ANDM central inspection and audit commission office

ANDM central inspection and audit commission office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ANDM central inspection and audit commission office, bahir dar, Bahir Dar.

14/12/2018
24/10/2018
በ12ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ አዲስ የተመረጡት የአዴፓ ቁጥጥርና ኦዲት ኮሚሽን አመራር የመጀመሪያውን ስብሰባ ጀምሮል የ2011 እቅድና አዲስ የኮሚሽን መዋቅርን ማጽደቅ ላይ ትኩረት አድርጎ እ...
24/10/2018

በ12ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ አዲስ የተመረጡት የአዴፓ ቁጥጥርና ኦዲት ኮሚሽን አመራር የመጀመሪያውን ስብሰባ ጀምሮል የ2011 እቅድና አዲስ የኮሚሽን መዋቅርን ማጽደቅ ላይ ትኩረት አድርጎ እየተወያየ ይገኛል። መልካም የስራ ዘመን!

የአዴፓ 12ኛው ጉባኤ 11 አባላት ያሉት የቁጥጥርና ኦዲት ኮሚሽን መረጠ1.ዶ/ር ፍሬው ተገኜ2.ኢንጅነር አወቀ ኃይለማርያም3. ፈቃዴ ዳምጤ4. ዘውዴ ታምር5. ስቡህ ገበያው6. እውነቴ አለነ7...
02/10/2018

የአዴፓ 12ኛው ጉባኤ 11 አባላት ያሉት የቁጥጥርና ኦዲት ኮሚሽን መረጠ
1.ዶ/ር ፍሬው ተገኜ
2.ኢንጅነር አወቀ ኃይለማርያም
3. ፈቃዴ ዳምጤ
4. ዘውዴ ታምር
5. ስቡህ ገበያው
6. እውነቴ አለነ
7. ቢያዝን እንኳሆነ
8. ዶ/ር ባለው ባዬ
9. መዓዛ በዛብህ
10. ሲ/ር እናትነሽ ሙሴ
11. አሰገድ መሬሳ ሆነዉ ተመርጠዋል::

የብአዴን ማዕከላዊ ቁጥጥርና ኦዲት ኮሚሽን በጓድ ተስፋየ ጌታቸው የብአዴን ማዕ/ኮሚቴ ፅ/ቤት ኃላፊ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማንን ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቹ፣ ለስራ አጋሮቹና ለመላው አባላችን...
26/07/2018

የብአዴን ማዕከላዊ ቁጥጥርና ኦዲት ኮሚሽን በጓድ ተስፋየ ጌታቸው የብአዴን ማዕ/ኮሚቴ ፅ/ቤት ኃላፊ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማንን ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቹ፣ ለስራ አጋሮቹና ለመላው አባላችን መፅናናትን እንመኛለን ፡፡ ነብስህን በአፀደ ገነት ያኑርልን!!!

13/07/2017

ሂስ እንዴት ይሰጣል

1. ሂስ በምንሰጥበት ስዓት ለሚሰጠው አካል ውጤታማ የሚሆንበትን መንገድ በማሳየት መሆን አለበት፡፡ ይህ ከሆነ ተቀባዩ ክፍተቶችን በአግባቡ በመሙላት ውጤት ማምጣት የሚችል ሲሆን ሂሱን በተቃራኒው ከሆነ ደግሞ ውጤቱ አሉታዊ ይሆናል፡፡
2. ሂስ ስንሰጥ ንግግራችን ላይ በፍፁም ስሜታዊነት መታየት የለበትም፡፡ ስሜታዊነት ከአስተማሪነቱ ይልቅ ለጥል ለድብድብና ለሌሎች አሉታዊ ድርጊቶች ስለሚጋብዝ ከገንቢነቱ ይልቅ ጥፋቱ ያመዝናል፡፡
3. ስልታዊ መሆን ፡- ሂስ ከምንሰጠው ሰው ጋር በምን ዓይነት መልኩ ልንግባባና የምንሰጠው ሂስ ሊቀበል ይችላል የሚለውን ውጤታማ ስልት መቀየስና መተግበር አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው፡፡
4. ሂስ ለሚሰጠው ግለሰብ የራሱ መተማመን ስሜቱን ልንጠብቅለት ይገባል፡፡ ምንም እንኳ ለሂስ ተቀባዩ ግለሰብ ክፍተቱ ላይ አተኩረን የምንሰጠው ነገር ገንቢ ቢሆንም የምንሰጥበት መንገድ ግን ስሜት ነኪ መሆን የለበትም፡፡
5. ሂስ በመስጠት ጊዜውና ሁነቱ አሁን ነው የሚለውን ግምት ውስጥ ማስገባት፡- ይህን ግምት ውስጥ ያስገባ ሂስ ሰጪ እና ተቀባይ በተሰጠው ነገር ላይ ለመግባባትና ክፍተትን ሞልቶ ውጤት ለማምጣት ብዙም አይቸገሩም፡፡
6. ለውጥ ፈላጊ መሆን አለብን፡- ካለፈው ነገር ላይ በመነሳት ለወደፊት የሚጠቅም ሂስ መሆን አለበት፡፡
7. ቁልፍ በሚባሉ ጉዳዮች በመረጃና በእውነት ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት፡፡ ይህ ሲሆን ተቀባዩ ክፍተቱን በትክክል እንዲያይ እንዲሞላ ለውጥ እንዲያመጣ ያደርገዋል፡፡
8. ሂስ የሚጀመረው በመጀመሪያ ለሰራው ስራና ላሳየው ተነሳሽነት ምስጋናና እውቅና በመስጠት መሆን አለበት፡፡
9. ነገሮች እንዲለወጡና ያለን ተነሳሽነት በምንሰጠው ሂስ ማሳየት አለብን፡፡
10. ሂሱን በምንሰጥበት ጊዜ የምናነሳቸው ጉዳዮች ለዚህ ተብሎ በተነሳው ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ የሚያጠነጥን መሆን አለበት፡፡ ከጉዳዩ ወጪ የሆነ ሂስ አስተማሪነቱ ያን ያህል የጎላ አይሆንም፡፡
በአጠቃላይ ሂስ ሰዎች ክፍተታቸውን እንዲያርሙና ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያግዝ አንደኛው መንገድ ነው፡፡ ሆኖም ሂሱን እንዲሁ እንደመጣልን ሳይሆን ከላይ በተጠቀሱትና ሌሎች መንገዶች ለተቀባዩ የማድረስ የታለመለትን ዓላማ እንዲያሳኩ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

የብአዴን ማእከላዊ ቁጥጥርና ኦዲት ኮሚሽን የበጀት አመቱን የስራ አፈጻጸም በመገምገም ተሞክሮዎችን ቀምሮ ለዞኖች በማውረድ እና የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል
30/06/2017

የብአዴን ማእከላዊ ቁጥጥርና ኦዲት ኮሚሽን የበጀት አመቱን የስራ አፈጻጸም በመገምገም ተሞክሮዎችን ቀምሮ ለዞኖች በማውረድ እና የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል

የምዕ/ጎጃም ዞን የብአዴን ቁጥጥርና ኦዲት ኮሚሽን በ10//09/09ዓ.ም በበጀት አመቱ እስከ አሁን ያለውን የአፈጻጸም ግምገማ እና ቀጣይ አቅጣጫ የዞን ስራ አመራር ሁሉም ባለበት እና ከሁሉም...
20/05/2017

የምዕ/ጎጃም ዞን የብአዴን ቁጥጥርና ኦዲት ኮሚሽን በ10//09/09ዓ.ም በበጀት አመቱ እስከ አሁን ያለውን የአፈጻጸም ግምገማ እና ቀጣይ አቅጣጫ የዞን ስራ አመራር ሁሉም ባለበት እና ከሁሉም ወረዳዋች የኮሚሽን ኃላፊዋች እና ብአዴን ኃላፊዋች ባሉበት በቡሬ ከተማ መድረክ እየተካሄደ ነው፦

15/12/2016

የምእራብ ጎጃም ዞን ቁጥጥርና ኦዲት ኮሚሽን በጥልቅ ተሃድሶ የ2008 አመት እቅድ አፈጻጸምና የ2009 አመት እቅድ ኦረንቴሽን ፕሮግራም
ፍኖት ሰላም 06/04/2009

ዴሞክራሲያችን ጥልቀት እንዲኖረው ማድረግ የወቅቱ ዋነኛ አጀንዳ ነው፡፡በሃገራችን ዲሞክራሲያዊ ስርአት ተዘርግቶ ህዝቦች ሉአላዊ የስልጣን ባለቤቶች እንዲሆን ከተደረገ ሩብ ምእተ አመት ተቆጥሯል...
20/09/2016

ዴሞክራሲያችን ጥልቀት እንዲኖረው ማድረግ የወቅቱ ዋነኛ አጀንዳ ነው፡፡
በሃገራችን ዲሞክራሲያዊ ስርአት ተዘርግቶ ህዝቦች ሉአላዊ የስልጣን ባለቤቶች እንዲሆን ከተደረገ ሩብ ምእተ አመት ተቆጥሯል፡፡ዲሞክራሲያችንም የልማታዊነታችን መሰረት ነው ብሎ የወሰደው ልማታዊ መንግስታችን ዲሞክራሲ ስር እንዲሰድ ባለፉት አመታት ሰፊ ስራዎችን ሰርቷል፡፡ ስለሆነም በመጣው ለውጥ ህብረተሰባዊ ዲሞክራሲያዊነት እያዳበረ በመምጣቱ ለየትኛውም ፀረ ዲሞክራሲያዊ ሁኔታና አያያዝ የማይመችና የሚጎረብጥ እየሆነ መቷል፡፡ አሁንም ግን ዲሞክራሲያዊነትን ማጥለቅ የወቅቱ ዋነኛ አንገብጋቢ አጀንዳ ነው፡፡በራሳችንም በህዝቡም ውስጥ ዲሞክራሲ በቀጨጨ ቁጥር ለዜሮ ድምር ፖለቲካ ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረ ይሄዳል፡፡ የኪራይ ሰብሳቢነት ዋሻ የሚመነጠረው በዲሞክራሲ ሃይል ብቻ ነው፡፡ስለሆነም በድርጅታችንም ውስጥ በህዝቡም ውስጥ የሚታዪ የፀረ ዲሞክራሲ ዝንባሌዎችን ያለምህረት መታገል ያስፈልጋል፡፡ ብዙሃነትን በብቃት ያስተናገደው ስርአታችን ማእከላዊ የብቃት ሚስጥሩ ዲሞክራሲያዊነት ነው፡፡
ድርጅታችንም በግልፅ እንዳስቀመጠው የመድረኩ ትግል ውጤቱ አንድም ተያይዞ ማደግ፣ አልያም ተያይዞ መጥፋት እንደሆነ በንድፈ ሃሳብ ብቻ ሳይሆን ከራሳችን አገር የውድቀትም ሆነ የዕድገት ጉዞ ያስቀመጠው ጉዳይ ነው፡፡ በኪራይ ሰብሳቢነት ጎራ የተሰለፉት የትምክህት የጥበት እንዲሁም የሃይማኖት አክራሪዎች ሃገራችንን የመዘነጣጠል አልያም በጉልበት ጠቅልሎ የገዥ መደብ የመሆን ፍላጎት እንጂ በመፈቃቀድ ላይ ተመስርቶ አብሮ የመልማት እና አገራዊ ግብ የሌለው በመሆኑ ይህ ወቅታዊ ትግል በልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች የበላይነት እንዲፈታ ከማድረግ ውጭ ሌላ አማራጭ የለንም፡፡ በመሆኑም የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች የበላይነት እንዲያገኙ ዋነኛው መፍትሄ ጥልቀት ያለው ዲሞክራሲ ሲሰፍን ብቻ ነው፡፡ ልማታዊነት በመድረክ አሸናፊ አስተሳሰብ ነው፡፡
በእርግጥ ዲሞክራሲያዊነት እንዲጎለብት ስለፈለግን ብቻ ይሆናል ማለት አይቻልም፡፡ ሰፊ ሁለንተናዊ ትግል የሚጠይቅ ነው፡፡ የብዙ አካላት ሚና ወሳኝ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ተተኪ የሌለውን ሚና የሚጫወተው ግን ራሱ ህዝቡ ነው፡፡ ዲሞክራሲያዊ ስርአት መዘርጋት ብቻውን ለዲሞክራሲ መረጋገጥ ዋስትና አይሆነውም ዘላቂ የሆነ ትግል ይጠይቃል፡፡ ተቋማት ከመገንባት በዘለለ እያንዳንዱ ተቋም፤ አደረጃጀት ፤ህዝብ፤ ቡድኖችና ግለሰቦች ጥብቅናውን በተግባር ማረጋገጥ አለበት፡፡
በዚህ መሠረት የመጀመሪያው ትልቁ ስራችን መሆን ያለበት ዴሞክራሲን ማስፋት deepening democracy ሊሆን ይገባዋል፡፡ ግጭት የመፍትሄ መንገድ የሚሆነው ሰዎች በዴሞክራሲያዊና ህጋዊ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ አመኔታ ሲያጡ ብቻ ነው፡፡ የራሳችን የ97 ዓ.ም የግጭት አፈታት ተሞክሯችን እንደሚያሳየው ዴሞክራሲን ማስፋት የግጭት መንገዶችን ይዘጋል፡፡ በአኳያው ዴሞክራሲ ማጥበብ የግጭት መንገዶችን ያሰፋል፡፡ ምንም እንኳ ዴሞክራሲን ማስፋት በብዙ መሰረታዊ ምክንያቶች የሚታመንበት መሠረታዊ መርሆዋችን በመሆኑ በራሱ ምክንያት መስፋት ያለበት መሆኑ ባያጠያይቅም አመጽን ለማስቀረት ባለው ፋይዳ ደግሞ በተለየ ትኩረት ልናሰፋና ልናጠልቀው የሚገባ ይሆናል፡፡
ስለሆነም ዴሞክራሲያችንን የማጥለቅ deepening democracy እንቅስቃሴ ማካሄድ አጣዳፊ ሆኖ ሊወሰድ ይገባዋል፡፡ ይህም ዴሞክራሲን በድርጅትና በህብረተሰብ ውስጥ ማስፋትና ጥልቀት እንዲኖረው ማድረግ ማለት ሲሆን ህብረተሰቡንና አባላት በችግር አፈታቱ ላይ ገንቢ ሚና የሚጫወትበት ዴሞክራሲን ከማስፋት የሚጀምር ሊሆን ይገባል፡፡
ስለሆነም ህዝባችን የሰላማችን ዋስትና ጥልቀት ያለው ዲሞክራሲያዊ ስርአት መሆኑን ተገንዝቦ ለተግባራዊነቱ በተደራጀ መንገድ መረባረብ ይገባዋል፡፡ ችግሮችን በዲሞክራሲያዊ መንገድ ለመፍታት አማራጭ የሌለው አድርጎ መውሰድ

27/05/2016
የብአዴን ማእከላዊ ቁጥጥርና ኦዲት ኮሚሽን በአዲስ አበባ ፣ ፓርላማ ፣ ውጭ ጉዳይ እና ፌደራል ላይ ባሉ የኦዲትና ቁጥጥር ኮሚሽን አመራሮች ጋር በኮሚሽኑ ተግባራቶች አፈፃፀም ላይ በአዲስ አበ...
27/05/2016

የብአዴን ማእከላዊ ቁጥጥርና ኦዲት ኮሚሽን በአዲስ አበባ ፣ ፓርላማ ፣ ውጭ ጉዳይ እና ፌደራል ላይ ባሉ የኦዲትና ቁጥጥር ኮሚሽን አመራሮች ጋር በኮሚሽኑ ተግባራቶች አፈፃፀም ላይ በአዲስ አበባ ከተማ ውይይት አካሄደ።

Address

Bahir Dar
Bahir Dar

Telephone

0582180551

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ANDM central inspection and audit commission office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share