ ያለው ለሌለው የሚያካፍልበት፤ በኀዘን ላይ የሚገኙ የሚጽናኑበት፣ የታመሙት የሚጎበኙበት፤ ዘመድ እና ጎረቤት በፍቅር የሚገናኙበት ታላቅ የማኅበራዊ ትሥሥር መድረክ ናቸው ብለዋል፡፡

እኒህን ሕዝባዊ እና ሃይማኖታዊ ክብረ በዓላት ይዘታቸው ሳይቀየር፤ ክዋኔያቸው ሳይበረዝ፣ መልእክታቸው ሳይቀነስ፤ ለምተው እና ተጠብቀው ለትውልድ እንዲተላለፉ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል።

#አሚኮ #ኢትዮጵያ🇪🇹

ባሕልን መጠበቅና ማስቀጠል ለትውልድ አደራ ነው! “ይህ ባሕል ሀብት ነው፤ ይህን ባሕል መጠበቅ፣ ለትውልድ ማስተላለፍ እና የእኛነታችን መገለጫ አድርጎ ማስቀጠል በእጅጉ ያስፈልጋል።” የባሕር ...
06/09/2026

ባሕልን መጠበቅና ማስቀጠል ለትውልድ አደራ ነው!

“ይህ ባሕል ሀብት ነው፤ ይህን ባሕል መጠበቅ፣ ለትውልድ ማስተላለፍ እና የእኛነታችን መገለጫ አድርጎ ማስቀጠል በእጅጉ ያስፈልጋል።”

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር
ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው

ባሕላችን የማንነታችን መሠረት፣ የትውልድ ድልድይ እና የሀገራችን የቱሪዝም ሀብት ነው።

ሻደይ፣ቡሄ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል፣ እንግጫ ነቀላ፣ አሱሪቴ፣ ከሴ አጨደ እና አቡር የመሳሰሉ ባህላዊ እሴቶችን መጠበቅና ማስቀጠል የሁላችንም ኃላፊነት ነው።

Address

Bahir Dar
6000

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 12:00

Telephone

+251582262889

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bahirdar City Communications posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Bahirdar City Communications:

Shortcuts

Share