Amhara Prosperity Party /APP/

Amhara Prosperity Party /APP/ "የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላምና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
•~•~•
ቴሌግራም ▶https://t.me/amharaapp

https://youtu.be/QIlSLB-FXCQ
07/08/2026

https://youtu.be/QIlSLB-FXCQ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ጠንካራ ሀገረ መንግስት በመገንባት የጋራ አሸናፊነትን የሚያጎናፅፍ የብ...

07/08/2026
07/08/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ ኦቢኤን ጋር ያደረጉት ቆይታ - ዛሬ ምሽት ይጠብቁን

07/08/2026

"ችግርን ወደ እድል በመቀየር የተሻለ፣ የላቀና ለልጆቻችን የሚሻገር ስራ ተሰርቷል"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)


~•~•~•~•
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊



"የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/
ዩቲዩብ:- https://www.youtube.com/

07/08/2026

ሰላም ውድ ስጦታ ፤ ጊዜ ትልቅ ሃብት ፤ ስራ ትልቅ ፀጋ ፤ ትብብር በጋራ መቆምና መልፋት ከምንጊዜውም በላይ የሚያስፈልግበት ዘመን ላይ መሆናችንን መገንዘብ ያስፈልጋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

~•~•~•~•
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊



"የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/
ዩቲዩብ:- https://www.youtube.com/

06/08/2026
06/08/2026
"ባለፉት የለውጥ ዓመታት በክልሉ በርካታ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል" ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አዲሱ ተርሚናል ጠቅላይ...
06/08/2026

"ባለፉት የለውጥ ዓመታት በክልሉ በርካታ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል" ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

የባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አዲሱ ተርሚናል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ሌሎችም መሪዎች በተገኙበት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾኗል።

በምረቃ መርሐ ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በክልሉ በርካታ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል። ክልሉ በችግር ውስጥም ኾኖ ሰፊ የኢንቨስትመንት ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

በተለይም በግብርና ልማት ማሻሻያ ላይ ያተኮሩ ሥራዎች በሰፊው ተከናውነዋል ነው ያሉት። ለዘመናት ሲጓተቱ የቆዩ የልማት ፕሮጀክቶች በፍጥነት እየተከናወኑ ስለመኾኑም ጠቁመዋል።

የቱሪዝም ዘርፉን የሚያነቃቁ ታላላቅ የቱሪዝም መዳረሻዎች መገንባታቸውንም ጠቅሰዋል። የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት እና የሎጎ ሐይቅ ሪዞርት በቅርቡ ከተገነቡት የቱሪዝም መዳረሻዎች መካከል ስለመኾናቸው በአብነት አንስተዋል።

ከተሞች ለነዋሪዎች የተመቹ እንዲኾኑ የሚያደርጉ አበረታች ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙም አንስተዋል። በባሕር ዳር፣ በጎንደር፣ በደሴ፣ በኮምቦልቻ እና በወልድያ ተስፋ ሰጭ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋልም ነው ያሉት።

ከደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አዲሱ ተርሚናል በተጨማሪ ቀደም ሲል በደብረ ማርቆስ እና ኮምቦልቻ የተገነቡት የአውሮፕላን ማረፊያዎች የቱሪዝም እና የኢንቨስትመንት መግቢያ መስኮቶች ኾነዋል ብለዋል።

በክልሉ እየተገነቡ ላሉት ፕሮጀክቶች እና የልማት ሥራዎች በቅርበት እየደገፉ ላሉት የፌዴራል መንግሥት መሪዎች ርእሰ መሥተዳድሩ ምሥጋና አቅርበዋል።

~•~•~•~•
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊



"የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/
ዩቲዩብ:- https://www.youtube.com/

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በባሕር ዳር ከተማ ልማቶችን ጎበኙ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆ...
06/08/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በባሕር ዳር ከተማ ልማቶችን ጎበኙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በባሕር ዳር ከተማ ቁልፍ የልማት ቦታዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸውም ከተማዋ ያላትን እምቅ አቅምና ተስፋ ሰጪ የልማት እንቅስቃሴዎች በግልጽ የታየ ሲሆን፤ እነዚህ ስትራቴጂካዊ የልማት ስራዎች የነዋሪዎቿን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ፣ የቱሪዝም እና የኢኮኖሚ መነቃቃትን የሚፈጥሩ እንዲሁም ከተማዋ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያላትን የንግድና የኢንቨስትመንት ማዕከልነት ሚና ይበልጥ የሚያጠናክሩ ናቸው።

በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቴክኖሎጂ ድጋፍ እየተካሄደ ያለውን ሪፎርምም ለማየት ችለዋል።


~•~•~•~•
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊



"የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/
ዩቲዩብ:- https://www.youtube.com/

"ባሕር ዳር ለአፍሪካ የልማት፣ የዕድገት እና የብልጽግና ተምሳሌት የምትኾን ከተማ ናት" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አዲሱ...
06/08/2026

"ባሕር ዳር ለአፍሪካ የልማት፣ የዕድገት እና የብልጽግና ተምሳሌት የምትኾን ከተማ ናት" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

የደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አዲሱ ተርሚናልን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) መርቀው ከፍተውታል።

በምረቃ መርሐ ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ባሕር ዳር ታሪክ እስከ ተፈጥሮ ሳይሰስቱ ውበት ያበዙላት ታሪክ ያጠገባት "የአፍሪካ የልማት፣ የዕድገት እና የብልጽግና ተምሳሌት የምትኾን ከተማ ናት" ብለዋል።

በኢትዮጵያ ሲደረግ ለነበረው የንግድ ሥርዓት መሸጋገሪያ ማዕከል ኾና ስታገለግል የቆየች ብትኾንም ባሕር ዳር በሚገባት የመልማት አቅም ልክ ሳትለማ መቆየቷን ጠቁመዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ቱሪዝምን የሚያነቃቁ በርካታ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በከተማዋ ሰፊ የኮሪደር ልማት እና የውስጥ ለውስጥ መንገዶች እየተሠሩላት መኾኑን ነው የገለጹት። የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም ግንባታ ሌላው የከተማዋ የልማት ማሳያ ስለመኾኑም አንስተዋል። እነዚህም ወደ አካባቢው ለሚመጡ ሰዎች አስደሳች ሁኔታን የሚፈጥሩ ናቸው ብለዋል።

ዕድል ስናገኝ እንጠቀምበት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ችግርን ወደ ዕድል በመቀየር ለልጆቻችን የሚተርፍ ሥራን መሥራት ልማት እናድርግ ነው ያሉት። ሰላም ውድ ስጦታ፣ ጊዜ ትልቅ ሀብት፣ ስራ ትልቅ ጸጋ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምንጊዜውም በላይ ለልማት መተባበር እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

~•~•~•~•
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊



"የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/
ዩቲዩብ:- https://www.youtube.com/

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Prosperity Party /APP/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share