ANRS Labour and Skill Bureau

ANRS Labour and Skill Bureau government

18/05/2026

በይፋት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተሰራ!!

የአማራ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ሰራተኛው፣ሰልጣኙና ስራፈላጊው በዲጂታላይዜሽን ስርዓት ውስጥ ማለፍ እንደሚገባ አስታውቀ።የቢሮው የተቋማት አቅም ግንባታ አግባብነትና ብቃት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬ...
13/05/2026

የአማራ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ሰራተኛው፣ሰልጣኙና ስራፈላጊው በዲጂታላይዜሽን ስርዓት ውስጥ ማለፍ እንደሚገባ አስታውቀ።
የቢሮው የተቋማት አቅም ግንባታ አግባብነትና ብቃት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሙላው ልመንህ በግምገማ መድረኩ እንደገለፁት ሲቪል ሰርቫንቱ፣ ሰልጣኙና ስራ ፈላጊው ዲጂታል ክህሎትን በመሰነቅ እንደሀገር እየተተገበረ የሚገኘዉን ኢኒሸቲቭ እውን ማደረግ ይገባል። በስልጠናው ሰራተኞችና ሰልጣኞችን በቤዚክና ኢንተርሚዲየት ደረጃ በማሰልጠንና በማብቃት ስራአጥ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ የክልል አመራሮችና ባለሙያዎች፣የዞን ሥራና ክህሎት ቡድን መሪዎች፣የግልና የመንግስት ኮሌጅ ዲኖችና የአይሲቲ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሲሆኑየዲጅታል አማራ ክህሎት ለዜጎች ፈጣን እና ምቹ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለን ዘርፍ ስለሆነ በቀጣይ ሰፊ ንቅናቄ በማድረግ በቁጭት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በክልል ደረጃ የተጀመረው የዲጂታል አማራ ኢኒሼቲቭ በቴክኖሎጂ ፈጠራ፣ ዕውቀትና ክህሎት የላቁ ዜጎችን ለማፍራት ታልሞ እየተሰራ እንደሚገኝ የተናገሩት ደግሞ አቶ ዘላለም ታዬ ሲሆኑ ሰልጣኞች ከስልጠናው በኋላ ሰፊ የስራዕድል መፍጠር እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።

የዲጂታል ሥርዓቱ ትግበራ የመረጃ አያያዝን ለማዘመን፣ አገልግሎትን ቀልጣፋና ግልጽ ለማድረግ እንዲሁም ለሥራ ፈላጊዎችና ለሠልጣኞች ቀላል ተደራሽነትን ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና እንዳለው አቶ ዘላለም ተናግረዋል።

‎በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ኩመር አፍጥጥ ቀበሌ በUNHCR ፣ በIHS እና RRS ድጋፍ በተለያዩ የሙያ ክህሎት ለሰለጠኑ ወጣቶች የተለያዩ የስራ  ማስጀመሪያ ማሽነሪዎች ርክክብ ድጋፍ...
09/05/2026

‎በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ኩመር አፍጥጥ ቀበሌ በUNHCR ፣ በIHS እና RRS ድጋፍ በተለያዩ የሙያ ክህሎት ለሰለጠኑ ወጣቶች የተለያዩ የስራ ማስጀመሪያ ማሽነሪዎች ርክክብ ድጋፍ አደረጉ ።

‎UNHCR ፣ IHS እና RRS የተባሉ ድርጅቶች በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ኩመር አፍጥጥ ቀበሌ መጠለያ ካምፕ ለሚገኙ ስደተኞች ድጋፍ እያደረጉ የሚገኙ ድርጅቶች ሲሆን ስደተኞችን ተቀብሎ እያስተናገደ ለአለው ማህበረሰብም ልዩ ልዩ ድጋፎችን እያደረጉ ይገኛሉ።

‎ድርጅቶቹ በኩመር አፍጥጥ ቀበሌ የተለያዩ ማሽነሪዎችን ማለትም ትራክተር፣የባጃጅ፣የደረቅ ጭነት ባጃጅ፤የወፍጮ፣የብየዳ ማሽን፣የቡልኬት ማምረቻ እና ሚክሰር ማሽን ድጋፍ አድርጓል ።

‎በድጋፉም የምዕራብ ጎንደር የዞን ተወካይ አስተዳዳሪ እና የዞኑ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስፋው በሪሁን ,የመተማ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግዛት ሰረፀ እና ሌሎች የዞን እና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የፕሮጀክቱ አመራሮች በተገኙበት ርክክብ ተደርጓል።

#‎መተማ ወረዳ ኮሙኒኬሽን
‎ሚያዝያ 23/2018

07/05/2026
የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ፖሊሲዎች በተግባር እየተተረጎሙ መሆኑ ተገለጸ።በባህር ዳር ከተማ ጣና ክፍለ ከተማ ከሚገኙ ወጣቶች ጋር በወቅታዊ የሰላም፣ የልማት እና የመልካም አ...
07/05/2026

የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ፖሊሲዎች በተግባር እየተተረጎሙ መሆኑ ተገለጸ።

በባህር ዳር ከተማ ጣና ክፍለ ከተማ ከሚገኙ ወጣቶች ጋር በወቅታዊ የሰላም፣ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተካሄደ።

በመድረኩ ላይ ወጣቶች በከተማው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ያላቸው ሚና እና ተጠቃሚነታቸውን ማሳደግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአብክመ ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አማረ አለሙ፤ መንግስት ለወጣቱ በክህሎት ግንባታ እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
"ወጣቱን በልማቱ ንቁ ተሳታፊ እና ተጠቃሚ የሚያደረግ ፖሊሲዎችና ስትራቴጅዎች ተቀርጸው ተግባራዊ እየተደረገ ያለ መሆኑን አውስተው መንግስት ወጣቱን ከዳር ተመልካችነት ወደ ንቁ ተሳታፊነት የሚያሸጋግሩ እና በአበርክቶው ልክ ተጠቃሚ እንዲሆን እየተሰራ ነው" ሲሉ አብራርተዋል፡፡

በሌላ በኩል የጣና ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ጌትነት ካሴ ወጣቱ በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ ያለውን ጉልበትና እውቀት ለልማት እንዲያውለው ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ መሆኑን ጠቁመዋል። በተለይም በከተማ ግብርና፣ በኢንዱስትሪ እና በአገልግሎት ዘርፎች ወጣቶች ተደራጅተው እንዲሰሩ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በመደርኩ ላይ ተናግረዋል።

በመድረኩ ተሳታፊ የሆኑት ወጣት ቴዎድሮስ አደራጀው እንደገለጹት ቀደም ሲል ወጣቶች በልማት ስራዎች ላይ ያላቸው ተሳትፎ በዘመቻ ስራዎች ላይ ብቻ የተገደበ አንደነበር አንስተው አሁን የተነደፈው እና ተግባራዊ እየሆነ ያለ አቅጣጫ ወጣቱ በልማቱ ውስጥ በባለቤትነት እንዲሳተፍና በላቡ ልክ ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያስችል ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ሌላኛዋ ሃሳብ የሰጠችው ወጣት የሽወርቅ አዲሱ መንግስት ወጣቱ የሥራ ባህሉን እንዲያሳድግና በሰለጠነበት ሙያ የስራ እድል እንዲያገኝ አመቺ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ትርጉም ያለሙ እንቅስቃሴ ማድረግ ይገባል ስትል ሀሳቧን ሰጥታለች።

በመጨረሻም ወጣቱ ከሥራ ዕድል ፈጠራ ጎን የሃገራቸውን የሰላም ዘብ እና ሁለንተናዊ ብልጽግ እንዲረጋገጥ ፋና ወጊ መሆን እንዳለበት እና የወጣቶችን የክህሎት ክፍተት በመለየትና የሥራ ቦታዎችን በማመቻቸት ረገድ መንግስት የሚጠበቅበትን ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል በመግባት ወጣቶችም በከተማው አስተዳደር የሰላም እና የልማት ስራዎች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ እና ባለቤትነት አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል።

ባህርዳር፥ ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም

https://www.ena.et/web/amh/w/amh_8768174
03/05/2026

https://www.ena.et/web/amh/w/amh_8768174

ደሴ ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን የተላመደ ብቁ የሰው ኃይል በማፍራት፣ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ስራና...

የአገልግሎት ጥራት አዲስ ምዕራፍ፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ የISO ትግበራን ጀመረ!!!በአማራ ክልል የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመንና ተቋማዊ ብቃትን ለማረጋገጥ እየተከናወነ ባለው ሰፊ ...
29/04/2026

የአገልግሎት ጥራት አዲስ ምዕራፍ፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ የISO ትግበራን ጀመረ!!!

በአማራ ክልል የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመንና ተቋማዊ ብቃትን ለማረጋገጥ እየተከናወነ ባለው ሰፊ የሪፎርም እንቅስቃሴ፣ የሥራና ክህሎት ቢሮ የዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃን (ISO)ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችለውን የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ በይፋ አካሂዷል።

ይህ ስምምነት በቢሮው ኃላፊ **ዶ/ር ስቡህ ገበያው እና በኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሰረት በቀለ መካከል የተፈረመ ሲሆን፣ ቢሮው በቀጣዮቹ ስድስት ወራት ውስጥ የዓለም አቀፍ ደረጃውን አሟልቶ ሰርቲፋይድ ለመሆን ያለውን ቁርጠኝነት ያረጋገጠበት ነው።

የተቋማዊ ሪፎርም ስኬት
የሥራና ክህሎት ቢሮ በክልሉ የሪፎርም ሥራ እንዲጀምሩ ከተለዩ ስምንት ግንባር ቀደም ተቋማት አንዱ ነው። ተቋሙ የሪፎርም ዕቅዱን ወደ ተግባር በለወጠበት በዚህ ወቅት፣ የISO ትግበራን እንደ ዋና መሳርያ በመጠቀም የአሰራር ግልፅነትንና ቀልጣፋ አገልግሎትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ይገኛል።

ከኮሌጆች ወደ ቢሮ ደረጃ
ቢሮው የጥራት ደረጃን የማስፈን ጉዞውን የጀመረው በስሩ በሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ላይ ሲሆን፣ እስካሁን የታዩ ውጤቶች ተስፋ ሰጪ ናቸው፡:

በ2017 በጀት ዓመት፡5 ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች የISO ትግበራን አጠናቅቀው ሰርቲፋይድ ሆነዋል።
ለ2018 የተያዘ ግብ፡ተጨማሪ 7 ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆችን የጥራት ማረጋገጫ ባለቤት ለማድረግ ዝግጅቱ ተጠናቆ ወደ ሥራ ተገብቷል።

ወደፊት የሚጠበቁ ውጤቶች ቢሮው የጥራት ደረጃውን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሲያደርግ፣ በክልሉ ያለውን የሥራ ስምሪት፣ የክህሎት ልማትና የኢንዱስትሪ ትስስር ሥራዎችን በዘመናዊና በሰለጠነ መንገድ ለመምራት ያስችለዋል። ይህም በዜጎችና በተገልጋዮች ዘንድ ያለውን አመኔታ ከመጨመሩም በላይ፣ ለክልሉ ልማት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ይጠበቃል።

ዛሬ የተጀመረው ይህ የISO ትግበራ ሂደት፣ ቢሮው ለጥራትና ለላቀ አገልግሎት የሰጠውን ከፍተኛ ቦታ የሚያሳይ ሲሆን፣ ለሌሎች ተቋማትም አርአያ የሚሆን ስራ ነው።

“መልካም የትግበራ ጊዜ”

27/04/2026
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለ16 ሺ ወጣቶች  የሥራ እድል መፍጠሩን የምዕራብ ጎንደር ዞን ሥራ እና ክህሎት መምሪያ አስታወቀ።  ወጣት ቅዱስ ተወልደ እና ወጣት ናትናኤል ጨቅላ በምዕራብ ጎንደር ዞን...
27/04/2026

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለ16 ሺ ወጣቶች የሥራ እድል መፍጠሩን የምዕራብ ጎንደር ዞን ሥራ እና ክህሎት መምሪያ አስታወቀ።

ወጣት ቅዱስ ተወልደ እና ወጣት ናትናኤል ጨቅላ በምዕራብ ጎንደር ዞን የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ነዋሪዎች ናቸው።

በብረታብረት እና በጣውላ ሥራ በግለሰብ ቤት ተቀጥረው ይሰሩ እንደነበር ያስታወሱት ወጣቶቹ አሁን ላይ የራሰቸውን ከፍተው ህይዎታቸውን እየመሩ እንደሚገኙ ነግረውናል፡፡

መንግሥት ያመቻቸላቸውን ብድር ተጠቅመው ውጤታማ እንደሆኑም አስረድተዋል፡፡ እየሰሩት ባለው ሥራ የበለጠ ውጤታማ ይሆኑ ዘንድ የገቢያ ትስስር እና የመስሪያ ቦታ እንዲመቻችላቸውም ባለ ራዕይ ወጣቶቹ ጠይቀዋል።
በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ልክ እንደነ ወጣት ቅዱስ ሁሉ ሌሎችንም ተጠቃሚ ለማድረግ ታልሞ እየተሰራ እንደሚገኝ የወረዳው ሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ተወካይ ሀላፊ አቶ እያሱ ደባስ አረጋግጠዋል።

እንደ ተወካይ ሀላፊ ገለጻ በወረዳው ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ ከ2ሺ 5 መቶ በላይ ወጣቶችን በቋሚ እና በጊዜያዊ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል። በቀጣይ ሌሎች ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት ይሰራል፡፡

የምዕራብ ጎንደር ዞን ሥራና ክህሎት መምሪያ ሀላፊ አቶ ኤፍሬም ወርቁ በበኩላቸው መንግሥት ካስቀመጣቸው የአምሰት አመት አቅጣጫ መካከል ወጣቶችን በተለያየ የሙያ ዘርፍ ተጠቃሚ ማድረግ መሆኑን ገልጸው ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መኾኑን ተናግረዋል፡፡

መምሪያው በበጀት ዓመቱ 24ሺ ወጣቶችን በቋሚ እና በጊዜያዊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር አቅዶ16ሺ ወጣቶችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።

ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመስራት ከ225 ሚሊዮን ብር በላይ የብድር ሁኔታዎችን በማመቻቸት ለሥራ ፈጣሪ ወጣቶች የተሰጣቸው መኾኑን ኀላፊው አስረድተዋል።
የገበያ ትሥሥር ለመፍጠር የተፈጠረው የሰላም ችግር እንቅፋት ሆኖ መቆየቱን የጠቀሱት ሀላፊው ያለውን አንፃራዊ ሰላም በመጠቀም የተሻለ ትሥሥር ለመፍጠር እየተሰራ እንደሚገኝም አመላክተዋል፡፡

ከመስሪያ ቦታ አለመመቻቸት ጋር ተያይዘው የሚታዩ እክሎችን ለመቅረፍ ከአጋር አካላት ጋር እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡ለሌሎች የዞኑ ሥራ ፈላጊ ወጣቶች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ዞኑ እንደሚሰራም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

መረጃው የአሚኮ ነው

የአብክመ የሥራ እና ክህሎት ቢሮ የ9 ወራት የሥራ አፈፃፀም እና የሪፎርም ትግበራ ሂደት አስመልክቶ ዛሬ ግምገማ አካሂዷል።የአብክመ የሥራ እና ክህሎት ቢሮ  የቢሮው ሥራ አመራር አባላት በተገ...
16/04/2026

የአብክመ የሥራ እና ክህሎት ቢሮ የ9 ወራት የሥራ አፈፃፀም እና የሪፎርም ትግበራ ሂደት አስመልክቶ ዛሬ ግምገማ አካሂዷል።

የአብክመ የሥራ እና ክህሎት ቢሮ የቢሮው ሥራ አመራር አባላት በተገኙበት የ9 ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ እና የሪፎርም ትግበራ ሂደት ግምገማ ዛሬ አካሂዷል።በግምገማ መድረኩ ላይ የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ስቡህ ገቢያው እንደተናገሩት ለውጤታማ የሥራ አፈፃፀም ጥራት ያለው እቅድ ማቀድ ወሳኝ መሆኑን አስታውቀዋል።

ዶ/ር ስቡህ በንግግራቸው ላይም የተገኘው አፈፃፀም በተቀመጠው የክልሉ የአምስት ዓመት የአሻጋሪ እና ልማት እቅድ ማዕቀፍ ውስጥ በተያዘው ጊዜ ውስጥ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የክህሎት ልማትና ሠላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት መፍጠር እና የቢሮው የሪፎርም ተግባራት ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደተሰራ ገልጸዋል።

በግምገማው ወቅት የቢሮው የዕቅድና በጀት ዝግጅት ዳሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ አፈራ ወርቁ በ9 ወራት ውስጥ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ላይ ዝርዝር ሪፖርት አቅርበዋል። በዚህም የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት እና የአካባቢያዊ ሥራ እድሎች ማስፋፋት ፣የክህሎት ስልጠናዎች : የሪፎርም ትግበራ ሂደትን በተመለከተ በተቋሙ አደረጃጀት፣ በአገልግሎት ማሻሻያ፣ በአዳዲስ እሳቤዎች እና በተቋማት አቅም ግንባታ ላይ የተከናወኑ ስራዎች ተገምግመዋል።

በመጨረሻም የቢሮው ኋላፊ ዶ/ር ስቡህ ገቢያው በተለይም በሪፎርሙ ትግበራ ወቅት የተሰሩ ስራዎች እና የአጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመዳሰስ በቀሪ ወራት የተሻሻለ ውጤት ለማስመዝግብ አቅጣጫ ሰጥተዋል። ከዚሁ ጋር አያይዘው የክህሎት ልማትን ከገበያ ፍላጎት ጋር ማገናኘት፣ በቢሮው የዲጂታል አገልግሎቶችን ማጠናከር እና በተቋማት ውስጥ የሰራተኛ ብቃትን ማሳደግ እንደ ቅድሚያ ተግባር መሰራት አለበት ብለዋል። የቢሮው ሥራ አመራር አባላትም የተገኘውን ውጤት በመጠቀም በቀሩትን ሶስት ወራት በተሻለ አፈፃፀም ለማጠናቀቅ ቁርጠኝነታቸውን አሳይተዋል።

Address

Bahirdar
Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ANRS Labour and Skill Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ANRS Labour and Skill Bureau:

Share