Anrs Trade and Market Development Bureau

Anrs Trade and Market  Development Bureau Amhara Trade Bureau is one of the governmental organization in Amhara Region, Bah it is government org.

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም  አደረሳችሁ!በዓሉ  የሰላም ፣ የመተሳሰብ ፣ የአብሮነት እንዲሁም የአገልጋይነት ሚናችንን የምንወጣበት እ...
07/01/2026

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በዓሉ የሰላም ፣ የመተሳሰብ ፣ የአብሮነት እንዲሁም የአገልጋይነት ሚናችንን የምንወጣበት እንዲሆን የአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ምኞቱን ይገልፃል።

መልካም በዓል!!
ኢብራሂም ሙሃመድ(ዶ/ር)
የአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ

በአማራ ክልል ከተሞች በኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት፣ በንግድ እና በገቢ አሰባሰብ ዘርፍ አበረታች  እድገት እየተመዘገበ ነው።     ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ በአማራ ክልል ከተሞች በኢንዱስትሪና ...
06/01/2026

በአማራ ክልል ከተሞች በኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት፣ በንግድ እና በገቢ አሰባሰብ ዘርፍ አበረታች እድገት እየተመዘገበ ነው።

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በአማራ ክልል ከተሞች በኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት፣ በንግድ እና በገቢ አሰባሰብ ዘርፍ አበረታች እድገት እየተመዘገበ መሆኑን በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የክልሉ የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ አሕመዲን ሙሐመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ክላስተር አስተባባሪ አሕመዲን ሙሐመድ(ዶ/ር) የሚመራ የክላስተሩ ቢሮዎች እና ተቋማት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ዛሬ በባህርዳር ከተማ ተካሂዷል።

የዘርፉ አስተባባሪ አሕመዲን ሙሐመድ(ዶ/ር) እንደገለጹት የክልሉን የ25 ዓመት አሻጋሪ የልማት ዕቅድ መሰረት ያደረገ አደረጃጀት በመፍጠር የክላስተሩ ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ እየተሰራ ነው።

ባለፉት ስድስት ወራት በክልሉ በኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት፣ በንግድ እና በገቢ አሰባሰብ ዘርፎች አበረታች ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል።

የከተማ የኢኮኖሚ ዘርፉ መነቃቃትም ለህዝቡ ምርትና አገልግሎትን በጥራት እንዲሁም በስፋት ማቅረብ እንዳስቻለ ተናግረዋል።

የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ እንድሪስ አብዱ በበኩላቸው የክልሉን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት በመጠቀም የኢንዱስትሪ ዘርፍ የልማት አቅምን የበለጠ ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት ከ182 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ከ1ሺህ 800 በላይ አልሚ ባለሃብቶች የንግድ ፈቃድ መስጠት መቻሉን ገልጸዋል።

አሰራርን በማዘመንና የአገልግሎት አሰጣጥን በማቀላጠፍ የክልሉን ኢንዱስትሪ የመልማት ዕምቅ አቅም በአግባቡ ለመጠቀም የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

የክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ኢብራሂም ሙሀመድ(ዶ/ር) በበኩላቸው ባለፉት ስድስት ወራት ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት የሚውል አንድ ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል የግብርና ምርት ማቅረብ ተችሏል።

ይህም የዘይት ፋብሪካዎችን ጨምሮ ሌሎች አምራች ኢንዱስትሪዎች በአቅማቸው ልክ እንዲያመርቱ ማድረጉን ጠቁመው ግብዓት የማቅረብ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

ከዚህ ጋር በማያያዝም በምርቶች ላይ ባዕድ ነገር በመቀላቀል ለገበያ ለማቅረብ በሚሞክሩ ህገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ እና ነዳጅን በህገ ወጥ መንገድ በሚከዝኑ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰዱንም ተናግረዋል።

ምርትን በመደበቅና ያለምንም ምክንያት የዋጋ ንረትን ሲያባብሱ በነበሩ 800 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ እንደተወሰደም ነው ያስታወቁት።


#ኢዜአ

ለገና በዓል በቂ የዕርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተገለፀ፡፡ታህሳስ 28/2018 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ዞን በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ደምቆ በዋለዉ የገና  በዓል ገበያ በቂ የሆነና ከፍተኛ ቁጥር ...
06/01/2026

ለገና በዓል በቂ የዕርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተገለፀ፡፡

ታህሳስ 28/2018 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ዞን በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ደምቆ በዋለዉ የገና በዓል ገበያ በቂ የሆነና ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ የእርድ እንስሳት ለገበያ መቅረቡን የወረዳዉ እንስሳት ሃብት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ አለሙ ገልፀዋል፡፡

ኃላፊዉ አያይዘዉም እንደ ሌሎች በዓላት ሁሉ በገና በዓል ገበያ የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ትላልቅ የደለቡ የዕርድ እንስሳቶችን ለገበያ የሚያቀርብበት ነዉ ብለዋል፡፡

ተመሳሳይ በሆኑ የበዓላት ወቅት በተለያየ መጠን እና አይነት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ የእርድ እንስሳቶች ለገበያ የሚቀርቡ ሲሆን ወረዳዉ ካለዉ የቆየ ልምድና በተመጣጣኝ ዋጋ ለግብይት ከሚያቀርባቸዉ የድልብ እንስሳቶች ላይ ለመግዛት ከተለያዩ ከተሞች የሚመጡ ነጋዴዎች እንዳሉ ኃላፊዉ ተናግረዋል፡፡

ወረዳዉ ተወዳዳሪ እየሆነና እዉቅና እያተረፈ በመጣበት የእንስሳት ድልብ ስራ በቀጣይ በተለያዩ የበዓል ገበያዎች ላይ በተሻለ መንገድ የደለቡና ጥራት ያላቸዉን የእርድ እንስሳቶችን ለገበያ በማቅረብ የሚሰራ ይሆናል ሲሉ አቶ ግርማ ተናግረዋል፡፡

ለዕርድ የሚዉሉ በቂ የድልብ እንስሳት ለገበያ ቀርበዉ እንዳገኙ በቦታዉ ላይ የተገኙ ነጋዴዎች እና ነዋሪዎች የተናገሩ ሲሆን በሌላ በኩል የግብይት ስርዓቱ በተመጣጣኝ ዋጋ እየተከናወነ እንደሚገኝ የድልብ እንስሳት ለመሸጥ ገበያ ላይ የተገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ሃሳብ ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም ኃላፊዉ የወረዳዉ አርሶ አደር ከግብርና ስራ ጎን ለጎን የእርድ እንስሳቶችን በማድለብ እና ለገበያ በማቅረብ እያደረገ ባለዉ ስራ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ እየሆነ መምጣቱን ያረጋገጥንበት ተግባር ነዉ ብለዋል፡፡

በባሕርዳር ከተማ እየተካሄደ የሚገኝ የገና በዓል የገበያ ድባብ በምስል።
06/01/2026

በባሕርዳር ከተማ እየተካሄደ የሚገኝ የገና በዓል የገበያ ድባብ በምስል።

በሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላ ጠራ ወረዳ በኮቱ ከተማ  በሰኞ ገበያ ላይ በዓልን ምክነያት በማድረግ ሲገበያይ ውሏል።የኮቱ ገበያ እጅግ በጣም ሰፉና ሁሉንም አይነት ግብይት የሚገኝበት ገበያ ሲሆን...
06/01/2026

በሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላ ጠራ ወረዳ በኮቱ ከተማ በሰኞ ገበያ ላይ በዓልን ምክነያት በማድረግ ሲገበያይ ውሏል።

የኮቱ ገበያ እጅግ በጣም ሰፉና ሁሉንም አይነት ግብይት የሚገኝበት ገበያ ሲሆን በዛሬው እለት ከተለያዩ አካባቢዎች የለተያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች በቦታው ተገኝተው ሲገበያዩ የዋሉ ሲሆን ፦

የውሎ የዋጋ ተመን ሲታይ ድልብ በሬ ከፍተኛ እስከ 120ሺ ብር፣ በግ ሙክት 24ሺ ብር ፣የፈየል ሙክት 27ሺ ብር ፣ወተት በሊትር 70ብር፣እንቁላል 20 ብር፣አውራ ዶሮ 1500 ብር ፣ቅቤ በኪሎ 1200ብር፣አይብ በኪሎ 200 ብር ሲገበያይ እንደዋለ ከንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት ያመላክታል

በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በጠገዴ ወረዳ ማክሰኞ ገበያ የገና በዓል ዋዜማ የገበያ ድባብ በምስል።        Tegedie Woreda Communication
06/01/2026

በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በጠገዴ ወረዳ ማክሰኞ ገበያ የገና በዓል ዋዜማ የገበያ ድባብ በምስል።

Tegedie Woreda Communication

በደሴ ከተማ የገና በአል ምክንያት በማድረግ የእንሰሳት እና የእንሰሳት ተዋፅኦ ግብይት እየተካሄደ ነው ።ደሴ፦(ደሴ ኮሙኒኬሽን)በደሴ ከተማ አስተዳደር  የገና በአልን ምክንያት በማድረግ ነዋሪ...
06/01/2026

በደሴ ከተማ የገና በአል ምክንያት በማድረግ የእንሰሳት እና የእንሰሳት ተዋፅኦ ግብይት እየተካሄደ ነው ።

ደሴ፦(ደሴ ኮሙኒኬሽን)
በደሴ ከተማ አስተዳደር የገና በአልን ምክንያት በማድረግ ነዋሪዎች የእለት ከዕለት ተግባራቸውን በጥሩ ሁኔታ እያከናወኑ ይገኛሉ።
ከዚህ ውስጥ አንዱ የእንሰሳትና የእንሰሳት ተዋፅኦ ግብይት አንዱ ነው።

የደሴ ከተማ አስተዳደር የእንሰሳትና አሳ ሀብት ተጠሪ ጽ/ቤት ክትትልና ድጋፍ በእንስሳት እርባታ እና ማድለብ ዜጎችን በማሰማራት በተለይ የሀገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ በምግብ ራስን መቻል ላይ መልካም ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።

የደሴ ከተማ አስተዳደር የእንሰሳትና አሳ ሀብት ተጠሪ ጽ/ቤት የእንሰሳትና እንሰሳት ምርት ተዋጽኦ ባለሙያ አቶ ጀማል መሀመድ እንደገለጹት የገና በአልን ምክንያት በማድረግ ለገበያ የሚቀረቡ እንሰሳት 4 ሽህ 7መቶ 83 የደለበ በሬ፣ 11ሺህ 5መቶ 23 በጎች፣ 1 ሽህ 7መቶ 15 ፍየል፣ ከ1ሺ 650 በላይ ዶሮ፣ እና 950ሺ እንቁላል ለገበያ የሚቀርቡ መሆኑን ገልጸዋል።

የገና በአልን ምክንያት በማድረግ ታህሳስ 27/2017ዓም በሰኞ ገበያ የእንሰሳት ግብይትን ቅኝት ባደረግነው መሠረትም፤ የደለበ በሬ (የስጋ በሬ) 60ሺ እስከ 250ሺ ብር፣ በግ ከ8ሺ እስከ 35ሺ፣ ፍየል ከ10ሺ እስከ 40ሺህ፣ የስጋ ዶሮ ከ600 እስከ1500፣ እንቁላል18 ብር እስከ 20ብር እየተሸጠ ይገኛል።

በምዕራብ ጎንደር ዞን በተለያዩ አካባቢዎች የገና በዓል ዋዜማ የገበያ ድባብ በከፊል።     ታህሳስ 28/2018ዓ.ም
06/01/2026

በምዕራብ ጎንደር ዞን በተለያዩ አካባቢዎች የገና በዓል ዋዜማ የገበያ ድባብ በከፊል።

ታህሳስ 28/2018ዓ.ም

"የገና በዓልን አስመልክቶ በብዛትና በጥራት የእርድ እንስሳት ለገበያ ቀርበዋል" የሰሜን ጎጃም ዞን እንስሳት እና አሳ ሃብት መምሪያ  በሰሜን ጎጃም ዞን የገና በዓልን አስመልክቶ በብዛትና በ...
06/01/2026

"የገና በዓልን አስመልክቶ በብዛትና በጥራት የእርድ እንስሳት ለገበያ ቀርበዋል" የሰሜን ጎጃም ዞን እንስሳት እና አሳ ሃብት መምሪያ

በሰሜን ጎጃም ዞን የገና በዓልን አስመልክቶ በብዛትና በጥራት የእርድ እንስሳት ለገበያ መቅረባቸው የሰሜን ጎጃም ዞን እንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት መምሪያ አስታወቀ።

የሰሜን ጎጃም ዞን እንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አንተነህ አዳሙ ዞኑ በእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፍ ትልቅ ፀጋ ያለው በመሆኑ ዘርፉን በማዘመን የአርሶ አደሩን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻልና ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

እንስሳትን በአይነት፣ በብዛትና በጥራት ደልበዋል ያሉት መምሪያ ኃላፊው የገና በዓልን ምክንያት በማድረግም 166ሺህ 120 የደለቡ ከብት፣56 ሺህ 197 ዳልጋ ከብት መቅረቡን ገልፀዋል።

በተጨማሪም 72 ሺህ 762 በግ እና 37 ሺህ 160 ፍየል ደልበው ለበዓል ገበያ መቅረባቸውን ነው የገለፁት።

አቶ አንተነህ አክለውም የህብረተሰቡን ፍላጎት ለማሟላትና ገበያን ማረጋጋት የሚያስችሉ 21 ሚሊዮን እንቁላል እና 120 ሺህ የሥጋ ዶሮ ቀርቧል ብለዋል።

በመጨረሻም ለ2018 ዓ/ም የልደት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ሰሜን ጎጃም ኮሙኒኬሽን

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም  አደረሳችሁ!በዓሉ  የሰላም ፣ የመተሳሰብ ፣ የአብሮነት እንዲሁም የአገልጋይነት ሚናችንን የምንወጣበት እ...
06/01/2026

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በዓሉ የሰላም ፣ የመተሳሰብ ፣ የአብሮነት እንዲሁም የአገልጋይነት ሚናችንን የምንወጣበት እንዲሆን የአብክመንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ምኞቱን ይገልፃል።

መልካም በዓል!!!

በከተማዋ ለገና በዓል  የፋብሪካና የግብርና ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ  ለህብረተሰቡ እየቀረቡ ነው።በእንጅባራ ከተማ የመጪው ገና በዓል ግብይት የተረጋጋና በቂ የምርት አቅርቦት ያለበት እንዲሆን...
05/01/2026

በከተማዋ ለገና በዓል የፋብሪካና የግብርና ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እየቀረቡ ነው።

በእንጅባራ ከተማ የመጪው ገና በዓል ግብይት የተረጋጋና በቂ የምርት አቅርቦት ያለበት እንዲሆን አስፈላጊው ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል።

የእንጅባራ ከተማ ንግድና ገበያ ልማትን ጽ/ቤት ተወካይ ሃላፊ ወ/ሮ እመነሽ ጋሻየ ÷ ለበዓሉ አስፈላጊ የፍጆታ እቃዎችን አቅርቦት ለማሳለጥ ከአጋር አካላት ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን አመልክተዋል፡፡

በዚህም ለበዓሉ አስፈላጊ የሆኑ የግብርና እና የፋብሪካ ምርቶች በበቂ መጠን በድንኳን ገበያዎች ጨምሮ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርቡ ተደርጓል ብለዋል።

በበዓል ግብይት ወቅት ዋጋ ጭማሪና ሕገ ወጥ የንግድ ተግባራትን ለመከላከል ከተማ አስተዳደሩ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በተለይም የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ተፈላጊነታቸው የሚጨምሩ ምርቶች ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት የማሕበረሰቡን ፍላጎት ለማሟላት ጥረት ተደርጓል ነው ያሉት፡፡

ለበዓሉ 329 ኩልታል ስኳር፣ 100 ኩንታል የዳቦ ዱቄት፣5ሽ ሊትር ዘይት፣እንቁላል፣ሽንኩርት የወተት ተዋፅኦዎች እና የአትክልትና የፍራፍሬዎች ግብዓቶች በስፋት ለሸማቹ ተደራሽ እየሆኑ እንደሚገኝ ተወካይ ሀላፊዋ አስታውቀዋል።

በዚህም ለተሳተፉ አቅራቢ ድርጅቶችና ለበረካ ዱቄት ፋብሪካ ምስጋና አቅርበዋል።

የበዓል ግብይቱ እስከ ነገ ታህሳስ 28/2018 ዓ.ም እንደሚቀጥል የጠቆሙት ሀላፊዋ ቀጣይም በከተማዋ በተለያዩ በሮች የድንኳን ገበያዎችን በማስፋፋት እንደሚሰራ ወ/ሮ እመነሽ ገልፀዋል።

"የንግድ ትርኢትና ባዛርን በዳንግላ ወረዳ እየተካሄደ ነው የዳንግላወረዳ  ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ከስርዓተ ምግብ ማጠናከር ፕሮግራም (FSRP) ጋር በመተባበር በግብርና ፣ በእንስሳት እ...
05/01/2026

"የንግድ ትርኢትና ባዛርን በዳንግላ ወረዳ እየተካሄደ ነው

የዳንግላወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ከስርዓተ ምግብ ማጠናከር ፕሮግራም (FSRP) ጋር በመተባበር በግብርና ፣ በእንስሳት እና እንስሳት ተዋፅኦ ምርቶች ላይ የወረዳውንና የከተማውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ የንግድ ትርኢትና ባዛር በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

የጽ/ቤቱ ሃላፊ ወ/ሮ የክቴ ፈጠነ መክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት እንዳሉት የዳንግላ ወረዳ የዳንግሌ በግን ጨምሮ በርካታ የእንስሳት ተዋጽኦ ውጤቶችና የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች መገኛ ናት ብለዋል።
ታህሳስ 27/2018

Address

Kebele
Bahir Dar
11

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Anrs Trade and Market Development Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Anrs Trade and Market Development Bureau:

Share