Amhara Rural Roads Construction Agencyአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ

  • Home
  • Ethiopia
  • Bahir Dar
  • Amhara Rural Roads Construction Agencyአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ

Amhara Rural Roads Construction Agencyአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ It is a non-profitable organization found in Amhara region working on road infrastructure developmen

የአማራ ገጠር መንገዶች ባለስልጣን ከየት ወደየት


የፌዴራል መንግስት የክልል መንግስታት መፈጠርን ተከትሎ ሁሉም የገጠር መንገድ ግንባታዎች፣ ጥገናዎችና በጀታቸው ከመጋቢት ወር 1985 ዓ.ም ጀምሮ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ወደ ክልል መንግስታት እንዲዛወሩ አደረገ፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ኘሮጀክቶችን፣ የሰው ኃይላቸውን፣ መሳሪያና ሌሎች ቁሳቁሶችን ለየክልል ስራና ከተማ ልማት ቢሮዎች አስረከበ፡፡ የአማራ ክልል ስራና ከተማ ልማት ቢሮም በክልሉ የሚገኙ የገጠር መንገዶችን ተረክቦ የገጠር መንገዶች መምሪያ አቋቋመ፡፡የፌዴራል መንግስት የክልል መንግስታት መፈጠርን ተከትሎ ሁሉም የገጠር መንገድ ግንባታዎች፣ ጥ

ገናዎችና በጀታቸው ከመጋቢት ወር 1985 ዓ.ም ጀምሮ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ወደ ክልል መንግስታት እንዲዛወሩ አደረገ፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ኘሮጀክቶችን፣ የሰው ኃይላቸውን፣ መሳሪያና ሌሎች ቁሳቁሶችን ለየክልል ስራና ከተማ ልማት ቢሮዎች አስረከበ፡፡ የአማራ ክልል ስራና ከተማ ልማት ቢሮም በክልሉ የሚገኙ የገጠር መንገዶችን ተረክቦ የገጠር መንገዶች መምሪያ አቋቋመ፡፡


የገጠር መንገዶች መስፋፋት ለክልሉ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት መፋጠን ወሳኝ በመሆኑ ላይ የበለጠ ግንዛቤ ስለተፈጠረና በቦርድ የሚተዳደር፣ የተጠናከረ፣ ቀልጣፋ ቢሮክራሲ የሚጠቀም የገጠር መንገዶች ተቋም ማደራጀት በማስፈለጉ የገጠር መንገዶች መምሪያ የሚለው ከስራና ከተማ ልማት ተገንጥሎ ጥቅምት 1987 ዓ.ም ራሱን ችሎ መጀመሪያ በድርጅት ቀጥሎ በባለስልጣን ደረጃ ተቋቋመ፡፡የገጠር መንገዶች መስፋፋት ለክልሉ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት መፋጠን ወሳኝ በመሆኑ ላይ የበለጠ ግንዛቤ ስለተፈጠረና በቦርድ የሚተዳደር፣ የተጠናከረ፣ ቀልጣፋ ቢሮክራሲ የሚጠቀም የገጠር መንገዶች ተቋም ማደራጀት በማስፈለጉ የገጠር መንገዶች መምሪያ የሚለው ከስራና ከተማ ልማት ተገንጥሎ ጥቅምት 1987 ዓ.ም ራሱን ችሎ መጀመሪያ በድርጅት ቀጥሎ በባለስልጣን ደረጃ ተቋቋመ፡፡


የአማራ ገጠር መንገዶች ባለስልጣን ከተቋቋመ ጊዜ ጀመሮ እስከ 2002 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ 2756 ኪ.ሜ የአዲስ መንገድ ግንባታ ስራ ያከናወነ ሲሆን በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን፣ በህብረተሰቡና በሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች አማካኝነት 4861.9 ኪ.ሜ የአዲስ መንገድ ግንባታ ስራ ተከናውኗል፡፡ ይህም የክልሉን የመንገድ ኔትወርክ በ1986 ዓ.ም ከነበረበት 3918.6 ኪ.ሜ በ2002 ዓ.ም መጨረሻ ወደ 7617.9 ኪ.ሜ አሳድጐታል፡፡ በመሆኑም በ1987 ዓ.ም በ1000 ኪ.ሜ ስኩዬር 20 ኪ.ሜ የነበረውን የክልሉ የመንገድ ሽፋን በ2002 ዓ.ም መጨረሻ 48 ኪ.ሜ በማድረስ የመንገድ ሽፋኑን ከእጥፍ በላይ ማሳደግ ተችሏል፡፡ በመልሶ ግንባታና ተከታታይ ጥገና የበርካታ ነባር መንገዶች የጥራት ደረጃም እንዲሻሻል ተደርጓል፡፡የአማራ ገጠር መንገዶች ባለስልጣን ከተቋቋመ ጊዜ ጀመሮ እስከ 2002 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ 2756 ኪ.ሜ የአዲስ መንገድ ግንባታ ስራ ያከናወነ ሲሆን በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን፣ በህብረተሰቡና በሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች አማካኝነት 4861.9 ኪ.ሜ የአዲስ መንገድ ግንባታ ስራ ተከናውኗል፡፡ ይህም የክልሉን የመንገድ ኔትወርክ በ1986 ዓ.ም ከነበረበት 3918.6 ኪ.ሜ በ2002 ዓ.ም መጨረሻ ወደ 7617.9 ኪ.ሜ አሳድጐታል፡፡ በመሆኑም በ1987 ዓ.ም በ1000 ኪ.ሜ ስኩዬር 20 ኪ.ሜ የነበረውን የክልሉ የመንገድ ሽፋን በ2002 ዓ.ም መጨረሻ 48 ኪ.ሜ በማድረስ የመንገድ ሽፋኑን ከእጥፍ በላይ ማሳደግ ተችሏል፡፡ በመልሶ ግንባታና ተከታታይ ጥገና የበርካታ ነባር መንገዶች የጥራት ደረጃም እንዲሻሻል ተደርጓል፡፡


በክልሉ ከሚገኘው 7617.9 ኪ.ሜ ጠቅላላ የመንገድ ኔትወርክ 3665.6 ኪ.ሜ የሚሆነው በባለስልጣኑ ስር የሚተዳደር ሲሆን 3952.3 ኪ.ሜ የሚሆነው ደግሞ በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የሚተዳደር ነው፡፡በክልሉ ከሚገኘው 7617.9 ኪ.ሜ ጠቅላላ የመንገድ ኔትወርክ 3665.6 ኪ.ሜ የሚሆነው በባለስልጣኑ ስር የሚተዳደር ሲሆን 3952.3 ኪ.ሜ የሚሆነው ደግሞ በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የሚተዳደር ነው፡፡


የነባር መንገዶች ጥገና ስራ በተመለከተ መንገዶች በየጊዜው ካልተጠኑ አገልግሎት እስከ ማቆም ሊደርሱ ስለሚችሉ ጥገና ያስፈልጋቸዋል፡፡ በመሆኑም ባለስልጣኑ ቀላልና ተከታታይ ጥገና፣ ወቅታዊ ጥገናና ድንገተኛ ጥገና ስራ በባለስልጣኑ ስር ባሉ የጎንደር፣ጐጃም፣ወሎና ደብረብርሃን የገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤቶች አማካኝነት እየተከናወነ ይገኛል፡፡ በክልሉ እስከ 1991 ዓ.ም ድረስ ከፍተኛ የሆነ የመንገድ መሰረተ-ልማት አለመስፋፋት ችግርና የበጀት እጥረትም ስለነበር በአብዛኛው ትኩረት ይሰጥ የነበረው ለአዲስ መንገዶች ግንባታ ስራ በመሆኑ ለነባር መንገዶች ጥገና ብዙም ትኩረት አይሰጥም ነበር፡፡ ከ1991 ዓ.ም ወዲህ ግን በክልሉ የመንገድ መሰረተ ልማትን በማስፋፋት ከዋና መንገድ ጋር ያልተገናኙ በርካታ ወረዳዎች እንደዲገናኙ በመደረጉና በፌዴራል ደረጃ የመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት ተቋቁሞ ለጥገና ስራ የበጀት ምንጭ እየሆነ በመምጣቱ ከግንባታው ጐን ለጐን የነባር መንገዶች ጥገና ስራም ትኩረት ተሰጥቶት በስፋት እየተሰራ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ከ1992-2002 ዓ.ም መጨረሻ ባሉት ዓመታት በመደበኛና ወቅታዊ የጥገና ዓይነቶች 16665 ኪ.ሜ የነባር ገጠር መንገዶች ጥገና ስራ ተከናውኗል፡፡ በባለስልጣኑ አስተዳደር ስር ያሉ ነባር የገጠር መንገዶች የጥገና ሽፋን ለማሳደግ በተደረገው ጥረት በ1992 ዓ.ም 16.5% የነበረውን የነባር መንገዶች ጥገና ሽፋን በ2002 ዓ.ም መጨረሻ 88.3% ማድረስ ተችሏል፡፡የነባር መንገዶች ጥገና ስራ በተመለከተ መንገዶች በየጊዜው ካልተጠኑ አገልግሎት እስከ ማቆም ሊደርሱ ስለሚችሉ ጥገና ያስፈልጋቸዋል፡፡ በመሆኑም ባለስልጣኑ ቀላልና ተከታታይ ጥገና፣ ወቅታዊ ጥገናና ድንገተኛ ጥገና ስራ በባለስልጣኑ ስር ባሉ የጎንደር፣ጐጃም፣ወሎና ደብረብርሃን የገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤቶች አማካኝነት እየተከናወነ ይገኛል፡፡ በክልሉ እስከ 1991 ዓ.ም ድረስ ከፍተኛ የሆነ የመንገድ መሰረተ-ልማት አለመስፋፋት ችግርና የበጀት እጥረትም ስለነበር በአብዛኛው ትኩረት ይሰጥ የነበረው ለአዲስ መንገዶች ግንባታ ስራ በመሆኑ ለነባር መንገዶች ጥገና ብዙም ትኩረት አይሰጥም ነበር፡፡ ከ1991 ዓ.ም ወዲህ ግን በክልሉ የመንገድ መሰረተ ልማትን በማስፋፋት ከዋና መንገድ ጋር ያልተገናኙ በርካታ ወረዳዎች እንደዲገናኙ በመደረጉና በፌዴራል ደረጃ የመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት ተቋቁሞ ለጥገና ስራ የበጀት ምንጭ እየሆነ በመምጣቱ ከግንባታው ጐን ለጐን የነባር መንገዶች ጥገና ስራም ትኩረት ተሰጥቶት በስፋት እየተሰራ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ከ1992-2002 ዓ.ም መጨረሻ ባሉት ዓመታት በመደበኛና ወቅታዊ የጥገና ዓይነቶች 16665 ኪ.ሜ የነባር ገጠር መንገዶች ጥገና ስራ ተከናውኗል፡፡ በባለስልጣኑ አስተዳደር ስር ያሉ ነባር የገጠር መንገዶች የጥገና ሽፋን ለማሳደግ በተደረገው ጥረት በ1992 ዓ.ም 16.5% የነበረውን የነባር መንገዶች ጥገና ሽፋን በ2002 ዓ.ም መጨረሻ 88.3% ማድረስ ተችሏል፡፡


ባለስልጣኑ በክልሉ የመንገድ መሰረተ ልማትን በማስፋፋት ለህብረተሰቡ የበለጠ ተደራሽ ለመሆን ያስችለው ዘንድ የመፈፀምና የማስፈፀም አቅሙን ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲያጐለብት የክልሉ መንግስት በተለይም በአለት አምስት አመታት የባለስልጣኑ አቅም በሰው ኃይል፣ በግንባታ መሳሪያ፣ በፋይናንስ፣ በአሰራርና በአደረጃጀት እንዲጠናከር ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ድጋፍ በማድረጉ ባለስልጣኑ በአምስት አመቱ የመንገድ ዘርፍ ልማት በመርሃ ግብር ከ100% በላይ አፈፃፀም በማስመዝገብ ስኬታማ በሆነ መልኩ አጠናቋል፡፡ባለስልጣኑ በክልሉ የመንገድ መሰረተ ልማትን በማስፋፋት ለህብረተሰቡ የበለጠ ተደራሽ ለመሆን ያስችለው ዘንድ የመፈፀምና የማስፈፀም አቅሙን ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲያጐለብት የክልሉ መንግስት በተለይም በአለት አምስት አመታት የባለስልጣኑ አቅም በሰው ኃይል፣ በግንባታ መሳሪያ፣ በፋይናንስ፣ በአሰራርና በአደረጃጀት እንዲጠናከር ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ድጋፍ በማድረጉ ባለስልጣኑ በአምስት አመቱ የመንገድ ዘርፍ ልማት በመርሃ ግብር ከ100% በላይ አፈፃፀም በማስመዝገብ ስኬታማ በሆነ መልኩ አጠናቋል፡፡


ባለስልጣኑ እስከ 1997 ዓ.ም ከ7 በማይበልጡ ኘሮጀክቶች የግንባታ ስራ ያከናውን የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአንድ ጊዜ 21 የራስ ኃይል የግንባታ ኘሮጀክትን ከፍቶ የግንባታ ስራ መስራትና 21 ኘሮጀክቶችን በአግባቡ መምራት በሚችልበት ደረጃ ላይ አቅሙን አሳድጓል፡፡ በመሆኑም በቀጣይ 5 ዓመታት ተግባራዊ ለማድረግ የተዘጋጀውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለማሳካት ከሚኖረው ቁልፍ ሚና አንፃር የገጠር መንገድ መሰረተ ልማትን ማስፋፋት ወሳኝ ቅደመ ሁኔታ ነው፡፡ ባለስልጣኑ ይህንን ተልዕኮ ባገናዘበ መልኩ የአምስት አመት የመንገድ ዘርፍ ልማት ዕቅድ ያዘጋጀ ሲሆን ከፍተኛ የገጠር መንገዶች ግንባታ በማከናወን በ5 ዓመቱ መጨረሻ የክልሉን የመንገድ ኔትወርክ አሁን ካለበት 7617.9 ኪ.ሜ ወደ 11617 ኪ.ሜ በማሳደግ የመንገድ ሽፋኑን አሁን ካለበት በ1000 ካሬ .ኪ.ሜ 48 ኪ.ሜትር ወደ 74 ኪ.ሜትር ለማድረስ ዕቅድ ተይዟል፡፡ በ5 ዓመቱ መጨረሻ የነባር ገጠርመንገዶች ጥገና ሽፋንም አሁን ከአለበት 88.3% ወደ 95% የሚደርስ ይሆናል፡፡ባለስልጣኑ እስከ 1997 ዓ.ም ከ7 በማይበልጡ ኘሮጀክቶች የግንባታ ስራ ያከናውን የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአንድ ጊዜ 21 የራስ ኃይል የግንባታ ኘሮጀክትን ከፍቶ የግንባታ ስራ መስራትና 21 ኘሮጀክቶችን በአግባቡ መምራት በሚችልበት ደረጃ ላይ አቅሙን አሳድጓል፡፡ በመሆኑም በቀጣይ 5 ዓመታት ተግባራዊ ለማድረግ የተዘጋጀውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለማሳካት ከሚኖረው ቁልፍ ሚና አንፃር የገጠር መንገድ መሰረተ ልማትን ማስፋፋት ወሳኝ ቅደመ ሁኔታ ነው፡፡ ባለስልጣኑ ይህንን ተልዕኮ ባገናዘበ መልኩ የአምስት አመት የመንገድ ዘርፍ ልማት ዕቅድ ያዘጋጀ ሲሆን ከፍተኛ የገጠር መንገዶች ግንባታ በማከናወን በ5 ዓመቱ መጨረሻ የክልሉን የመንገድ ኔትወርክ አሁን ካለበት 7617.9 ኪ.ሜ ወደ 11617 ኪ.ሜ በማሳደግ የመንገድ ሽፋኑን አሁን ካለበት በ1000 ካሬ .ኪ.ሜ 48 ኪ.ሜትር ወደ 74 ኪ.ሜትር ለማድረስ ዕቅድ ተይዟል፡፡ በ5 ዓመቱ መጨረሻ የነባር ገጠርመንገዶች ጥገና ሽፋንም አሁን ከአለበት 88.3% ወደ 95% የሚደርስ ይሆናል፡፡


በሌላ መልኩ ሁሉን አቀፍ የገጠር መንገድ ተደራሽነት ኘሮግራም (universal Rural Road Access Program) አማካኝነት በሁሉም የገጠር ቀበሌዎች ክረምት ከበጋ የሚያስኬድ መንገድ በመገንባት የቀበሌ ማዕከላቱን ከዋናና አገናኝ መንገዶች ጋር ለማገናኘት በተሰበሰበ መረጃ ከ3113 የገጠር ቀበሌዎች መካከል 918 ቀበሌዎች ከዋናና አገናኝ መንገዶች ጋር የተገናኙ ሲሆን ቀሪ 2195 ቀበሌዎችን ለማገናኘት በአምስት አመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ 18000 ኪ.ሜትር የቀበሌ መንገዶች ግንባታ ለማከናወን ዕቅድ ተይዟል፡፡ በአምስት አመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በመደበኛና ወቅታዊ የጥገና አይነቶች 34640 ኪ.ሜትር የቀበሌ መንገዶች ጥገና ለመስራትም ታቅዷል፡፡በሌላ መልኩ ሁሉን አቀፍ የገጠር መንገድ ተደራሽነት ኘሮግራም (universal Rural Road Access Program) አማካኝነት በሁሉም የገጠር ቀበሌዎች ክረምት ከበጋ የሚያስኬድ መንገድ በመገንባት የቀበሌ ማዕከላቱን ከዋናና አገናኝ መንገዶች ጋር ለማገናኘት በተሰበሰበ መረጃ ከ3113 የገጠር ቀበሌዎች መካከል 918 ቀበሌዎች ከዋናና አገናኝ መንገዶች ጋር የተገናኙ ሲሆን ቀሪ 2195 ቀበሌዎችን ለማገናኘት በአምስት አመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ 18000 ኪ.ሜትር የቀበሌ መንገዶች ግንባታ ለማከናወን ዕቅድ ተይዟል፡፡ በአምስት አመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በመደበኛና ወቅታዊ የጥገና አይነቶች 34640 ኪ.ሜትር የቀበሌ መንገዶች ጥገና ለመስራትም ታቅዷል፡፡


የባለስልጣኑን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም የበለጠ በማጠናከርና የተፈጠረውን አቅም አሟጦ በመጠቀም እንዲሁም የክልሉን ህብረተሰብ ከመቸውም ጊዜ በላቀ ደረጃ በመንገድ ልማት ስራው የሚሳተፍበትን ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የአምስት አመቱን ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት ይደረጋል፡፡የባለስልጣኑን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም የበለጠ በማጠናከርና የተፈጠረውን አቅም አሟጦ በመጠቀም እንዲሁም የክልሉን ህብረተሰብ ከመቸውም ጊዜ በላቀ ደረጃ በመንገድ ልማት ስራው የሚሳተፍበትን ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የአምስት አመቱን ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት ይደረጋል፡፡

የልማት ደም ሥር እና የአህጉራዊ ውህደት ማሳያ የኢትዮጵያ የመንገድ መሠረተ ልማት እመርታ፣ አገራዊ ተስፋ እና የቀጣናው የኢኮኖሚ ትስስር ምዕራፍ*****************************...
28/08/2026

የልማት ደም ሥር እና የአህጉራዊ ውህደት ማሳያ የኢትዮጵያ የመንገድ መሠረተ ልማት እመርታ፣ አገራዊ ተስፋ እና የቀጣናው የኢኮኖሚ ትስስር ምዕራፍ
*****************************

የአንድ ሀገር ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ፣ የማህበራዊ ትስስር ጥንካሬ እና የዘመናዊነት ደረጃ የሚለካው በመሬት ላይ በሚዘረጉ ጠንካራና ዘላቂ የመሠረተ ልማት አውታሮች ጭምር ነው።

የመንገድ መረብ ለሀገር ኢኮኖሚ እንደ ደም ሥር በመቆጠሩ ያለ መንገድ የተቀናጀ እድገትንም ሆነ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል አይታሰብም።

የዓለም ባንክ መረጃ እንደሚያመላክተው በታዳጊ ሀገራት የገጠር መንገድ ሽፋን በ10 በመቶ ባደገ ቁጥር የገጠር ድህነት በ0.6 በመቶ የመቀነስ እና የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ እድል ደግሞ በ20 በመቶ የማደግ አቅም አለው።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዘላቂ ልማት ግቦች (SDGs) ማዕቀፍ መሠረትም የተቀናጀ የመንገድ መረብ መዘርጋት የእናቶችና የሕፃናት ሞትን በ35 በመቶ የመቀነስ እና የትምህርት ተደራሽነትን በ25 በመቶ የማሳደግ ታላቅ አቅም እንዳለው በጥናት ተረጋግጧል።

ይህንን ዓለም አቀፋዊ እውነት መሠረት በማድረግ ኢትዮጵያ በመንገድ ዘርፍ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የጻፈች ሲሆን፣ በ2010 ዓ.ም የነበረውን የ126 ሺህ 773 ኪሎሜትር የመንገድ መረብ፣ ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ ብቻ ከ53 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ አዳዲስ መንገዶችን በማንጠፍ በ2018 ዓ.ም አጋማሽ ወደ 180 ሺህ 232 ኪሎ ሜትር ማሳደግ ችላለች።

ይህ አገራዊ እመርታ የትራንስፖርት አውታሩን ወደ 245 ሺህ ኪሎ ሜትር ለማድረስ ለተያዘው ታላቅ አገራዊ ግብ ጠንካራ መነሻ የሆነ ሲሆን፣ ለዚህ ስኬት የመንግሥት የበጀት ትኩረት ከ2010 ዓ.ም ከነበረበት ከ30 ቢሊየን ብር በታች ተነስቶ በ2019 ዓ.ም ወደ 121 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በማደግ ከአራት እጥፍ በላይ ጭማሪ በማሳየት የካፒታል በጀት የ21 ነጥብ 4 በመቶ ድርሻ እንዲይዝ አድርጎታል።

ይህ የመንገድ መሠረተ ልማት እመርታ የኮንክሪትና የአስፋልት ዝርጋታ ብቻ ሳይሆን ዘመናዊ ሀገር የመፍጠር፣ የቴክኖሎጂ ተደራሽነትን የመጨመር እና ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍልን የማረጋገጥ ትልቅ አገራዊ ምሰሶ ነው።

ይህ አገራዊ ስኬት አህጉራዊ አድማስን ያቀፈ ሲሆን፣ በአፍሪካ ያለውን የትራንስፖርትና የሎጂስቲክስ ወጪ በመቀነስ የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና (AfCFTA) ስምምነትን በውጤታማነት ለማስፈጸም ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

እንደ ላሙ ፖርት-ደቡብ ሱዳን-ኢትዮጵያ ያሉ የኮሪደር ልማቶች እና የጋራ ድንበር መቆጣጠሪያዎች በመሬት የተከበቡ ሀገራት የባሕር በር እንዲያገኙ እና እንደ IGAD፣ COMESA እና EAC ያሉ ቀጠናዊ ማህበረሰቦች በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፍ እንዲቀራረቡ በማድረግ የኢትዮጵያን አህጉራዊ መሪነትና አዲሱን የልማት ከፍታ በተግባር አረጋግጧል።

Ethiopian Broadcasting Corporation

27/08/2026
የአገር ኢኮኖሚ ነቀርሳ የሆነውን ሙስና ከመሠረቱ ለማስወገድ በጋራ ልንቆም ይገባል፡፡አንድ አገር ጠንካራ ሠራተኛ ህዝብ ካለው፣ ለም መሬትና ምቹ የተፈጥሮ ፀጋ ባለቤት ከሆነና አገራዊ ልማትን ...
26/08/2026

የአገር ኢኮኖሚ ነቀርሳ የሆነውን ሙስና ከመሠረቱ ለማስወገድ በጋራ ልንቆም ይገባል፡፡

አንድ አገር ጠንካራ ሠራተኛ ህዝብ ካለው፣ ለም መሬትና ምቹ የተፈጥሮ ፀጋ ባለቤት ከሆነና አገራዊ ልማትን እውን ለማድረግ የሚጥር ቁርጠኛ መንግስትና ምቹና የሚያሰራ ፖሊስ ከዘረጋች ለማደግ ያላት ተስፋ ከፍተኛ ነው፡፡

እነኚህ ቅድመ ሁኔታዎች ተሟልተው በአጭር ጊዜ ውስጥ ድህነትን በመቅረፍ ወደ አደገ ደረጃ የተሻገሩ አገራት እንዳሉ ይታመናል፡፡ ይህን ልማታዊ ስኬት የተጎናፀፉ አገራት ቀጣይነት ያለው እድገትን ሊያስመዘግቡ የሚችሉት በስነ ምግባሩ የታነፀ፣ ለአገሩ ዕድገት ቀናዒ የሆነ ዜጋና አስተዳደር ሊኖረው ይገባል፡፡

በሌላ በኩል ምቹ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አቅም ሊኖራቸው ያልቻሉ ነገር ግን የአገርን አንጡራ ሀብት በቁጠባና ለታለመለት ዓላማ እንዲውል የሚያደርግ የሚችሉ ታማኝና አገር ወዳድ ዜጎች ያላት አገር ግን ምንም እንኳ አገራዊ እድገቷ ውስንና አዝጋሚ ቢሆንም በየጊዜው ለውጥና እድገት ማምጣቷ አይቀሬ ነው፡፡

በዚህ ረገድ አገራችን ፈጣሪ ሁሉንም ነገር አሟልቶ የሰጣት በሩቅም በቅርብም የሚያውቋት የሚመኟት፣ የሚያጓጓ የተፈጥሮ ሀብት ያላት የአፍሪካ የውሃ ማማ የምትባል ጠንካራና ሰርቶ የማያደክም ሠራተኛ ህዝብ ያላት ስትሆን ካለፉት ስምንት ዓመታት ወዲህ ደግሞ ይህን አገራዊ እምቅ ሀብት አቅም እንደሆነ የተረዳና ይህንን አቅም ወደ ብልጽግና ለመቀየር በቁርጠኝነት የሚሰራ መንግስትና መሪ ያላት አገር ነቺ፡፡ ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት ይህ ሁኔታ አገራችን ለመበልጸግ ምቹ ሁኔታዎች ናቸው፡፡

ይሁንና ከለውጡ በፊት በነበረው አገዛዝ ተፀንሶ አሁን በከፍተኛም ሆነ በዝቅተኛ ደረጃ የሙስና አደጋዎች የተገራጡባት አገር መሆኗ ወደ ብልጽግ ለምናደርገው ጉዞ ትልቅ እንቅፋት ነው፡፡ ሙስና በባህርይው የመንግስትን ስልጣን መያዝ የሚጠይቅ ነው፡፡

በስልጣን ላይ ያለው ግለሰብም ሆነ ቡድን ለአገር ልማት ቀናዔ ካልሆነና እያንዳንዱን አጋጣሚ ለግል ጥቅም መጠቀም የሚሻ ከሆነ በአገራችን የተፈጠረው የላቀ ልማትና ብልጽግና እድል ለከፍተኛ አደጋ መጋለጡ አይቀርም፡፡

በተለይም አገራችን የጀመረችውን የብልጽግና ጎዳና በአጭር ጊዜ ለማሳካት በቢሊዮን ዶላሮች በጀት በመመደብ በከፍተኛ ጥረት እያደረገችበት ባለችበት ወቅት ይህንን አጋጣሚ ለዝረፍያ መጠቀም የሚፈልጉ አያሌ ሰዎች እንዳሉ እሙን ነው፡፡

መንግስት ለመሰረት ልማት ዝርጋታ፤ ለማኑፋክቸሪንግና ለከተማ ልማት የሰጠውን ልዩ ትኩረት በውል የተረዱ እነኚህ መዥገሮች አጋጣሚውን ለዝረፍያና ለምዝበራ እየተጠቀሙ ያሉበት ሁኔታ ካልተገታና በማህበረሰቡ ዘንድ መልካም አስተዳደር ማስፈን ካልተቻለ አገራችን የቱንም ያህል የሚያሰራ ፖሊስ፣ ፕራግማቲክ የሆነ ሊደርሽፕና ከፍተኛ የሆነ የተፈጥሮ ሀብት ቢኖራትም የምንሻውን ልማትና ብልጽግና እውን ለማድረግ ይቅርና በጊዚያዊነት እየፈተንን ያለውን የኑሮ ውድነት እንኳ ለመግታት የምንቸገር ይሆናል፡፡

በመሆኑም ሙስና የሚፈጥረው አደጋ በውል የተረዳና ችግሩን በስር ነቀል መልኩ ለመግታት የተነሳው የብልጽግና መንግስት የጀመረውን የፀረ- ሙስና ትግልና የህግ ማስከበሩ ተግባር በውጤት እንዲደመደም ሁሉም ዜጋ ከመንግሰት ጎን በመቆምና አምርሮ በመታገል ይህንን የአገር የልማት ነቀርሳ ለማስወገድ ከመቼውም ጊዜ በላይ በቀርጠኝነት ሊነሳ ይገባዋል፡፡

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዩች እንኳን ለ1ሺህ 501ኛ የመውሊድ በአል እንኳን አደረሳችሁ ። በአሉ ለመላ ለሀገራችን  እምነት ተከታዩች ሁሉ በአሉ የሰላም የፍቅር የአንድነትና የመተሳሰብ...
24/08/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዩች እንኳን ለ1ሺህ 501ኛ የመውሊድ በአል እንኳን አደረሳችሁ ።

በአሉ ለመላ ለሀገራችን እምነት ተከታዩች ሁሉ በአሉ የሰላም የፍቅር የአንድነትና የመተሳሰብ ይሁንላችሁ ።

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ

የኢትዮጵያ የመንገድ መሠረተ ልማት እመርታና የመፃኢ እድገት አቅጣጫአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአንድ ሀገር የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የማህበራዊ ትስስር እና የለውጥ ደረጃ ከ...
22/08/2026

የኢትዮጵያ የመንገድ መሠረተ ልማት እመርታና የመፃኢ እድገት አቅጣጫ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአንድ ሀገር የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የማህበራዊ ትስስር እና የለውጥ ደረጃ ከሚለካባቸው ዋነኛ መስፈርቶች አንዱ የመንገድ መሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ ስርጭትና ጥራት ነው።

መንገድ የሀገር የደም ስር ነው ሲባል ማጋነን አይደለም፤ ያለ መንገድ ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚ፣ ልማትና ዕድገት ሊታሰብ አይችልም።

የመንገድ መሠረተ ልማት በጥራትና በብዛት መኖር የዜጎችን እንቀስቃሴ ከማቀላጠፉ ባሻገር፣ ምርቶችና ጥሬ ዕቃዎች በፍጥነት ወደ ማምረቻዎችና ገበያዎች እንዲደርሱ በማድረግ ረገድ ቁልፍ ሚና ይጫወታል።

ኢትዮጵያ ላለፉት አስርት ዓመታት፣ በተለይም ባለፉት ስምንት ዓመታት፣ ለመንገድ መሠረተ ልማት ልዩ ትኩረት በመስጠት ክልሎችን እርስ በርስ፣ ዋና ከተማውን ከክልሎች እንዲሁም ዞኖችን ከዞኖች የሚያስተሳስሩ መጠነ ሰፊ ሥራዎችን ስታከናውን ቆይታለች።

በ2010 ዓ.ም የነበረው የ126 ሺህ 773 ኪሎ ሜትር አጠቃላይ የመንገድ ሽፋን በ2018 ዓ.ም አጋማሽ ወደ 180 ሺህ 232 ኪሎ ሜትር አድጓል። ይህም ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ ብቻ ከ53 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ አዳዲስ መንገዶች መገንባታቸውን ያሳያል።

በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ደግሞ ይህንን አኃዝ ወደ 245 ሺህ ኪሎ ሜትር ለማድረስ በዕቅድ እየተሰራ ይገኛል።

በ2010 ዓ.ም ከ30 ቢሊየን ብር በታች የነበረው የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በጀት በ2019 ዓ.ም ወደ 121 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በማደግ ከአራት እጥፍ በላይ ጭማሪ አሳይቷል።

ተቋሙ በየዓመቱ ከሀገሪቱ አጠቃላይ የካፒታል በጀት 21 ነጥብ 4 በመቶ ድርሻ በመውሰድ ቀዳሚው የመሠረተ ልማት ተጠቃሚ ለመሆን ችሏል።

የ75 ዓመት ዕድሜ ባለጸጋው የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር፣ ሀገራዊ የንግድ ኮሪደሮችን የሚያጠናክር ጠንካራ የፌዴራል የመንገድ መረብ በመዘርጋት ላይ ይገኛል። ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ ብቻ 182 ፕሮጀክቶች ወደ ግንባታ የገቡ ሲሆን፣ 71 ግዙፍ ፕሮጀክቶች ግንባታቸው ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሆነዋል።

የሀገሪቱን የንግድና የኢንዱስትሪ ማዕከላት የሚያገናኙ እንደ አዲስ አበባ-አዳማ፣ ሞጆ-መቂ-ባቱ-አርሲ ነገሌ እና ድሬዳዋ-ደዋሌ ያሉ የፍጥነት መንገዶች ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ።

ከለውጡ በፊት የነበረው የፍጥነት መንገድ ሽፋን 84 ነጥብ 7 ኪ.ሜ ብቻ የነበረ ሲሆን÷ በአሁኑ ወቅት ተጨማሪ የፍጥነት መንገዶች ተጠናቅቀው ለአገልግሎት በቅተዋል።

በቀጣይም ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ፣ ጅማ፣ ደብረ ማርቆስ እና ነቀምቴ የሚዘልቁ አራት አዳዲስ የፍጥነት መንገዶችን ለመገንባት የአዋጭነት ጥናት ተጠናቅቋል።

በሚቀጥሉት 10 ዓመታት የሀገሪቱን የፍጥነት መንገዶች ርዝመት ወደ 1 ሺህ 600 ኪሎ ሜትር ለማድረስ ታቅዷል።

ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያን ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚያገናኙ እና ቀጣናዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ ግዙፍ የመንገድ ፕሮጀክቶች ተገንብተው ለኢኮኖሚው ከፍተኛ አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው።

አዳዲስ መንገዶችን ከመገንባት ባሻገር የነበሩትን ደረጃ ማሻሻል፣ መጠገን እና የዕድሜ ዘመናቸውን ማራዘም የመንገድ አስተዳደሩ ዋነኛ ትኩረት ነው።

በተለይም የከባድ ተሽከርካሪዎችን የጭነት መጠን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የሚዛን ጣቢያዎች ተስፋፍተዋል፤ ያሉትም ዲጂታላይዝ ተደርገዋል።

ይህ አሰራር የተሽከርካሪዎችን ክብደት ከሰው እጅ ንክኪ ነፃ በሆነ መንገድ በመመዝገብ፣ የአሰራር ግልጽነትን ለማስፈንና በከባድ ጭነት ምክንያት የሚደርስ የመንገድ ብልሽትን በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።

በጥቅሉ፣ የገጠርና የከተማ ትስስርን በማጠናከር፣ የኢኮኖሚ ኮሪደሮችን በማሳደግና ሀገር አቀፍ ልማትን በማፋጠን ረገድ የመንገድ መሠረተ ልማት ዝርጋታው ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የዕድገትና የብልጽግና ምዕራፍ እየመራት ይገኛል።

Fana Broadcasting Corporate S.C.)

የመንገድ መሠረተ ልማት ግንባታችን ወጪ ቆጣቢ፣ ጥራት ያለውና ረጅም ግልጋሎት እንዲሰጥ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ የመንገድ ልማት ሥራ በኪሎ ሜትር ብዛት ብቻ የሚለካ ሳይሆን በጥራቱ፣ በዘላቂነቱ...
20/08/2026

የመንገድ መሠረተ ልማት ግንባታችን ወጪ ቆጣቢ፣ ጥራት ያለውና ረጅም ግልጋሎት እንዲሰጥ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡

የመንገድ ልማት ሥራ በኪሎ ሜትር ብዛት ብቻ የሚለካ ሳይሆን በጥራቱ፣ በዘላቂነቱ እና ለህብረተሰቡ በሚያመጣው አገልግሎት የሚመዘን ነው።

ጥራት ያለው መንገድ የጉዞ ጊዜን ያሳጥራል፣ የተሸከርካሪና የመለዋወጫ ወጪን ይቀንሳል፣ የትራንስፖርት ደህንነትን ያረጋግጣል፣ እንዲሁም የአካባቢውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ያጠናክራል።

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ በክልሉ የሚገነቡና የሚጠገኑ መንገዶች እና ድልድዮች የተፈለገውን የጥራት ደረጃ እንዲያሟሉ በመድረግ እየሰራ ይገኛል።

በተለይም አስቸጋሪ የተራራማ መሬት አቀማመጥን በኢንጂነሪንግ ጥበብ በማሸነፍ የሚገነቡ መንገዶች የባለሙያዎችን ክህሎት፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና የልማት ቁርጠኝነት ያንጸባርቃሉ።

በክልሉ በተራራማና ፈታኝ የቶፖግራፊ ሁኔታዎች ውስጥ ሳይቀር ተራራዎችን በመቁረጥ፣ ገደሎችን በማለፍ እና የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ምቹና ደህንነቱ የተጠበቀ የመንገድ እየተገነባ ይገኛል።

በዚህም ኤጀንሲው የተፈጥሮ እንቅፋቶችን ወደ ልማት እድሎች በመቀየር ህብረተሰቡን ከገበያ፣ ከትምህርት፣ ከጤና እና ከሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች ጋር በማስተሳሰር ለክልሉ ዘላቂ እድገት መሰረት ለመጣል በከፍተኛ ትጋት በመስራት ላይ ነው።

ኤጀንሲው በየዓመቱ በስድስቱ የጥገና ጽ/ቤቶች በሚከናወኑ የመንገድና የድልድይ ፕሮጀክቶች ላይ የጥራት ቁጥጥርና ክትትል ስራዎችን በስፋት ያከናውናል።

በተጨማሪም በፕሮጀክቶች፣ በኳሪ ሳይቶች እና በግንባታ ግብዓቶች ላይ የጥራት ምርመራና ክትትል በማካሄድ የግንባታ ሥራዎች በተቀመጠው መስፈርት መሰረት እንዲከናወኑ ያደርጋል።

የመንገድ ሀብት አስተዳደርን ለማዘመን የተጠናቀቁ መንገዶችን እና ድልድዮችን በዲጂታል ስርዓት በመመዝገብ ወደ ዳታቤዝ ያስገባል። ይህም የመንገድ ሀብት መረጃዎችን በተደራጀ መልኩ ለማስተዳደርና ለውሳኔ አሰጣጥ ለመጠቀም አስፈላጊ መሰረት ይፈጥራል።

በተጨማሪም የመንገድና የድልድይ ፕሮጀክቶችን ዲጂታላይዝ በማድረግ የመንገድ መስመሮች መረጃ ማጥራት፣ የመንገድ ሁኔታ ጥናት፣ የድልድዮችና የሌሎች ስትራክቸሮች መረጃ መሰብሰብና ማደራጀት በዘመናዊ አሰራር ያከናውናል።

ኤጀንሲው ፕሮጀክቶችን በጥራት፣ በቅልጥፍና እና በተጠያቂነት በማስፈጸም የሚገነቡት መንዶችና ድልድዮች ለረጅም ዘመናት አገልግሎት እንዲሰጡ ከማድረግ አኳያ የግብዓትና የግንባታ ቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት ለክልሉ ዘላቂ ልማት መሰረት የሆነ የመንገድ መረብ ለመገንባት ቁርጠኛ ሆኖ እየሰራ መሆኑን ሲገልጽ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ነው።

ወጭ ቆጣቢ፣ ጥራትና ረጅም አገልግሎት የመንገድ ግንባታ ስራዎቻችን መለያዎች ናቸው፡፡

17/08/2026
የመንገዶች/ስትራክቸሮች ግንባታ አፈፃፀምየአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ በ2018 በጀት አመት ለሚያከናውነው የመንገድና ስትራክቸር ግንባታ ስራ ከክልሉ መንግስት ብር 1,370,0...
15/08/2026

የመንገዶች/ስትራክቸሮች ግንባታ አፈፃፀም
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ በ2018 በጀት አመት ለሚያከናውነው የመንገድና ስትራክቸር ግንባታ ስራ ከክልሉ መንግስት ብር 1,370,000,000 በጀት ተመድቦ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ በመሆኑም፡-

የመንገዶች ግንባታ አፈፃፀም
ኤጀንሲው በበጀት አመቱ ከ33 ፕሮጀክቶች መካከል በ13 የመንገድ ግንባታ እና 7 የመንገድና ስትራክቸር ግንባታ ፕሮጀክቶች አማካይነት 102.15 ኪ/ሜ መንገድ ለመገንባት አቅዶ 90.79 ኪ.ሜ መንገድ በመገንባት ከዓመቱ ዕቅድ 88.88% ፈፅሟል፡፡

የስትራክቸር ግንባታ አፈፃፀም
ኤጀንሲው በ2018 በጀት ዓመት ለስትራክቸር ግንባታ በተደራጁ 13 እና ለስትራክቸርና መንገድ ግንባታ በተደራጁ 7 ፕሮጀክቶች አማካይነት ተጀምረው ያደሩና በአዲስ የሚጀመሩ የተለያየ መጠን ያላቸው 227 (136 ፓይፕ ከልቨርቶች፣ 48 ስላብ ከልቨርቶች፣ 22 ስላብ ድልድዮች፣ 20 ቲ-ገርደር ድልድዮች፣ 1 ቦክስ ገርደር ድልድይ) የስትራክቸሮች ግንባታ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ የተገባ ሲሆን፣ በ203 የተለያዬ መጠን ባላቸው ስትራክቸሮች የግንባታ ሥራ አከናውኗል፡፡

በበጀት አመቱ የግንባታ ሥራ ከተከናወነባቸው 203 የተለያዬ መጠን ካላቸዉ ስትራክቸሮች መካከል ከ2 ሜትር እስከ 40 ሜትር ርዝመት ያላቸዉ የ53 አነስተኛ ፣ መካከለኛ እና ትላልቅ ድልድዮች ግንባታ እንዲሁም የ136 ቱቦዎች ቀበራ ሥራ ተጠናቋል፡፡ የ9 አነስተኛ፣ መካከለኛ እና ትላልቅ ድልድዮች ግንባታ አፈፃፀም ከ50 እስከ 99% (ፐርሰንት) የደረሰ ሲሆን የ5 አነስተኛ፣ መካከለኛ እና ትላልቅ ድልድዮች ግንባታ አፈፃፀም ደግሞ ከ50% (ፐርሰንት) በታች ሆኖ ይገኛል፡፡ ቀሪ 24 አነስተኛ እና መካከለኛ ድልድዮች ደግሞ በበጀት ዓመቱ በዕቅድ ተይዘው ግንባታቸው አልተጀመረም፡፡

በአጠቃላይ በ2018 በጀት ዓመት የተለያዬ መጠን ባላቸው ስትራክቸሮች ግንባታ ኤጀንሲው በአማካይ 84.77% አፈፃፀም አስመዝግቧል፡፡

በበጀት አመቱ የተፈጠረ የስራ እድል
በኤጀንሲው በበጀት አመቱ በዋናው መስሪያ ቤት፣ በመንገድና ድልድይ ግንባታ ፕሮጀክቶች እና በመንገድ ጥገና ስራዎች ለ17,949 ወንዶች እና ለ7,439 ሴቶች በድምሩ 25,388 ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ወንድ= 14,228 (79%)፣ ሴት= 4,153 (56%) በድምሩ 18‚381 (72.40%) የሚሆኑ ወገኖችን የስራ እድል ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የህፃናት ማዋያ ህንፃ ግንባታ  ተጠናቀቀ።የመንግስት ሠራተኞችን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ፣ ሠራተኞች ሙሉ ትኩረታቸውን በመደበኛ ስራቸው ላይ ...
13/08/2026

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የህፃናት ማዋያ ህንፃ ግንባታ ተጠናቀቀ።

የመንግስት ሠራተኞችን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ፣ ሠራተኞች ሙሉ ትኩረታቸውን በመደበኛ ስራቸው ላይ እንዲያተኮሩ በተለይም በጋብቻ ላይ ያሉ ሴት የመንግስት ሠራተኞች ከወሊድ በኋላ የሚኖርባቸው ድርብርብ ኃላፊነት ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በሌላ በኩል የመንግሰት ሠራተኛው ባለበት የኢኮኖሚ ውስንነት ልጆቹን ለማሳደግ ሞግዚት ለመቅጠር የሚችልበት ሁኔታ አናሳ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡

በመሆኑም በመንግስት መስሪያ ቤቶች አካባቢ የህፃናት ማቆያ ማዘጋጀት ለወላጆችም የአእምሮ እረፍት የሚሰጥ ለህፃናቱ በመንግስት የስራ ስዓት ወላጆቻቸውን በቅርብ እንዲያገኙና በሰለጠነ ሞግዚት እንክባካቤ እንዲያገኙ በማድረግ ትልቅ አስተዋፅዖ አድርጓል፡፡

የአብክመ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ በመንግስት ተቋማት በውስጥ አቅማቸው የህፃናት ማቆያ በሚያዘጋጁበት ወቅት የሰለጠኑ ሞግዚት መቅጠር እንዲችሉ የስራ መደብ በመፍቀድ በፈጠረው ምቹ ሁኔታ በአብዛኛው የመንግስት ተቋማት የህፃናት ማቆያ እንዲቋቋም በመደረጉ የመንግስት ሠራተኛው ላይ ትልቅ እፎይታ መፍጠር ተችሏል፡፡

በዚህ ምክንያት የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የኤጀንሲው ሠራተኞችን በዚህ ረገድ እየገጠማቸው ያለውን ችግር ለመጋራትና በዘላቂነት ለመፍታት በ388 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ሲያስገነባው የነበረው የህፃናት ማዋያ ህንፃ ግንባታ በመጠናቀቁ በቅርቡ ለአገልግሎት እንደሚውል ይታመናል፡፡

በኤጀንሲው የገነባው የህፃናት ማዋያ ህንፃ መኝታ ቤቶች፣ ሳሎን፣ መመገቢያ ክፍሎች፣ ሽንት ቤቶች፣ የእቃ ማጠቢያ ክፍል፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽን ማስቀመጫ፣ ሻወር ቤቶች፣ ቢሮ፣ የህፃናት ጡት ማጥቢያ፣ የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ እና ለተንከባካቢ ሞግዚቶች የሚያገለግሉ በአጠቃላይ 18 ክፍሎች አሉት።

በመሆኑም በኤጀንሲው የተገነባው የህፃናት ማዋያ ህንፃ ግንባታው በመጠናቀቁ ለአገልግሎት ሲጀምር እድሚያቸው ከ6 ወር እስከ 4 አመት ላሉ 40 ህፃናት በማዋያነት የሚያገለግል ሲሆን የግንባታ ስራውን በመጠናቀቁ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

ይህ እጅግ ያማረና ደረጃውን የጠበቀ የህፃናት ማዋያ ህንፃ ግንባታ ኤጀንሲው ከፍተኛ በጀት በመመደብ ለሠራተኞች ልጆች አገልግሎት እንዲውል ለማድረግ በኤጀንሲው ከፍተኛ አመራሮች የተወሰደው አርአያነት ያለው ተግባር ያለን ምስጋና ታላቅ ነው፡፡

ወጭ ቆጣቢ፣ ጥራትና ረጅም አገልግሎት የመንገድ ግንባታ ስራዎቻችን መለያዎች ናቸው፡፡

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የተቋቋመበት ዋና አላማ በክልሉ አዳዲስ መንገዶችንና ድልድዮችን ለመገንባትና ነባር መንገዶች ያልተቋረጠ አገልግሎት እንዲሰጡ በተለያዩ የጥገና ስል...
12/08/2026

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የተቋቋመበት ዋና አላማ በክልሉ አዳዲስ መንገዶችንና ድልድዮችን ለመገንባትና ነባር መንገዶች ያልተቋረጠ አገልግሎት እንዲሰጡ በተለያዩ የጥገና ስልቶች ተከታታይ ጥገና ለማድረግ ሲሆን ይህንኑ አላማውን ለማሳካት የ2018 ዓ.ምን ዕቅድ አዘጋጅቶ ወደ ስራ በመግባት በርካታ ተግባራትን አከናውኗል።

በመሆኑም ኤጀንሲው በ2018 በጀት አመት ያከናወናቸው የዋና ዋና ተግባራት አፈፃፀሞች እንደሚከተለው ቀርበዋል።

የነባር መንገዶች ጥገና አፈፃፀም
የተገነቡ መንገዶች የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ በየወቅቱ ተገቢውን ጥገና እንዲያገኙ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ የመንገድ ጥገና ስራዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው መከናወን አለባቸው።

በመሆኑም ኤጀንሲው በ2018 ዓ.ም ከፌዴራል መንገድ ፈንድ ጽ/ቤት በተመደበ ብር 1‚268‚209‚880.55 በጀት በ289 የጥገና መስመሮች 5,288.35 ኪ.ሜ /87.58%/ መደበኛ እና 749.99 ኪ.ሜ /12.42%/ ወቅታዊ በድምሩ 6‚038.34 ኪ.ሜ ነባር መንገዶችን ለመጠገን አቅዶ በ6ቱ ጥገና ጽ/ቤቶች (ጎጃም፣ ጎንደር፣ ወሎ፣ ሰሜን- ሸዋ፣ ደብረ- ታቦር እና ወልድያ) በወቅታዊ 731.99 ኪ.ሜ፣ በመደበኛ 4,881.01 ኪ.ሜ በአጠቃላይ 5,613.00 ኪ.ሜ የነባር መንገዶች ጥገና በማከናወን የአመቱን እቅድ 92.96% ፈፅሟል።

በኤጀንሲው በበጀት አመቱ በመደበኛ የጥገና ስልት ከተከናወነው 4‚881.01 ኪሜ የነባር መንገዶች ጥገና መካከል 3‚324.67 ኪ.ሜ በመሳሪያ የተከናወነ ሲሆን ቀሪው 1‚556.34 ኪ.ሜ የሚሆነው ደግሞ በሰው ሃይል የተጠገነ ነው።

ኤጀንሲው በበጀት አመቱ የነባር መንገዶችን ጥገና ለማከናወን በእቅድ ከያዛቸው 289 የጥገና መስመሮች መካከል የ270 መስመሮችን ጥገና ሙሉ በሙሉ አጠናቋል።

Address

Ethiopia , Amhara
Bahir Dar

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
18:00 - 19:00
Tuesday 09:00 - 17:00
18:00 - 19:00
Wednesday 09:00 - 17:00
18:00 - 19:00
Thursday 09:00 - 17:00
18:00 - 19:00
Friday 09:00 - 17:00
18:00 - 19:00
Saturday 09:00 - 17:00

Telephone

+251582201711

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Rural Roads Construction Agencyአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Amhara Rural Roads Construction Agencyአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ:

Shortcuts

Share