22/08/2026
እንኳን ለሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
በክልላችን ከነሐሴ ወር መጀመሪያ አንስቶ በዋግኽምራ፣ በሰሜን ውሎና አካባቢው በድምቀት የሚከበሩት ሻደይ፣ አሸንድየና ሶለል ረጅም ዘመናትን የተሻገሩ የሕዝባችን መገለጫ በዓላት ናቸው፡፡
የሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል በዓል በልጃገረዶችና በወጣቶች ባሕላዊ ጨዋታ ደምቀው በአደባባይ ይከበራሉ።
ልዳገረድችና ወጣቶች በክረምቱ የለመለሙ ዕፅዋትን በመጠቀም ባሕልና እሴታቸውን የሚገልጹበት እንዲሁም ወደ ብርሃኑ የመስከረም ወር እና አዲስ ዓመት ለመሸጋገር የተስፋና የደስታ ማብሰሪያቸው ነው፡፡
ሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጎብኚዎችን የሚስቡ የሕዝባችን ማህበራዊ ቁርኝትና አብሮነት የሚያጠናክሩ የማይዳሰሱ ባሕላዊ ቅርሶቻችን ናቸው።
በዓላቱን ስናከብር ሕዝባችን ለዘመናት ጠብቆ ያቆያቸውን ባህላዊ እሴቶች በማክበርና በማሳደግ፣ ለተከታዩ ትውልድ ትውፊታዊ ይዘታቸውን ጠብቀን ለማስተላለፍ በጋራ በመሥራት ሊሆን ይገባል፡፡
መልካም የሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል በዓል!