Amhara Health Bureau - አብክመ ጤና ቢሮ

Amhara Health Bureau - አብክመ ጤና ቢሮ This page is an official page of the Amhara Regional Health Bureau.

የተሟላ የጤና አገልግሎት ማህበረሰቡ ጥራት ያለው፣ ፍትሃዊ እና ሰውን ያማከለ ሕክምና በፍጥነት እንዲያገኝ ያስችላል። የጤና ተቋማት ይህንን ግብ ለማሳካት የመድኃኒት አቅርቦት፣ የዘመናዊ መሣሪ...
20/08/2026

የተሟላ የጤና አገልግሎት ማህበረሰቡ ጥራት ያለው፣ ፍትሃዊ እና ሰውን ያማከለ ሕክምና በፍጥነት እንዲያገኝ ያስችላል። የጤና ተቋማት ይህንን ግብ ለማሳካት የመድኃኒት አቅርቦት፣ የዘመናዊ መሣሪያዎች ድጋፍ እና የሰለጠነ የሰው ሃይል ማሟላት ይኖርባቸዋል።

በህክምና ተቋማት የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን በማሻሻል ተገልጋዩ ህብረተሰብ የተሟላ የጤና አገልግሎት በጥራትና በፍጥነት እንዲያገኝ ለማስቻል በቅንጅት እየተሠራ ነው፡፡ ባለፉት ዓመታት የጤና ተደራሽነቱን ለማስፋት በተደረገ ጥረት ውጤት ቢመዘገብም በጥራትና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ አሁንም ተግዳሮቶች አሉ፡፡

ጤና ጣቢያና ጤና ኬላዎችን በመገንባት ህብረተሰቡ በቅርበት የህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ እየተደረገ ቢሆንም የአገልግሎት ጥራት መጓደል ችግር በሚፈለገው ልክ ተፈቷል ማለት አይቻልም ።
ስለሆነም የጤና ተቋማት ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ስራ በቅንጅት መስራት ይኖርባቸዋል።

ጥራት ያለው እና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት በጋራ እና በቅንጅት መስራታቸው የህብረተሰቡን ጤና ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው። ተቋማት ሀብትን በማስተባበር፣ ልምድ በመለዋወጥ እና የክትትል ስራዎችን በአንድነት ማከናወን ይኖርባቸዋል።

የክልሉ ጤና ቢሮ   የአፈፃፀም ገምጋሚ ቡድን  የ2018 ዓ.ም  የሐምሌ ወር እቅድ አፋፃፀም ግምገማ አካሄደ‎‎በመድረኩ የጤናው ዘርፍ  የሐምሌ ወር እቅድ አፋፃፀም ሪፖርት ቀረቦ ውይይት ተደ...
20/08/2026

የክልሉ ጤና ቢሮ የአፈፃፀም ገምጋሚ ቡድን የ2018 ዓ.ም የሐምሌ ወር እቅድ አፋፃፀም ግምገማ አካሄደ

‎በመድረኩ የጤናው ዘርፍ የሐምሌ ወር እቅድ አፋፃፀም ሪፖርት ቀረቦ ውይይት ተደርጎበታል።

‎የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ገስጥ ጥላሁን እንደተናገሩት በ2018 ዓ.ም የሐምሌ ወር እቅድ ክንውን በዳይሬክተር እና በኬዝቲም ደረጃ ስንገመግም በጤናው ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለማጠናከር እንደሚረዳ አስገንዝበዋል።

‎አቶ ገስጥ አክለውም የመረጃ ጥራት ከቢሮ ጀምሮ እስከታችኛዉ መዋቅር ያለውን አሰራር ማጠናከር በጤና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያለው አስተዋጾ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

‎የሚሰሩ ስራዎችን ተጠያቂነት ባለዉ መልኩ መረጃን መያዝ እና ሪፖርት ማድረግ እንደሚገባም አስታውቀዋል።

‎በክልሉ ጤና ቢሮ የእቅድ ክትትል ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አማረ በበኩላቸው በተለይም ዳይሬክቶሬቶችና የፕሮግራም አስተባባሪዎች ሪፖርታቸውን በየወቅቱ መከታተል እንደሚገባቸው የተናግረዋል ።

‎የመረጃ ጥራት ችግሮች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን የመረጃ ጥራት ችግሮችም ለሚመለከታቸው ግብረ መልስ መሰጠቱንም በውይይቱ ወቅት ተነስቷል።

‎በቀጣይም ሁሉም አፈፃፀም ግምገማ ቡድን አባላት የመረጃ ጥራት ችግሮችን መስተካከላቸውን መከታተል ይገባል ያሉት አቶ አማረ ናቸው።

‎ዕቅድ አፈፃፀሙ እንደ ክልል የተሻለ አፈፃፀም ቢኖርም የዞን እና ወረዳ መካከል ያለው የአፈፃፀም ልዮነት የስፋ መሆኑ በግምገማው ወቅት ተመላክቷል።

‎የአፈፃፀም ልዮነትን ለማጥበብ በቀጣይ መሰራት እንዳለበትም ተገልጿል።

‎በቀጣይ ወራቶች ጥሩ አፈፃፀም ያለቸውን ፕሮግራሞችን አጠናክሮ ማስቀጠልና ወደ ኋላ የቀሩትን በመደገፍ የተሻላ አፈፃፀም እንዲመጣ መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል።

‎በቀጣይ ወደ ኋለ የቀሩበትን እንዲኬተሮች በመለየት በትክክል እቅድ ውስጥ በማስገባት የተሻለ ጤና አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀት ይኖርባቸዋል።

‎በግምገማ መድረኩ ላይም የአፈፃፀም ግምገማ ቡድን አባላት ተሳትፈውበታል።

‎ #አብክመጤናቢሮ


‎ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም

ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለሁሉም...****‎የተቀናጀ እና ሰውን ያማከለ የጤና አገልግሎት ለተሻለ የጤና ስርዓት መፈጠር ምክንያት ነው። ከዚህ አኳያ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለማህበ...
20/08/2026

ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለሁሉም...
****
‎የተቀናጀ እና ሰውን ያማከለ የጤና አገልግሎት ለተሻለ የጤና ስርዓት መፈጠር ምክንያት ነው። ከዚህ አኳያ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለማህበረሰቡ ለመስጠት የሁሉም ባለድርሻዎች ትብብር አስፈላጊ ነው።

‎የህክምናና የመድኃኒት አቅርቦት፣ የጤና መሠረተ ልማትቶችን ማስፋፋት ፣ አስፈላጊ የጤና አገልግሎቶችን በሁሉም የክልላችን አካባቢዎች በጥራት ለህብረተሰቡ መስጠት ተገቢ ብቻ ሳይሆን ግዴታ ጭምር ነው።

‎ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለማህበረሰቡ መስጠት የአማራ ክልል ጤና ቢሮ አንዱ ዋና ተግባር በመሆኑ ይህንኑ ለመተግበርም ጥረት እየተደረገ ይገኛል። ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት በቋሚነት ለማህበረሰቡ ለመስጠትም የሁሉም ባለድርሻ አካላት ትብብር አስፈላጊ መሆኑ ጥርጥር የለውም።

‎ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋንን ለማሳካት ጥራት ያለው እና ደህንነቱ የተጠበቀ የጤና አገልግሎት መስጠት ወሳኝ እና አስፈላጊ ነው። በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ላይ ለአገልግሎት ጥራት መጓደል ምክንያት የሚሆኑ ችግሮችን በመለየት ወደ ሥራ በመገባቱ የተሻለ ጥራት ያለውን የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

‎በመስክ ምልከታ በተገኙ ግኝቶች ላይ በመመስረት አገልግሎቱን ለማሻሻል የሚያስችሉ ስራዎች በሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ላይ ስሰሩ ቆይተዋል፡፡

‎የባላሙያዎችን አቅም መገንባት፣ ተቋማትን በመድሃንቶችና በሌሎች የህክምና ግብዓቶች ማደራጀት፣ የስነ ምግባር ችግሮችን ማረም እንዲሁም ተከታታይ የሆነ ድጋፍና ክትትል ማድረግ በዓመቱ ከሚሰሩ ስራዎች የሚጠቀሱ ናቸው።

‎በተጨማሪም ተከታታይ የሆነ የምክክር መድረክ በጤና ተቋማት፣ በማህበረሰቡና በባለሙያዎች መካከል እንዲካሄድ ማድረግና የቦርድ አመራሮች ወደ ተቋማት ጠጋ ብለዉ ችግሮችን እየፈቱ እንዲሄዱ በልዩ ትኩረት የሚሰራ ሲሆን የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ጉልህ ሚና ይኖረዋል፡፡

‎ማህበረሰቡ በተደጋጋሚ ከሚያነሳቸው ጉዳዮች አንዱ በጤና ተቋማት ዉስጥ የመድሐኒቶችና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች በበቂ ሁኔታ ያለመኖር ችግር እንደመሆኑ መጠን ችግሩን ለማረምም በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።

ባለፈው በጀት ዓመት በመንግስትና በአጋር ድርጅቶች አማካይነት ከሚቀርቡ የህክምና ግብዓቶች በተጨማሪ ህብረተሰቡን በስፋት በማሳተፍ ተቋማት በቂ ግብዓት እንድኖራቸዉ የተሰራበት ዓመት ነዉ።

‎ሞዴል የማህበረሰብ መድሐኒት ቤቶችን ማስፋፋት፣ ለኦዲትና ለአገልግሎት አሰጣጥ ምቹ የሆኑ መድሐኒት ቤቶችን ከማሳደግ አንጻር የተሰሩ ስኬታማ ተግባራትን መዘርዘር ይቻላል።

‎የማህበረሰቡን ፍትሐዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በዓመቱ ዉስጥ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ተጠቃሚ አባላት ምጣኔ ከማሳደግ አንፃር ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጀምሮ በተደረገ ርብርብ ወደ የዓመቱን አፈጻጸም 92 በመቶ በማሳደግ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡


‎ #አብክመጤናቢሮ

በኪንፋዝ በገላ ወረዳ  ለመኪና አስቸጋሪ በሆነ መንገድ ለማህበረሰቡ የጤና አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶች ወደ ቀበሌዎች እና ወደ ክላስተር ጤናጣቢያዎች ሲሰራጭ የሚያሳይ ምስል፡፡ለችግሮች ሳንበገ...
20/08/2026

በኪንፋዝ በገላ ወረዳ ለመኪና አስቸጋሪ በሆነ መንገድ ለማህበረሰቡ የጤና አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶች ወደ ቀበሌዎች እና ወደ ክላስተር ጤናጣቢያዎች ሲሰራጭ የሚያሳይ ምስል፡፡
ለችግሮች ሳንበገር ማህበረሰቡ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን እንተጋለን!
አብክመ ጤና ቢሮ
ነሀሴ 14/2018 ዓ.ም

19/08/2026

የበሽታዎች መከ/መቆ/ እና የኤች አይቪ/ኤድሰ ዘርፈ ብዙ ምላሽ ዳይሬክቶሬቶች የአፈጻጸም ግምገማና የእቅድ ትውውቅ መድረክ
ነሀሴ 13/2018 ዓ.ም

‎የአዊ ብሔ/አስ/ጤና መምሪያ ከእንጅባራ ከተማ አስ/ ጤና ጽ/ቤት ጋር በመቀናጀት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በግል በጤናው ዘርፍ የተሰማሩ አካላት  ጋር ውይይት አካሄደ፡፡‎‎በእንጅባራ ...
19/08/2026

‎የአዊ ብሔ/አስ/ጤና መምሪያ ከእንጅባራ ከተማ አስ/ ጤና ጽ/ቤት ጋር በመቀናጀት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በግል በጤናው ዘርፍ የተሰማሩ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

‎በእንጅባራ ከተማ የሚገኙ የግል ጤና ተቋማት የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዙሪያ ከፍለው መታከም ለሚይችሉ አቅመ ደካሞችና አረጋውያን ነፃ የህክምና አገልግሎት ለመስጠትና መኖሪያ ቤት ግንባታ ውይይት አድርገዋል ።

‎የውይይት መድረኩትን የመሩት የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ሠውነት የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንደ ሀገር ከተጀመረ 5 ዓመታት እንዳስቆጠረ አንስተው በዚህ በጀት ዓመት ተቋማት እየተቀናጀ ለዜጎች የተሻለ ድጋፍ እየደረጉ መሆኑን ተናግረዋል።

‎ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በ17 ዘርፎች አገልግሎት እየተሰጠ ነው ያሉት አቶ አለሙ የግል ጤና ተቋማትንና ሌሎችን በማስተባበር ለአቅመ ደከሞች የሚሆኑ ደረጃቸውን የጠበቁ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት አቅደው እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።

‎የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በህዝቡ ዘንድ ባህል ሆኖ እንዲቀጥል መስራት እንደሚገባ የገለፁት ኃላፊው በእንጅባራ ከተማ የተጀመረው የግል የጤና ተቋማት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሁሉም በብሔረሰብ አስተዳደሩ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ተጠናክሮ እንደሚቀጥ ተናግረዋል።

‎የአዊ ብሔረሰብ አሰተዳደር ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አየለ አልማው የግል የጤና ተቋማት የዜጎችን ጤና ለማሻሻል የጀርባ አጥንት መሆናቸውን አንስተው መንግስት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ልዩ ትኩረት በመስጠት በተሰራው ስራ በርካታ ዜጎች እየተሳተፋ አቅመ ደካሞችና አረጋውያን እየደገፉ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

‎የጤና ተቋማት ከሌሎች ተቋማት በተለየ ሁኔታ በሰባዊነት ላይ የሚሰሩ እንደመሆናቸው ከፍለው መታካም ለማይችሉ ፣ አቅመ ደካሞችና አረጋዊያን ነፃ ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል።

‎ለውይይቱ መነሻ ሀሳብ ያቀረቡ የአዊ ብሔረሰብ አሰተዳደር ምክትል ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አህመድ ሁሴን በብሔረስብ አስተዳደሩ በ2018 ዓ/ም በክረምት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተሰሩ ስራዎች በገንዘብ ሲተመን 9 ሚሊዮን 814 ሺህ 411 የሚሆን በጤናው ዘርፍ አገልግሎት መስጠታቸውን ተናግረዋል።

‎የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በየሳምንቱ በትኩረት እየተገመገመ የተመራ በመሆኑ የወባ ወረርሽኝን 50 በመቶ መቀነስ ተችሏል ነው ያሉት።

‎የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ መቶ አለቃ አበራ ገረም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በጤናው ዘርፍ አዲስ ሳይሆን ከህሙማን የጎደለውን እያሟሉና በነፃ ህክምና እየሰጡ እንደነበረ አንስተው ሁሉም የግል የጤና ተቋማት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት መሳተፍ ይገባል ብለዋል።

‎ከፍለው መታካም ለሚይችሉ አቅመ ደካሞችና አረጋውያን ነፃ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት አስፈላጊውን ሁሉ አቅም የፈቀደውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ተሳታፊ በግል ጤና ዘርፍ የተሰማሩ ተናግረዋል። የበጎ ፈቃድ ሰራ የክረምት ብቻ ሰራ ሳይሆን ዓመቱን ሙሉ የሚስራባት መሆን ይገባል ነው ያሉት።

‎በመጨረሻም ለመኖሪያ ቤት ግንባታ ሰባት አባላት ያሉት የገንዘብ አሰባሳቢ ኮሚቴ በመቋቋም ውይይቱ ተጠናቅቋል።

‎ #አብክመጤናቢሮ


‎ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም

ጡት ማጥባት‎‎ህጻኑ በቂ ወተት እየጠባ (እያገኘ) መሆኑን ለማወቅ ‎⇒በቀን ቢያንስ 6 ጊዜ ያህል ሽንት መሽናቱን፤‎⇒ ክብደቱ እየጨመረ መሄዱን፤ እና‎⇒ የህጻኑ ሽንት ፈዘዝ ያለ ቀለም ያለው...
19/08/2026

ጡት ማጥባት

‎ህጻኑ በቂ ወተት እየጠባ (እያገኘ) መሆኑን ለማወቅ
‎⇒በቀን ቢያንስ 6 ጊዜ ያህል ሽንት መሽናቱን፤
‎⇒ ክብደቱ እየጨመረ መሄዱን፤ እና
‎⇒ የህጻኑ ሽንት ፈዘዝ ያለ ቀለም ያለውና ከበድ ያለ ሽታ የሌለው መሆኑን መከታተል
‎ያስፈልጋል፡፡
‎መልካም መሰረት ለመገንባት በመጀመሪያዎቹ 6 ወራት የጡት ወተት ብቻ መስጠት
‎• በመጀመሪያዎቹ 6 ወራት ህጻኑ ለእድገቱ የሚያስፈልገዉን ምግብና ዉሀ ከጡትዎ ወተት ብቻ ማግኘት ይችላል፤ ስለዚህ 6 ወር እስኪሞላው ህጻኑ የእናት ጡት ወተት ብቻ መጥባት አለበት፡፡
‎• ይህ ማለት በጤና ባለሞያ ካልታዘዘ በቀር ከጡት ወተት ሌላ ምንም አይነት ነገር ማለትም የተለያዩ የእንስሳትና የፋብሪካ ወተቶችን፣ ምግቦችን፣ ፈሳሾችን እና ዉሀን የመሳሰሉትን መስጠት ፈጽሞ አይመከርም፡፡
‎• በመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት (180) ቀናት ከጡት ወተት ውጭ ተጨማሪ ነገር መስጠት የጡትዎን ወተት የማመንጨት ብቃት እንዲቀንስ ከማድረጉም በተጨማሪ ህጻኑን ለተለያዩ በሽታዎች ያጋልጣል፡፡

‎የእናት ጡትን በአግባቡ ማጥባት ሲባል
‎ህጻኑ ቀንና ሌሊት የቻሉትን ያህል ጊዜ ማጥባት ጡቶችዎ በቂ ወተት እንዲያመነጩ ከመርዳቱ በተጨማሪ ጡቶችዎ በጣም አግተው ህመም እንዳያስከትልብዎ ይከላከላል፡፡ህጻኑ ተጨማሪ መጥባት መፈለጉም በደንብ እያደገ ለመሆኑ ጥሩ ማሳያ ምልክት ነው፡፡ጡቶችዎ በጣም እንዳያግቱ የማጥቢያ ሰዓትዎ ማሳለፍ የለብዎትም፤ ህጻኑ ሳይጠባ እንኩዋን ቢቀር
‎የተወሰነው ወተት አልበው ጡቶችዎ ላላ እንዲሉ ማድረግ አለብዎት። ያለቡትን የጡትዎን ወተት በንጽህና ከድነው በማስቀመጥ ህጻኑን መመገብ ይችላሉ፤ ያለቡትን የጡትዎን ወተት ግን ከ 8 ሰዓት በላይ ማስቀመጥ የለብዎትም፡፡
‎ጡት ማጥባት ህጻኑ በተወለደ በአንድ ሰዓት ጊዜ ውስጥ መጀመር አለበት፡፡ ይህም
‎• ህጻኑ ጥሩ የአልሚ ምግብና በሽታ የመከላከል አቅም ያለውን የመጀመሪያ ወተት (እንገር) እንዲያገኝ ይረዳል፡፡
‎• ህጻኑ በመጀመሪያው አንድ ሰዓት ውስጥ ያለውን የተሻለ ተፈጥሯዊ ጡት የመጥባት ብቃትና ፍላጎት ለመጠቀም፤ እንዲሁም የእናት ጡት የተሻለ ወተት የማመንጨት አቅም እንዲኖረው ያደርጋል፡፡
‎• በዚህ የህይወት መነሻ በሆነችው አንድ ሰዓት ጊዜ ውስጥ ከእናት ጡት ውጭ ሌላ ፈሳሽ ወይም ወተት መስጠት ህጻናት እነዚህን ጥቅሞች በቀሪ ዘመናቸው እንዲያጡ ያደርጋል፡፡
‎• ስለሆነም ህጻኑ እንደተወለደ (እንግዴ ልጅ ከመውጣቱ በፊትም ቢሆን) ወዲያውኑ ወደ
‎ደረትዎ አስጠግተው ይያዙ፡፡ከዛም በመጀመሪያ የጡትዎን ጫፍ የሕጻኑን ከንፈሮች ያስነኩ፤
‎በመቀጠልም የሕጻኑ አፍ በሚከፈትበት ጊዜ ህጻኑን በደንብ አስጠግተው ጡትዎን ያጉርሱት፡፡
‎መልካም መሰረት ለመገንባት በመጀመሪያዎቹ 6 ወራት የጡት ወተት ብቻ መስጠት
‎• በመጀመሪያዎቹ 6 ወራት ህጻኑ ለእድገቱ የሚያስፈልገዉን ምግብና ዉሀ ከጡትዎ ወተት ብቻ ማግኘት ይችላል፤ ስለዚህ 6 ወር እስኪሞላው ህጻኑ የእናት ጡት ወተት ብቻ መጥባት አለበት፡፡
‎• ይህ ማለት በጤና ባለሞያ ካልታዘዘ በቀር ከጡት ወተት ሌላ ምንም አይነት ነገር ማለትም የተለያዩ የእንስሳትና የፋብሪካ ወተቶችን፣ ምግቦችን፣ ፈሳሾችን እና ዉሀን የመሳሰሉትን መስጠት ፈጽሞ አይመከርም፡፡
‎• በመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት (180) ቀናት ከጡት ወተት ውጭ ተጨማሪ ነገር መስጠት የጡትዎን ወተት የማመንጨት ብቃት እንዲቀንስ ከማድረጉም በተጨማሪ ህጻኑን ለተለያዩ በሽታዎች ያጋልጣል፡፡

#አብክመጤናቢሮ


‎ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም

በዓለም ከተማ እናት ሆስፒታል የተዘረጋው ዲጂታል አሰራር የአገልግሎት አሰጣጡን እያዘመነ ነውዲጂታል የአሰራር ስርዓት ቀደም ሲል ይስተዋሉ የነበሩ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በመቅረፍ ዘርፉ...
19/08/2026

በዓለም ከተማ እናት ሆስፒታል የተዘረጋው ዲጂታል አሰራር የአገልግሎት አሰጣጡን እያዘመነ ነው

ዲጂታል የአሰራር ስርዓት ቀደም ሲል ይስተዋሉ የነበሩ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በመቅረፍ ዘርፉን እያዘመነ ይገኛል።

ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር በሚስተናገድባቸው የጤና ተቋማት ከወረቀት ነፃ የሆነ አሰራር መዘርጋት አገልግሎቱን ፈጣን፣ ቀልጣፋና ወጪ ቆጣቢ አድርጎታል።

በሰሜን ሸዋ ዞን መርሃቤቴ ወረዳ ዓለም ከተማ በሚገኘው እናት ሆስፒታል የተጀመረው ከወረቀት ነፃ የሆነ የህክምና አገልግሎት ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው ተገልጋዮች ተናግረዋል።

ለህክምና አገልግሎት የተገኙት አቶ አድማሱ በየነ አገልግሎቱ በወረቀት በሚሰጥበት ወቅት የወረፋ ስርዓት ችግሮች ያጋጥሙ እንደነበር አስታውሰው፣ አሁን ግን እንደ አመጣጣቸው ፈጣን አገልግሎት ማግኘት መጀመራቸውን ገልጸዋል።

ሌላኛው ተገልጋይ አቶ ብርሃኑ ጨቡዱ በበኩላቸው፣ ከዚህ በፊት የአገልግሎት ቅልጥፍና ችግሮች ይገጥሟቸው እንደነበር ጠቅሰው፣ የወረቀት አልባ ህክምና አገልግሎቱ ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል።

የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ አለባቸው አቢወይ ቀደም ሲል በነበረው ተለምዷዊ አሰራር የመረጃ አደረጃጀት ምቹ አለመሆን ለቅሬታ መንስኤ እንደነበር አስታውሰዋል።

ወደ ወረቀት አልባ አሰራር ከተገባ በኋላ ችግሮቹ መፈታታቸውን የገለጹት ስራ አስኪያጁ፣ በዓመት እስከ ሁለት ሚሊዮን ብር የሚደርስ የህትመት ወጪ ማዳን ተችሏል ብለዋል።

ሆስፒታሉ እስከሚቀጥለው መስከረም ወር ድረስ አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ በሁሉም የስራ ክፍሎች ለማስፋፋት አቅዶ እየሰራ ይገኛል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ ምክትል ሀላፊ አቶ ተፈሪ ይደነቅ ይህን ስኬታማ አሰራር ወደ ሌሎች የጤና ተቋማት ለማስፋት እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

ምክትል መምሪያ ሀላፊው የተገልጋዮችን እርካታ ለማሳደግና አሰራርን ከቴክኖሎጂ ጋር በማስተሳሰር ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት ባለድርሻ አካላት ድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።(አሚኮ)
ነሀሴ 13/2018ዓ.ም

"ለኅብረተሰብ ለውጥ የምንተጋበት አንዱ ዘርፍ ጤናማ ትውልድ መፍጠር ነው"አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን እና የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ሁሉን አቀፍ የጤና ፖሊሲ በሚዲያ አጋርነት እና በቀጣይ ሥራዎች በ...
18/08/2026

"ለኅብረተሰብ ለውጥ የምንተጋበት አንዱ ዘርፍ ጤናማ ትውልድ መፍጠር ነው"

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን እና የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ሁሉን አቀፍ የጤና ፖሊሲ በሚዲያ አጋርነት እና በቀጣይ ሥራዎች በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።

በስምምነቱ ጤና ቢሮ ከጤና ፖሊሲ አተገባበር፤ ከቅድመ መከላከል እና በጤናው ዘርፍ ስለሚደረጉ አጠቃላይ እንቅስቃሴዎች ተገቢ መረጃ በመስጠት ሙያዊ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተቀምጧል።

አሚኮ በበኩሉ የጤና ዘርፍ ሂደቶችን ለሕዝብ እና መንግሥት ለማሳወቅ በሁሉም የሚዲያ አማራጮቹ እንደሚሠራ ተመላክቷል።

ተቋማቱ የእናቶችን እና የጨቅላ ሕጻናትን ጤና በሚያሻሽሉ፤ የሥርዓተ ምግብ አገልግሎትን በሚያዘምኑ፤ ኤች አይ ቪ (ኤድስ) መከላከል እና መቆጣጠር፤ የውኃ ሳኒቴሽን፣ ሃይጅን (WASH) እና የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ላይ በይበልጥ በትኩረት እንደሚሠሩ በስምምነቱ ተገልጿል።

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ሰጥዬ አሚኮ በሁሉም የማሠራጫ ጣቢያዎቹ ማኅበረሰቡ ጤናውን እንዲጠብቅ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት እና ዘገባዎችን በመሥራት ውጤታማ ሥራ ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸዋል።

ከጤና ቢሮ እና ከጤና ባለሙያዎች ጋር በቅንጅት በመኾን ትክክለኛ መረጃ እና ዕውቀት ለመስጠት ስምምነት መደረጉን ተናግረዋል። ለኅብረተሰብ ለውጥ የምንተጋበት አንዱ ዘርፍ ጤናማ እና ፍሬያማ ትውልድ መፍጠር ሥንችል ነው ብሎ በማመን ተቋሙ ሢሠራ ቆይቷል ብለዋል።

በጤናው ዘርፍ ይበልጥ ለመሥራት ጥረት ይደረጋል ነው ያሉት። የጤና ቢሮ እና ባለሙያዎችን በመጠቀም ለኅብረተሰቡ ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማድረስ ይሠራል ብለዋል።

ስምምነቱ በወረቀት ብቻ የሚቀር ሳይኾን ሲከናወኑ የነበሩ ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የሚያስችል መኾኑንም አንስተዋል።

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኀላፊ አብዱልከሪም መንግሥቱ አሚኮ በቴክኖሎጅ ታግዞ የሚሠራው፤ በግቢው ውስጥ የሚያከናውናቸው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የአረንጓዴ ልማት ተግባራት እና የግቢ ውበት የሚደነቅ መኾኑን አንስተዋል።

ጤናማ፣ አምራች፣ የበለጸገ እና ደስተኛ ማኅበረሰብ ለመፍጠር እና ከዚህ በፊት በጤናው ዘርፍ የነበሩ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚዲያ ጥቅም ወሳኝ መኾኑን ገልጸዋል። አሚኮ የጤና ቢሮው ጠንካራ ተግባራትን እንዲሁም ክፍተቶችን በመለየት ውጤታማ የጤና አገልግሎት እንዲሰጥ በቅርበት ኾኖ ሢሠራ ቆይቷልም ብለዋል።

የግንዛቤ ክፍተቶችን ለማረም፤ የእናቶች እና ሕጻናትን ጤና ለማሻሻል፤ ተላላፊ እና ተላላፊ ያልኾኑ በሽታዎችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር፤ ጽዱ አካባቢን ለመፍጠር፤ ማኅበረሰቡ የሥርዓተ ምግብ ለውጥ እንዲያመጣ፤ ሕዝቡ በቤቱ ጤናውን እንዲጠብቅ ለማስቻል የሚዲያ ሥራ ወሳኝ መኾኑንም ተናግረዋል።

ከአሚኮ ጋር ይበልጥ በመቀናጀት የጤና ባለሙያዎች እና የሥራ ኀላፊዎች ተሳታፊ እንዲኾኑ፤ የኮሙዩኒኬሽን አጠቃቀማቸውን ይበልጥ እንዲያሳድጉ በቅርበት እንደሚሠራ አመላክተዋል።

ስምምነቱ በወረቀት ብቻ የሚቀር ሳይኾን ቋሚ የአየር ሰዓት በመጠቀም፤ የተለያዩ ሁነቶችን በማመቻቸት ተገቢውን መረጃ በመስጠት በተግባር ይደገፋል ብለዋል። ማኅበረሰቡ ከመሠረታዊ የጤና ችግሮች እንዲላቀቅ በጋራ ውጤታማ ተግባር እና የአገልግሎት ለውጦችን ለማምጣት በትኩረት ይሠራል ነው ያሉት።

የተቋማቱ የሥራ ኀላፊዎች የአሚኮ የስፖርት ማዘውተሪያ እና የአረንጓዴ ልማት ቦታዎችንም ጎብኝተዋል።

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Health Bureau - አብክመ ጤና ቢሮ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Amhara Health Bureau - አብክመ ጤና ቢሮ:

Shortcuts

Share