Amhara Civil ServiceAnd Human Resource Development Bureau

Amhara Civil ServiceAnd Human Resource Development Bureau Amhara Civil Service And Human Resource Development Bureau

"በምርጫው ሀገር እና ሕዝብ አሸንፈዋል" ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደባሕር ዳር: ግንቦት 25/2018 ዓ.ም  ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ ትናንት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሰባ...
02/06/2026

"በምርጫው ሀገር እና ሕዝብ አሸንፈዋል" ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ

ባሕር ዳር: ግንቦት 25/2018 ዓ.ም

ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ ትናንት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ማካሄዷንና በአማራ ክልልም ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሐዊ ኾኖ መጠናቀቁን ገልጸዋል። በምርጫው ሀገር እና ሕዝብ ማሸነፋቸውን ጠቅሰዋል።

"ከጥንትም ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ትልቅ አሻራ ያሳረፈው የክልላችን ሕዝብ ትናንት ደግሞ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ያለውን ቀናዒ ፍላጎት ለዓለም አሳይቷል፤ በአማራ ክልል ምርጫ ማካሄድ ድምጽ ከመስጠት ባሻገር ነው" ብለዋል።

በክልላችን ምርጫ እንዳይካሄድ፤ ዜጎች መብታቸውን እንዳይጠቀሙ፤ በሕዝብ ድምጽ የተመረጠ መንግሥት እንዳይመሠርት፣ ክልሉ ሁልጊዜ በድህነት እና በግጭት ውስጥ እንዲኖር የሚፈልጉ የውይይት እና የሰላም ተቃራኒ ኃይሎች ብዙ ጥረት ማድረጋቸውንም አንስተዋል። "ይሁን እንጂ በሕዝባችን አስተዋይነት እና በጸጥታ ኃይላችን ጀግንነት እነርሱ የፈለጉት ሳይኾን ሕዝብ የፈለገው ኾኗል" ነው ያሉት።

የክልሉ ሕዝብ ትናንት ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ያሳየው ተሳትፎ፣ ጽናት እና ትዕግሥት የብልሃት እና የጥበብ ምንጭ መኾኑን ያሰመሰከረበት ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ምርጫው ሕዝቡ ለፈተና የማይበገር፤ በዛቻ እና በማስፈራሪያ የማይሰበር፣ ለሰላም እና ለሀገረ መንግሥት ግንባታ የትኛውንም መስዋዕትነት እንደሚከፍል ያሳየበት እንደሆነ አስታውቀዋል። "የክልላችን ሕዝብ በትናንትናው ምርጫ የፖለቲካ ሥልጣን የሚገኘው በሕዝብ ድምጽ እንጂ በኃይል አለመኾኑን ግልጽ መልዕክት ያስተላለፈበት ነው" ብለዋል።

የአማራ ክልል ሕዝብ ሰላም ወዳድነቱን፣ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ፈላጊነቱን፤ በሕግና በሕዝብ ይሁንታ ለሚጸና መንግሥት ቀናዒነቱን በግልጽ እንዳሳየም አብራርተዋል። ለዚህ ደግሞ የከበረ ምስጋናዬን ከጥልቅ አክብሮት ጋር ማቅረብ እወዳለሁ ነው ያሉት።

"ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ ምርጫው በክልላችን በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረገው ለሀገር መከለካያ ሠራዊት፣ ለክልላችን የጸጥታ ኃይል፣ በየደረጃው ለሚገኙ የክልላችን አመራሮች እና ለመላው የክልላችንን ሕዝብ በራሴ እና በአማራ ክልል መንግሥት ስም የላቀ ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል ርእሰ መሥተዳድሩ።

ለሀገር እና ለሕዝብ በአንድነት መሥራት ምን አይነት ስኬታማ ውጤት እንደሚያስገኝ ምርጫው ሕያው ምስክር መሆኑንም አስገንዝበዋል።

በምርጫው ጫፍ ረገጥ አስተሳሰቦች እስከ አደረጃጀቶቻቸው በሕዝብ ደምጽ ከሽፈዋል፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ ሀገራችን ኢትዮጵያ አሸንፋለች ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ባስተላለፉት መልእክት።

Amharamediacorporations

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ድምጽ ሰጡ። በባሕርዳር ከተማ ምርጫ ክልል የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ምክትል ጠ...
01/06/2026

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ድምጽ ሰጡ።

በባሕርዳር ከተማ ምርጫ ክልል የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ፓርቲውን ወክለው በባሕር ዳር ከተማ ለክልል ምክር ቤት ዕጩ ኾነው የቀረቡት ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በከተማዋ ድምጽ ሰጥተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ርእሰ መሥተዳድሩ ድምጽ የሰጡት በባሕርዳር ከተማ ግሽ ዓባይ በሚገኘው ሕዳሴ የምርጫ ጣቢያ ነው።

amhara prosperity

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው
01/06/2026

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው

ነገ ሰኞ ግንቦት 24/2018 ዓ/ም  7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመላው አገሪቱ ይከናወናል።ታዲያ እርስዎስ ድምፅዎን በመስጠት በአገርዎ የዴሞክራሲ ጎዞ ላይ አሻራዎን ለማሳረፍ ዝግጁ ይሁኑ።
31/05/2026

ነገ ሰኞ ግንቦት 24/2018 ዓ/ም 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመላው አገሪቱ ይከናወናል።
ታዲያ እርስዎስ ድምፅዎን በመስጠት በአገርዎ የዴሞክራሲ ጎዞ ላይ አሻራዎን ለማሳረፍ ዝግጁ ይሁኑ።

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ 📌የተመወገቡ መራጮች 54 ሚሊዮን 57 ሺህ 871  ናቸው።📌 ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች  42 ናቸው📌 10 ሺህ 438  የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎች ይወዳደራሉ📌  የግል ...
30/05/2026

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ

📌የተመወገቡ መራጮች 54 ሚሊዮን 57 ሺህ 871 ናቸው።

📌 ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች 42 ናቸው

📌 10 ሺህ 438 የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎች ይወዳደራሉ

📌 የግል እጩ ተወዳዳሪዎች 80 ናቸው።

📌 የምርጫውን ሂደቱን እንዲከታተሉ የሚላኩ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች 250 ሺህ ናቸው።

📌 ለታዛቢነት የአፍሪካ ሕብረት እና የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) ተወካዮቻቸውን ልከዋል፤

📌 59 አባላት ያሉት የአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን በቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት አሁሩ ኬንያታ እየተመራ ሥራውን ያከናውናል።

📌ኢጋድ 26 አባላት ያሉት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድንን ያሰማራል

📌 በሀገር ውስጥ የተደራጁ 55 ሲቪክ ማኅበራት ከምርጫ ቦርዱ ፈቃድ አግኝተው ወደ ሥራ ገብተዋል፤ 55ቱ የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች 1 ሺህ 562 የምርጫ ታዛቢዎችን አሰማርተዋል።

#አሚኮ

ከነገ በስቲያ "ሰኞ" የት ነዎት?7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሊከናወን የቀሩት  ቀናት 2 ብቻ ናቸው።ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመላው አገሪቱ ይከናወናል።ታዲያ እርስዎስ ድምፅዎን በ...
30/05/2026

ከነገ በስቲያ "ሰኞ" የት ነዎት?

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሊከናወን የቀሩት ቀናት 2 ብቻ ናቸው።

ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመላው አገሪቱ ይከናወናል።

ታዲያ እርስዎስ ድምፅዎን በመስጠት በአገርዎ የዴሞክራሲ ጎዞ ላይ አሻራዎን ለማሳረፍ ዝግጁ ይሁኑ።

የመጨረሻው የቤት ሥራ፦ የምርጫ ካርድዎን ፈትሸዋል?የቀሩት 2 ቀናት ብቻ ናቸው! ለምርጫው ዕለት ዝግጁ ነዎት? አሁኑኑ የምርጫ ካርድዎን እና መታወቂያዎን በአቅራቢያዎ ማዘጋጀትዎን ያረጋግጡ። ...
30/05/2026

የመጨረሻው የቤት ሥራ፦ የምርጫ ካርድዎን ፈትሸዋል?

የቀሩት 2 ቀናት ብቻ ናቸው! ለምርጫው ዕለት ዝግጁ ነዎት? አሁኑኑ የምርጫ ካርድዎን እና መታወቂያዎን በአቅራቢያዎ ማዘጋጀትዎን ያረጋግጡ።

የትኛው ምርጫ ጣቢያ እንደተመዘገቡ ያስታውሱ። ሰኞ ጠዋት ወደ ምርጫ ጣቢያዎ ሲያቀኑ ህጻናት፣ አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞችን በማስቀደም ሰብአዊነትዎን ያሳዩ።

የእርሶ ዝግጁነት ለዲሞክራሲያዊ ሂደቱ ስኬት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። ዝግጅታችንን አጠናቀን ሰኞን እንጠብቃለን!

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ:-1. 54 ሚሊዮን 57 ሺህ 871 መራጮች ተመዝግበዋል፣2.በአጠቃላይ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች ይወዳደራሉ፤3. 10 ሺህ 438 የፖለቲካ ፓርቲ እጩዎች እንዲሁም4. 80 የ...
29/05/2026

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ:-

1. 54 ሚሊዮን 57 ሺህ 871 መራጮች ተመዝግበዋል፣

2.በአጠቃላይ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች ይወዳደራሉ፤

3. 10 ሺህ 438 የፖለቲካ ፓርቲ እጩዎች እንዲሁም

4. 80 የግል እጩዎች በምርጫው ይወዳደራሉ።

5. ፓርቲዎች በተደለደለላቸው የአየር ሰዓት 19 የክርክር መድረኮችን በአምስት ቋንቋዎች አካሂደዋል፤

6. ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከ250 ሺህ በላይ ተወካዮቻቸውን የምርጫውን ሂደት እንዲከታተሉ ይልካሉ፤

7. ለታዛቢነት የአፍሪካ ሕብረት እና የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) ተወካዮቻቸውን ልከዋል፤

8. 59 አባላት ያሉት የአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን በቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት አሁሩ ኬንያታ እየተመራ ሥራውን ይሰራል፤

9. ኢጋድ 26 አባላት ያሉት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድንን ያሰማራል፤

10. በሀገር ውስጥ የተደራጁ 55 ሲቪክ ማኅበራት ፈቃድ ወስደው ወደ ሥራ ገብተዋል፤ 55ቱ የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች 1 ሺህ 562 የምርጫ ታዛቢዎችን አሰማርተዋል።

11. የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭትን በተመለከተ በአዲስ አበባ ለ33፣ በአፋር ለ32፣ በአማራ ለ130፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ለ22፣ በማዕካላዊ ኢትዮጵያ ለ35፣ በድሬዳዋ ለ48፣ በጋምቤላ ለ14፣ በሐረሪ ለ3፣ በኦሮሚያ ለ179፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ለ56፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ለ22 ክልሎች የምርጫ ቁሳቁስ ተሰራጭቷል።

28/05/2026

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Civil ServiceAnd Human Resource Development Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Amhara Civil ServiceAnd Human Resource Development Bureau:

Share