Amhara Region Grand Ethiopian Renaissance Dam Coordination Office

Amhara Region Grand Ethiopian Renaissance Dam Coordination Office እንዳጋመስነው እንጨርሰዋለን!

01/09/2026
30/08/2026
30/08/2026

የዓባይ ንጉሦች ሆነናል ፤ የቀይ ባሕር ንጉሦችም እንሆናለን ኡስታዝ ጀማል በሽር ከኢቲቪ የመውሊድ ልዩ ...

30/08/2026
30/08/2026
29/08/2026

የጁሊየስ ኔሬሬ ግድብ እና የግብፅ የፖለቲካ ማወናበጃ
+++++++++++

| ታንዛኒያ በሁለት ነጥብ ዘጠኝ ቢሊዮን ዶላር ሙሉ በሙሉ በራሷ የገንዘብ አቅም ያስገነባችውን የጁሊየስ ኔሬሬ የውኃ ኃይል ማመንጫ ግድብ አስመርቃለች። ነገር ግን የግብፅ ተቋማትና ሚዲያዎች የራሳቸው "የልማት አጋርነት" እና የፋይናንስ ድጋፍ ውጤት አስመስለው ለማቅረብ አሳሳች የፖለቲካ ማወናበጃ ሲያካሂዱ ሰንብተዋል።

ግድቡ የናይል (ዓባይ) ተፋሰስ አካል ባልሆነውና ወደ ሕንድ ውቅያኖስ በሚፈሰው የሩፊጂ ወንዝ ላይ የተገነባ በመሆኑ፤ በውኃ ድርሻዋ ላይ ስጋት የሌላት ግብፅ፣ በዝቅተኛ ጨረታ በተቋራጭነት ያገኘችውን መደበኛ የንግድ ሚና በሕዳሴው ግድብ ምክንያት የደረሰባትን የዲፕሎማሲ ሽንፈት ለማካካስና የላይኛው ተፋሰስ ሀገራትን አንድነት ለመሸርሸር እየተጠቀመችበት እንደሆነ ዲፕሎማቶች አጋልጠዋል።

የግብፅ ኩባንያዎች በክፍያ የተሰማሩ የንግድ ተቋራጮች ብቻ መሆናቸው እየታወቀ፤ ግድቡ በተመረቀበት ወቅት የግብፅ ሚዲያዎች ይህንን መደበኛ የተቋራጭነት ሚና ወደ “ልማት አጋርነት” እና የገንዘብ ድጋፍ ትርክት በመቀየር አሳሳች የሕዝብ ግንኙነት ዘመቻ እያካሄዱ ይገኛሉ። ግድቡ የሚገነባበት የሩፊጂ ወንዝ ወደ ሕንድ ውቅያኖስ የሚፈስና የዓባይ ተፋሰስ አካል ባለመሆኑ፤ ግብፅ በውኃ ድርሻዋ ላይ ስጋት ስለሌላት ብቻ ግንባታውን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ዓለም ዓቀፍ ገጽታዋን ለመገንባት እየሠራችበት ነው።

የፍትሐዊ የውኃ አጠቃቀም ማዕቀፍ የሆነውን የኢንቴቤ ስምምነት የፈረሙትን እንደ ታንዛኒያ እና ኢትዮጵያ ያሉ የላይኛው ተፋሰስ ሀገራትን አንድነት ለመሸርሸርና ልዩነት ለመፍጠር ያለመ የፖለቲካ ስልት መሆኑም እየተገለጸ ነው። የቅኝ ግዛት ውሎችን አምርረው በተቃወሙት በጁሊየስ ኔሬሬ ስም በተሰየመ ግድብ ላይ የቅኝ ግዛት ውል አራማጇ ግብፅ ያላትን ተሳትፎ የዲፕሎማሲ ድል አድርጋ ማቅረቧም ሌላው ታሪካዊ ተቃርኖ መሆኑን ያመለክታል።

የታንዛኒያው የጁሊየስ ኔሬሬ የውኃ ኃይል ማመንጫ ግድብን በተመለከተ ግብፅ ለምን አሳሳች መረጃን ትለቃለች? ዓላማውስ ምንድን ነው? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንጋፋ ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፣ የታንዛኒያው ጁሊየስ ኔሬሬ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ግድብ በሩፊጂ ወንዝ ላይ የተገነባ ነው። የኃይል ማመንጨት አቅሙም ሁለት ሺህ 115 ሜጋ ዋት ነው። ግድቡ ዘጠኝ ታላላቅ ተርባይኖች ያሉት ሲሆን፤ አጠቃላይ የግንባታ ወጪውም.....

ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ https://gw.press.et/am-digital-content/share/am-stories/4eb3dxsfwcwhewnemqwybx5bxe

29/08/2026
29/08/2026

Address

Bahir Dar
NO

Telephone

+251918769668

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Region Grand Ethiopian Renaissance Dam Coordination Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Amhara Region Grand Ethiopian Renaissance Dam Coordination Office:

Shortcuts

Share