18/08/2026
የህፃናት ማቆያ ማዕከል ለሠራተኞች ውጤታማነትና ለተቋማት አፈጻጸም የላቀ አስተዋጽዖ እንደሚኖረው ተገለፀ።
የህፃናት ማቆያ ማዕከል መኖሩ የሠራተኞችን የሥራ ተሳትፎና ውጤታማነት በማሳደግ ለተቋማት የሥራ አፈጻጸም የላቀ አስተዋጽዖ እንዳለው ተገለፀ።
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ የህፃናት ማቆያ ማዕከልን ተግባራዊ በማድረግ፣ ሠራተኞች ልጆቻቸውን በሚሰሩበት አካባቢ በምቾት እንዲያቆዩና ጡት የሚያጠቡበት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን አስታውቋል።
የመምሪያው ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት ነጋ እንደገለፁት፣ የህፃናት ማቆያ ማዕከሉ መኖሩ በተለይም ሠራተኛ እናቶች ስለልጆቻቸው ያላቸውን ጭንቀት በመቀነስ በሥራቸው ላይ የተሻለ ትኩረት እንዲያደርጉ ያግዛል።
ይህም ሠራተኞች የሥራ ተሳትፎአቸውን እንዲያጠናክሩ፣ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በብቃት እንዲወጡና የተቋሙን የሥራ አፈጻጸም እንዲያሻሽሉ የሚያስችል መሆኑን ኃላፊዋ ገልፀዋል።
እናቶች ልጆቻቸው በአጠገባቸው በደህና መቆየታቸውን ሲያውቁ ከልጆቻቸው ጋር በቀላሉ ለመገናኘትና በሥራቸው ላይ በተረጋጋ መንፈስ ለመስራት የተሻለ እድል እንደሚያገኙም ገልጸዋል።
የህፃናት ማቆያ ማዕከሉ ለሠራተኞች ደህንነትና እርካታ፣ ለተቋሙ ውጤታማነት እና ለአገልግሎት ጥራት የራሱ የሆነ አስተዋጽዖ እንዳለውም ኃላፊዋ አስረድተዋል።
ማዕከሉ ለህፃናት ይበልጥ ምቹና ማራኪ እንዲሆን ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር የተለያዩ የማሻሻያ ሥራዎች ማከናወኑን ወ/ሮ ሰላማዊት ነጋ ገልጸዋል።
በተቋሙ የህፃናት ማቆያ አገልግሎት መጀመሩ ልጆቻቸውን በአቅራቢያቸው በማግኘታቸው ሥራቸውን በተረጋጋ መልኩ ለማከናወን እንደሚያስችላቸው የመምሪያው ሠራተኞች ተናግረዋል።
በአጠቃላይ የህፃናት ማቆያ ማዕከል ለሠራተኛ እናቶች ምቹ የሥራ አካባቢን ከመፍጠር ባለፈ፣ የሠራተኞችን ተሳትፎና ውጤታማነት በማሳደግ የተቋማትን አገልግሎት ጥራትና የሥራ አፈጻጸም ለማሻሻል አስፈላጊ ማህበራዊ ድጋፍ መሆኑ ተገልጿል።
ማእከላዊ ጎንደር ዞን ኮሚዩኒኬሽን
ከአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ
ፌስቡክ https://www.facebook.com/share/191YyDU2YK/
ዩቲዩብ http://www.youtube.com/
ቴሌግራም https://t.me/AmharaBureauofFinance
ዋትስአፕ https://whatsapp.com/channel/0029Vb8BHKA4SpkAKHBs6M0H
ኢንስታግራም https://www.instagram.com/amhara415?igsh=MTh1Nzd3dnNpaWRxMg==
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/.finance.bureau?_r=1&_t=ZS-98Pv19CAtHA
ዌብሳይት http://www.amharabofec.gov.com/
ኤክስ (ትዊተር) https://twitter.com/