04/09/2026
የሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች ለልምድ ልውውጥ ባህርዳር ከተማ ገቡ፤
በሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ በአቶ ሄኖክ ሙሉነህ የተመራ የአመራርና ባለሙያዎች ቡድን ለስራ ጉብኝትና ለልምድ ልዉዉጥ ባህርዳር ከተማ ገብቷል።
የጉብኝት ቡድኑ በባህርዳር በላይ ዘለቀ አየር ማረፊያ ሲደርስ በአማራ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አባይ መንግስቴ፣ በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ሰጥዬን ጨምሮ የቢሮዉ ምክትል ቢሮ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገዉላቸዋል።
ቡድኑ በባህርዳር በሚኖረው ቆይታ ከአማራ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ እና ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ በመምከር የልምድ ልውውጥ እና የአጋርነት ስምምነትም ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጫኑ።
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/
Ticktock: https://www.tiktok.com/?_t=ZM-8uQMisH1Hd7&_r=1
Website: https://www.amharacomm.gov.et