29/05/2026
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ የ2018 በጀት አመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀምን ገመገመ፡፡
===========================================
ባህርዳር ግንቦት 19/2018 ዓ.ም (ኢቴቢ)፤ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ የቢሮው ምክትል ሃላፊ፣የማኔጅመንት አባላት እና አፈፃፀሙን ለመገምገም ከክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር የመጡ አመራሮች በተገኙበት የ2018 በጀት አመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀሙን ገምግሟል፡፡
በግምገማው የቢሮው የቴክኖሎጂ ስራወች ማለትም እንደ ስማርት ሲቲ ግንባታ፣ ስታርታፕ ስራወች፣ የቴክኖሎጂ ፈጠራ እና የተለሙ ሲስተሞች፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና እና የፋይዳ ሀገር አቀፍ ዲጂታል መታወቂያ አሰጣጥ እንዲሁም ሌሎች ስራወች ቀርበው ተገምግመዋል፡፡
የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ የቻለ ይግዛው እንደተናገሩት በ25 አመታት የአማራ ክልል ስራቴጂክ እቅድ ላይ ለቴክኖሎጂ ስራወች ልዩ ትኩረት መሰጠቱ የክልሉ መንግስት በሁሉም ልማቶች ላይ የሚያካሂደውን ስራ የተሳለጠና ውጤታማ እንዲሆን ቁርጠኝነቱን የሚሳይ ነው ብለዋል፡፡
የሌሎች ተቋማት በተዋቀሩበት ልክ ተቋሙ ወደ ታች ያልተዋቀረና ባልተሟላ የሰው ሀይል በመስራት አስደሳች ውጤት እየተገኘ ያለ መሆኑን አቶ የቻለ በማስረዳት በዚህ ተግባር ከዚህ በፊት ትኩረት ያልነበራቸው የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ትኩረት እያገኙ እና ክልሉ ወደ ዲጅታላይዜሽን አሰራር ሙሉ በሙሉ የሚገባበት ሁኔታ እየተፋጠነ ነው ብለዋል፡፡
ከክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር የመጡ አመራሮች አቶ ነጋ ይስማው እና አቶ አባይነው በበኩላቸው የቢሮው እቅድ አፈፃፀም በጥሩ ደረጃ የሚገኝ መሆኑን በማስረዳት ቀሪ ስራወችን ለመፈፀም በጥንካሬ መስራት ይገባል በማለት ግምገማው ተጠናቋል፡፡