Ethiopian Ombudsman Bahirdar Branch

Ethiopian Ombudsman Bahirdar Branch በሕግ የተደነገጉ የዜጎች መብቶችና ጥቅሞች በአስፈጻሚው አካ? አዋጅ ቁጥር 1142/2011 የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋምን እንደገና ለማቋቋም የወጣ አዋጅ፡፡

......27/12/2018......ወደ 2019 አዲስ አመት በኩራት ለመሻገር የሚያበቃ የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ሰርተናልን? እስኪ ሳንሻር ቆም ብለን እራሳችንን እንመርምር፡፡የሠራ ቢሻገ...
02/09/2026

......27/12/2018......

ወደ 2019 አዲስ አመት በኩራት ለመሻገር የሚያበቃ የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ሰርተናልን? እስኪ ሳንሻር ቆም ብለን እራሳችንን እንመርምር፡፡

የሠራ ቢሻገር
ያልሰራ ቢመለስ
መልካም አስተዳደር
ምንኛ ቢታደስ !

ተቋማዊ ራስን መፈተሽ ለላቀ የመልካም አስተዳደር ጉዞ !!!………….27/12/2018………..ሂላችንም እንደምናውቀው የዘመን መለወጫ በባህላችን የደስታ፣  የአበቦች መታያ፤ ጉም ጭጋጉ ተወግዶ የ...
02/09/2026

ተቋማዊ ራስን መፈተሽ ለላቀ የመልካም አስተዳደር ጉዞ !!!

………….27/12/2018………..

ሂላችንም እንደምናውቀው የዘመን መለወጫ በባህላችን የደስታ፣ የአበቦች መታያ፤ ጉም ጭጋጉ ተወግዶ የብርሃን ማብሰሪያ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም እንደ አንድ ተቋም ያለፈውን አካሄድ መዝኖ፣ የተጓዙትን መንገድ ገምግሞና ስህተትን አርሞ ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚሸጋገሩበት ታላቅ መንፈሳዊና ማህበራዊ ድልድይ እንጂ።

ለአንድ ግለሰብ ዘመን መለወጥ የዕድሜ ቁጥር መጨመርን ብቻ ሳይሆን የህሊና ምልከታን እንደሚጠይቅ ሁሉ፣ ለአንድ ተቋም ደግሞ የአዲስ ዓመት መባቻ ማለት የመልካም አስተዳደር ጉዞውን ቆም ብሎ የሚፈትሽበት፣ የአገልግሎት ጥራቱን የሚመዝንበት እና የወገኖችን በህግ የተደነገገ መብት ማስከበሩን የሚያረጋግጥበት ተቋማዊ ኦዲት የሚያደርግበት ወርቃማ ወቅት ነው ማለት ይቻላል።

እናም አዲሱን ዓመት በደስታና በአዲስ ተስፋ ለመቀበል ከመሸጋገራችን በፊት፣ ተቋማት “ባለፈው ዓመት ለህዝባችን በመልካም አስተዳደር በኩል ምን ሰራን? የአገልግሎት መስኮቶቻችን ምን ያህል ግልጽና ፍትሃዊ ነበሩ?” ብለው ራስን መጠየቅ ከይስሙላ በዓል አከባበር ይልቅ ዘላቂና እውነተኛ የተቋም ግንባታ መደላደል የተሻ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም።

ተቋማዊ ራስን መፈተሽ (Self-Reflection) ለምን ያስፈልጋል?

በማህበራዊና ፖለቲካዊ ፍልስፍና ታሪክ ውስጥ የመልካም አስተዳደርና የተቋማት ጥራት ያለ አስተዳር ኦዲትና ያለ ተቋማዊ ምርመራ ሊጎለብት እንደማይችል ምሁራን ያስገነዝባሉ። ጥንታዊው ግሪካዊ ፈላስፋ ሶቅራጥስ (Socrates) “ያልተፈተነ ሕይወት ለመኖር ዋጋ የለውም” እንዳለው ሁሉ፣ በዘመናዊ አስተዳደርም “ያልተፈተነና ያልተገመገመ ተቋማዊ አሠራር ለሕዝብ ጠቃሚ አገልግሎት ሊሰጥ አይችልም።”

አንድ ተቋም መልካም አስተዳደርን በጥሩ መሰረት ላይ ለመትከል ከፈለገ፣ ከአዲሱ ዓመት ጩኸትና አቀባበል በፊት የውስጥ አሠራሩን፣ የባለሙያዎቹን ሥነ-ምግባር፣ የቅሬታ አቀራረብ ሥርዓቱን እና ለሴቶች፣ ሕፃናት፣ አረጋውያንና አካል ጉዳተኞች የፈጠረውን ተደራሽነት በጥልቀት ሊመረምር ይገባል ብሎ መናገር ይቻላል።

ታዋቂው የማኔጅመንት መምህር ፒተር ድራከር (Peter Drucker) ሲናገር፡
“የማይለካ ነገርን ማስተዳደር አይቻልም፤ የማይፈተን አሠራር ደግሞ ሊሻሻል አይችልም።” ብሏል፡፡

ስለሆነም ዘመን ከመቀየሩ በፊት የውስጥ አሠራርን፣ የሀብት አጠቃቀምን እና የአገልግሎት እርካታን መለካትና ማወቅ የነገው ስኬት መሰረት እንደሆነ ከግምት ማስገባት ያስፈልጋል።

የመልካም አስተዳደር ምሰሶዎችና የተቋማት ኃላፊነት

መልካም አስተዳደር በወረቀት ላይ የተጻፈ መመሪያ ወይም የቃል ኪዳን ሰነድ ብቻ አይደለም፤ በዕለት ተዕለት አገልግሎት ላይ የሚገለጥ የተቋም መገለጫ እንጂ። የዓለም ባንክና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) የመልካም አስተዳደር መሠረቶች አድርገው የሚያስቀምጧቸው የሚከተሉት ናቸው፡-

1. ሕግን ማክበርና ማስከበር (Rule of Law)
2. ግልጽነት (Transparency)
3. ተጠያቂነት (Accountability)
4. አሳታፊነትና ምላሽ ሰጪነት (Responsiveness & Inclusivity) ናቸው።
የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ኮፊ አናን (Kofi Annan) የመልካም አስተዳደርን አስፈላጊነት ሲገልጹ፡

“መልካም አስተዳደር ምናልባትም ድህነትን ለማስወገድና ልማትን ለማፋጠን የሚረዳው አንድ ዋናውና ወሳኙ መሣሪያ ነው።” ብለው ነበር።

በመሆኑም አዲሱን ዓመት ስንቀበል ተቋማቶቻችንን፡

• ለተገልጋዮች ተገቢውን አገልግሎት ስንሰጥ ነበርን?
• ችግሮቻችን ምን ነበሩ? ጠንካራ ጎናችንስ?
• ተገልጋዩ ስለ 2018 በጀት አመት አገልግሎታችን ምን ይላል?
• ሴቶችና አካል ጉዳተኞች በእኩልነትና ያለ አድልዎ አገልግሎት አግኝተዋል?
• ለአረጋውያንና ሕፃናት የሚገባቸው ልዩ እንክብካቤና ቅድሚያ ተሰጥቷል?
• ተቋማችን የሙስናና የአሠራር ጉድለቶች የጸዳ፣ ግልጽነት ያለው እንዲሆን ምን አደረግን? ወዘተ
ብሎ መጠየቅና የአሠራር ማሻሻያዎችን (Reform) ማቀድ የሁሉም አስተዳዳሪዎችና ሠራተኞች ግዴታ ነው ብሎ መናገር ይቻላል።

አዲሱ ዓመት፡ ለመልካም አስተዳደር የተስፋና የተሐድሶ ምዕራፍ

ዘመን ሲቀየር አሮጌ አስተሳሰብና በደል አብሮ ሊቀየር እንደሚገባ ዕሙን ነው፡፡ በበጀት ዓመቱ የተሰሩ ስህተቶችን መደበቅ ወይም "ባለፈው አልፏል" ብሎ ችላ ማለት መልካም አስተዳደርን አይገነባም። ይልቁንም የተፈጸሙ ጉድለቶችን በግልጽነት በመቀበል፣ ተጠያቂነትን በማረጋገጥና አሠራርን በማዘመን ወደ አዲሱ ዓመት መሸጋገር ተቋማዊ ብስለትን ያሳያልና እንጠቀምበት ለማለት እንወዳለን።

ታላቁ የሰብዓዊ መብት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ (Nelson Mandela) እንዳሉት፡
“ስኬት ማለት ፈጽሞ አለመውደቅ አይደለም፤ ይልቁንም በወደቅን ቁጥር ተነስተን ጉዞአችንን መቀጠል መቻላችን ነው፡፡”

ስለሆነም ተቋማት ባለፈው ዓመት የነበሩባቸውን የመልካም አስተዳደር እክሎች፣ የቢሮክራሲ እንግልቶችና የአገልግሎት መዘግየቶች በግልጽ ገምግመው፣ በአዲሱ ዓመት የተሻለ፣ ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊና ለዜጎች ክብር የሚሰጥ አገልግሎት ለመስጠት ራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸው ዛሬ ላይ ቆም ብለው ማሰብ አለባቸው፡፡

አዲሱ ዓመት የጽጌረዳ አበባዎች የሚፈኩበትና አየሩ በበጎ መንፈስ የሚሞላበት ወቅት እንደመሆኑ መጠን፣ የተቋማቶቻችን አሠራርና አገልግሎትም እንደ አዲሱ ዓመት የታደሰና የጠራ እንዲሆን መስራት የአቅዳችን አንዱ አካል ቢሆን መልካም ነው፡፡

ወደ አዲሱ ዓመት ከመሸጋገራችን በፊት አሁኑኑ ቆም ብለን ተቋማችንን እንመርምር! ጉድለቶቻችንን እንረም፤ ስኬቶቻችንን አጠናክረን እንቀጥል! መልካም አስተዳደር በምኞት ሳይሆን በቁርጠኝነት፣ በፍትሃዊነትና በዕለት ተዕለት ተግባር የሚገነባ የህዝብ እምነት መገለጫ ነው። አዲሱ ዓመት የሕግ የበላይነት የሚነግስበት፣ የተጋላጭ ወገኖች መብት የሚከበርበት እና የተቋማት አገልግሎት ለዜጎች እፎይታ የሚሰጥበት የላቀ የመልካም አስተዳደር ዘመን ይሁንልን
ለማለት እንወዳለን!

• ተዘጋጀ በህዝብ ግንኙትና ኮሙኒኬሽን ክፍል
ነሐሴ 27, 2018ዓ/ም
ባህር ዳር

.........27/12/2018.........
02/09/2026

.........27/12/2018.........

እስኪ ቀጥለው ያሉት ጥያቄዎች ላይ እንወያይባቸው………27/12/2018……………......በህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ከፍል የተዘጋጀ.........ጥያቄ 1፡ አንድ የግል ትምህርት ቤት የአካል ...
02/09/2026

እስኪ ቀጥለው ያሉት ጥያቄዎች ላይ እንወያይባቸው
………27/12/2018……………
......በህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ከፍል የተዘጋጀ.........

ጥያቄ 1፡ አንድ የግል ትምህርት ቤት የአካል ጉዳት ያለበትን ሕፃን ‹‹ለህጻኑ የሚሆን መሰረተ ልማት የለኝም" በሚል ምክንያት የመመዝገብ ጥያቄ ውድቅ ቢያደርገው ሕግ ጥሷል ልንል እንችላለን? ይህ ድርጊት ተቋማዊ የመልካም አስተዳደር በደል ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል? እንዴት?

ጥያቄ 2፡ በግል ፋብሪካ ውስጥ ሕፃናትን ለአደገኛ ሥራ ማሰማራት (Child Labour) በሚመለከተው ተቋም ክትትል ሳይደረግበት ቢቀር፣ የመንግሥት የቁጥጥር አካላት ተጠያቂነት ከሕግ እንዴት ይታያል?

ጥያቄ 3፡ በአንድ የመንግሥት ሆስፒታል የሕፃናት ሕክምና ክፍል በኦክስጅን እጥረት ምክንያት የሕፃናት ሕይወት ቢልፍ፣ የተቋሙ አስተዳደር "የቴክኒክ ችግር ነው" ቢል ሕጋዊና አስተዳደራዊ ኃላፊነቱ ምንድን ነው ብሎ መናገር ይቻላል? ከመልካም አስተዳደርስ አንጻር ምን ግንኙነት ይኖረዋል፡፡

ጥያቄ 4፡ በአንድ የግል ኩባንያ ውስጥ አንዲት ሴት ሠራተኛ እርጉዝ በመሆኗ ብቻ የዕድገት/የደረጃ እድል ከተከለከለች ወይም ከተሰናበተች፣ ኩባንያው የጣሰው ሕግና የመልካም አስተዳደር መርህ ምንድን ነው?

ጥያቄ 5፡ በሰራተኞች ምደባ ወቅት ለሴቶች የተሰጠውን የልዩ ትኩረት (Affirmative Action) መብት አፈፃፀም መመሪያ ሳይከተሉ በመቅረት ምደባ ማካድ የመልካም አስተዳደር ውድቀት የሚሆነው እንዴት ነው?

ጥያቄ 6፡ የግል ድርጅቶች ለሴቶች የወሊድ ፈቃድ በሚሰጡበት ወቅት በሕግ ከተደነገገው ቀናት ቀን ቀንሰው ቢሰጡ ወይም ያለ ክፍያ እንዲወጡ ቢገደዱ ሕጋዊ ውጤቱ ምንድን ነው? ከመልካም አስተዳር አንጻርስ እንዴት ይታያል?

ጥያቄ 7፡ አንድ የመንግሥት የመሬት አስተዳደር መሥሪያ ቤት በገጠር መሬት ይዞታ ምዝገባ ወቅት የሴቶችን ስም አብሮ ለመመዝገብ ፈቃደኛ ባይሆን፣ የትኛው ሕግ ማለት እንችላለን? ወይስ የተጣሰ ህግ የለም? የመልካም አስተዳደር በደልስ ሊባል ይችላል? እንዴት?
ጥያቄ 8፡ አንድ አዲስ የሚገነባ የመንግሥት ወይም የግል ሕንፃ ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ (Ramp/Elevator) ሳይኖረው የሚመለከተው የመንግስት መሥሪያ ቤት የግንባታ ፈቃድ ወይም የይዞታ ማረጋገጫ ቢሰጠው፣ የትኛው ሕግ ተጣሰ ማለት እንችላለን? አስተዳደራዊ በደልስ ተፈጸመ ሊባል ይችላል?

ጥያቄ 9፡ አንድ የአካል ጉዳተኛ በቂ ችሎታና መስፈርት እያለው "በአካል ጉዳቱ ምክንያት ሥራውን ማከናወን አይችልም" በሚል ግምት በውድድር ሳይካተት ቢቀር አስተዳደራዊ በደል ተፈጽሞበታል ልንል የምንችለው እንዴት ነው?

ጥያቄ 10፡ በባንክ ወይም በገንዘብ ተቋማት የማየት ጉዳት ያለባቸው ሰዎች በራሳቸው ፊርማ አካውንት እንዳይከፍቱና "ምስክር አምጡ" ተብለው ቢገደዱ ሕጋዊ መሠረቱ ምንድን ነው? የመልካም አስተዳደር ችግሩስ ምን ሊሆን ይችላል?

02/09/2026
የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ
27/08/2026

የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ

27/08/2026

ለፍትህና ለህዝብ ጥቅም ቆራጥ አቋም መያዝ ይገባል!
🌿🌿🌿🌿🌿

የህዝብ አገልግሎት የተሰጠው አካል የግል ጥቅሙን ሳይሆን የህዝብና የሀገርን ጥቅም በውሳኔዎቹ ሁሉ ማዕከል ማድረግ አለበት።

አድሏዊነትንና ጉቦኝነትን በቆራጥነት በመታገል ህግንና አሰራርን ብቻ መከተል የፍትሃዊነት መሰረት ማድረግ ያስፈልጋል።

እያንዳንዱ አሰራር ለህዝብ ግልጽ እንዲሆን ማድረግ እና ለሚፈፀሙ ስህተቶች ኃላፊነት መውሰድ ብልሹ አሰራርን ያከስማል።

ብልሹ አሰራርና ሙስና የእድገት ፀር፣ የፍትህ ጠላት ናቸው። ሀገርና ማህበረሰብ የሚገነቡት በታማኝነት፣ በቅንነትና በጠንካራ የሞራል ልዕልና ላይ ነው።

ኃላፊነትዎን ይወጡ፤ የህዝብ ሀብትና ንብረት የጋራችን በመሆኑ ጥበቃና እንክብካቤ ልናደርግ ይገባል።

መብትዎን ይወቁ፤ አድሏዊነትና ብልሹ አሰራር ሲያጋጥምዎት አይቀበሉ፣ በዝምታም አይለፉ!

ዝምታ ለብልሹ አሰራር ነዳጅ ነው፤ በቆራጥነት መታገል ግን የሁሉም ዜጋ ድርሻ ነው!

እስኪ እራስዎን ይፈትሹ……….20/12/2018…………1 የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ከሚከተሉት ጉዳዮች መካከል የትኛውን     የማየት ሥልጣን የለውም?•  A. የመንግሥት ሠራተኞች አስተዳደራዊ ...
26/08/2026

እስኪ እራስዎን ይፈትሹ

……….20/12/2018…………

1 የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ከሚከተሉት ጉዳዮች መካከል የትኛውን
የማየት ሥልጣን የለውም?

• A. የመንግሥት ሠራተኞች አስተዳደራዊ በደል አቤቱታዎች
• B. በፍርድ ቤት በሂደት ላይ ያሉ ወይም ፍርድ ያገኙ ጉዳዮች
• C. በአስፈፃሚ አካላት የሚወጡ መመሪያዎች መብትን መጋፋታቸውን ማረጋገጥ
• D. የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጥ ዝግጅት

2 ዋና ዕንባ ጠባቂው እና ምክትል ዋና ዕንባ ጠባቂው የሚሾሙት በማን ነው?

• A. በፌዴራል የዳኝነት አስተዳደር ጉባኤ
• B. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
• C. በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት
• D. በኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት

3 የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የተሰጠውን ውሳኔ ወይም የውሳኔ ሐሳብ ተቋማት ካልተቀበሉት የሚያደርገው እርምጃ ምንድን ነው?

• A. በተቋሙ ላይ የገንዘብ መቀጮ መጣል
• B. ጉዳዩን ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማለት
• C. የተቋሙን የበላይ ኃላፊ ወዲያውኑ ከሥልጣን ማገድ
• D. ጉዳዩን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርት ማድረግ

4 የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አቤቱታዎችን የሚቀበለው በምን ዓይነት መንገድ ነው?
• A. በጽሑፍ፣ በቃል ወይም ተቋሙ በራሱ ተነሳሽነት (በራስ ጥረት)
• B. በጠበቃ በኩል በሚቀርብ የጽሑፍ ማመልከቻ ብቻ
• C. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲመራለት ብቻ
• D. በፍርድ ቤት ትእዛዝ ሲመራለት ብቻ

5 የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ከመረጃ ነፃነት (Freedom of Information) ህግጋት ጋር ያለው ቁልፍ ድርሻ ምንድን ነው?
• A. የግል መገናኛ ብዙኃንን ይዘት መቆጣጠር
• B. ዜጎች ከመንግሥት አካላት መረጃ የማግኘት መብታቸውን ማስጠበቅ
• C. የጋዜጠኞችን ፈቃድ መሰረዝ እና ማገድ
• D. የመንግሥት ምስጢራዊ መረጃዎችን ለሕዝብ እንዳይወጡ መከልከል

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ፤ እንኳን ለ1 ሺህ 501ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!በዓሉ የሠላምና የፍቅር በዓል እንዲሆንላችሁ መልካም    ምኞ...
25/08/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ፤ እንኳን ለ1 ሺህ 501ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በዓሉ የሠላምና የፍቅር በዓል እንዲሆንላችሁ መልካም
ምኞቱን ይልጻል፡፡

በአትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም
የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
ነሐሴ 19 ቀን 2018ዓ/ም

ሙስና የመልካም የመንግስት አስተዳደር ውድቀት አንዱ ማሳያ      .........................//..............................                   18...
24/08/2026

ሙስና የመልካም የመንግስት አስተዳደር ውድቀት አንዱ ማሳያ

.........................//..............................

18/12/2018

በአለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት 'ሙስና' መቅሰፍት ነው። ጥፉ፣ ብልሹ፣ ግም እና በመሰል ነውርን በሚገልጡ ቃላት ይተረጎማል። አለቃ ኪዳነወልድ ቀጥለውም ሙስናን 'መበስበስ፤ ጥፉነት፣ ጥፋት፣ መከራ'... እያሉ ይፈቱታል። ሙስና በሃይማኖታዊ አስተምህሮ ሀጢያት፣ በዓለማዊ ሕጎች ወንጀል የሆነ፣ በማህበረሰቡ ቀደምት ብሂሎች ውግዝ ነው። በፈላስፎችና በማህበራዊ ሳይንስ ምሁራን በዘቀጠ እሴት መገለጫነቱ፣ ተያይዞ ገደል እንደሆነ ያነሳሉ።

ኦክስፎርድ መዝገበቃላትም ሙስናን (Corruption) ከአለመታመን/እምነትን ከማጉደል፣ ምግባረ ቢስነት፣ ጉበኝነት እና በመሰል ቃላት ይገልጸዋል። ከዝቅጠትና ከመቆርቆዝ ጋር ያቆራኘዋል።

የፍልስፍና ምሁሩ ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ አርስቶትል፣ ሊሰሮ፣ ማኪያቬሊ የተሰኙ ፈላስፎችን በመጥቀስ የነገረ-ሙስናን ትንታኔ ባቀረቡበት አንድ ጽሁፍ ሙስና የማህበረሰቡን የሞራል፣ የሕግና ፍትሕ እሴቶች ይንዳል፤ የፖለቲካ ብክለት መገለጫ ነው፤ የነባር ግብረ ገባዊ እሴቶች መናድ ማሳያ ነው፤ ለማኅበረሰብ ሕልውና አደጋ ነው፡፡ እናም ሙስና ምቾት፣ ቅምጥልነትና ራስ ወዳድነት መንፈስ የተጠናወተው እኩይ ምግባር መላበስ ነው። በጥቂቶች ብዙሃኑን የሚበክል ድርጊት ነው። እናም ኢ-ፍትሐዊነት፣ የግል ጥቅም አሳዳጅነት፣ ሥርዓተ ነውረኝነት፣ አድልዎ እና የሞራል ዝቅጠት እንዲለመዱ ያደርጋል ይላሉ።
ጥናቶች ሙስናን በተለያዩ ደረጃዎችና መልኮች ይገልጹታል። መጠነ ሰፊ ሙስና፣ አነስተኛ ሙስና፣ ፖለቲካዊ መስና እና ስልታዊ ሙስና በሚል ይመደባሉ።

መጠነ ሰፊ ሙስና (Grand Corruption) ከፍተኛ የመንግስት ሹመኞች የህዝብ የሆኑ ሀብቶችን ለራሳቸው ጥቅም ለማመቻቸት የመንግስትን ፖሊሲ እና አሰራር በማዛባት የሚፈጸም ነው። ይህ የሙስና አይነት በአንድ አገር መልካም አስተዳድር ለማስፈን፣ የሕግ የበላይነት ለማረጋገጥና ኢኮኖሚ መረጋጋትን ለመፍጠር የሚደረግን አካሄድ ይገዳደራል።
ጥቃቅን ወይም አነስተኛ ሙስና (petty corruption) በታችኛው የመንግስት መዋቅርና በመከከለኛ ደረጃ ያሉ የመንግስት ሹመኞችና ሰራተኞች ከህዝብ ጋር በሚኖራቸው አገልግሎት አሰጣጥ ኅላፊነትን በመተው ለግል ጥቅም በመሻት የሚፈጸም ነው። በጤና፣ በትምህርት፣ በጸጥታና በሌሎች አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ዘንድ መደበኛ ስራቸውን ለማከናወን ተጨማሪ ክፍያ ወይም ጉቦ መጠየቅ የዚህ ሙስና ማሳያ ነው። እናም ጉቦ፣ ስርቆት፣ ማጭበርበር፣ የተገልጋዮች ላይ አድልዎ መፈጸም የመሳሰሉትን የሙስና ተግባራትን ያካትታል። በርግጥ እነዚህ ድርጊቶች እንደ ገንዘቡ መጠን ስፋት ሁኔታ ተመዝነው በመጠነ ሰፊ ሙስና ምድብ ሊካተቱ ይችላሉ።

ሌላው ፖለቲካዊ ሙስና /Political corruption/ ነው። ይህ ሙስና በፖለቲካ ውሳኔ ሰጭዎች አማካኝነት የሚፈጸም ነው። ይህም ፖለቲካ ውሳኔ ሰጭዎች ስልጣናቸውን ለማስቀጠል፣ ገጽታቸውን ለመገንባት፣ ሀብት ለማካበት በመፈለግ ተቋማትንና ህጋዊ አሰራሮችን በራሳቸው መንገድ የሚቀርጹበት ሂደት ነው።
ስልታዊ/ስርዓታዊ /Systemic corruption/ ሙስና አይነት ደግሞ ማህበረሰቡ በመላ ማንኛውንም ጉዳይ ለመከናወን ሙስናን እንደ መደበኛ ስርዓት የሚወስድበት አጋጣሚ ሲፈጠር ነው። ይህም አብዛኛው የመንግስት ተቋማት አገልግሎት የሚሰጡበት መንገድ በሙስና አሰራሮች የተተበተበ እና አብዛኘው ተገልጋይ አማራጭ በማጣት በተደራጁ ጥቂት ግለሰቦች ወይም ቡድኖችን ኮቴ በማሽተት የሚሄዱበት ሁኔታ ነው።

ስርዓታዊ ሙስና ተቋማትን እንዲሁም በፖለቲካዊና ማህበረ ምጣኔ ስርዓት ላይ የተቀመጡ ግለሰቦችን ባህሪም የሚጎዳ ነው። እንዲህ አይነት ሙስና በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ስር የሰደደ፣ ወጥ፣ የተደራጀና ለማስወገድ የሚከብድ ይሆናል።

ሙስና በግል እና በህዝብ ተቋማት ውስጥ በተለያየ መልኩ ይፈጸማል። በመንግስት ተቋማት ዘንድ እንደሚዘወተር በብዛት ቢገለጽም ከአነስተኛ አገር በቀል እስከ ድንበር ተሻጋሪ ኩባንያዎች እንዲሁም መንግስታዊ ባልሆኑና በግል ድርጅቶችም የከፋ እንደሆነ ጥናቶች ይጠቁማሉ። ይህም የገበያ ስርዓቱን ያቃውሳል፤ የማህበረሰቡን ኑባሬ ይበክላል።

ሙስና ድህነትን ያባበሳል፤ ሰብዓዊ መብትና ክብርን ይገፋል፤ አካባቢን ይሸረሽራል፤ ዕድገትን ይጎትታል፤ ውስጣዊና በአገራት መካከል ግጭት ይቀሰቅሳል፤ የመንግስትን ቅቡልነት እና ዴሞክራሲ ይፈታተናል።

መልኩ ምንም ይሁን ምን ሙስና ጠንክሮ መስራትን የሚኮንን፣ ሳይሰሩ መብንላትን የሚያጀግን፣ የአጋርነትን ሞራል የሚሰብር፣ ሀገርን ለውጫዊ ደህንነት ስጋት አደጋ የሚጥል፣ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን የሚያቀጭጭ፣ ውስጣዊ ስርዓትና መረጋጋትን የሚፈትን፣ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እና አጠቃላይ ዘላቂ ልማትን የሚገታ ነው። በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ታዳጊ አገራት ሙስና 'በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ' ሆኗል። (ምንጭ ከድረ ገጽ)

Address

0947111122
Bahir Dar
1957

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Ombudsman Bahirdar Branch posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Ombudsman Bahirdar Branch:

Shortcuts

Share